Monday, November 2, 2015

ሻቢያዎች ለምን ታገሉ?

ለማ ኃይሌ
 ጥቅምት ወር 2013 በፈረንጆች አቆጣጠር አምስት መቶ አካባቢ ኤርትራውያን ያሳፈረች መርከብ ሜዲትራንያን ባህር ባለችው ላምፔዱሳ ወደብ አካባቢ ሰጥማ 350 ኤርትራውያን በሞቱ ጊዜ ጉድ አያልቅበት የአቶ ኢሳያስ መንግሥት “የአፍሪካ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ሊሻገር ሲሉ ጀልባቸው ተገልብጦ በሜዲትራኒያ ባህር አለቁ” በማለት የራሱ ዜጎች መሆናቸውን ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ አለምን ጉድ ያሰኘ ዜና በቴሌቪዥኑ አስተጋባ። ድርጊቱ የተፈጸመው በአውሮጳ ክልል በመሆኑ ግን ዜናው ሰፊ የስርጭት ሽፋን አገኘ። ትራጄዲው አለምን አናወጠ። ይሄኔ ሳይወድ በግድ የራሱ ዜጎች መሆናቸውን ለመቀበል ተገደደ። ያም ሆኖ ጲላጦሳዊነት የሚያጠቃው ይሄ መንግስት ሌላ ጉድ ይዞ ብቅ አለ፤- “ለኤርትራ ወጣቶች ፍልሰትና እልቂት ግንባር ቀደም ተጠያቂው የአሜሪካ መንግስት ነው” በማለት ኃላፊነቱን ከራሱ አወረደ።

 እስኪ አስቡት! አሜሪካን የሚያህል ታላቅ መንግሥት አንዲት የወጠጤ ግንባር እምታክል፤ የለት ጉርስዋን ያመት ልብስዋን እንኳን ለመሸፈን ዳገት የሆነባት፤ በዘመናችን የአፍሪካ ኖርዝ ኮርያ ተብላ እምትጠራ አገር ምን ጋሬጣ ልትፈጥርበት ትችላለችና ነው አሜሪካ እንቅልፍ አጥታ፤ የሰው ሃይልና በጀት መድባ የኤርትራ ወጣቶች አገራቸውን እየጣሉ እንዲወጡ እምትደክመው? ሰው ለጥልም ሆነ ለፍቅር እኩያውን ይፈልጋል። ፤ምነው እኚህ ሰዎች እኩያቸውን ቢፈልጉ? እነዚህ መሪዎች ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት አሜሪካውያን ኤርትራ የምትባል አገር ከነመፈጠርዋ እንኳን እንደማያውቁ ይረዳሉ? ኤርትራ ኩዌት አይደለች ዘይት የላት፤ ኖርዝ ኮሪያ አይደለች ኑክሌር ቦምብ የላት ደቡብ ኮሪያ አይደለች ቴክኖሎጂ የላት በምንዋ ነው የአምስት ሚልዮን ምስኪኖች አገር ኤርትራ የነጮቹ ቀልብ ልትስብ እምትችለው?። ጂኦ- ፖለቲካ፤ ጦር ሠፈር ቅብርጥሴ…ወዘተ እንኳን እንዳይባል ያ ከቀዝቃዛው ጦርነት አብሮ የቀዘቀዘ ጉዳይ ነው። ፍሎሪዳ ላይ ቁጭ ተብሎ አፍጋኒስታን ላይ ያለ አሸባሪ በላፕቶፕ በአንድ ክሊክ አፈርድሜ እምታበላበት ዘመን ላይ ሆነህ ስለ ቃኘው ስቴሽን ማሰብ ተላላነት ብቻ ነው ሊሆን እሚችለው። በዛሬ ዘመን አገሮች አሜሪካ ጦር ሰፈሯን እንድትሰራ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ውድድር የገቡበት መሆኑ ሳይረሳ።

 ለመሆኑ ኢሳያስ ለዚህ ትራጄዲ አሜሪካንን በተጠያቂነት እንዴት ሊመርጡ ቻሉ? እውነት ኤርትራ ባላት ጂኦግራፊያዊ ስፍራ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ወሳኝ ሆና ነው? በኔ እምነት ከዚህ አስተሳሰብ በስተጀርባ ያለው ታሪክ አንድ መፅሃፍ እሚወጣው ይመስለኛል። ይህ አሜሪካ ጠላታችን የሚባለው ፤ አመራሩ ያለበትን ትልቅ የማንነትና ቁመትህን ልክ ያለማወቅ ቀውስ እሚያመለክት ነው ። የፀጥታና የድንበር ውዝግቡ ያለው ሰላሳ አመት ከተዋጉዋት ኢትዮጵያ ጋራ ሆኖ እያለ ዘሎ በቦታው የሌለውን አሜሪካን መክሰስ ሳይካትሪስት እሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። እንደሚባለው ከሆነ ኢትዮጵያን በቅኝ ገዢነት ሲከሱ እንዳልነበሩ ሁሉ ከቅርብ ጊዜ ወድህ ቋንቋው ተለውጦ ከፈደሬሽን እስከ ውድቀተ-ደርግ ያለውን ጊዜ “የአሜሪካ ቅኝ አገዛዝ በኢትዮጵያ እጅ” እየተባለ መፃፍና መናገርም ተጀምሮአል።

የዛሬ አመት ተኩል ገደማ የተላለፈው የፕረዚደንቱ እንተርቪው፤ “ኢትዮጵያ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በሁዋላ የተፈጠረች አገር ናት” የሚለው ትንተና፤ ከዚሁ ጋራ አጣምረህ ስታየው እነዚህ ሰዎች ለራሳቸው የሰጡት የጦዘ ግምት ያሳያል። አሜሪካንን በጠላትነት የመረጡበት ምክንያት የኢትዮጵያ ጠላትነት ለእነሱ ዝና አይመጥንም ብለው ስለሚያምኑ ነው። ስለዚህ አለም እነሱ እንደ ቬትናሞች አሜሪካንን በሠላሳ አመት ትግል አሸነፉ ብሎ እንዲያምን ይፈልጋሉ። ይህ እንግዲህ የነሱ የሰላሳ አመት ትግል ተመጣጣኝ ዋጋ (ጠላት) እንዲያገኝ ማለት ነው። በቅኝ የገዛችንና ሠላሳ አመት የተዋጋናት፤ ያቺ በስንዴ ልመና ባንድ ወቅት አለምን ያስቸገረች ኢትዮጵያ ናት ቢሉ ግን ትግላቸውና የትግላቸው ውጤት ሚዛኑ ይቀንሳል፤ ዋጋውም ያሽቆለቁላል። በአጭሩ ኢትዮጵያ እነሱ ላስቀመጡት -በምጣኔ ሃብት አዋቂዎች አነጋገር inflated price- አትመጥንም። በነሱ ቤት አሜሪካ ባትኖር ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጋር በፈዴሬሽን አትዋሃድም ነበር፤ የነፃነት ትግላቸውም እንደዛ መራራ የሆነው በአሜሪካ ምክንያት ነው። ከባድሜ የወጡትም አሜሪካ ወያኔዎችን ስለረዱ ነው። 

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህልውና የተመሰረተው በአሜሪካ ነው። በአሁኑ አያያዛቸው ወደፊት ግንቦት 24 የናጽነት ቀናቸውን “ኤርትራ ከአሜሪካ ቅን አገዛዝ የወጣችበት” ተብሎ እንዳይከበር እሚያሰጋ ነው። አንዳንዴ ሳስበው ሻቢያዎች በቅዝቃዛው ጦርነት ወቅት የነበረውን የአሜሪካ ተወዳዳሪ ሶቭዬት ህብረትን በዚህ ዘመን የተካነው እኛ ነን እሚሉ ይመስላሉ። አሜሪካ እምትጠላን ይላሉ ገራገሮቹ ወንድሞቻችን - ለአፍሪካ መጥፎ ምሳሌ ስለሆንን ነው። እንዴት? የሚል ጥያቄ ስታስከትል “ምክንያቱም በራስ መተማመን የሚለውና ብድርን የማይፈቅደው ፖሊሲያችን ለተቀሩት አፍሪካውያን ምሳሌ እንዳይሆንና በዚህም የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዛቸው እንዳያከትም አሜሪካና አውሮፓ ብርቱ ስጋት ስለአላቸው ነው።” በማለት ያብራራሉ። በቅርቡ በአልጀዚራ የቀረበ ፊልሞን የተባለ የሻቢያ ወጣት ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በተለዬ ችግር እየደረሰብን ያለው የመንግስታችን ፖሊሲ በራሳችን ስለሚቃኝ፤ለአለም ገንዘብ ተቋም፤ ለአለም ባንክ እማናጎነብስ፤ በትክክል ነፃ መንግስት ስለሆን ነው” በማለት ጋዜጠኛዋን አስደምሞአል። በነሱ አመለካከት ስድሳ ወደ የሚጠጉ የአፍሪካ ሃገራት ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም አስልፈው ሰጥተው አንዲት ሃገር ኤርትራ ብቻ በጽናት መቆምዋን ነው። ሁኔታው ያስቃልም ያሳዝናልም አንድ ያስመራ ወዳጄ ያጫወተኝ እዚህ ላይ ታወሰኝ። አልበሽርና ኢሳያስ ሲገናኙ ይተራረባሉ አሉ-የዛሬው አያርገውና። አልበሽር የወያኔዎችን የቁጥር እድገት ሲነግረው ያ ፊቱን ጨምድዶ” ታያለህ! ኢትዮጵያን በእድገት ሩጫው ብቻ አይደለም በቅርቡ አልፈናት እንሄዳለን “ ይለዋል። ጨዋታ አዋቂው በሽር “ድረሱባት እንጂ አልፋችሁ መሄዱስ ይቅርባችሁ” ይለዋል።

 አቶ ኢሳያስ “ለምን” ይላል፤ አልበሽርም መልሶ “አይ እናንተ ከፊት ስትሮጡ እነሱ ከኋላ ሆነው በተቀደደው ሱሪያችሁ መስኮት መቀመጫችሁን እያዩ እንዳይስቁባችሁ ብዬ ነው” አለው ይባላል። አሉ ነው አልነበርኩም። ወደ ራስችን እንመለስ። ነፍሳቸውን ይማርና ዘውዴ ረታ የኤርትራ ጉዳይ በሚለው መጽሃፋቸው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ፍፃሜ ማግሥት ጀምሮ በማህበረ-አንድነት መሪነት የባህረ ነጋሽ ኢትዮጵያውያን ከናት አገራቸው ለመቀላቀል ስላደረጉት ተጋድሎ፤ የአፄ ሃይለሥላሴ መንግሥትም የባህረ ነጋሽ ህዝብ ወደናት አገሩ ለመመለስ ያደረገውን ተጋድሎ መሰረት በማድረግ በአለም ሸንጎ ፊት በስመ ጥሩዎቹ የአገራችን ዲፕሎማቶች በነአቶ አክሊሉ ሃብተወልድ፤ ሌሬንሶ ታእዛዝና ሌሎችም አማካይነት ስላካሄደው ዲፕሎማሲያዊ ትግል በስፋት አሳይተውናል። ኢትዮጵያውያንም እንደ ህዝብ በጉዳዩ የጠራ ግንዛቤ እንድንይዝ ረድቶናል። ምክንያቱም በራሳችን መንግሥትም የተፈፀሙ ስህተቶችም አሳይተውናል። በዚህም በደርግ ጊዜ ከነበረው የድንቁርና አካሄድ፤ በዚህኛው መንግሥት ካየነው የተዛባ ታሪክ ትንተና ወጥተን ሚዛናዊ የሆነ ግንዛቤ ለመጨበጥ ችለናል። ነገር ግን ከነጻነታቸው ወድህ ባለው ጊዜ በሃማሴን ጽንፈኞች በኩል እሚነገረውና እሚተረተረው ውሸት ሁሉ ደምረን ቀንሰን ስናዬው፤ የኤርትራ ችግር ከግንጠላው በኋላም በፊት ከነበረው ብሶበት እየቀጠለ መሆኑ ሲታይ፤ የዚች አገር የግንጠላ ተጋድሎ መነሻ ታሪክ ከሌላ አንግል በጥልቅ መመርመር ያለበት ጉዳይ መሆኑ ነው። ኤርትራ ተገነጠለች ማለት ተነስታ ህንድ ወይም ሰላማዊ ውቅያኖስ ውስጥ ተተከለች ማለት አይደለም። ያው በቦታዋ ነው ያለችው። የዚች አገር መሪዎች ስለራሳቸው የሚኖራቸው አመለካከት የተጣመመ ከሆነ ለጎረቤቶቻቸው የሚኖራቸው ፖሊሲም ጤናማ አይሆንም። ስለራሳቸው የጦዘ እና ያበጠ አመለካከት የነበራቸው እንደነሂትለር የመሳሰሉ እብዶች በታሪክ ምን ሰርተው እንዳለፉ ማስታወሱ ጠቃሚ ነው። ስለሆነም አሁን የሻቢያ መሪዎች የያዙት አሜሪካን እኩያህን አድርገህ እስከ መቁጠር የሚያደርስ እብደትና ኢትዮጵያንና ሌሎች የአካባቢው አገሮችንም ቁልቁል የማዬት አባዜ ምንጩን ለማወቅ ትግሉ የተካሄደበትን ምክንያት እስካሁን ሲነገረን ከነበረው በተጨማሪ ምርምር ተካሂዶ ልንደርስበት ይገባል።


 የዛሬይቱ ኤርትራ መሪዎች ፤የደጋ ክርስቲያኖች በንጉሱ ዘመን አባቶቻቸው አንድነትን ሲመርጡ እነሱ መገንጠልን የመረጡበት ምክንያት ኢትዮጵያውያን በውል ማወቅ ያለብን ይመስልኛል። አባቶቻቸው የታገሉት ለፈደሬሽን ወይ ለኮንፈደሬሽን ለካፒታሊዝም ወይ ለሶሻሊዝም ሳይሆን ኢትዮጵያ አገራቸውን ለማግኘት ነበር። ታገሉ አገኙም። ነገር ግን ልጆቻቸው ኢትዮጵያዊነትን ተጠየፉት። በአባቶቻቸው የነበረው ኢትዮጵያዊነት ወዴት ሄደ? እውን እነዚህ ሰዎች በረሃ የወጡት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋራ ከፍላጎትዋ ውጭ በመዋሃድዋ ወይም ፈዴሬሽኑ በመፍረሱ ነው? ፌደሬሽኑ ባይፈርሥ መሸፈታቸው ይቀር ነበር? ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃኒዬ በአንድ ወቅት እንደገለጡት ፌደሬሽኑ የቆላ ሞስሊሞች ወደ ክርስቲያን ኢትዮጵያ በመግባቱ የነበራቸውን ፍራቻ ለማስወገድ የተቀመጠ የጋራ አካፋይ ነው።

ክርስቲያኖቹ የታገሉት በኦሪትም በሃዲስም ይዘዉት ለኖሩት ማንነት-ለኢትዮጵያዊነት ነበር። ፌደሬሽን ይሁን አሃዳዊ ለነሱ ጉዳያቸው አልነበረም። እንዲያውም ንጉሱ እንደ መሲህ ይታዩ የነበሩት ይበልጥ በነዚህ ወገኖች አካባቢ እንደነበረ ይታወቃል። በንጉሰ ነገሥቱ ዘመን በአሥመራ ማህበረ ሀዋርያት ይታተም የነበረው መዝሙረ ዳዊት ፈልጋችሁ ብታነቡ በመግቢያው ለአምላክ የሚሰጠውን ውዳሴ ለጃንሆይ ሲያዥጎደጉዱት እንደነበረ፤ ንጉሱ አስመራ ለመጎብኘት ሲገቡ የህዝቡ አቀባበል በመጽሃፍ ቅዱስ ታሪክ ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሩሳሌም ሲገባ የነበረውን ትእይንት የሚያስታውስ እንደነበር ነው። ታዲያ የነዛ በኢትዮጵያ ብሔረትኝነት እና በንጉሰ ነገሥቱ ፍቅር ልባቸው ይነድ የነበሩት አባቶች ዘመናዊ አስኳላ የተማሩ ልጆቻቸው የአንድነቱ መንገድ ትተው የግንጠላውን ለመከተላቸው መሰረታዊው ምክንያቱ ምን ይሆን? በመሰረቱ የአንድ አገር ኢኮኖሚ የተቆጣጠሩ፤ ከሌሎች ዜጎች የተሻለ የኑሮ ደረጃ የነበራቸው ማህበረሰቦች ተጨቁነናል፤ ተበድለናል ብለው በረሃ ሲወጡ በታሪክ እሚታወቅ ነገር አይደለም። የደርግ ግፍ አስበርግጎት በገፍ በረሃ የገባው ወጣት ትተን በንጉሱ ዘመን የኢሳያስና ስብሃት ኤፍሬም የደጋው ክርስቲያን ትውልድ የበረሃ ትግሉን የተቀላቀሉበት ዋና ምክንያት ግን የሰለጠነች ኤርትራ ኋላ ቀር ከሆነች ኢትዮጵያ መዋሃድ ያሳደረባቸው ቁጭት ነው። በሌላ አነጋገር ሰዎቹ በረሃ የወጡት ያስመራ ስልጣኔን ከኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት ለመታደግ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጽሁፎቹ ጥልቅ ትንታኔ ገናና እየሆነ የመጣው ኤርትራዊው ዮሴፍ ገብረህይወት

 The Eritrean Oblomov-loving-Asmara the superfluous way በሚል ርእስ ያቀረብው አስገራሚ ትንተና እና ሊሎች ጽሁፎቹ የኤርትራን ችግር ከሌላ አንግል ለማዬት እሚረዱ ናቸው። http://asmarino.com/articles/2046-the-eritrean-oblomovloving-asmara-the-superfluous-way

ዮሴፍ እንዲህ ይላል፡ Here is a fact that the nationalists would undoubtedly have a hard time to swallow: the golden age of Asmara happens to be neither in the Italian era nor in the Independence era; those g those g those golden years happen to fall exactly on the re olden years happen to fall exactly on the reign of Haile Selassie, starting to build up in the 50s to reach Selassie its apex in the 60s, only to abruptly end in the early 70s when ghedli (ታጋዮች ለማለት ነው) showed up at the doorsteps of Asmara in full force.

What then explains this riddle, since it doesn’t fit at all with the narrative that the nationalists have been telling the masses? This question has special relevance because the ghedli generation’s concept of modernity was entirely shaped from the impressions that this colonial city had left on them. In fact, it was with the saving of “Asmara ci In fact, it was with the saving of “Asmara civilization” in their tion” in their mind that they went through hell for 50 years. Wher mind that they went through hell for 50 years. e from came this perceived threat? Did Asmara have it so bad during the Haile Selassie era to warrant 50 years of insanity? To begin with, why can’t we say that Asmara’s golden age was during the Italian colonial era, given that it was after all the Italians that built it? There are two major reasons: First and foremost, as pointed above, 

Asmara remained a small Asmara remained a small sleepy little town for much of the colonial sleepy little town for much of the colonial era sleepy little town for much of the colonial era; it was only when Italy decided to invade Ethiopia that Asmara abruptly mushroomed five folds in the last six years. If there was no vibrant Asmara for much of the colonial era to begin with, one cannot talk of a “golden age” of a city that was never there. And, second, if we are to confine ourselves to the last six years, there were three things bedsides its brief “age” that would make a mockery out of these perceived golden years. ዮሴፍ የሚለውን እንደገና ልብ ብለን እናስተውለው! In fact, it was wi In fact, it was with the saving of “Asmara civilization” in their mind that they went through hell for 50 years. ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎችና የፖለቲካ ሰዎች አትኩሮት ሊሰ for 50 years. ጡት እሚገባ ጉዳይ ነው። ይህንን የምለው ያለምክንያት አይደለም።

 ዛሬም ብዙ ፖለቲከኞቻችን የምእራባውያኑን ቋንቋ ተከትለው የኤርትራ ችግር “Annexation” ወይም በኃይል የመያዝ ነው ሲሉ ይደመጣሉ። ከያትውልድ መሪዎች አንዱ ያሬድ ጥበቡ በቅርቡ በፌስቡክ አምዱ ያወጣው ጽሁፍ እንዲህ ይላል፡ “የኤርትራ ጉዳይ የannexation ወይም አስገድዶ የመያዝ ጥያቄ ነው የሚለው የምሁሩ ትንተና ተገቢው ትኩረት ያልተሰጠው ሩቅ ጠማችና ሃገር አደላዳይ አመለካከት ነበር ። በሚገርም አጋጣሚ፣ እኔ ለኢህዴን አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ካዘጋጀሁት ጥናታዊ ሰነድ ጋር ተመሳሳይ ነው ። በህዳር 1976 ለሚካሄደው ጉባኤ "የኤርትራ ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት የተሰጣቸውን የፌዴሬሽን መብት በመግሰስ ከኢትዮጵያ ጋር አንድ እንዲሆኑ የተደረገበት ሂደት በመሆኑ፣ የannexation ጥያቄ ነው፣ መፍትሄውም ሪፍሬንደም ማካሄድ ነው" የሚል ሰነድ ነበር ያዘጋጀሁት ። ይህን ሰነድ የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ለነበሩት ለነታደሰ ጥንቅሹ አስረክቤ ወደ ደቡብ ወሎ ለመስፋፋት ላቀድነው ወታደራዊ ዘመቻ ለመሳተፍ የኢህዴንን ታጋዮች ይዤ ከቤዝ አምባችን የሳምንታት የእግር መንገድ ጉዞ ርቀን ሄድን ። ከሁለት ወራት በላይ የፈጀውን ወታደራዊ ስምሪት አጠናቀን ወደ ሰቆጣ ከተማ ስመለስ ፣ እነ ታደሰ ጥንቅሹ የኔን ጥናት ለአባላት እንዳይሰራጭ አፍነው ፣ በረከት ሌላ "የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው" የሚል ሰነድ አቅርቦ፣ አባላትን በዚያ ሰነድ ላይ ብቻ ሲያወያዩ ደረስኩ ። ለጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴው የመረረ ተቃውሞዬን ከማቅረብ ውጪ፣ በዚያ በረፈደ ሰአት (ጉባኤው መከፈቻ ቀርቦ ስለነበር) ማድረግ የምችለው አልነበረም ። በተጨማሪም የበረከትም የጥናት ፅሁፍም ቢሆን ፣ በአፈታቱ ላይ "ነፃነት አሁኑኑ" የሚል ሳይሆን ፣ ከኔው አመለካከት ጋር የሚስማማ በሪፍሬንደም እንዲፈታ የሚጠይቅ ስለነበር ፣ ጉዳዩን አለዝቤ ለመያዝ ወሰንኩ ።”

የያሬድ ጥበቡ ትውልድ በዘመኑ የኢትዮጵያን ችግር የተነተነበት መንገድና ለችግሮቹም መፍትሔ ብሎ ያቀረባቸው ከግራ ዘመም አይዲኦሎጂው እሚመነጩ ነበሩ። ትውልዱ የነበረው የአገርና የወገን ፍቅር የማያሻማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር የህልውና ችግር ሆኖ እያለ ታሪኩን በአግባቡ ያላጠናው ትውልድ መሰረታዊ ያገራችን ችግር “የመድብና የብሔር” ብሎ በመደምደም ለለፉት አርባ አመታት ለገባንበት ችግር ምክንያት ሆኖአል። ትውልዱ የኤርትራ ችግርም ቢሆን ከሞላ ጎደል የተሟላ ስእል ያገኘው በዘውዴ ረታ መጽሐፍ እንደመሆኑ መጠን በፋኖነት ዘመኑ የኤርትራን ችግር አስመልክቶ የነበረው እውቀቱና ትንተናው ውሃ እሚቋጥር አይሆንም። እንደሚታወቀው በእንግሊዞች ዘመን የኤርትራ መፃኢ እድል ለመወሰን ሲንሸራሸሩ የነበሩ ሁለቱ አመለካከቶች (ነጻ መንግስት ወይም ከኢትዮጵያ መዋሃድ) ሃይማኖት ላይ የተመሰረቱ ነበሩ። ቆላ ሙስሊሞች ሙሉ ለሙሉ ነፃነት ሲሉ እጅግ ብዙሃኑ ደጋ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያ ወይም ሞት አሉ።

ፌደሬሽን ሁለቱን እሚያስታርቅ ሆኖ ተገኘና ኤርትራ በፈደሬሽን ከኢትዮጵያ ጋራ ተዋሃደች። የመጀመሪያ የሸንጎ ምርጫም ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ 35 ክርስቲያኖች እና 35 ሞስሊሞች የምክር ቤት አባላት፤ ክርስቲያን ፕረዚዴንት ሙስሊም አፈጉባኤ ሆነው ተዋቀሩ። ብዙም ሳይቆይ በዋናነት በደጋ ክርስቲያኖች ትግልና በንጉሰ ነገስቱ ድጋፍ ፌዴሪሽን ፈረሰ። እስላሞች የፈራነው ደረሰ አሉ። የነአዋተ የበረሃ የነፃነት ትግልም ተጀመረ። ከውህደት በኋላ ለኤርትራ በተሰጠው ልዩ ጥቅም ከሌላው ጠቅላይ ግዛት በበለጠ በብዛት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጎረፉት የደጋ ኤርትራ ወጣቶች መሃል አገሩን ካዩ በሁዋላ ካደጉባት አስመራ ጋራ በማወዳደር ኋላ ቀርዋ ኢትዮጵያ ያስመራን እድገት የምታጨናግፍ አድርገው ይቆጥርዋት ጀመር። ንጉሰ ነገስቱ “በቅኝ አገዛዝ ቅስሙ የተሰበረ ህዝብ ነው” በማለት ሞራሉን ለማደስ ያደረጉት ሁሉ ከመጤፍ የቆጠረው አልነበረም። ለወጣቶቹ በጊዜው የታያቸው ባለ እንዱስትሪዋ ኤርትራ ከ”ኋላቀርዋ አገር” ከተላቀቀች ከወደቦችዋ ጋር በአፍሪካ በእድገትዋ ከአውሮፓ አገሮች የምትስተካከል አገር ልትሆን እንደምትችል ነበር።

ወጣቶቹ የዩኒቨርስቲ ቆይታቸውን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋራ ለመቀራረብና ለመዋሃድ አላዋሉትም በአንጻሩ ራሳቸውን የተለዩና በስልጣኔ ከፍ ያሉ አድርገው በመቁጠር “የተባበሩት መንግስታት አንዲት በእንዱስትሪ የበለፀገች አገር እጅግ ፊውዳልና ኋላ ቀር ከሆነች አገር አቆራኛት” የሚል ቁጭት ነበር እሚያንገበግባቸው። ይህንን በማስረጃ እንይ። ኪዳኔ ሐጎስ ካናዳ አገር የሚኖር በንጉሱ ዘመን የቀዳማዊ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረ እንደ ያኒዎቹ ወጣቶችም ለኤርትራ ነጻነት በውቅቱ በረሃ የገባ ሰው ነው። ባለፈው መጋቢት ወር ሃሊፋክስ ካናዳ ለሚገኘው ቮይስ ኦፍ ኤሪትሪያ በሰጠው ኢንተርቪው https://www.youtube.com/watch?v=5267XGueEUA እንዲህ ይላል” የኤርትራ ህዝብ ከአካባቢው ህዝብ የሚለየው ነገር ቢኖር መተጣጠፍ የሚችል፤ የፈጠራ ጥበብ የተላበሰ ብልሃተኛ ህዝብ መሆኑ ነው።

ሞደርን ኢትዮጵያን የፈጠራት የኤርትራ ህዝብ ነው። ገብረሚካኤል አምባዬ የሚባል ኤርትራዊ እሸት የምትባል አውሮፕላን ሰራላቸው። እንዲያውም ከተጋድሎአችን አላማ አንዱ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ወደፊት እንዳንራመድ አስሮ ስለያዘን የራሳችን መንግስት መስርተን ወደፊት ለመወንጨፍ ነበር” አስምሮም ለገሰ የተባለ አንትሮፖሎጂስት ይሄ “እኛ የተሻልን ነን” ለሚለው እሳቤ ሁነኛ ኢዲኦሎግ ነው። በ1988 እኤአ በጆን ሃፕኪን ዩኒቨርስቲ ሰለ ኤርትራ በኢኮኖሚ ራስን የመቻል ብቃት አስመልክቶ በሰጠው ዲስኩር ለዚሁ ማስረጃ ብሎ ያቀረበው ምክንያት “ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ” ያስባለ ነበር። “ስፖርት ብቻ ሳይሆን ኤርትራውያን ቴክኖሎጂ ከሰውነታቸው የተዋሃደ ነው፤ ስለሆነም አገራችን የእንዱስትሪ እኮኖሚ ለመገንባት አይቸግራትም።” ብሎ የጀመረው የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ለማስረጃ ብሎ ያቀረበው ነገር ትንሽነቱን በሰው መሃል ያጋለጠ ጉዳይ ነበር። እንዲህ ነበር ያለው፡ “ለዩኒቨርስቲ ትምህርት አስመራን ለቅቄ ወደ አዲስ አበባ በሄድኩበት ወቅት ይዤአት የሄድኩኝ ካቻቪቴ ነበረችኝ። አማራዎቹ የክፍል ጓደኞቼ ስምዋን ስለማያውቁ ጠበንጃ መፍቻ ይሉዋት ነበር።” ይህ ለፕሮፌሰሩ የኤርትራውያን ከኢትዮጵያውያን በተሻለ ቴክኖሎጂ ማወቅን የሚያረጋግጥ ነበር።

ዳሩ ምን ይሆናል በቦታው ከነበሩ ፓናሊስቶች አንዱ የሆነው ጄምስ ማካን የተባለ ፕሮፌሰር“ ካቻቬታ ጣልያንኛ ነው በትግርኛ ምንድነው እምትሉት?” በማለት ላቀረበው ምፀታዊ ጥያቄ፤ ፕሮ/ለገሰ በመሸማቀቅ “የትግርኛ ቃል የለውም ያው ካቻቪቴ ነው እምንለው” ከማለት ውጭ አማራጭ አልነበረውም። የፕሮ/ለገሰ አመለካከት የዛሬዎቹ የኤርትራ መሪዎች መሰረታዊ እምነት ነው። በረሃ የወጡበት አላማ ዞሮ ዞሮ የሚያርፈው እዚሁ ነው። ከ30 አመታት ጦርነት በኋላ በድል አስመራ የገቡት እኒያ ዮሴፍ፤ “ያስመራ ስልጣኔ ተከላካዮች” በማለት ያጠመቃቸው ታጋዮች፤ ያገር መሪነት ሚና ሲጨብጡ ያሳዩት ባህርይ ይህንኑ ሲወጡ የነበራቸው እምነት የሚያሳይ ነበር። አሥመራ በገቡ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ያን ሁሉ ጠራርገው ያስወጡት ለፍቶ አደር ኢትዮጵያዊ ያቺ ሰወጡ የነበረችውን አሥመራ ውበት ለመጠበቅ ሲሉ ነበር።

ኢትዮጵያን የተመለከትዋት በቅኝ ገዥዎች አይን እንደ ጥሬ ሃብት አቅራቢ ሲሆን በአረቦች ላይ ሽርደዳ በአፍሪካ መሪዎች ላይ ማሾፍ የየቀኑ ሥራ አድርገዉት ነበር። የመከላከያ ኃይል ብቃታቸው ማነጻጸሪያ እስራኤልን ሲመርጡ በኢኮኖሚው እቅዳቸው ሲንጋፖርን በአጭር ጊዜ ለመድረስ አቅደው ነበር። ኤርትራ ከ”ናጽነት” በኋላ ያስየችው እብደት ቀረሽ ባህርይ ሌሎቹ፤ ነጻነታቸውን ከኮለንያሊስቶቹ እንግሊዝና ፈረንሳይ ካገኙ አገሮች የተለዬ የሆነበት ምክንያት ትግሉ የተካሄደበት ምክንያት የተለዬ በመሆኑ ነው። ዛሬም ከ25 አመት በኋላ በጦርነት ተሸንፈው፤ በኢኮኖሚውም ተንክታኩተው፤ 4ኤም ተነስተህ የዳቦ ወረፋ እምትይዝባት አገር ይዘው እንኳን ሻቢያዎች ዛሬም ከቁመታቸው ልክ የማሰብ አባዜ አልተዋቸውም። ማርች 28-2015 በአዋተ.ኮም ሰለ አቶ ኢሳያስ የወጣው ጽሁፍ ዝሆን አክላለሁኝ ብላ የፈነዳችውን እንቁራሪት ታሪክ እሚያስታውስ ነው፡፡ ጉዳዩ ኢሳያስ አረቦችንና እስራኤልን ለማስታረቅ ራሳቸውን በእጩነት ስለማቅረባቸው ይመለከታል። 

A diplomat from the region informed Gedab News that the Eritrean president, “either thinks highly of himself or underestimates the Arab leaders to consider brokering any deal between the Arab countries and Israel, a feat countries with leverage failed to ac Israel, a feat countries with leverage failed to achieve.” hieve.” http://awate.com/isaias- http://awate.com/isaias-wants-a-bigger-role-in-the-yemeni-crisis/ crisis/ ሻቢያዎች ሰላሳ አመታት የታገሉለትን ነፃነትን ካገኙ በኋላ ዛሬም ቢሆን ከኢትዮጵያ ጋራ ከቅድመ ነፃነት በበለጠ ችግር ውስጥ የገቡበት ምክንያት ከመጀመሪያው የወጡበት አላማ ተፈፃሚ ሊሆን አለመቻሉ ነው።

የወጡበት አላማ ነፃ አገርን በመመስረት ብቻ የሚፈጸም ቢሆን አስመራ ከገቡበት አንስቶ ይህንን ለማሳካት ይችሉ ነበር። ነገር ግን እነሱ ከሌሎቹ በቅኝ ተገዥነት ከቆዩ ህዝቦች እሚለያቸው ይሄ ካከባቢው እኛ እንሻላለን የሚለው የበላይነት ስሜት ሲሆን ነገር ግን የሄ እሱነታቸው የአካባቢው ጌታ መሆን ስላላስቻላቸው እረፍት፤ እርካታና ሰኩሪቲ ሊሰማቸው አልቻለም። እነሱ ሲወጡ ቁልቁል ያዩዋት ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ባይኖራትም ቢያንስ እዛም እዚህም በበቀሉ ህንጻዎች ምክንያት ዛሬ አንጋጠው የሚመለከትዋት አገር ሆናለች። እንደተመኙላትም አልፈረስችም። በረሃ ሲወጡ “ወደባት አዴይ” እያሉ የዘፈኑላቸው ምጽዋና አሰብም ጄነራል ኤልትሪክና ጄኔራል ሞተርስ ሆነው አልተገኙም፤ የወደብ ባለቤትነት በራሱ ኢኮኖሚ አለመሆኑ የገባቸው 50ሺ ዜጎቻቸውን በትግሉ ካጡ በኋላ ነው። ገብሩ አሥራት “ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል መጽሐፉ በገጽ 153 “የሻቢያ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ውጥን’ በሚለው ክፍል ሐምሌ 1983 ዓ/ም አስመራ ላይ በተደረገውና 40 ጥናቶች በቀረቡበት የኢኮኖሚ ኮንፈረስ ላይ የተነገረውና የተተነተነው ሁሉ በወቅቱ ምን ያህል እንዳስቆጣው ይናገራል።

ኮንፈረንሱ አንድ ቀኝ ገዥ ሃይል ቅኝ በያዘው አገር ለማድረግ ያቀደውን የሚገልጽበት እስኪምስል ድረስ ጥናት አቅራቢዎች ነጻ አወጣን በሚሉት አገራቸው ስለሚመሰርቱት የኢኮኖሚ ስራት ሳይሆን ገለጻቸው በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስለሚኖራቸው ድርሻ ነበር። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለሚኖራቸው ሼር፤ ካምፓኒዎቻቸው በኢትዮጵያ ስለሚሰሩት መንገድ አይነት ነበር። የዚህ ሁሉ ምክንያት እኛ የተሻልን፤ የስለጠንን ነን የሚለው ሰወጡ የነበረው አስተሳሰብ ሲመለሱ የምንመራው እኛ ወደሚለው ማደጉ ያመጣው ጣጣ ነበር። እነዚህ የዋሆች ኢትዮጵያውያን በጊዜ ሂደት ሊያድጉ ሊለወጡ ይችላሉ የሚል እይታ ኖሮአቸው አያቅም። ለነሱ ኢትዮጵያ የብሄሮች ድምር ስለሆነች ፈራሽ ነች። የማፍረሱ ስራ ኮንትራቱን የወስዱት እነሱ ሲሆኑ የሁሉም ብሄር ነጻ አውጪ ነን ባይ ድርጅቶችም በአስመራ ጽፈት ቤቶቻቸውን ከፍተውን ባንዲራዎቻቸውን ሰቅለው ይኖራሉ ከዚያ እየተንቀሳቀሱም ኢትዮጵያን ይወጋሉ። ሻቢያዎቹ ኢትዮጵያ በትናንሽ መንግስት ተከፋፍላ እንሱ የአካባቢው ዋነኛ ህይል ለመሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በጣም የሚያመው የደብረ ቢዘን ልጆች ሶማሌ ድረስ ተጉዘው የአልሸባብ ጀሃዲስቶች ኢትዮጵያን እንዲያደሙ መርዳታቸው ነው። ይህም ጂሃዲስቱን አልሻባብን የረዱበት ዋነኛ ምክንያትም ይኸው እስከዛሬ የሚደክሙበት ያለው የኢትዮጵያ መበታተን ህልም ነው። የሻቢያዎቹን አካሄድ አይቶ አይቶ አንቅሮ የተፋቸው ኤልያስ ክፍሌ ያለው እዚህ ላይ ሊጠቀስ ይገባዋል። 

“From what I have observed personally over the past “From what I have observed personally over the pastfew years, few years, few years, and as many knowledgeable people have informed me for a long for a long Time, Shabia considers Eritrea not free until Ethio , Shabia considers Eritrea not free until Ethiopia is divided into is divided into is divided into Multiple mini ultiple mini-states. http//mereja.com/for states. http//mereja.com/for states. http//mereja.com/forum/viewtopic.php?t=1001 um/viewtopic.php?t=100199 um/viewtopic.php?t=100199

አንዳንድ የዋህን ኢትዮጵያውያን የድህረ ነጻነት ኤርትራና ኢትዮጵያ ፍጥጫ የሁለቱ አስመራና አዲስ አበባን በትጥቅ ትግል የተቆጣጠሩ ሃይሎች የመጠፋፋት ጉዳይ አድርገው ይመለከቱታል። ይህ ግን ቁንጽልና ጉዳዩን በጥልቀት ካለመመልከት የመጣ ነው። የኢትዮጵያን የኤርትራ ጉዳይ ከአሜሪካ-ራሻ ይመሳሰላል። በሶቭዬት ህብረትና በአሜሪካ የነበረው ቀዝቃዛው ጦርነት ዛሬም መልኩን ቀይሮ ሌላ ዙር ቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ። በኮሚዩኒዝም ጊዜ ተቃርነዋል ዛሬ ኮሚዩኒዝም በሌለበት ሁናቴ ወደ አደገኛ ቅራኔ እየገቡ ነው። ለአሜሪካኖች ዋነኛው ነገር ሩሲያ የነሱን ልእለ ሃያልነት እምትወዳደር መሆን አለመሆንዋ እንጂ የፖለቲካ ሲስተምዋ አይደለም። በተመሳሳይ መንገድ ለሻቢያ መሪዎች ኢትዮጵያ ማን ይምራት ማን ዋናው ጉዳይ የነሱ እንዳስትሪ ጥሬ እቃ አቅራቢ ትሆናለች አትሆንም ነው፤ ኤርትራዊ ማንነት በኢትዮጵያዊነት ላይ ብልጫው ጎልቶ መታየቱ ነው። ይህ እንዴት ይሆናል? መልሱ ሙዝ የመላጥ ያህል ቀላል ነው፤ ኢትዮጵያ በትናንሽ መንግስታት መከፋፈል አለባት። ሻቢያዎች በረሃ ሲወጡ ይዘዉት የወጡት የተሻልን ነን የሚል ስሜት፤ በአፍሪካ ትልቁ ጦር የደመሰስን ነን የሚል ጉራ ተደምሮ የፈጠረባቸው ስካር ገና አልበረደም። ራሳቸውን የእስራኤል ተምሳሌት አድርገው የቀረጹ ሰዎች አሁን የጅቡቲ እኩያ ምድባቸውን አእምሮአቸው ሊቀበለው አይችልም። የሚፈልጉት እነሱ እስራኤል እኛ አረቦች እንድንሆንላቸው ነው። ትልቁ አደጋ ሻቢያዎች ኤርትራዊ ማንነት በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ብልጫ አለው ብለው እሚያምኑ ግብዞች መሆናቸው ነው። ይህንን በቀላል ምሳሌ ማሳዬት ይቻላል። ፕሮፌሰር ጌድዎን አባይ በሙያው የሂሳብ ፕሮፌሰር ሲሆን ሲናገር አፍ እሚያስከፍት የዘመኑ የሻቢያ ሰባኪ ነው። ፕሮፌሰር ጌድዎን ስለ ኤርትራ ማንነት ሲናገር ጀርመናዊው የሂትለር የፕሮፓጋንዳ ሃላፊ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ጎብልስን ያስንቃል።

 እዚህ ቪዲዮ ውስጥhttps://www.youtube.com/watch?v=HML4dOqXorc ጌድዎን ዋሽንግቶን ውስጥ ለሻቢያ እምነት ተከታዮች(ልብ በሉ ወጣቶች በቦታው የሉም) ኤርትራዊ ማንነት ከሌሎች ማንነቶች ሲወዳደር ያለውን ብልጫ ጣራ በሚነካ ጩከትና ትእቢት ሲለቀው ይታያል። ስሙን ሳይጠራ ከኤርትራዊነት ጋራ እየተነፃፀረ እሚጎሸመው ያለው ያው የፈረደበት የኛው ኢትዮጵያዊነት መሆኑ የኤርትራውያን ሚዲያ ለሚከታተል ግልጽ ነው። ጌድዎን በዚህ የቪድዮ ሰባካው ክ40ኛው ደቂቃ ጀምሮ ከሚለው በጥቂቱ እንመልከት፤ 
  • ኤርትራዊ ማንነት ዛሬ አንድ ነገር ነገ ሌላ ነገር አይልም ።እንደ እሥሥት አይቀያየርም 
  • ኤርትራዊ ማንነት በሌሎች ሳንባ    አይተነፍስም። በራሱ እንጂ በድጋፍ አይቆምም 
  • ኤርትራዊ ማንነት እንደወርቅ በሳት የተፈተነ ነው 
  • ኤርትራዊ ማንነት በተረት የተመሰረተ አይደለም። ምኞት የወለደውም አይደለም። 
  • ከአማራና ከትግሬ ጋራ አምልኮ መፈፀም ኤርትራውነትን ያደበዝዛል  
ምንም እንኳን ጌድዎን ይህን ይበል እንጂ መሬት ላይ ያለው ሃቅ እሚያሳዬው ሌላ መሆኑ እሱም ልቡ አይስተውም። በደርግ ጊዜ በኢትዮጵያ ጠላትነት ላይ የቆመው ብሄረተኝነት ከናጽነት በኋላ የተሰጠው ተስፋ ሁሉ ውሃ ስለበላው ኤርትራዊነት በአዲስ ራእይ ማቆም አልተቻለም።ሻቢያዎቹ ኤርትራዊነትን ለማቆም ብቸኛ አማራጫቸው አሁንም በኢትዮጵያ ጠላትነት ዙርያ ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ካሳለፉት መከራ ብዙ የተማሩ በመሆናቸው ሻቢያ በስልጣን እንዲቆይ የሚረዳውን ያደርጋሉ ተብሎ አይጠበቅም። ኢትዮ ወኤርትራ ግንኙነት አንድ ቀን እርቅና ሰላም መውረዱ አይቀሬ ነው። ነገር ግን ይህ የሚሆነው ሻቢያ ያመጣው ያልተገራ ብሄረተኝነት(Wild Nationalism)ሲሰክን ብቻ ነው። ሻቢያ ፕላኑን 180 ዲግሪ ማዞር ይኖርበታል። ይህም በትናንሽ መንግስታት ከተከፋፈለች ኢትዮጵያ ሊያገኘው ያቀደውን ሰርዞ አንድነትዋ ከተጠበቀ፤ ሰፊ እምቅ ሃብት ካላት አገር በመከባበር እንዴት መጠቀም እንደሚችል ማዬት መቻል አለበት። ሻቢያዎች ከተሰቀሉበት ማማ ወርደው ከህዝብ ብዛታቸውና ከኢኮኖሚ አቅማቸው ተመጣጣኝ የሆነ በአካባቢው የሚኖራቸውን ስፍራ እየመረራቸም ቢሆን መቀበል አለባቸው። ኢትዮጵያን የማተራመስ አጀንዳም ግብጽ በረጅም እጅዋ ያልቻለችው እነሱ በውክልና ሊያስፈጽሙት እንደማይችሉ ሊረዱት ይገባል። ይህ ሲሆን ነው ለኢትዮጵያውያን እርቅና ሰላሙ ትርጉም ሊሰጥ የሚችለው። 

No comments:

Post a Comment