Thursday, October 2, 2014

አማራው የራሱ ሚዲያ ኖሮት ቃል በቃል ምላሽ እስኪሰጥ ድረስ፥ ምላሽ ለጀዋር መሃመድ የቃለ ምልልስ ቅጥፈት

በአበበ ተድላ፣ እሑድ መስከረም 18 ቀን 2007 ዓም (By Abebe Tedla, Sunday September 28, 2014) Source፦ https://www.facebook.com/abebe.tedla.1/posts/1495262307392717

በትክክለኛው መሆን የነበረበት በሚዲያዎች ይህ ሰው የሰጠው ቃለመጠይቅ እየተደመጠ ቃል በቃል ምላሽ መሰጠት ነበረበት። ነገር ግን አማራው በሁሉም ዘርፍ ሊከላከልለት የሚችል አካል ስለሌለው እና ሚዲያውንም ጨምሮ መሳ ለመሳ የሆነ የተጠናከረ ሃይል ለጊዜው ስለሌለው፣ በግሌ ለግለሰቡና ለሱ ሃሳብ አራማጆች መልስ ልሰጥ ተገድጃለው። እዚህ ጋር ቃለመጠይቁን ፖስት ማድረጌ መርዝ ንግግሩን ማሰራጨት ቢሆንም አዲስ ሃሳብ ሳይሆን ሁሌ የሰማነው ስለሆነ እና ባግባቡ መልስ እስከተሰጠበት ችግር የለውም ብዬ ነው ለመረጃነት አብሬ ያቀረብኩት። መልሱም ቃል በቃል ሳይሆን ጠቅለል ባለ መልኩ በሁለት ክፍሎች ከቀረቡት የተወሰኑ የከፉ ውሸቶችን/ግነቶችን
ነው።
1. “በአንድነት ስም ያሉ ፓርቲዎች (ባንተ አገላለፅ አማራዎች) እኔ ኦሮሞነቴን እንኳን ሊቀበሉ አይፈልጉም ኦሮሞ ነኝ ስል ዘረኛ ይሉኛል።” ጀዋር መሃመድ
እንግዲህ ከዚህ የበለጠ ውሸት ምን ሊኖር ይችላል። ማን «ኦሮሞ ነኝ» ብለህ «ኦሮሞ አይደለህም» ያለህ አለ? ይልቅስ አስበኸው ታውቃለህ ኢትዮጵያዊያን በጣም የተቀላቀልን ስለሆንን የተለያየ ብሄር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን «የለም አንዱን ወገኔን መካድ አልፈልግም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ» ሲሉ መብታቸውን እንደተከለከሉ እና አንዱን ክደው አንዱን እንዲመርጡ እንደተገደዱ? ከኦሮሞ ይልቅ አማራ ማንነቱን እንዲያጣ እንደተካደ ልብ ብለህ ታውቃለህ? «ኢትዮጵያዊ ነኝ፣ ብሄር መቁጠር አልፈልግም» ሲል አማራ «የለም እንዲህ የሚሉት የድሮው ስርአት ናፋቂዎች ናቸው» እየተባለ ኢትዮጵያዊ ነኝ እንዳይል ጥረት ይደረጋል፣ አፉን ያዘጉታል። «እሺ እንግዲህ የቸገረ ከሆነ እና ወደኋላ ተመልሰን ብሄር መቁጠር ግድ ከሆነ ልቁጠር አማራ ነኝ» ሲል «የለም አማርኛ ተናጋሪ እንጂ አማራ የሚባል ብሄር የለም» ይሉታል። ሰዎች አማራ ብሄር ብለው እያሳደዱት፣ እየገደሉት እነሱ «አይደለም አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ተሰደዱ» ይላሉ አስሰዳጆቹም አማርኛ ቋንቋ እየተናገሩ። አሁን ሰሞኑን ደግሞ «ከመሃል አገር የመጡ፣ ከሰሜን የመጡ» መባል ተጀምርዋል። አማራው ተለይቶ ሲጠቃ እያየን «አማራው ተጠቃ» ላለማለት። እንግዲህ ኢትዮጵያዊም መሆን፣ አማራም መሆን የተነፈገው አማራ እያለ አንተ እሹሩሩ ለተባልክ፣ ምን ተብለህ ነው «ኦሮሞ ነኝ ስል ኦሮሞነቴን አልተቀበሉኝም» የምትለው? «የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ» ማለት ይሄ ነው። አዎን ምንም ስለ ብሄር እኩልነት ብናወራ ብሄር ከሃገር አይበልጥም ስለዚህ "Oromo First" and "Ethiopia out of Oromia" ማለትህ እንዳሳፋሪነት ቢጠቀስ ኦሮሞነትህን መካድ አይደለም። አንተ ያለህበት አገር አሜሪካ በሃገር ጉዳይ/ጥቅም ምንም ድርድር የለም እና «በሃገር መደራደር አትችልም» ነው የተሰጠህ መልስ እንጂ «ማን ኦሮሞ ነኝ አትበል፣ ቋንቋህን አትናገር፣ ባህልህን አትጠብቅ፤» አለህ? ግልፅ ነው መጀመሪያ ሰው ስለራሱ፣ ከዛ ስለቤተሰቡ፣ ከዛ ስለቤተዘመድ፣ ከዛ ስለአካባቢው ሰው (ባንተ አስተሳሰብ ስለብሄርህ በለው) ያስባል። ነገር ግን ስለራስህም ሆነ ስለሌላው ለማሰብ የሚቻለው መሬት ላይ ቆመህ፣ አገር ላይ ቆመህ ነው እንጂ አየር ላይ ቆመህ ስላልሆነ «ቅድሚያ ስለሃገር ማለት ነበረበት» ተብለህ ብትወቀስ አይገርምም። ለነገሩ አንተና መሰሎችህ እንደ ኤህነግ (ሻቢያ) ከኢትዮጵያ መሬት ላይ ቆርሳቹ አዲስ አገር ስለማቋቋም እንጂ (ያውም በሸሪያ የሚተዳደር አገር) ስለእኩልነት ስለማታስቡ አገር የምትሉት ማንን እንደሆነ ይታወቃል። በሚቀጥለው ነጥብ ላይ መልስ እሰጥበታለው።
2
2. “የአንድነት ፓርቲዎች (በተለይም አማራዎች) ትንሿን የፌደራሊዝም መብታችንን እንኳን ሊቀበሉ ዝግጁ አይደሉም።” ጀዋር መሃመድ
ብሄርተኝነት አይንን እንደሚከልል ቢታወቅም ይሄን ያህል ግን እንደሚያሳውር እና አንድ የማሰቢያ አእምሮን ቆርጦ እንደሚያወጣ በጀዋር እና መሰሎቹ መረዳት ችያለው። እንዴት ነው ነገሩ እነሱ (ትህነግ፣ ኦነግ፣ ወዘተርፈ) ያሉትን የብሄር ፌደራሊዝም (ያውም የአማራውን ብሄር መብት ያላካተተ የብሄር ፌደራሊዝም) አለመቀበል ማለት አጠቃላይ የፌደራሊዝምን ስርአት አለመቀበል ነው ያለው ማነው? «በድሮው ስርአት አልተወከልንም፣ ድምፃችን አልተሰማም» የሚል ወገን እንዴት ነው 1/3 የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ አማራው ባልተወከለበት የተካሄደ የመሬት ሽንሸና ያለማመንታት ተቀበሉ የሚሉን? ሲጀመር ድሮም አሁንም እኮ አማራው ደሃ ነው። «ጥቂት የአማራ ልሂቃን ናቸው አገሪቱን ከሌላው ብሄር ልሂቃን ጋር ሆነው የጨቆኑት፣ ያ ደሞ የኦሮሞ ልሂቃንንም ይጨምራል፤» ሲባሉ «የለም እነኛ ኦሮሞዎች ኦሮሞን አይወክሉም፤» ይሉናል። እኔምለው መቼ ነበር አማራው ታዲያ ይወክሉኝ ብሎ ልሂቃኑን ልኮ የተወከለው? በቃ የተደራጀ ጉልበት ያለው ያሻውን አድርጎ አለፈ እንጂ። «ከቀደሙት መሪዎች መልካም ነገራቸውን ተምረን፣ ጥፋታቸውን እንዳይደገም አድርገን እንለፍ፤» ሲባሉ የለም «መጀመሪያ ይሄንን የሰራነውን የብሄር ካርታ ተቀበሉና፤» ይላሉ። አለበለዚያ እምቢ ካልክ በደፈናው የድሮ ስርአት ናፋቂ ሌላም ሌላም ስም ይሰጥሃል ነው ጨዋታው ማለት ነው? ስታስቡት በሰሜን ትግራይ፣ በምስራቅ አፋር፣ በምዕራብ ቤኒሻጉል፣ በደቡብ ደሞ ኦሮሚያ እያላቹ፣ አጎቶችህ ኦነግ ከትህነግ (ወያኔ) ጋር ተስማምቶ፣ አማራንም ሆነ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ህዝበ ውሳኔ ሳይጠይቅ የተፈጠረ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ ባንቱስታን ስታይል የተከተለውን አከላለል ተቀበሉ ስትሉ አታፍሩም? አዲስ አበባን ጨምሮ ቁጥራቹ ያነሰበት ቦታ «የለም በታሪክ የኛ ነበር» ትላላቹ ልክ ምድር ስትፈጠር ጀምሮ ኦሮሞ ብቻ እዛ ቦታ የኖረ ይመስል
(ታሪክ እኮ የ200 አመት ብቻ ሳይሆን 500 ከዛም 1000 ከዛም 3000 እያለ ይቀጥላል፤ ቅንጭብ አድርጋቹ አትውሰዱ)። ያውም እንደኢትዮጵያ ባለ ብዙ ሲቪል ዋር ውስጥ ባለፈች፤ ህዝብ ከቦታ ቦታ በጦርነት፣ በረሃብ፣ በተለያየ ምክንያት በሚሰደድባት በሚቀላቀልባት ሃገር፤ «ይሄ ቦታ የኛ ብቻ ነው» ሲባል እንዴት ሰው አያፍርም? እህ በአማራ መካከል በዛ ያለ ኦሮሞ ሲኖር ደሞ የአማራ ክልል ብላቹ ቁራጭ ከሰጣቹት መሬት ላይ ልዩ ዞን ምናምን ተብሎ ለብቻ ይከለላል። ምነው ኦሮሚያ የተባለው ክልል ውስጥ በርካታ ያውም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር አማራ ያለበት ቦታ ልዩ ዞን አልተፈቀደም?
«አማራው የመምረጥ የመመረጥ መብት አለው፣ ኦሮሚያ በተባለው ቦታ ሁሉ ነው፤» ያልከው ሳታፍር በዛውም የትህነግን የምርጫ ድራማ እያፀደክላቸው ማለት ነው? እስቲ ሃረር፣ ድሬዳዋን እንመልከት፥ አማራም፣ ኦሮሞም፣ ሃረሪም፣ ሶማሌም፣ ሌላውም አለ። ነገር ግን አማራው ብዙ ቁጥር ቢኖረውም ተለይቶ መብቱ እንዳይከበር እና በሌሎች መልካም ፍቃድ እንዲኖር የተደረገበትን ስርአት ነው እንግዲህ አንተና መሰሎችህ ያለድርድር ተቀበሉ የምትሉት? አሳፋሪ ነው። የሁሉንም መብት የሚያከብር ሁሉን አቀፍ የሆነ ስርአት ማሰብ አትፈልጉም።
«አገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ ሳይኖራት የተለያየ አገር ከምትሆን (አሁን አማርኛ ፌደራል ቋንቋ ብቻ ነው)፣ ቢሆን ህዝቡ ከመረጠ ሁለት ብሄራዊ ቋንቋ ይኑራት፣ እና አንድ ሰው ሌላ የሃገሪቱ አካባቢ ሲሄድ ሌላ ሃገር የሄደ ይመስል አዲስ ቋንቋ ያውም ብሄራዊ ቋንቋ ያልሆነ ማጥናት ሊገደድ አይገባም፣ ቋንቋ ማወቅ መልካም ቢሆንም፤» ሲባል «የድሮ ስርአት ናፋቂዎች» ምናምን ትላላቹ፣ እንዲህ ያለ «ቢቻል ሁለት ብሄራዊ ቋንቋ ይኑረን» የሚል ሃሳብ ድሮ ያለ ይመስል። አንድ አማራ የተባለ ክልል ውስጥ ተወልዶ አማርኛ ብቻ የሚናገር ወይንም የሌላ ክልል የተባለ ግን ከተማ ስለሆነ አማርኛ በብዛት ስለሚነገር አማርኛ ብቻ እየተናገረ ያደገ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ አማርኛ ስለሆነ የሚናገረው ትግራይ ተብሎ የተከለለው ልሂድ ቢል ትግርኛ ማጥናት አለበት። ወይ ደሞ ኦሮሚያ ተብሎ ወደተከለለው ቢሄድ ምንም እንኳን ብዙ አማርኛ ቋንቋ የሚነገር ቢሆንም የስራው ቋንቋ ኦሮምኛ ብቻ ስለሆነ የግድ ኦሮምኛ ማጥናት አለበት። ምናለ ሁለት የስራ ቋንቓቋ ቢኖረን? እኔ በቋንቋዬ ልጠቀም ያለ ሰው በሚሊዮን የሚቆጠር ሰው እንዴት በቋንቋው እንዳይጠቀም ይገደዳል? ምሳሌ ደብረዘይት፤ ወደ ሶማሌ ወደተባለውም ከሄደ እንዲሁ ማለት ነው። ታዲያ ስንት ቋንቋ ያጥና ያ/ያቺ ሰዉ በገዛ አገሩ ለመኖር? ሌሎቹ
3
ብሄሮች ግን አማርኛን በተለያየ አጋጣሚ ስለሚማሩ የናንተ ተብሎ ከተከለለው ውጪ አማርኛ ይጠቀሙ ተብለው የተከለሉ ቦታዎችም ይሰራሉ። ከዚህ በላይ አፓርታይድ ስርአት አለ። ህዝቡ እስከመረጠ ድረስ አገሪቱ ሁለት ብሄራዊ ቋንቋ (ፌደራል ቋንቋ አላልኩም) ቢኖራትና እና «ሌላው ህዝብ ደሞ ከብሄራዊ ቋንቋ በተጨማሪ አካባቢያዊ ቋንቋ ይጠቀሙ ቢያንስ ሁሉንም የሚያግባባ ነገር ስለሚያስፈልግ እንደ አንድ ሀገር የሚያግባባን ነገር እንዲኖር » ሲባል «የለም፣ አካኪ ዘራፍ ከኦሮምኛ ውጪ ኦሮሚያ ተብሎ በትህነግ የተሰመረው ቦታ አይነገርም፤» ትላላቹ። ትህነጎቹም ደሞ «ከትግርኛ ውጪ ሌላ ቋንቋ እዚህ አካባቢ አይነገርም» እንደሚሉት፣ ወዘተርፈ። አማራም ሆኖ «ከአማርኛ ውጪ እዚህ የአማራ ተብሎ ትህነግ ያሰመረው ውስጥ እንዳይነገር» የሚል ካለ ከናንተ አይለይም። በግሌ አማርኛና ኦሮምኛ ብዙ ተናጋሪ ስላላቸው የሀገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ ቢሆኑና ሁሉም በየአካባቢው ከራሱ ቋንቋ በተጨማሪ በብሄራዊም ቋንቋ(ዎች) ቢጠቀም አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ ያስማማል ባይ ነኝ። ያኔ ውድድሩ ለሁሉም እኩል ይሆናል። አገሪቱ የሁሉም ትሆናለች ማለት ነው። ኬንያ እኔ ከምናገረው ተመሳሳይ የሆነ ስርአት ነው የምትከተለው። «በጣም ውድ የሆነ ነገር ነው የምታስበው፣ ከሃገሪቱ ኢኮኖሚ አኳያ አያዋጣም፤» ለምትሉ ስንዋጋ ከምንኖር እና ገንዘቡ ለስለላ ከሚውል ለቋንቋ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች ቢውል እና ሰላም ብንሆን ይሻላል ባይ ነኝ። ግን ውሳኔው የህዝብ ነው። አለበለዚያ ወይ ቁርጥ ባለው ፓስፖርት መጠየቅ እኮ ነው የቀረው ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀስ በገዛ አገራችን። ያ ደሞ አይሆንም፣ አንቀበልም። ምክንያቱም አከላለሉ አማራን ግምት ውስጥ ያስገባ አልነበረምና። እንዲሁም ደሞ በብሄር ክልል ድንበር መቼም ልንስማማ አንችልም፤ ተቀላቅለን ስለኖርን የብህር ክልል ማስመር አይቻልም አሁን እንዳለው ጉልበት ያለው ድንበር ያስምር ካልሆነ በስተቀር ጨዋታው። ለነገሩ ህገመንግስት የተባለው የኢትዮጵያ ድንበር ሳይሆን የአገሪቱን ክልል ያላቸውን ድንበር ስለሆነ የሚጠቅስ ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ራሱ በህገመንግሱቱም የለችም። ይሄ የጋራ ቋንቋ እንዳይኖረን የተደረገው ዘዴ ትህነጎች (ወያኔዎች) ትግራይን ለግል ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍል በጋራ ለመጠቀም ብለው ኤርትራዎች ያደረጉትን «ኤርትራን ለግል፣ ሌላውን ኢትዮጵያ በጋራ» ብለው መጀመሪያ እንዳሰቡት ማለት ነው። በተጨማሪም አላማው አገሪቱን በረጅም ጊዜ ለማፍረስ ነው። «እንደ ሃገር አንድም ይሁን ከዛ በላይ ብሄራዊ ቋንቋ ይኑረን፤» እንደሃገር ስትባሉ «ኢትዮጵያ እንድትኖር የሚፈልጉ የቀድሞ ስርአት ናፋቂዎች፤» ትላላቹ። ለመሆኑ ሌላ ቦታ ተውና አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ በሆነችው አርከበ የሆነች ሰአት ከመሾሙ በስተቀር ለምን ኦሮሞ ከንቲባ ብቻ ሁሌ ይሾማል በትህነግ ዘመን? ሌላ የሚመጥን ሰው የለም? ይሄንን ነው ዋና ከተማ መብት ሳይኖር «ሁሉም ቦታ አማራም ማንም የመመረጥ መብት አላቸው» የምትለው? ለነገሩ የትስ ማንም ይሾም ማን ትህነግ ነው የሚያስተዳድረው፣ ጉልቻ ማለዋወጥ ካልሆነ፣ እንዲያው ለነገሩ አነሳሁት እንጂ። ችግሩ ምን መሰለህ የአንድነት ፓርቲ የሚባሉትም ኦሮሞውን እንዳይከፋው በሚል ይሄንን አሳፋሪ የአከላለል ሸፍጥ ሲያነሱ እና ስለ ችግሩ ሲከራከሩ፤ አማራ በአከላሉ አለመወከሉን ሲናገሩ አይሰሙም። «አማራውን ሲፈልገው ይከርፋው ኢትዮጵያ የምትባለውን ስም እስከጠራን የትም አይሄድም» በሚል የተሳሳተ ግምት። አልፎ አልፎ «የወልቃይት ጠገዴ ከዚህ በፊት ትግራይ ሆኖ አያውቅም አሁን ነው ወደ ትግራይ የተከለለው» ከማለት በስተቀር። ፕ/ር አስራት ወልደየስ የተቃወሙትን እና ህይወታቸው ያለፉበትን ምክንያት አማራው 1/3 የኢትዮጵያ ህዝብ ሆኖ ሳለ አንድም አማራ ሳይወከል ህገመንግስት ተብዬው ጭምር እንደፀደቀ የአንድነት ፓርቲዎችን ጨምሮ ማንም ሲቃወም አይሰማም። ስለዚህም የልብ ልብ ተሰማቹ እና by default ሁሉም ሰው ይሄ ብዙ ሚሊዮን አማራም ሆነ ሌላውን ኢትዮጵያዊ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ የሚያደርግ ሲስተም የአለም ምርጥ ፌደራሊዝም እንደሆነ የትህነግ (ወያኔ) አፈቀላጤ ሆነህ እየተናገርክ ከዚህ ውጪ አይታሰብም ትላላቹ። የሚገርመው ደግሞ «በኦነግም ቻርተር ላይም ይሁን አሁን ኦሮሚያ ተብሎ በተከለለው ውስጥ ያለው ሌላው ኢትዮጵያዊ እኩል የመምረጥ የመመረጥ መብት አለው፣ መብታቸው እየተከበረ ነው፤» ያልከው? አሳፋሪ ሰው ነህ «የትህነግ ምርጫ የውሸት ነው፤» እንዳላልክ አሁን ደሞ የኢትዮጵያ ህዝብን ንቀህ፣ አያስተውልም ብለህ፣ ይሀው ሌላ ውሸት ታወራለህ። በመጀመሪያ ትህነግ ህገመንግስት ተብዬው ወረቀት ላይ ስለ እኩልነት ያልፃፈው ህግ አለ? ስለሰብአዊ መብት አከባበር ምን ያልፈረመው ወረቀት አለ ትህነግ አይተገብርም እንጂ? እኛ ህግ ወረቀት ላይ መፃፍ መቼ ቸገረን መተግበሩ እንጂ? ሀገሪቱ እንደሃገር የራሷ ብሄራዊ ቋንቋ ባይኖራትም እኮ ህገመንግስት ተብዬው «ሁሉም ሰው በመላ ሃገሪቱ ተዟዙሮ መኖር ይችላል፤» እያለ እኮ ነው ትህነግ ስልጣን ከያዘ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያላቆመው
4
የአማራውን የዘር ማፅዳት ዘመቻ የሚካሄደው። ያውም ሰዎች ለዘመናት ከኖሩበት አገር «አማራ ናቹ» ብቻ በሚል (ልብ በል አማርኛ ተናጋሪ አላልኩም፣ አማራ እንጂ)። ግን አስበኸው ታውቃለህ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ትተህ አማራው ብቻ በገዛ ሃገሩ ሀገር እንዳይኖረው የተደረገው ህዝብ ቁጥሩ ከትግራይ ወይንም ከሶማሌ ህዝብ ተብሎ ክልል ተከልሎ ከተሰጠው በላይ እንደሆነ? ማሰብ ተሳነህ ጠባብ ብሄርተኝነት ስንት ነገር ያነበበን ሰው፣ የተለያየ አገር በማየት እንኳን ልምድ የቀሰመውን ፖለቲከኛ ሰው፣ በገዛ ሃገሩ ሁለተኛ ዜጋ ሲሆን የሚፈጠረውን፣ ይቺን እንዳያስብ አሳወረው መሰል፤ ያውም «ተበድለን ነበር» ከሚል ወገን ማለት ነው። ሌላው በቀደመው ዘመን ንጉስ የሚናገረው ቋንቋ እና ንጉስ የሚከተለው ሃይማኖት ህዝቡ በግድ እንዲከተል ማድረግ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የትም የነበረ ነው። በዚህ ዘመን ይሄ ቀርቷል፣ ከተወሰኑ የእስላም ሃገሮች ሁሉም በእስልምና ህግ እንዲተዳደር ከሚደረግበት ሁኔታ በስተቀር። አንተም የነሱ ግርፍ ስለሆንክ ይሀው አንተ ያልከው ካልሆነ ሞቼ እገኛለው ትላለህ፤ የቀደሙትን የራሳቸውን አላማ ብቻ አካሄዱ እያልክ እየወቀስክ። አትርሳ በ21ኛው ክፍለ ዘመን አንተ «አትጫኑብኝ» ስትል ሌሎች ላይ አለመጫንህን አስብ፣ አንደ IS (ISIS) የማታስብ ካልሆነ በስተቀር። ለነገሩ የOMN ሎጎም የየመን፣ ወይም የግብፅ ባንዲራ ሲመስል እያየን፣ የእስላም አክራሪዎች ሚዲያ እንደሆነ አይጠፋንም። የኦነግ ባንዲራ ሌላ ነው፤ «ኦነግ ይሄንን የአረብ ሃገሮች ባንዲራ የመሰለውን ጥቁር፣ ቀይ፣ ነጭ አያውቀውም ነበር» እንዳትሉኝ ኦነግ ሲመሰረት ይሄንን ባንዲራው ያላደረገበት። የኦሮሞን እኩልነት ጥያቄ የእስላም አክራሪዎች ጠምዘው የእስላም ሃገር ለመመስረት እየሰሩ እንደሆነ ጸሃይ ያወቀው አደባባይ የሞቀው ስለሆነ ብዙም ስለዛ እዚህ አላወራም።
3. “የኦሮሞ ራስን መቻል ለአማራ ስጋት አይደለም ምክንያቱም ለምሳሌ በኦሮሚያ ገንዘብና ሃብት አማራዎችንም ሆነ ሌሎችን በአማርኛ እያስተማርናቸው ነው።” ጀዋር መሃመድ
በጣም ከሚያሳፍሩ ንግግሮቹ አንዱ ይሄ ነው። የሆነ ሰዉ ግብፅ ወይንም የመን እየኖረ ከኦሮሞ ውጪ ላለው ኢትዮጵያዊ በመልካም ፈቃደኝነትና በአንተ ችሮታ፤ ስጦታ የሰጠህና የፅድቅ ስራ አስመሰልከው እኮ። እኔምለው ጀዋር ይሄ ትናንት ትህነግና ኦነግ ኦሮሚያ ብለው ያሰመሩትም ሆነ ሌላ የተከለለው ክልል ተብዬው ሁሉ በኢትዮጵያዊያን በጋራ የተገነባ ትናንት ወረቀት ላይ ከመሰመሩ በፊት በኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቀረጥ በከፈለው የተገነባ ሃገር መሆኑን ረሳኸው? ቀረጥ ከፍዬ እንደዜጋ ያለኝን መብት ደግነት አደረከው ትንሽነትህን ሲያሳይ። እነኚህ ሰዎች እኮ አገሬ ብለው እየኖሩ ሳለ በድንገት ይሄ ኦሮሚያ ሌላም ሌላም ክልል እየተባለ በጎጠኞች ተሸነሸነ እንጂ እኮ አገራቸው እየኖሩ ያሉ ሰዎች እኮ ናቸው በናንተ ችሮታ እያስተማራቹሃቸው ያሉ ያስመሰልካቸው። ያውም ትምህርት ሲጨርሱ ሌላ ክልል ተብዬ ሄደው ሊሰሩ እንጂ የኛ ባላቹትማ የግድ ኦሮምኛ መማር አለባቸው ሌላው ቀርቶ የኦሮሞ ቁጥር ትንሽ በሆነበት በተለይ በከተሞች። እንደመብት ሁሉም አፉን በፈታበት ቋንቋ ይማር ማለት ትክክል ሆኖ አንተ ግን ውለታ ለሌላው የዋልክ አስመሰልከው። መሆን የነበረበት ሁለቱም ቋንቋ፣ የስራ ቋንቋም የትምህርት ቋንቋም ሆኖ ሁሉም ሁለቱንም መማራቸው ትክክል ሲሆን እናንተ ግን ልክ እንደ ደግነት አማርኛን እንዲማሩ እንደፈቀዳቹ ስታደርጉ አያንቅህም? ከዛም ደሞ «ይሄን የመሰለ ፌደራሊዝም ስለሌለ ይሄንን መጀመሪያ ከተቀበላቹ ነው የምንደራደር» ስትልም አታፍርም? የምታብጠለጥሉዋቸው። በተለይ ከአፄ ምኒሊክ ጀምሮ የቀደሙት መሪዎች እኮ የሁላችንም አገር በሚል ሁሉም መሃል ሀገር አካባቢ ነው በኢትዮጵያዊያን ገንዘብ (በኦሮሞ ብቻ ሳይሆን) ልማት የሰሩት እንጂ የብሄር አገር መርጠው አልሰሩም። አጼ ምኒሊክ አንኮበር ለብቻ ምንም አልሰሩም። ደረቆቹ እንዳንተ ያሉት በሁሉም ኢትዮጵያዊ የተገነባ ሃገር (ልማቱ እንዳቂሚቲ ቢሆንም ማለቴ ነው) በሁሉም ኢትዮጵያዊ ደም በምእራብ ከደርቡሽ፣ በምስራቅ ከቱርክ እና ዚአድባሬ፣ እንዲሁም በሰሜን ከብዙ ጠላት በኦሮሞ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ደም የተጠበቀን አገር ድንገት ተነስታቹ «የኛ ብቻ ነው» ስትሉ፣ ሌላውን በናንተ መልካም ፈቃድ እንደሚኖር ስታደርጉ፣ ትንሽ አያንቃቹም። ለነገሩ አማራው አዚም የፈሰሰበት ይመስል ተኛላቹ ፈነጫቹ። እርግጥ አማራው እንዴት አይተኛ ከደርግ ጀምሮ ሲቀጠቀጥ፣ እንደብሄርም እንዳይኖር ያልተቃጣበት ሴራ የለምና። «በእኩልነት መብታችን ባህላችን ይከበር» ሌላ «እኛ የበላይ ሆነን እኛ የፈቀድነው ብቻ ይሁን» ሌላ! አየው ሌላ ወየው ሌላ እንዲሉ!
5
4. “የኦሮሞ ተማሪዎች በጠራራ ፀሃይ በትህነግ ወታደሮች መገደል በቂ ሽፋን አላገኘም፤ አብረውን ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አልጮሁም፤ በተለይም በአማራ ልሂቃን ሚዲያዎች ለዞን 9 ብሎገርስ ከተሰጠው ትኩረት አኳያ።” ጀዋር መሃመድ
መቼስ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም አሉ። እኔ እንግዲህ እስካየሁት ድረስ ጀዋርን ካገነኑት ሚዲያዎች አንዱ የሆነው እነ ኢሳትን ጨምሮ ይሄንን ሲዘግቡ ነበር፤ ምስጋና ቢስ ቢሆኑም፤ ያውም ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን ሰልፈኞቹ ሰልፍ ላይ ምን ይዘው እንደወጡ እያየን፤ ስንት ሰው አብሮአቸው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ስለሆኑ ተሰልፍዋል። እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ይደረግ? አማራው ይኸው 23 አመት በትህነግና አጋሮቹ ሲጨረስ መቼ ነበር ኢትዮጵያዊ ለአማራ ሲሰልፍ ያየህው? ባሁኑ ሰአት ጭምር አማራው እየተጨፈጨፈ ማለት ነው። ሌላም ብዙ ኢትዮጵያዊ እያለቀ ያልተጮኸላቸው ብዙ አሉ፣ ምን ስለ ኦሮሞ ብቻ ታወራለህ? እንዲያውም «ኢትዮጵያዊ ናቹ ይሉናል፣ ስንሞት ግን ኢትዮጵያዊ ናቹ ብለው አይጮሁልንም፤» ነው ያልከው ደሞ? ካንተ የበለጠ ሚዲያዎች ሁሉ ሲዘግቡት እኮ ነበር። ምናልባት አንተ በጠባብነት ስለታወርክ ሌላው የሚያደርገው ሁሉ አልታይህ ብሎህ ይሆናል። እኔምለው ልጆቹ ወያኔ እና እናንተ አስተምራቹሃቸው ይዘው የወጡትን መፈክር ረሳኸው እንዴ? «ኦሮሚያ ለኦሮሚያ ብቻ፣ አማራ፣ ትግሬ ኦሮሚያ ከተባለው ይውጣ» እኮ ነው ያሉት መፈክራቸውን ባይናችን እያየን? የቱጋር ነው ያሳደጋቹሃቸው ልጆች ስለኢትዮጵያ ያነሱት እና ኢትዮጵያዊያን ያልጮሁላቸው የምትል? ሌላው ቢቀር ደብረማርቆስ ጭምር እኮ አማራው የኦሮሞን ወገኖቻችንን አትግደሉ ብለው ሰልፍ ወጥተውላቸው ነበር፤ ምኑ ከሃዲ ነህ። እንደዚህም ሆኖ ነበር እንግዲህ ህዝቡ የወያኔን ያልታጠቁ ወጣቶችን ግድያ ያወገዘ፣ በምንም ሁኔታ ትክክል አይደለምና። ዝም ያለ የለም፣ ምንም ይሁን ጥያቄያቸው የጠገቡ የትህነግ ደህንነቶችና ወታደሮች የወሰዱት እርምጃ ግፍ ጥጋብ ነውና። በጣም የሚያሳዝነው የጠገበ የትህነግ ወታደር ኦሮሞ ኢትዮጵያዊያንን ለገደለ የትህነግ አሻንጉሊት ኦህዴድ ኦሮሞዎችን አደራጅቶ ከርታታ የአማራ ደሃዎችን እየገደለ እያሰደደ ነበር። ኢሳት እርሙን ያንን እውነታ ከጊምቢ ዘግቦ መልሶ ይቅርታ አለ፣ ስትጮሁ ስለተደራጃቹ ፈርቶ ያልተደራጀው አማራ አፈር ለምን አይግጥም ብሎ ዜናውን ይታረም አለ! እንግዲህ የቱጋር ነው ታዲያ የኦሮሞ ኢትዮጵያዊያን በግፍ መገደል አትኩሮት አላገኘም የምትለው? የወጣቶቹም ሆነ የሌሎች እስረኞች ጉዳይ ሁሌም ያለ የወያኔ ግፍ ሲሆን እስካሁንም የሚዲያዎችን ትኩረት እንደሳበ ነው። ለመሆኑ የታሰሩት የልጆቹ ብሄር ምን እንደሆነ ማን ያውቃል እኔ በግሌ ብሄራቸውን አልቆጠርኩም በኢትዮጵያዊነታቸው ነው የማውቃቸው? የሚያሳዝነው የምትለው ለዚህም አንተ ለታየህ የኦሮሞ ወጣቶች ግድያ ትኩረት አላገኘም ለምትለው ነገር «ተጠያቂው አማራው ነው» ማለትህ ነው። መቼ ነው ከአማራው ራስ ወርዳቹ እየገደላቹ ያለውን ትህነግ የምትቃወሙ? ለነገሩ አንተ ንግግርህ ሁሉ በተቃዋሚ ስም የወያኔ አፈቀላጤ ሆነህ ሰራህ እንጂ ምንም ወያኔን የሚቃወም ነገር አልወጣህም፤ ትህነግ ስልጣን ለብቻ ቶሎ ይስጠን ከማለትህ ውጪ። ጀምረህ እስክትጨርስ አንገቱን እንዲደፋ የተደረገውን አማራ፣ እንዲያውም «እንዳያቆጠቁጥ አድርገን እናጥፋው» ብለህ የወያኔን ፉከራ ነው የደገምከው። በነገራችን ላይ ኦህዴድ እና ኦነግ ልዩነታቸው አንድ ብቻ ነው። ኦህዴድ «ትህነግ እስኪጠግብ በስሩ ተለጥፌ ኦሮሚያ የምትባል አገር ቀስ እያልኩ እሰራለው» ሲሆን ኦነግ ደግሞ «የለም ያኔ ስንገናኝ መስመር ያሰመርንባትን ኦሮሚያ የምትባለዋን ሙሉ በሙሉ ዛሬ ይሰጠኝና እንዳሻኝ ካሁን ጀምሮ ልዘዝበት» ሲል ገና ከርሱ ያልሞላው ትህነግ «የለም ገና ብዙ የኢትዮጵያን ንብረት ስለምዘርፍ» ብሎ ኦነግን «አሁን የፈለከውን ስልጣን አልሰጥህም» ብሎ አባረረው። እኔምለው ግን አማራው ባሁኑ ሰአትም ጨምሮ ላለፉት 23 አመታት ተራ በተራ ክልል ተብለው ድንበር ከተበጀላቸው በኢትዮጵያ መሬት በትህነግ እና አጋሮቹ ባሁኑ ሰአት ጭምር ሲጸዳ (ስለ ጋንቤላ ተብሎ ስለተከለለው አካባቢ መስማት ባትፈልግም ከሌላውም ሰው ቢሞትም በተለይ ስለከፋው የአማራው እልቂት ሰሞኑን ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ነው) ምንም ሰልፍ አላየንም እኮ ለዚህ እልቂት እንዴት አየሀው ታዲያ ኢትዮጵያዊያኖቹን አትወቅሳቸውም ታዲያ ለዚህስ? ወይስ እሰየው እያልክ ነው? ታዲያ አማራው «ኢትዮጵያዊ ሆኜ ሰልፍ ሳይወጡልኝ» መች አለ? የአማራ ነፍስ የዶሮ ነፍስ ይመስልሃል? ለነገሩ «ቀና ቀና የሚል ክርስቲያን በሜንጫ አንገቱን ነው የሚባል» ያለ የአማራ ነፍስን አሳንሶ ቢቆጥር እና
6
ምንም እንዳልተፈጠረ ዝም ቢል አይደንቀኝም። እርግጥ አንተና መሰሎችህ ብቻ ሳይሆን ብዙ አለማቀፍ የሰብአዊ መብት ተቋማት በመቶዎች የሚቆጠር ህይወት ሲጠፋ እንኳን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈፀመ የሚሉ አማራው በሚሊዮን የሚቆጠር ሰው ሲጠፋም ዝም ስላሉ አይገርመኝም። አማራው ስለተኛ ለሱ ታዲያ ማን ይከራከርለት? አንድ ነገር ግን እስማማለሁ። አንድ የትህነግ አባል የሆነች ሴት የሆነ ሰሞን እንደተለመደው አማራውን ሲጨርሱ ሰዉ ሲንጫጫ «ተዉት የዲያስፖራ ፖለቲካ እንደ ፈንዲሻ አንድ ሰሞን ቻቻ ብሎ ፀጥ ይላል» ያለችው ውስጤ «እውነት ነው እንዴ?» ብሎ ሁሌ ያቃጭላል። ምክንያቱም አንድ ነገር አንድ ሰሞን ሲሰማ «ሃይ፣ ሃይ» ይባላል፤ ከዛ ይረሳል፤ አዲስ ሲመጣ ደሞ እንደገና «ሃይ፣ ሃይ» ይባላል እንጂ የተቀናጀ ነገር የለም። የኦሮሞውም እልቂት «እንዲሁ ተዘንግቷል» ከሆነ ለብቻቸው ባይሆንም ልክ ነው፤ የመርሳት ችግር በደንብ ስላለ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ። አጠቃላይ «የኢትዮጵያዊው የmemory span እንደገና መታየት አለበት» ከሆነ ሃሳብህ እሺ፤ ብዙ ነገር ትተን የፊት የፊት ብቻ ስንጮህ ይሰማልና።
5. ድምዳሜ።
አንደኛ፦ ጀዋር መሃመድ በግልፅ ወያኔ መሆኑን አረጋገጠልን። ከወያኔ ይልቅ ሙሉ ጊዜውን አቅም የሌለውን አንገቱን እንዲደፋ የተደረገውን አማራን በማውገዝ ያሳለፈ ሲሆን የሚገርመው እዚህ ሆኖም ኢትዮጵያን አሁንም እንደሚያስተዳድር እንደ ትህነግ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ነበር የሚዘባርቀው። ምናልባት ውስጥ ለውስጥ ግንኙነት ስላለው ሊሆን ይችላል። ሁለተኛ፦ ደጋግሞ ሲናገር እንደሰማቹት «ተንቀን፣ ተንቀን» ይላል። ማን ማንን እንዴት እንደናቀ ባይናገርም እንግዲህ ካንዱ ጋር ሲከራከር ምን እንዳለው እኔንጃ። የአማራ ህዝብ ምንም በማያውቀው « በአማራው ወይንም በአማራው ኤሊት ተንቀን» ይላል። እርግጥ ነው በአለማችን፣ በግለሰቦች ወይንም ቡድኖች እልህ መያያዝ ምክንያት ስንቱ ሰላማዊ ህዝብ እንዳለቀ እናውቃለን፤ «ዝሆኖች ሲጣሉ የሚጎዳው ሳሩ ነው፤» እንደሚባለው ማለት ነው። ሌላም ሳንሄድ በመለስና ኢሳያስ ወይንም በትህነግ(ወያኔ) እና ኤህነግ(ሻቢያ) እልህ መያያዝ ያለቀውን ሰው ቤቱ ይቁጠረው። ስለዚህ ይህ ሰው እና መሰሎቹ ከየትኛው ግለሰብ ይሁን ቡድኖች ከፍተኛ የሆነ እልህ እንደተጋባ ባናውቅም ለእልህ ሲባል ምን አይነት አደገኛ ጉዞ እየሄደ እንደሆነ ልብ በሉ። የዚህ አይነት ሃሳብ ብዙ ጊዜ የዝቅተኝነት ስሜት በሚሰማው ሰው የሚታይ ባህርይ ሲሆን «ከዚህ ህመሙ እግዚአብሄር ይማረው» ከማለት በስተቀር ምንም ማለት አይቻልም። መለስ «የባንዳ ልጅ» እየተባለ አንገቱን እየደፋ ስላደገ የዝቅተኝነት ስሜት ያሳደረበትን «ኢትዮጵያዊነት» የሚባለውን እሴት ለማዋረድ የቻለውን ሁሉ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ የምትባል አገር አምርሮ እነደጠላ፣ «ሃገሪቱ» እንጂ «ኢትዮጵያ» ብሎ ሳይጠራ፣ ሊበታትናት የቻለውን ሁሉ አድርጎ ሞተ። ግን ደሞ እንቅስቃሴው ተንቆ የሚተው አይደለም። ጠላቱን የሚንቅ ፖለቲካ ያልገባው ነው። እነ ትህነግ (ወያኔ) እና ኤህነግ(ሻቢያ) ተንቀው ነው ይኸው ዛሬ ያለንበት ጥፋት ላይ ያደረሱን። ሶስተኛ፦ ጠባባብ ብሄርተኝነት መቼስ በቀላሉ የማይለቅ አደገኛ በሽታ ስለሆነ እና አመለካከትን ሁሉ አሳውሮ «እኛ» ከሚለው አውጥቶ «እኔ» ወደሚለው ያመጣል እና ከጀዋር ሃሳብ ላይ ልክ ትህነጎቹ (ወያኔዎች) ላይ እንደታየው የሱ ወገን የሆነው ቅዱስ ደሙ ንፁህ፣ ሌላው ደሞ ወንጀለኛ ይሆናል (ሂትለርን አስቡ እዚህ ጋ ተመሳሳይ ናቸውና ጠባብነታቸው ጥላቻቸው)። «አንተስ እዚያው ገባህ አይደል ስለአማራ አተኮርክ» እንዳትሉኝ። አልታመምኩም ባይ ነኝ ምክንያቱም አንደኛ አማራን ለይቶ ስላጠቃ ምላሽ ብቻ የሰጠው ሲሆን፣ በተጨማሪም «አማራውን ከሰው በታች አታድርጉት፣ ከሰው እኩል አድርጉት» ከማለት ውጪ «የአማራ ድንበር እዚህ ጋር ነው፣ ይሄ ክልል የአንድ ብሄር ነው» ብዬ አላምንም። ይልቅስ ሁሉም ሰው በጋራ በእኩልነት ስለመኖር እንመካከር ባይነኝ።
በመጨረሻም ከማስተባበር ችሎታው ተምረን ራሳችንን ለማዳን እኛም ተባብረን እንስራ። ግባችን የተለያየ ቢሆንም ከጠላት አካሄዶች መማር ጥሩ ነው፣ አትርሱ። እንደሰማቹት «ኦሮሞን በኢኮኖሚ፣ በትምህርት፣ በሌላም እናጠናክር» ነው ያለው፤ እየሰሩም ነው። የትግሬዎቹ ጉዳይ ፀሃይ የሞቀው ስለሆነ ብዙም ስለዛ አላወራም። ስለዚህ አማራው ብቻ ነው እንዳይማር፣ ሃብት እንዳይኖረው፣ እንዳይደራጅ የተደረገውና፤ አማራው «ለሰው ብሎ ሲያማ፣ ለኔ ብለህ ስማ» በልና ትምህርት ወስደህ ወገንህን አደራጅ። ያለጠያቂ
7
በራሳቸው ሚዲያ የማይሆን ነገር ሲናገሩ የራስህ ሚዲያ ቢኖርህ ኖሮ ቃል በቃል መልስ መስጠት ይቻል እንደነበር አትርሳ። ጀዋር እና መሰሎቹ ከጥላቻ ህመማቸው ፅኑነት ምክንያት አማርኛን እንኳን መናገር መስማት አይፈልጉም። የጥላቻ ፖለቲካቸውን ለማስፋፋት ስለሚፈልጉ ብቻ ነው በአማርኛ ፕሮግራም የጀመሩት እንጂ «የኦሮሚያ ቲቪ» በሚል አማርኛን ምን አመጣው? «የኢትዮጵያ» ቢሉ በምንም ቋንቋ መናገር ይችላሉ? ወይ እንደነአሜሪካ ጉልበት አለው ብለው ፍላጎታቸውን ለማስፈፀም በሁሉም ቋንቋ ማቅረብ ካላሰቡ በስተቀር። ስለዚህ ይሄ አካሄዳቸው ትህነግ እንዳደረገው አማራውን ጨምሮ ሌላውን ኢትዮጵያዊ ለማወናበድ የጀመሩት ዘዴ ነው። ምንም እንኳን እንደኢሳት ያሉ (በአብዛኛው በጀት የሚያዋጣው አማራው እንደሆነ ብናውቅም) ኢሳት የኢትዮጵያ እስከተባለ እያንዳንዱን የአማራ ጥቃት አንስቶ እንዲከራከር አንጠብቅ። የኢትዮጵያ ከተባለ የሁሉንም ኢትዮጵያዊ በደል መናገር ስላለባቸው በጥልቀት ገብተው ስላንድ ብሄር መናገር ይቸገሩ ይሆናልና። በኢትዮጵያዊነታችን እስካመንን ኢሳትን መቃወም ሳይሆን ኢሳት ያልሸፈነውን የአማራ በደሎች አማራው በደሉን የሚያስረዳበት የራሱ የአማራ ሚዲያ መኖር አስፈላጊ ነው ባይ ነኝ። በዚህ ላይ ቢሰራ ይሻላል። አማራው «ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ፣ አለበለዚያ ድንጋይ ነው ብለው ይጥሉሃል» የተባለው እየሰራ እንደሆነ ልብ በል። ኢትዮጵያን ሁሉም ባህሉና ቋንቋው ተከብሮ፣ እንዲሁም አነስተኛ ቁጥር ያላቸውም መብታቸው ተከብሮ ብዙሃን የሚመሩበት የሰላም አገር አድርጎ ያሳየን። አበበ ተድላ መስከረም 2007 ዓ.ም.

No comments:

Post a Comment