ሙሉቀን ተስፋው
የዐማራ ወጣቶች እንዲረዱት! ብዙ ወገኖች ስለዐማራ ሕዝብ ስንጽፍ ዘረኛ የሆንን ይመስላቸዋል፡፡ አዎ ምክንያቱም ወያኔ ያስለመዳቸው መዝገበ ቃላት እንዲህ ስለሆነ፡፡ የዐማራ ሕዝብ በጉምዝ፣ በወለጋ፣ በጂማ፣ በአርሲ፣ በሐረር፣ በወልቃይት፣ በራያና በሌሎችም ቦታዎች ዕልቂት ሲደርስበት ‹‹ወገኖቻችን ተጎዱ›› ብሎ መጻፍ ዘረኝነት ነው ዛሬ፡፡ ስለአገር አንድነት ማውራት ትህምከተኝነት ነው ዛሬ፡፡ ለዐማራው ሕዝብ መላ ኢትዮጵያ እሾህና አሜካላ ስትሆን ስለአገር አንድነት ሲባል ዝም ማለት ነው ከዘረኝነት ወይም ከትህምከት አስተሳሰብ ነጻ የሚያደርግ፡፡ ትግሬ ወያኔ ከዐማራው ቤት ተከራይቶ እየሰለለ ዐማራውን ለዘመዶቹ አሳልፎ ሲሰጥ መቃወም ዘረኝነት ነው፡፡ ለእነዚህ ቡድኖች ዐማራ ነኝ ብሎ መናገር ትህምከት ነው፡፡ አገር በጎሳ ፖለቲካ ከእዚያ እና ከዚህ ተወጥራ ልትጠፋ አንድ ሰኞ እየጠበቀች ባለችበት በአሁኑ ወቅት ዐማራ ይደራጅ ማለት ዘረኝነት ነው፡፡ ወልቃይት ዐማራ ነው ማለት እንደ አገር አለማሰብ ነው፡፡
አዎ ይህን ስንል፤ ስለዐማራ ሕዝብ ስንናገር የሚያመው ብዙ ሰውና ቡድን ነው፤ ግን ገና እንናገራለን፡፡ ስንጽፍ የሚያቅለሸልሸው ሰውና ቡድን የትየለሌ ነው ግን ገና ገና እንጽፋለን፡፡ ምክንያቱም ያገባናልና፡፡ ስለዐማራ ሕዝብ መናገር ከሚገባን አንጻር ካየነው ገና አልተናገርንም፤ ይህን ያክል በመቶኛ ከማለት ምንም ብንል ይሻላል፡ ፡ ገና አልተናገርንም አልጻፍንም፡፡ የዐማራ ሕዝብ የሠራውን ታሪክ ለመክተብ ሰማይ ብራና ዝናማትም ቀለም ሆነው ቢያገለግሉ አይበቁም፡፡
በተቃራኒው በዐማራ ሕዝብ ላይ የደረሰውን ዕልቂት ለመግለጽ እንዲሁ፡፡ ስለዚህ ነው የምንናገረው፤ ስለዚህ ነው የምንጽፈው፡፡ የዐማራ ሕዝብ ላይ የደረሰው ፍጅት፤ የታቀደው የዕልቂት ድግስ እስኪቆም ደረስ፣ የዐማራን ሕዝብ ሕልውና በሚገባ እስክናረጋግጥ ድረስ እንናገራለን፣ እንጽፋለን፤ ይህ የእኔ ቃል ብቻ አይደለም፤ የብዙ ሚሊዮን ዐማሮች ሐሳብ እንጅ፡፡
የዐማራ ሕዝብ ማንንም ለመበቀል አይደራጅም፤ ግን አጥፊዎቹን የእጃቸውን ይሰጣል፡፡ ዐማራ አገር አያፈርስም፤ ግን የሚያፈርሱትን ወገኖች አይቀጡ ቅጣት ይቀጣል፡፡ ሁሉም የዐማራ ወጣቶች እንዲገነዘቡት የሚያስፈልግ ነገር አለ፤ ስለዐማራ ስትናገሩ አንገታችሁን እንድትደፉ የሚፈልግ ቡድንና ሰው ብዙ ነው፡፡ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የዐማራውን መደራጀት ብሎም ለመብቱ መቆም የሚደረገውን ተጋድሎ የሚቃወም ቡድን ወይም ሰው ሁሉ ከወያኔ ጋር እኩል ጠላታችን ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ወገኖች የእኛን መኖር አይሹምና፡፡ ወይም ነባራዊውን ሁኔታ ያልተገነዘቡ በምኞት ዓለም ውስጥ የሚዳክሩ ናቸውና፤ ትግላችንን ወደ ኋላ የሚጎትቱ ዘገምተኞች ናቸውና፡፡
አገር በግልጽ የትግሬ ሆናለች፤ ትግሬዎችም ‹‹ኢትዮጵያ የሁላችንም እኮ ናት፣ ሁሉም ይጋሩት›› የሚል ድምጽ ሲያሰሙ አላየንም፡፡ ወደ ፊትም አንጠብቅም፡፡ ምክንያቱም እንደነሱ አባባል ‹‹ዘረኞች አይደሉምና››፡፡ አያችሁ በዚህ ዘመን ዐማራ አገራችን የጋራ እናድርግ የሚለውን ጥያቄ መስማት አይሹም፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ነውና ነገሩ፡፡ ይህን ስትሉ ሌሎችን ሥልጣን ፈልጋችሁ ነው የሚሉ ኃይሎች ብዙ ናቸው፡፡ ይህን ስትናገሩ የነፍጠኛ ልጆች ናችሁ የሚሏችሁ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይህን ስትናገሩ ትህምከተኛ ናችሁ የሚላችሁ ይበዛል፡፡ እናንተም መልሱ፡፡ ይህ ትናንት አይደለም፡፡ ዛሬ ዕልፍ ነበልባል የዐማራ ወጣቶች አለን፡፡ አዎን እኛ ትህምከተኞች ነን፤ ነፍጠኞች ነን- ድሮስ ልጅ የአባቱን ካልወረሰ፤ ሥልጣንም እንሻለን በሏቸው፡፡
ትህምከታችን እኮ ነው እንዲህ በአንዴ ያነቃነቃቸው፤ ነፍጣችን እኮ ነው የመከታቸው፡፡ በመጨረሻም፤ ሌሎች ሕዝቦች እንዲረዱት የምንሻው ነገር ቢኖር እኛ ዐማሮች ማንንም ለመበቀል አልተንቀሳቀስንም፤ ዐማራ በዘረኝነት አይታማም፤ ይህ ትውልድም የትናነቱ የአባቶቹ ልጅ ነው፡፡ ይህን እያወቀ መንገዳችን የሚዘጋ ግን ከዐማራ ሕዝብ ጋር ምንም ሕብረት የለውም፡፡
የአፋር አብዮታዊ ዲሞክራሲ አንድነት ግንባር ሕወሃት በጎንደር ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት በማውገዝ መግለጫ አወጣ
No comments:
Post a Comment