Thursday, November 5, 2015

ላጲሶን ለማወቅ በትዕግስት ያንብቡት!!!

መሰለ ተሬቻ ከበደ፣ ሐሙስ ጥቅምት ፳፭ ቀን ፪ሺህ፰ ዓም

 ምንጭ፦ https://www.facebook.com/amanuel.abinet/posts/773206409456281

 ዶክተር ላጲሶ ለኢትዮጵያ መሀበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ እሴቶች ምንም ክብር የሌላቸው፤ የኢትዮጵያንም ታሪክም ሆነ የታሪክ ምሁራንን እንደው እንዳሻቸው ለመጠልሸት ሳይታክቱ ከአርባ አመታት በላይ የተጉ፤ ይህንንም የሚያደርጉበትን ምክንያት “እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ” ከሚለው ትዕቢታቸው በሻገር ለማወቅ የሚያዳግት ሰው ናቸው፡፡ ከልጅነቴ አንስቶ እኚህን ሰው ሳወቃቸው የኢትዮጵያን ታሪክ እና የታሪክ ሊቃውንት ሲያጠለሹ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትግር፣ አማራ፣ ሀድያ፣ ሀርላ፣ … ወዘተ እያሉ ሲከፋፍሉ ሲሆን እጅግ በሚያስደንቅ ሀፍረተ-ቢስ በሆነ መንግድ እየተገለባበጡ ከመጣው ስርዓት ጋር እንደ ኮሶ ተውሳክ እየተጣቡ በዚህ መያዣ መጨበጫ በሌለው ትንታኔያቸው/አሉባልታቸው ሲያታልሉበት ኖረዋል፡፡ ደረግ ስልጣን ላይ በነበረ ዘመን ከማርክስ በላይ ማርክሲስት ሆነው ያልዘላበዱት የማርክሲስት ርዕዮታለም አልነበረም፡፡ እኔ አንደኛ ክፍል እያለሁ አንስቶ የእርሳቸውን ህልመኛ ርዕዮት-አለም ስጋት አድጋለሁ፡፡ ዛሬ ታዲያ የዛን ግዜ ስብከታቸውን ባስታወስኩ ቁጥር ለብቻዬ የምስቅበት ግዜ ብዙ ነው፡፡ በኋላ መቶ ሰማንንያ ድግሪ ተሸከርክረው የጎሳ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ ሆነው ስናይ እኔና ጓደኞቼ እጅግ ነበር የተደናገርነው፡፡ ይህ ተውልድ እኝህን ሰው እኩይ ስራ አበክሮ መርምሮ ወግድ ወዲያ ሊላቸው የተገባ ነው፡፡ 

አሁን እዚህ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አብክሮ ላደመጠው እንኳን ከእጅግ ተራ የቦታና የግዜ የእውነታ/fact ስህተት እስከ ከፍተኛ የሀሳብ ፍልሰት በግድፈት የተሞላ እንደ ሆነ ለማወቅ አያዳግተውም፡፡ አሁን በቅርብ በሰጡት ቃለ-ምልልስ የኢትዮጵያ የደብተራ አሉባልታ የኢትዮጵያን ታሪክ ያጠኑት ምሁረን ማለትም ስርገው ሀብለስላሴ፣ ታደስ ታምራት፣ መርድ ወልደ አረጋይ፣ ባህሩ ዘውዴ … እና ሌሎችም ደብተራዎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያም ታሪክ በደብተራነት ጉድፍ የተሞላ ነው፤ ተስተካክሎ መፃፍ ይኖርበታል ብለው ነበር። አሁን በዚህ ቃለምልልስ ደግሞ አዋቂ መስለው የእነኚህኑ ምሁራን ስራ እያዛቡ መልሰው ሊተርኩት ሲዋጁ ይስተዋላሉ፡፡

«አማራ የአገው ወታደር የነበረ ነው» ይሉና መልሰው እራሱን የቻለ፣ የሰለሞን ስረው መንግስትን የተከል እና ከግብፃውያን እየዶለተ ሌሎችን ጎሳዎች እያረደ የገዛ ነው ይላሉ፡፡ ንግስት እሌኒ የሐድያ ሙስሊም ነበሩ፣ እጅግም ተፈርተው 75 አመታት ከልጅ ልጆቻቸው ጋር አንቀጥቅጠው ገዝተዋል ይሉና፤ የሰለሞን ስረው መንግስት የአማራዎች ነበር ይላሉ፡፡ እንደ አማራ ፈርጀው ያቀረቡትን አፄ ዘርዓ ያቆብን መልሰው አክሱምን እየሩሳሌም አደረገ ይሉታል፡፡ አፄ ዘርዓ ያቆብ በ1416 ዓ.ም ሞተ ይሉና መልሰው ደግሞ በ1550 ዓ.ም የደብረ ምጥማቅን የአበው ስብሰባ ጠርቶ በቅዱስ ኢዎስጣጤዎስ እና በቅዱስ ተክለ ሐይማኖት ሀይማኖተ ቀኖናን በተመለከተ ለዘመናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክሰርስቲያን የነበረውን መከፋፈል አስወገደ ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳንን፣ የታቦት ስርዓትን፣ አምልኮ ማርያምን… ወዘተ የደነገገው ዘርዓ ያቆብ ነው … ወዲያም ሲል ክብረ-ነገስት እና ፍትሀ ነገስት በአንድ ወቅት ተተረጉመው የሰለሞን ስረው መንግስት መለኮታዊ ስልጣን ማስጠበቂያ ሆኑ … ውዳሴ ማርያም መጀመሪያ በፈረንሳይ ተፃፈ ብለው ያበቁና መልሰው ደግሞ ከአረብኛ ተተረጎመ ይላሉ፡፡ … እነኚህ ሁሉ አንድ ታሪክን አነበብኩ ከሚል ሰው የማይጠበቁ ለይቅርታም እጅግ የሚያስቸግሩ ስህተቶች ናቸው፡፡

የብሉይ እመነት በኢትዮጵያ እና በአረቢያ ገልፍ ከክርስትና በፊት የነበረ ሀይማኖት ስለመሆኑ እጅግ ብዙ ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡ የታቦትንም ስርዓት አፄ ዘርዓ ያቆብ አልደነገጉም፡፡ ከከሳቴ ብርሀን ዘመን እንስቶ የነበረ ነው፡፡ ክብረ ነገስት በዓረብኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች ከተፃፉ ልዩ ልዩ ታሪኮች ተወጣጥቶ የተቀናበረ ሲሆን የተፃፈውም በ13ኛው መ.ክ.ዘ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ፍተሃ ነገስት ግን መጀመሪያ የተፃፈው አንድ አብድ አል-አሳል በተባለ ግብፃዊ ስሆን በ15ኛው መ.ክ.ዘ እንደ ተተረጎመ ያታመናል፡፡ ከ16ኛው መ.ክ.ዘ መባቻ በፊት ግን ስራ ላይ ስለመዋል ምንም የተገኘ ማስረጃ የለም፡፡ በአፄ ዳዊት ዘመን የተተረጎመው ታምረ ማርያም እንጂ ውደሴ ማርይም አይደለም፡፡ ዘርዓ ያቆብ የነገሱት እ.ኤ.አ ከ1434 እስክ 1468 ዓ.ም ሲሆን የደብረ ምጥማቅ ጉባኤም የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1450 ዓ.ም ነበር፡፡ የኢዎስጣጤዎስ የሀይማኖት ንቅናቄ ከብሄርም ሆነ ከደቂቀ አስጢፋኖሶች ጋር ምንም የማይያያዝ መሰረቱን በደብረ ቢዘን ያደረገ የስርዓተ ቀኖና አጠባበቅ አለመግባባት ነበር፡፡ … ንግስት እሌኒ ሀድያ ይሁኑ የደዋሮ ተወላጅ እስከ ዛሬ ምሁራን ሙሉ ለሙሉ አልተግባቡትም፡፡ ነገር ግን ብዙሀን ምሁራን ግን የደዋሮ ተወላጅ እንደነበሩ ይስማማሉ ።

ዶ/ር ጌታሁን ዴሊቦ የከምባታ እና ሀድያ ተወላጅ ሲሆኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህረታቸውን የሱዳን ኢንቴሪየር ሚሲዎን አቋቁሞት በነበረው የኩየራ የስጋ ደዌ ተጠቂ ሰፋሪዎች ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት ባይብል አካዳሚ እና የዶክትሬት ትምህርታቸውን በሆዋርድ በተባለ የአሜሪካን ጥቁሮች ዩንቨርስቲ ስለመከታተላቸው ይታወቅ እንጂ፤ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪያቸውን የት እና እንዴት ባለ ሁኔታ እንደተከታተሉ አይታወቅም፡፡ የዶክተሬት ድግሪ የሟሟያ ስራቸውን ለመረመረው፤ ከታሪክ አጠናን መንገድ እስከ መረጃ አሰባሰብ በበርካታ ግድፈቶች የተሞላ፣ እንኳን ለዶክተራል ለመጀመሪያ ድግሪ ሟሟየነት የማይመጥን፣ ከዚህ የተነሳ ምራቅ በዋጡ ምሁራን ለማጣቀሻነት ያልዋለ/የማይውል በሚሲዎኖች የዘመናት አትዮጵያን የማፍረስ የአሉባልታ ሴራ የተሞላ የሴራ ድርሳን ስለመሆኑ ለመረዳት አያዳግተውም፡፡ የእርሳቸውን ስራ ሲጠቅሱ ያየሁት ከመረጃ ይልቅ በስሜት ሞገድ የሚናጡ ጎሰኛ የታሪክ ፀሀፊዎችን ብቻ ነው፡፡ ቀድሞ ነገር ለግዕዝ ቋናቋ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው ሰው እንደሆኑ እየተዋቅ የታሪክ መረጃዎች በግዕዝ ቋንቋ ስለተያዙበት የመሐከለኛው ዘመን እና የቤተ-ክርስቲያን ጉዳይ እርሳቸውን ማናገር ተገቢ ነገር መስሎ አይታይም።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉበትን ሁኔታ ለሚመረምር ግን የእኝህን ሰው የአመታት የአትዮጵያን ታሪክ የማጠልሽት አባዜ ለመረዳት ከባድ አይሆንበትም፡፡ የከንባታና የሀድያ ማህበረሰብ ለሚሲዎን ሐይማኖታዊ ተልዕኮ የተመቸነው ከሚል እሳቤ በተሰራ አፍትሀዊ መድሎ፤ በእነ አቶ የሀንስ በኪሶ አቅራቢነት በእነ ሙላቱ ባፋ አስተኝታኝነት፤ የስጋ ደዌ ተጠቂ ያልሆኑት የከምባታ-ሀድያ ተወላጆችን በኩየራና በአከባቢው ከመስከረም 1944ዓ.ም ጀምሮ ሀገሬውን ከመሬቱ እየገፉ እንዲሁም የሌላ ብሄር ሰፋሪን ወደ ጎን እየከሉ እንዲሰፍሩ የህክምና አገልግሎቱም የበተለይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገብት ሁኔታ ውሎ አድሮ በ1966 እና 1983 ዓ.ም የስርዓት ለውጦች ወቅት ምን እነዳስከተለ በተጨባጭ ይታወቃል፡፡ በትንሹ በ1983 ዓ.ም የፖለቲካ ለውጥ ወቅት ከ2000 በላይ የከንባታና የሀድያ በሀገሬው የኦሮሞ ብሄር ተወለጆች ጥቃት እንዲፈናቀሉና ሀብት ንብረታቸው ለዝርፊያ እንዲዳረግ የተደረገበት መሰረታዊ ምክንያት ደ/ር ጌታሁን ዴሊቦን ከልጅነት በመድሎ ኮትኩቶ ያደረጀ የሚሲዎኖች ኢፍትሀዊ ስራ ነበር፡፡ 

ይህን እርሳቸውን የፈጠረ የሚሲዮን መድሎአዊ አሰራር ለማየት የማይዳዱት የዶ/ር ጌታሁን ምሁራዊ እይታ፤ “የአማራን መድሎ” ለማየት ሲተጋ፤ “አያ ጅቦ በማያውቁት ሀገር ቁረበት አንጥፉልኝ አለ” ሚለውን ተረታዊ ምሳሌ ያሳስባል፡፡ ታዲያ ይህ የሚሲዎኖች መድሎአዊ አሰራር ከመሬት ስሪት ጋር ተቆራኝቶ የፈጠረውን መሀበራዊ ቀውስ፤ ሌላኛው የተደናገረ የጎሳ ብሄርተኛ የታሪክ ተመራማሪ ነኝ ባይ ጌታሁን በንቲ የአማሮች ነፍጠኞች ኢፍትሀዊ ሴራ እንደሆነ አድርጎ በሁለኛ የድግሪ የሟሟያው አቀረበው፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይመለስ እንዲሉ ይህንኑ የተንሸዋረረ የታሪክ አረዳዱን፤ ጌታሁን በንቲ ለዶክተራል ድግሪው የአዲስ አበባን ታሪክ ሲፅፍ ደገመና አረፈው፡፡ የዛሬው ለጲሶ፤ ቅድመ 66 ዓብዮት ጌታሁን ዲሌቦ፤ ሀፍረትን የማያውቁ… ሀገር ለማፍረስ የተጉ የምሁርነትን ካባ በተግባር ሳይሆን በአስመሳይነት የተጎናፀፉ ሰው እንደሆኑ ማወቁ እጅግ ጠቀሚ ነው፡፡ 

No comments:

Post a Comment