ለወገን ችግር ደራሹ ወገን ነው!
ባለፉት ፳፬(ሃያ አራት) ዓመታት በዐማራው ነገድ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል የቱን ያህል የከበደ እንደሆነ የሚያውቀው የግፉ እና የመከራው ተሸካሚ የሆነው ዐማራው መሆኑኑን ማንም አይስተውም። ያም ሆኖ ግን፣ ሰብአዊነት የሚሰማው ማናቸውም ሰው፣ በሰዎች ላይ የሚፈጸምን ግፍ እና በደል በራሱ ላይ እንደተፈጸመ በመቁጠር፣ድርጊቱን ለማስቆም የሚችለውን ሁሉ ያደርጋል። ለተራቡት የርሃብ ማስታገሻ ያጎርሳል፤ ለታረዙት የእርቃን መሸፈኛ ከፈን ይለግሣል፤ ለተጠሙት የውኃ ጠብታ ያስጎነጫል፤ አልፎ ተርፎም ግፍ ፈጻሚዎች ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል።
በዓለም ዙሪያ በስደት የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በወገኖቹ ላይ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ የሚፈጽመውን ግፍ ለዓለም ኅብረተሰብ ከማጋለጥ በተጨማሪ ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ ላጡ ወገኖቹ የሚችለውን ያህል እጁን ከመዘርጋት የታቀበበት ወቅት የለም። ይህ ተግባሩ በሕይዎት ሳለ የመንፈስ ልዕልናን ሲያጎናጽፈው፣ በመጨረሻ የሕይዎት ዘመኑም «ስራብ አብልታችሁኛል? ስጠማ አጠጥታችሁኛል? ስታረዝ አልብሳችሁኛል? እንግዳ ስሆን አስተናግዳችሁኛል? ስታሰር አስፈትታችሁኛል?» ተብለው ከፈጣሪያቸው ለሚጠየቁት ጥያቄ አዎንታዊ መልስ እንዲኖራቸው የሚያስችል በመሆኑ የጽድቅን ጎዳና መከተሉን ያሳያል። ይህ ተግባር ለረጅውም ሆነ ለተረጅው ሥጋዊ እና መንፈሣዊ ጉዳዮችን አጣምሮ በቀና ጎዳና መጓዝን የሚያመለክት በመሆኑ ይበል የሚያሰኝ ነው።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ከተመሠረተበት ዕለት ጀምሮ ለማድረግ የሚሞክረው ይህንኑ ተግባር ነው። ስለሆነም «ለወገን ችግር ደራሹ ወገን መሆኑን» በማጉላት፣ በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው ለከፍተኛ ችግር ለተጋለጡ ወገኖቻችን የችግር ማቃለያ፣ የቀን መግፊያ የሚሆን ዕርዳታ በማሰባሰብ ላይ ይገኛል። ሰሞኑን ደግሞ በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን እንዲሁም በደቡብ ክልል በቤንቺ ማጅ ዞን፣ በጉራፈርዳ ወረዳ ካለፈው የ2004 ዓም ዕልቂት በተአምር ተርፈው የነበሩትን በርካታዎቹን ዐማራዎች ገድለው የቀሩትን በማፈናቀላቸው፣ ለዕለት ምግብ፣ ልብስ እና መጠለያ የሰው እጅ እንዲመለከቱ አድርገዋቸዋል። ለነዚህ ወገኖች ካለእኛ ካለወገኖቻቸው ሌላ ሊታደጋቸው የሚችል ባለመኖሩ፣ ሞረሽ-ወገኔ ለእነዚህ ወገኖች ሕይዎት ማቆያ የሚሆን ዕርዳታ ለማሰባሰብ ተዘጋጅቷል። ስለሆነም ሰብአዊነት የሚሰማን ሁሉ፣ በጭፍን የዘር ጥላቻ ላይ ተመሥርቶ ከጥይት አልፎ በርሃብ አሰቃይቶ ለመግደል የተወሰነባቸውን ወገኖቻችንን ሕይዎት ለመታደግ በሚከተለው የባንክ ሂሳብ ቁጥር የምትችሉትን ዕርዳታ እንድትለግሱ በተፈናቃይ ችግረኞች ስም ይጠይቃል።
Bank of America
Account Number: 435030804511
Router Number: 051000017
SWIFT Number: BOFAUS3N
ሞረሽ ወገኔ ዐማራ ድርጅት
No comments:
Post a Comment