Wednesday, October 5, 2016

ምን ስም ይሰጠዋል?

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ማክሰኞ መስከረም ፳፬ ቀን ፪ሺህ፱  ..              ቅፅ   ቁጥር 

በዓለም ላይ የነበሩና ያሉ ዘረኞች፣ ግፈኞችና አምባገነኖች የተለያዩ ምክንያቶች እየፈለጉ ሕዝብ ገድለዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል። በዚህም ተግባራቸው፣ « ናዚ፣ ፋሽስት፣ ጨፍጫፊ፣ አረመኔ» ወዘተርፈ ተብለዋል። ከእነዚህ እጅግ በከፋ ሁኔታ የዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በአጠቃላይ፣ በተናጠል ደግሞ በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በአኙዋኩ፣ በኑኤሩ፣ በሶማሊው፣ በአፋሩ፣ በሲዳማው ወዘተርፈ ነገዶች ላይ የሚፈጽመው ሁለንታናዊ ግፍ በምን ቃላት ሊገለጽ እንደሚችል የቋንቋ ሊቃውንት ሊያስቡበት የሚገባ ነው። ከላይ የተገለጹት የጭካኔ እና የአረመኔነት ስያሜዎች በፍፁም የወያኔን ማንነትና ዕውነተኛ ባሕሪ አይገልጹትም። ይገልጹታል ከተባለም ተለምዶአዊ በመሆኑ፣ የቃሎቹ የያዟቸው ጽንሰ ሀሳቦችና ድርጊቶቹ የሚጣጣሙ አይደሉም። በምንም ታምር ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የኖረ በዓልን ለማክበር ቄጤማ ይዘው በተቀመጡ ሽማግሌዎች፣ ሕፃናት፣ ሴቶችና ወንዶች ላይ ከሰማይ በአውሮፕላን፣ ከምድር በመትረየስ የሞት ዶፍ ማውረድ በምንም መመዘኛ ምክንያታዊነት የለውም። እገዛዋለሁ የሚለውን ሕዝብ፣ ያውም «ለብሔር/ብሔረሰቦች እኩልነት» ቆሜአለሁ እየለ ጧት ማታ በሚምል የገዛ ወገኑን የደበደበ አረመኔ የሚባል ቡድን በዓለም ታሪክ ስለመኖሩ በእርግጠኝነት ለመናገር አይቻልም።
የትግሬ ወያኔ ፣ በሀሰት ያሰራቸውን የኅሊና እስረኞች በራሱ የፍርድ ሂደት ቢያቀርባቸው አደረጉ ያላቸውን ስለማድረጋቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ስለሆነም እስካሁንም የሚሠራው ትያትር ሕዝቡ ያወቀበት መሆኑን በመረዳቱ፣ በቂልንጦ፣ በጎንደርና በደብረታቦር እስር ቤቶች በቁጥጥሩ ሥር ያሉትን እስረኞች በእሳት ለኩሶ፣ ንፁሐን ዜጎችን አጠቃ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ጨረሰ። እስረኞችን የወባ መድኃኒት ነው ብሎ፣ ማላታይን አጠጥቶ ፈጀ። ኤች አይ ቪ ቫይረስን በመርፌ እየወጋ ሕዝብ ጨረሰ። የዐማራውን ነገድ ቁጥር ለመቀነስና ፈጽሞ ለማጥፋት ባለው ዕቅድ፣ ዐማራ ሴቶችን ለይቶ በወሊድ ቁጥጥር ስም ታማሚና መካን አደረገ። የዐማራ ወንዶችን የመራቢያ አካላቸውን እየቀጠቀጠ፣ ሰዎችን በቁማቸው ጉድጓድ ውስጥ ከቶ አሰቃየ። እንዲህ ዓይነት ፍፁም አረመኔና ፋሽስት የተባለ ቡድን ከወያኔ በቀር የኢትዮጵያ ታሪክ አያውቅም።
ግፈኛውና ዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን ባለፈው እሑድ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓም በደብረ ዘይት ከተማ የእሬቻን የኦሮሞ ባህላዊ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተሰበሰቡ ንፁሐን ዜጎች ላይ የፈጸመው ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት የጅምላ ግድያና ፍጅት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በጽኑ ያወግዛል።
ግድያው ወያኔ ለ25 ዓመታት ካደረጋቸው የሚለየው፣ ላለፉት ዘጠኝና አሥር ወራት በተከታታይ በሐረርጌ፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በአርሲ፣ በኢሉባቡር፣ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በጎጃምና መሰል ክፍለሀገሮች የዘለቀው ሕዝባዊ እንቢተኝነትና የዐማራው የማንነት ትግል ገዝፎና ገፍቶ ምኒልክ ቤተመንግሥት በራፍ ላይ በመድረሱ፣ በወያኔና አሽከሮቹ ላይ የፈጠረው የፍራት መጠን ከፍተኛ መሆን በአልሞት ባይ ፍርግጫ ያላቸውን የመጨረሻ ኃይል ያሳዩበት መሆኑ ነው። ነፃነትን የተጠማ፣ ማንነቱን ለማስከበር ቆርጦ የተነሳን ሕዝብ፣ ይህ ዓይነቱ የፈሪ በትር የታጋዩን ሕዝብ ወኔ ያጎለብታል እንጂ፣ እንደማይቀንሰው የኢትዮያ ሕዝብ ደጋግሞ ለዓለም ማኅበረሰብ አሳይቷል። በመሆኑም የትግሬ ወያኔ ፍርሀት በወለደው ስሜት በእሬቻ በዓል ተሳታፊዎቹ ላይ የወሰደው ዘግናኝና ሰቅጣጭ የጅምላ ፍጅት፣ የወያኔን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ጭካኔ ከማሳየት በቀር፣ የሥልጣን ዕድሜውን ያራዝማል ተብሎ አይታሰብም። በአንፃሩ የወያኔን ዕድሜ በእጅጉ የሚያሳጥር፣ የሕዝቡን ነባር አንድነት ወደነበረበት ደረጃ የሚመልስ ነው። እንዲያውም የትግሬ ወያኔ ጠባብና አናሳ ቡድን ለሥልጣን ዕድሜው ማራዘሚያ በኦሮሞውና በዐማራው ነገዶች መካከል በሀሰት ገንብቶት የነበረው የጥላቻ፣ የመጠራጠርና የመገፋፋት ድልድይ ይሰብራል።
ሰሞኑን ደብረዘይት ላይ የፈሰሰው የኦሮሞው፣ የዐማራውና መሰል ነገዶች ልጆች ደም፣ ትናንት ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ደብረታቦር፣ ደብረማርቆስ፣ ነፋስ መውጫ፣ ወረታ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ደባርቅ፣ ዳንግላ፣ ኮሶ በር፣ ቡሬ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ወዘተርፈ ላይ ከፈሰሰው የዐማሮች ደም የሚለየው አንዳችም ነገር የለም።  በሁሉም አካባቢዎች በወያኔ ነፍሰ ገዳዮች የፈሰሰው ደም የኢትዮጵያውያን ደም ነው። ወያኔ ከሁሉም በላይ የዐማራውንና የኦሮሞውን ልዩነት ሊያሰፋው የሚፈልገው ሁለቱ ነገዶች አንድ ከሆኑ ኢትዮጵያን ሊገዛና ሊዘርፋት እንደማይችል ስለሚያውቅ ነው። ይህንን የትግሬ-ወያኔን መሰሪ ሴራ፣ የኦሮሞውና የዐማራው ልጆች «አውቀንባችኋል» በማለት ወደ ነባሩ አንድነታችን በፍጥነት መመለስ ወያኔን አይሞቱ ሞት የሚገድለው እንደሆነ አይጠረጠርም። ስለሆነም የመከራ ጊዜአችን ለማሳጠር የሁለቱ ነገዶች አንድነት ፍቱን የወያኔ አገዛዝ ማርከሻ እንደሚሆን ተረድተን፣ ፍትሕ የተነፈጉ ፍትሕን እንዲያገኙ፣ በአረመኔዎች የተገደሉ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር፣ ኢትዮጵያውያን በነገድ ሳይሆን፣ በዕኩልነት ላይ በተመሠረተ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ እንድናተኩር ያሻል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የኢትዮጵያ ትንሣዔ በትግላችን ዕውን ይሆናል!

Thursday, September 1, 2016

ሞረሽ ለዐማራ ሕዝብ!!!


ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ረቡዕ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፮

ከሞረሽ  ወገኔ  የዐማራ ድርጅት የተሰጠ የነፍስ አድን ጥሪ!
የተከበርከውና ጀግናው የዐማራ ሕዝብ ሆይ!
የትግሬ ወያኔ አገዛዝ «ዐማራውን አከርካሪውን ሰብረነዋል»፣ «ዐማራው ላይመለስ ገድለን ቀብረነዋል» በማለት ይሳለቅብሃል። በእርግጥም ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ገድሎ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደግሞ አሰድዶ ከመኖሪያ ቀያቸው አፈናቅሏል። ሆኖም ግን ከሞቱት በላይ፣ ካሉት በታች ሆነህ የምትኖረው የቀረኸው ዐማራ፣ ከገባህበት የቁም መቃብር ለመውጣት ዘወትር ትግልህን እንዳላቋረጥክ እኛ አብረንህ የምንታገለው ልጆችህ ቀዳሚ ምሥክሮችህ ነን። በተለይም ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ መግነዝህን ቀደህ እና በጣጥሰህ፣ የተጫነብህን  የመቃብር ድንጋይ እና አፈር ፈነቃቅለህ ከፈጽሞ ጥፋት ራስክን ለማዳን እያደረግኸው ላለው ተጋድሎ እና የጀግንነት ተግባር ያለን አድናቆት እናአክብሮት እጅግ ከፍ ያለ ነው። ለምታደርገው ራስክን  ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግ ተፈጥሮአዊ የመከላከል ትግል፣ እኛ በስደት የምገኝ ልጆችህ ምንጊዜም ከጎንህ የማንለይ መሆኑን ስናረጋግጥልህ በታላቅ አክብሮት እና ወገናዊነት ነው።
ዛሬ ይህንን ጥሪ እንድናስተላልፍልህ የተገደድነው፣ ጨካኙ፣ አረመኔው እና ፀረ-ዐማራ የሆነው  የትግሬ ነፃ አውጪ ወራሪ ቡድን፣ በመላው የዐማራ ሕዝብ ላይ፣ ካለፉት ሁሉ በመጠኑና በስፋቱ የተለየ፣ ይፋ በሆነ ሁኔታ ጦርነት ማወጁ ነው። የጥቁር ናዚው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ በዐማራው ላይ እጅግ መጠነ-ሰፊ የሆነ የዘር ማጥፋት ዘመቻ መክፈቱን፣ በወያኔ ታዞ አዳሪ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ ለወታደሩና ለፀጥታ ኃይሉ ሙሉ የመግደልና የማሰር ሥልጣን መስጠቱን፣ በብዙኃን የመገናኛ መሣሪያዎች ሰምተናል። በዚህም መሠረት፣ የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን ለመጨፍጨፍ፣ እጅግ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ  ነፍሰ በላ ገዳዮቹን፣ በተለያዩ የትርንስፖርት መንገዶች ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር፣ ደባርቅ፣ ወዘተርፈ በማጓጓዝ ላይ እንደሆነ አውቀናል።
እኛ በስምህ ተደራጅተን፣ በአረመኔው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ እየተፈጸመብህ ያለውን የዘር ጥቃት ለዓለም ማኅበረሰብ በማሰማት ላይ የምንገኝ ልጆችህ፣ የምናቀርብልህ ጥሪ አለን። ይኸውም፥ አንተን በደመኛ ጠላትነት ፈርጀው፣ ፕሮግራም አዘጋጅተው እና ተደራጅተው፣ ላለፉት 41 ዓመታት የዘር ፍጅት ሲፈጽሙብህ የኖሩት የትግሬ-ወያኔዎች ዛሬም የጥፋት በትራቸውን እንዳልሰበሰቡት አንተም አሳምረህ ታውቀዋለህ። እንዲያውም ከሌሎች ነገዶች ያልተቀላቀሉበት፣ የትግሬ-ወያኔ ብቻየሆኑ ነፍሰ-በላ ገዳዮች፣ የፌድራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት መለዮ ለብሰው፣ አንተን የዋሁን እና ደጉን የዐማራ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ  ከፍ ሲል በተዘረዘሩት ከተሞች የተሰማሩ መሆናቸውን ዕለት በዕለት የምትመሰክረው ሃቅ ነው። ስለሆነም ሌላ ከውጪ የሚመጣ ደጋፊ ኃይል ሳትጠብቅ፣  ራስክንና ቤተሰብህን ከጥቃቱ መከላከል እንድትችል አስፈላጊውን መሰናዶ ታደርግ ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን። ከታሪክም እንደምንገነዘበው፣ ዐማራው የራሱን እና የአገሩን ጠላቶች ከጓሮው ገብተውለት ቀርቶ፣ ከጉያቸው እየገባ የዶግ አመድ የማድረግ የቆየ የጀግንነት ታሪክ እና ባህል ባለቤት ነው። ስለሆነም ይህን በእብሪት ተወጥሮ፣ ከብብትህ የገባውን የትግሬ-ወያኔ መንጋ፣ በጎበዝ አለቆችህ በመመራት አስፈላጎውን መከላከል በማድረግ፣ ይህን የጣሊያን እንቁላል አቅራቢና አልጋ አንጣፊ የነበሩትን የባንዳ ልጆች ጥርቅም፣ በተለመደው ጀግንነትህ ፍላጎታቸውን የቀን ሕልም እንደምታደርገው እምነታችን ከፍ ያለ ነው።
በአሁኑ ሰዓት፣ አጥፊው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደሴ እና  በደብረ ታቦር በሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ አልሞ ተኳሽ ነፍሰ ገዳዮቹን አሰማርቶ ለጅምላ ግድያ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል።  ከዚህበተጨማሪም  ነፍሰ በላዎቹ የትግሬ-ወያኔዎች በከተሞች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሚኒባሶች እና የሕዝብ ማመላሻዎች  መኪናዎች መትረየስ እና ላውንቸር ጠምደው ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ላንተ መንገር «ለቀባሪው ማርዳት» ይሆንብናል። ስለሆነም፣ አንተ ጀግና እና ኩሩ የሆንከው የዐማራ ሕዝብ፣ ይህ የትግሬ-ወያኔ አጥፍቶህ ከመጥፋቱ በፊት፣ አጥፊውን ኃይል ቀድመህ ለማጥፋት ክንድህን አስተባብረህ ለመብትህና ለነፃነትህ ተዋደቅ። «ከዘላለም ባርነት እና ውርደት የአንድ ቀን ነፃነት» ይመረጣልና፣ አንተም እንደ አባቶችህ፣ ለልጆችህ እና ለልጅ ልጆችህ ኩራትን እና ነፃነትን ለማውረስ በወራሪው እና በዘረኛው ጠላትህ በትግሬ-ወያኔ ላይ የተባበረ ክንድህን አንሳ። «ጅብ ከሚበላህ፣ ጅቡን በልተህ ተቀደስ» ይባላልና፣ አንተን ሊያጠፋ የተፈጥሮ ድንበርክን ተከዜን ተሻግሮ የመጣውን፣ ይህ የሰከረ መርዘኛ እባብ እንዳያመልጥህ በር በሩን ዘግተህ መተናፈሻ በማሳጣት ለትውልዱ የማይረሳ ትምህርት ሰጥተህ እንደምትሸኘው እምነታችን ጽኑ ነው። የትግሬ-ወያኔ ያቀደልህን ሞት እና የዘር ዕልቂት ትውልድህን ከፈጽሞ ጥፋት እንድትታደግ ጥሪያችን ስናቀርብ፣ በእኛ በኩል ማድረግ የሚምንችለውን ሁሉ ለማድረግ የምንሰስተው አንዳችም ነገር አለመኖሩን ስናረጋግጥልህ በታላቅ አክብሮት ነው።
ለብአዴን አባላት እና አካላት!
ይድረስ «ለብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» አካላትና አባላት! የቆየው እና መልካሙ ባህላችን፣ እንደሚያስገነዝበን «ከባዕዳ ቆርሰህ ወደ ወገንህ ዙረህ ጉረስ» የሚል ነው። የትግሬ-ወያኔ ለእናንተ ባዕድ እንጂ፣ ወገናችሁ እንዳልሆነ፣ በየቀኑ የሚፈጸምባችሁን አድልዖ እና በደል ከእናንተ የተሻለ የሚያውቀው የለም። የትግሬ-ወያኔ እናንተን የሚያያችሁ፣ የወገኖቻችሁ መቁረጫ እና መፍለጫ የምሣር እጀታ (ዛቢያ) አድርጎ እንጂ፣ እንደትግል አጋር አድርጎ አለመሆኑን ትስቱታላችሁ አንልም። ይህም በመሆኑ ምንጊዜም አያምናችሁም። ባለመታመናችሁ ደግሞ ዘወትር በስለላ እና በክትትል ውስጥ ያላችሁ ናችሁ። አሁን የወልቃይት-ጠገዴን የማንነት ጥያቄን ተከትሎ የተቀጣጠለው የሕዝባዊ እንቢተኝነት ማዕበል የትግሬ-ወያኔን ጠራርጎ አፈር ሳይቀላቅል ይቆማል ብላችሁ የምታስቡ እና የምታምኑ ከሆናችሁ፣ የምታስቡት በአዕምሮአችሁ ሳይሆን፣ እንደሚባለው በሆዳችሁ ነው ማለት ነው። በአዕምሮአችሁ የምታስቡ ከሆነ፣ የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 41 ዓመታት በዐማራው እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ ገደቡን አልፎ በመፍሰሱ፣ እንደጎርፍ የፈሰሰው የንፁሐን ዜጎች ዕንባ ከፈጣሪ ደጅ የደረሰ መሆኑን አምናችሁ ተቀበሉት። ስለዚህ ምንጊዜም ከተበዳዮች ጎን የሚቆመው የዕውነት አምላክ ፍርዱን የሚሰጥበት ቀን ላይ በመሆናችን፣ የትግሬ-ወያኔ እናንተንም ሆነ እናንተ የወጣችሁበትን የዐማራ ነገድ አጥፍቶ፣ ወደ ምሽጉ እንዳይሄድ፣ ከወገናችሁ ጎን የምትቆሙበት ወቅት ላይ መሆናችሁን ልብ እንድትሉ አደራ እንላለን።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የገዳዩ አካል ብትሆኑ፣ ሥራችሁ በምድርም በሰማይም ይቅር የማይባል ከፍተኛ ወንጀል እና ኃጥያት መሆኑን ከወዲሁ እንድትገነዘቡት እንሻለን። ዛሬ በድብቅ የሚቀር አንዳችም ነገር የለም። ዕድሜ ለዘመኑ ቴክኖሎጂ፣ የምትሠሩትን ማናቸውንም መልካምም ሆነ መጥፎ ሥራ በድምፅ፣ በምስል፣ በሰነድ ተቀርጾ፣ በደቂቃዎች ውስጥ ለእኛ ከጉዳዩ ባለቤቶች ቀርቶ ለዓለም ማኅበረሰብ የሚደርስ መሆኑን አታውቁም ለማለት አንደፍርም። በመሆኑም፣ የእያንዳንዳችሁ እንቅስቃሴ በሕዝቡ ዕይታ ውስጥ ያለ ስለሆነ፣ ከአይቀሬው የትግሬ-ወያኔ ውድቀት በኋላ፣ ተበዳዩ ሕዝብ ለሚያቀርብላችሁ ጥያቄ የምትሰጡት ምክንያት ዋጋ አይኖረውምና፣ ከወዲሁ ከወገናችሁ ጎን እንድትቆሙ በወገናችን በዐማራው ስም ጥሪአችን እናቀርብላችኋለን። በመሆኑም ወገናዊነታችሁ ለወገናችሁ እንጂ፣ ለቅኝ ገዣችሁ ወያኔ እንዳይሆን አደራ እንላለን።
በተቃራኒው ይህንን ጥሪ ተላልፋችሁ፣ ከዐማራው ደመኛ ቡድን ጋር ቆማችሁ የወገናችሁ መቁረጫ ምሣር እጀታ ከሆናችሁ፣ ሞታችሁ አካላዊ ብቻ ሳይሆን፣ መንፈሣዊምም ጭምር እነደሚሆን ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ይህን ጥሪ ተላልፋችሁ በወገናችሁ ላይ አንዳች ጥፋት ብትፈጽሙ፣ በኋላ ላይ ለሚከተለው የከፋ እርምጃ፣ ሕዝባችን «እጄን በእጄ» የሚለው ፀፀት ተሸካሚ እንዳይሆን፣ ከወዲሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናቀርባለን።
በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ የዐማራ ነገድ ልጆች፥
የፖሊስ ሠራዊት ዋና ተግባር የሕዝብን ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ እንጂ፣ ሕዝብን ሰላም መንሳት እና ማሸበር፣ አልፎም ዘር ማጥፋት አይደለም። የመከላከያ ሠራዊት ዋና ተግባርም የአገሩን ሉዓላዊነት እና አንድነት ከውጪ ወራሪዎች መከላከል እንጂ በሰላማዊው የገዛ ወገኑ ላይ ጥይት በመተኮስ መጨፍጨፍ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። ይህንን የምታደርጉ ከሆነ ግን ከዚያ በኋላ ለሚመጣው ሕዝባዊ ምላሽ ተጠያቂዎቹ እናንተው እንጂ ሕዝቡ አይሆንም። በመሆኑም አፈሙዛችሁን በአሸባሪው የወያኔ ቡድን ላይ በማዞር ሕዝባዊ ወገንተኝነታችሁን እንድታሳዩ ከወዲሁ ትጠየቃላችሁ።
ለትግራይ ሕዝብ!
አባቶቻችን እንደሚነግሩን ትግሬና ዐማራ አንድ ዓይነት ሃይማኖት የሚከተሉ፣ ከግዕዝ የተቀዳ ቋንቋ የሚናገሩ፣ በታሪክ እና በመልከዐ-ምድር አቀማመጥ የተቆራኙ፣ የተጋቡ እና የተዋለዱ፣ በዚህም ምክንያት የወል የሆነ ሥነልቦና የገነቡ መሆናቸውን ነው። ካለፉት 50 እና 60 ዓመታት በኋላ ግን ያ የቀድሞ ታሪክ መልኩን ለውጧል። በተለይም ደግሞ ከአብራክህ የወጣው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ ላለፉት 25 ዓመታት በጨበጠው የፖለቲካ ጡንቻ ተጠቅሞ፣ ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ በዐማራው ላይ የዘር ፍጅት መፈጸሙን መቼም ቢሆን፣ የለም አልተደረገም እንደማትለን ተስፋ አለን።
የትግሬ-ወያኔ ቡድን የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ዋና ጠላቶች መሣሪያ በመሆን፣ ኤርትራን አስገንጥሎ፣ አገሪቱን ተፈጥሮአዊ የቀይ ባሕር ባለቤትነቷን በማሳጣት መተናፈሻ ያጣች፣ የበይ ተመልካች ያደረጋት መሆኑን ታውቃለህ። በዚህም የተነሳ፣ በትውልድ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በመከዐ-ምድር ወዘተርፈ አንድ ከሆነው የኤርትራ ሕዝብ ጋር ጥቁር ደም አቃብቶ ኑሮህ የሰቀቀን እንዲሆን ማድረጉን ትዘነጋዋለህ አንልም። ይህ ቡድን አንተን ማኅበራዊ መሠረቱ በማድረግ፣ በፈለገው ጊዜ የፈለገውን የሚያስፈጽምብህ ሁነኛ የጥፋት መሣሪያው እንደሆንክ በመቁጠር፣ ያለፈው አልበቃ ብሎት፣ ዛሬም በዐማራው ነገድ ላይ አጠቃላይ የሆነ የዘር ፍጅት ለመፈጸም በወታደርነት እና በደህንነት ሠራተኛነት የተሰለፉት ልጆችህ ዐማራውን እንደፈለጉ እንዲያስሩ እና እንዲገድሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
የትግሬ-ወያኔ ባዘዘው ትዕዛዝ መሠረት የትግራይ ሕዝብ ዛሬም የወያኔ መሣሪያ ሆኖ በዐማራው ላይ ተከታታይ የዘር ፍጅት ከፈጸመ፣ በትግሬ ሕዝብ እና በዐማራ ሕዝብ መካከል በተከታታይ ትውልዶች ምንጊዜም ሊታረቅ ከማይችል የጠላትነት ስሜት ውስጥ የሚገባ መሆኑን ልብ ልትለው ይገባሃል። ስለሆነም ከጊዜአዊ ስሜት እና «ወያኔ የእኛ መንግሥት ነው» ከሚለው የጧት ጤዛ እምነት ወጥተህ፣ የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን እንድታጠፋ የሰጠህን ትዕዛዝ ከመፈጸም እንድትታቀብ ወገናዊ ጥሪያችን እናቀርባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የትግሬ-ወያኔ ዓላማ አስፈጻሚ መሆንክን ከቀጠልክ፣ ትውልዱ እንደ እስካሁኑ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ እና ተንደላቆ በመላ አገሪቱ የመኖር ዕጣው የሚሟጠጥ መሆኑን ልናስገነዝብህ እንወዳለን። ዛሬ የትግሬ-ወያኔ የዘረጋው ዐማራን የማጥፋት ዘመቻ በሁሉም በትግራይ ልጆች ተቀባይነትን ካገኘ፣ በትግሬና በዐማራው መካከል ለዘመናት ተገንብተው የነበሩ ግንኙነቶች ድልድይ እስከ ወዲያኛው የማይጠግኑ መሆናቸውን መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። ስለሆነም ለጊዜአዊ ጥቅም እና ለልጆችህ ገደብ የለሽ አምባገነናዊ ሥልጣን መራዘም ብለህ፣ ከቋሚው እና ዘላለማዊው ወንድምህ የዐማራ ነገድ ጋር የተቃባኸው ደም «ባለፈው ይብቃ»  ብለህ፣ ከሕዝቡ ጎን እንድትቆም የጠበቀ አደራችንን እናስተላልፍልሃለን። የዚህ ጥሪ ተቀባይነት ማግኘት፣ ጥቅሙ ለዐማራው ሳይሆን ፣ ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ የትግሬ ትውልድ መሆኑን ልብ ብለህ፣ ከአጥፊው የትግሬ-ወያኔ ቡድን ራስክን እንድትለይ ጥሪያችን እናቀርባለን!
በዐማራነት እና በኢትዮጵያ አንድነት ለምታምኑ የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች!
የድርጅቶቹ መኖር ዋጋው ሕዝብን ከጥፋት ለመከላከልና ወደ ተሻለ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሕይዎት ለመምራት መሆኑ ግልጽ ነው። ሕዝብ ከሌለ ድርጅቶች አይኖሩም። በመሆኑን የእነዚህ ድርጅቶች መኖር ፋይዳው፣ ቆምንለት ለሚሉት የኅብረተሰብ ክፍል ኅልውና መጠበቅ የሚችልበትን ሁሉ፣ ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር እያገናዘቡ ማድረግ ነው።  በዚህ ረገድ ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን የዐማራውን ነገድ ዘር ለማጥፋት ይፋ የሆነ የዘር ፍጅት አዋጅ አውጇል። ይህ የዘር ፍጅት በስፋት እንዳይቀጥል፣ ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቅ አገርም ታሪክ እንዳትሆን፣ ይህ አጥፊ ቡድን የተያያዘውን የጥፋት ጉዞ ማስቆም የግድ ከሚለው ወቅት ላይ ተደርሷል። የትግሬ-ወያኔን ከጥፋት መንገዱ ማስቆም የሚቻለውም፣ ከያዘው የፖለቲካ ሥልጣን፣ በተያያዘው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ትግል አሽቀንጥሮ መወርወር ሲቻል ብቻ ነው። ለዚህም በመጀመሪያ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የዐማራው ነገድ ልጆ አንድነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዛሬ አስፈላጊ ነው። ቀጥሎም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ድርጅቶች፥ ልዩነቶቻቸውን አጣብበው፣ አንድ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ዙሪያ በመሰባሰብ፣ አጥፊው ቡድን አጥፍቶን ሳይጠፋ በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል። ለዚህ ዕውን መሆንም፣ ማንንም ያላገለለ የዘመቻ ሥራ ሊሠራ የሚችል ግብረኃይ ተቋቁሞ፣ የሚከተሉት ሥራዎች  በአፋጣኝ እንዲሠሩ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።
አንደኛ፦ የዕለቱን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተለ ዝርዝር መረጃዎችንና ዘገባዎችን ወጥነት እና ተከታታይነት ባለው መልኩ ለዓለም ማኅበረሰብ፣ ለዓለማቀፋዊ እና  አሕጉራዊ ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሚያቀርብ የመረጃ ሥርጭት አካል መሰየም።
ሁለተኛ፦ በዲፕሎማሲው መስክ መልካም ስም ያላቸውን ሰዎች በማቀናጀት ወያኔ አገሪቱንና ሕዝቡን ወደ ጥፋት ጎዳና እየወሰዳት መሆኑን ሳይሰለቹና ሳይዘናጉ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካሎች የሚሰጥና የሚያግባባ ቡድን መፍጠር፤
ሦስተኛ፦ በትግሬ-ወያኔ ግፈኛ ቡድን ለተገደሉ፣ ለታሰሩ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ የሚያሰባስብና የሚለግስ ቡድን መፍጠር፣
አራተኛ፦ ወያኔ አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች ባስቸኳይ ተገናኝተው፣ መጭውን የአገራችን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ወጥ እና ተደጋጋፊ የሆነ ሥራ በአስቸኳይ መጀመር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።
በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ነፃነት ወዳዱ እና ጀግናው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! «አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል» እንዲሉ፣ የዐማራው፣ የኦሮሞው፣ የሶማሌው፣ የአኙዋኩ ወዘተርፈ ችግር የእያንዳንዳችን ችግር ነው። የዐማራው ፍጅት ያንተም ፍጅት ነው። የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ሕዝብ ላይ እንዳደረሰው በደል ሁሉ፣ የበደሉ መጠን በዓይነት እና ሁኔታ ይለያይ እንጂ፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ፈጽሞታል። ይህ የአገር፣ የታሪክ፣ የባህልና የማንነት ጠር የሆነ ቡድን፣ እስከ ዛሬ በዐማራው ላይ ያደረሰው በደልና ግፍ አልበቃ ብሎት፣ በግልጽና በይፋ በአዋጅ፣ የዐማራን ዘር ለማጥፋት ለወታደሩና ለጸጥታ ሠራተኛው ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህ ጥፋት በዐማራው ላይ ተፈጽሞ የማይቀር፣ ሁሉንም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ነገዶች ለማጥፋት ወደኋላ የማይል መሆኑን ባለፉት ዘመናት በተለያዩ ቦታዎች የወሰዳቸው አስከፊና ዘግናኚ ርምጃዎች ምንነቱን አሳይቷል። እሳትን ማጥፋት በሩቁ ነውና፣ ይህ በዐማራ ሕዝብ ላይ የታወጀው የዘር ፍጅት በእያንዳንዳችን ደጅ ከመድረሱ በፊት ከዐማራው ወገንህ ጋር በመቆም እሳቱን ከዚያው ላይ ለማጥፋት የተለመደ ኢትዮጵያዊ ትብብርህንና ጀግንነትክን ዳግም እንድታስመሰክር ጥሪአችን ስናቀርብልህ በታላቅ አክብሮት ነው። የዐማራው መዳን የኢትዮጵያ መድኅነት ነው። ሞትና ስደት ባለፈው ይብቃ! ናዚያዊው የትግሬ-ወያኔ አጥፊ ቡድን ነውና፣ አጥፍቶን ሳይጠፋ ቀድመን ለማጥፋት ከተቀጣጠለው የዐማራ ነገድ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ጎን እንቁም!
በመጨረሻም፥ ከላይ የዘረዘርናቸውን ተግባሮች ካከናወንን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን የትግሬ-ወያኔ የጫነብንን የናዚ-ዓይነት አገዛዝ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አሽቀንጥረን ለመጣል እንደምንችል ጥርጥር የለንም። ለዚህም ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይርዳን።

ወያኔ አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ እርሱን ለማጥፋት እንተባበር!
ድል ለሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት


Wednesday, August 17, 2016

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደውሚስጢራዊ አዲስ ሤራ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ማክሰኞ ነሐሴ ፲ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.             ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፪

ላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል እንደሆነ፣ በተከታታይ በተደረጉት የሕዝባዊ እንቢተኝነት ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽ ታይቷል።
ይህ የሕዝብ አመጽ ያርበደበደው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን በማጣቱ፣ የእርሱ ምርኮኛ የሆነውንና በጥቅማጥቅም የገዛውን የትግራይ ትውልድ በነቂስ አስታጥቆ፣ በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ ለመዝመት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስተማማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ። የትግሬ-ወያኔ ከሚያደርገው ሠፊ የጥፋት ዝግጅቶች ውስጥ፣ የትግራይን ትውልድ «በትግልህ ያገኘኸውን ልዩ መብትና ነፃነት፣ ትምክተኞች፣ ነፍጠኞች፣ የድሮው ሥርዓት አራማጆችና ዐማሮች ሊነጥቁህ ነውና ዐማራን ለማጥፋት ዝመት፣ ተንቀሳቀስ» በማለት፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በአርማጭሆ ነዋሪዎች ላይ ክተት አውጇል። በአጠቃላይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም ሰሞኑን በጎጃምና በጎንደር የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ቡድኖችን በማሰማራት ሌሊት ሌሊት ወጣቱን እየፈነ ወደ ማሰቃያ እስር ቤቶቹ እያስገባ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ድርጊቱ ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ሊሳካለት እንደማይችል በመረዳት፣ በመላ ኢትዮጵያ የሚያካሂደው ሌላም ሠፊ የጥፋት ዕቅድ አቅዶ ለተግባራዊነቱ በጥድፊያ እየሠራ መሆኑ እየተሰማ ነው። ይህም መጠነ ሠፊ የሆነ ጥፋት ያነጣጠረው በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ እንደሆነ ታውቋል። የትግሬ-ወያኔ በእነዚህ ነገዶች ሕዝብ ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመወጣት ያቀደው ዕቅድ፣ «በዐረብ ኢሚሪቶችና በሻዕቢያ የሚታገዙ አሸባሪዎች፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ እየተንቀሳቀሱ ነው» የሚለውን ሀሳብ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ፣ በተለይም ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ሸሪክ የሆነውን የምዕራቡን ዓለምና የአሜሪካንን ልብ ለማማለል እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ረገድ በቅርብ ቀናት ውስጥ የትግሬ-ወያኔ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳርና መሰል ከተሞች፣ የሕዝብ ክምችት በሚበዛባቸው ቦታዎች፣ በመንግሥታዊ ተቋሞች፣ በመገናኛ አውታሮች ወዘተርፈ ፈንጅ በማፈንዳት እኩይ ዓላማውን በተግባር እንደሚያውል ውስጥ አዋቂዎች አስጠንቅቀዋል። ፈንጂዎችን ራሱ አፈንድቶ፣ «የዐማራ እና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንዲህ አደረጉ» በማለት ለደጋፊዎቹ  የተቀነባበረ የሤራ መረጃ በማቅረብ፣ «ሕገ-መንግሥት» ተብየውን አግዶ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አገዛዝ በማወጅ፣ በሁሉም ቦታዎች ለወያኔ ጄኔራሎች የመግደልና የማሰር ሥልጣን በመስጠት በዐማራውና በኦሮሞው ነገዶች ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊና አሰቃቂ ዕልቂት ለመፈጸም ቁርጠኛ አቋም መያዙ ታውቋል።
በሰኔ 1980 ዓ.ም. «ነፃ ላወጣህ መጣሁ» ባለውና በራሱ ነገድ በሆነው የሀውዜን ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ላይ ያን የመሰለ የተቀነባበረ ሤራ ሠርቶ ሕዝብ ያስጨረሰ ድርጅት፣ «ጠላቶቼ ናቸው» ባላቸው የዐማራና የኦሮሞ ነገድ ሕዝብ ላይ ይህን ዓይነቱን ድርጊት አያቅድም፣ አይፈጽምም፣ አያደርጉትም፣ አይሆንም የሚያሰኝ አመክንዮ አይኖርም። ኢትዮጵያዊ የሆኑትንና «ለትግሬ-ወያኔ ዓላማ አንገዝም፣ አባልም አንሆንም» ያሉትን የትግራይ ልጆች፣ «አባሎቼ ናቸው» የሚል የተቀነባበረ የሐሰት መረጃ፣ ለደርግ የመረጃ አካላት እያቀበለ ወገኖቹን ያስጨፈጨፈ ድርጅት ይህን አያስብም አይባልም። በሂደት እንዳስተዋልነው፣ ወያኔ «አደርገዋለሁ፣ አጠፋዋለሁ» ብሎ ያቀደውንና ያለው በተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ ያለበት አንድም አጋጣሚ አላየንም። ይህንም እኩይ ድርጊት አያደርገውም ለማለት የሚያስችል ምክንያት ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው።
የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጠፋለሁ ብሎ አቅዶ መነሳቱ ይታወቃል። በዕቅዱ መሠረትም 5 ሚሊዮን ዐማራ አጠፋ። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመራርን ከሦሥት ከፈለ፥ የአገር ቤትና ስደተኛ ሲኖዶሶች እንዲሁም ገለልተኛ በሚል። የሃይማኖቱ ነባር ተቋሞችን፣ ለምሣሌ ያህል፥ የዋልድባን፣ የዝቋላ አቦን እና የማኅበረሥላሴን ገዳማትን አቃጠለ፤ ቅጥረ ግቢያቸውን መነጠረ። የሃይማኖት አባቶችን አሰደደ። ቱባ ባለሥልጣኖቹ ዐባይ ፀሐየ፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሣሞራ የኑስ ሌሎችም በአደባባይ፣ «ዐማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል፣» «ገድለን ቀብረነዋል» ማለታቸውን አንዘነጋም። እናም ባለፉት 25 ዓመታት ገድለው ካልጨረሱት ውስጥ የቀረውን የዐማራና የኦሮሞን ነገዶች ሕዝብ «አስቸኳይ ወታደራዊ» አገዛዝ በማወጅ ሊጨርሱት ቁርጥ ሀሳብ ማድረጋቸውን የዐማራውና የኦሮሞው ነገድ አባሎች ለአፍታም መጠራጠር አይኖርባቸውም። ስለሆነም፣ የትግሬ-ወያኔ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ጥፋት ተልዕኮው ሳይገባ፣ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዕቅዱን ለማክሸፍ መተባበር ይጠበቅባቸዋል።
ከሁሉም በላይ «ሺህ ጋን ቢታለብ ወይ በገሌ» እንዳለችው ድመት፣ ዐማራው በብሔርተኞቹ ድርጅቶች በቀና ስለማይታይ፣ ልጆቹ በመካከላቸው አለን የሚሏቸውን ጥቃቅን ልዩነቶች በማርገብ፣ በአንድነት በመቆም ለወገናችን መከታ መሆን ይጠበቅብናል። የዐማራው ምሁራንና ፖለቲካኞች በአንድነት መቆም፣ የአንድነት ኃይሉን ለተፈላጊው አጠቃላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት ጽኑ መሠረት ስለሚሆን፣ የዐማራው ምሁራን በቅድሚያ የነገዳቸውን አንድነት ዕውን በማድረግ፣ በሌሎች አቻ ቡድኖችና ድርጅቶች ላይ መልካም ተጽዕኖ ማሳደር ይጠበቅባቸዋል። ይህን ለማድረግ ስበቦችን መደርደር አስፈላጊ አይደለም። በወገናችን አንገት ላይ ሳንጃ ተጥሏል፤ በግንባርና ደረቱ ላይ አፈሙዝ ተደግኗል። ስለዚህ ይህ ጊዜ አይሰጥምና በዐማራ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች ከያላችሁበት «አለን» ብላችሁ በጋራ የምትሠሩበት መንገድ ካሁኑ ካልጀመራችሁ፣ ይህንም ለወገናችሁ በግልጽ ካላሳያችሁ፣ የጥፋቱ አካል እንጂ፣ የመፍትሔው አካል ናችሁ ብሎ ማኅበረሰቡም ሆነ ታሪክ  ሊያወሳችሁ እንደማይችል በእርግጠኝነት መናገር ድፍረት አይሆንም። ስለሆነም ሁላችንም ለዐማራው ኅብረትና አንድነት ኅሊናችን ከፍተን በቅንነት እንነሳ! በዚህ የመከራ ጊዜ የዐማራው ልሂቅ በአንድነት ቆሞ፣ ለወገኖቹ ቤዛ ካልሆነ ምንጊዜም ዐማራው አንድ ይሆናል ለማለት ያስቸግራል። እንኳን የአንድ ታላቅና ታሪካዊ ነገድ ልጆች ቀርቶ፣ በክረምት እባብና ጓጉንቼር በአንድ ጉድጓድ ይኖራሉ። ይህ ክፉ የወያኔ ዘመን ዐማራውን ቀርቶ፣ ዐማራና ኦሮሞውን በአንድ ካላሰላለፈ የኢትዮጵያ አንድነት ርቆ የተሰቀለ ባዶ ተስፋ ከመሆን አያልፍም።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ዐማራነት ነፃነት፣ ዕኩልነት አንድነት ነው!

ኢትዮጵያ በቆራጥና ጀግና ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

መግለጫ በቶሮንቶና አካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሽዋ ከፍለ ሀገር ልጆች የተላለፈ ጥሪ


ላለፉት  ሃያ አምስት ዓመታት ዘረኛውና ክፋፋይ የወያኔ አገዛዝ በመላው  ኢትዮጵያውያን ላይ፤ በተለይ ደግሞ በአማራው ላይ በቃላት ሊገለጽ በማይችል ለሰው አይምሮ በጣም ከባድ በሚሆኑ የግድያ፣ ህዝብ የማፈናቀል፣ የግፍና የበደል ዶፍ ሲወርድበት  የቆየው የጎንደር- በጌምድር ክፍለ ሀገር ሕዝብ በሰላም እየታገለና በትእግስት ችሎ ችሎ ባለፉት 15 ቀናት ውስጥ ከሞት ውጭ የቀረኝ አማራጭ ስለሌለ፤ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ለማንነቴ፣ እንዲሁም የጎንደር ሕዝብ ለመብቴና ለኢትዮጵያዊነቴ የመጨረሻውን መስዋእትነት እከፍላለሁ ብሎ በመነሳቱ የወያኔ የጸጥታና የጦር ሃይል እንደለመደው ለመግደልና ለማሰር ሲሞክር ከሕዝቡ ጋር ግጭት አድርጓል፤ አሁንም ሕዝቡ በመፋለም ላይ ይገኛል። በመጀመሪያ የጎንደር ሕዝብ ቆራጥነቱ፣ ጀግንነቱና ወኔው አኩርቶናል፤ ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ማውለብለቡ ከልብ አስደስቶናል።  ኖር!  ኖር ! እንላለን።

 በጎጃምም የባህር ዳር ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ለጎንደር ሕዝብ ድጋፉን ሲያሳይ እና ለወያኔ አልገዛም ሲል  በመነሳቱ፤ በአግአዚ ጦር በጭካኔ መጨፍጨፉና መደብደቡ ቢያሳዝነንም፣ ቢያስቆጣንም የሕዝቡ ቆራጥነትና እምቢተኛነት እጅግ አኩርቶናል፤ ከጎንህም ነን አለንልህ እንላለን። ችግሩ ችግራችን፣ ስቃዩ ስቃያችን፣ ሞቱ ሞታችን ነውና  ክጎንደር - በጌምድር ክፍለ ሀገር ከተወለዱ ልጆቹ፣ ክጎጃም እና ከወሎ ከ/ሀገር ከተወለዱ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመወያየትና በመመካከር አስፈላጊውን ሁሉ እርዳታ ለመስጠት ነሐሴ 1 ቀን 2008 ( Aug 7, 2016) ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባ በአንድ ድምጽ ወስነናል፤ ቃል ገብተናል። ስለዚህ ይህን ታሪካዊና የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ትግል በምትችሉት መጠን እርዳታና ድጋፍ እንድታደርጉ የትግሉም አካል እንድትሆኑ የአገርና የሕዝብ አድን ጥሪ እናስተላልፋለን።


 ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘላለም  ትኖራለች! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ! 

ቶሮንቶ፤ ካናዳ   እርዳታና ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ፤ 647 219 2804  ይደውሉ  

Monday, August 15, 2016

ከታሪክ መዝገብ ለመሆኑ አማራ ማነው ኀይሌ ላሬቦ

ዛሬ በሥልጣን ላይ ያለው የወያኔ መንግሥት ዐማራ በተባለው ኅብረተ-ሰብላይ ብዙ ግፍና ዐመፅ እንደፈጸመና እንዳስፈጸመ በገፍ ይነገራል። በኅብረተሰቡ ላይ ተፈጸሙ ከተባሉት ድርጊቶች አብዛኞቹ በሥዕል የተቀረጹ፣ ለሰው መብት በቆሙ ባስተማማኝ ብሔራዊና ዓለም-ዐቀፍ ድርጅቶች ከነማስረጃቸው የተጠናቀሩ፣ እሙን በሆኑ ያይን ምስክሮች የተደገፉ ስለሆኑ ማስተባበሉ ከመደናቈርና የአተካራ ግብግብ ከመግጠም ውጭ ሌላ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የግፎቹ ኢሰብኣዊነትና የፈጻሚዎቻቸውም አውሬነት ለሚሰማ ሁሉ ከመዘግነን አልፎ፣ ሰው ሁኖ መፈጠሩን ራሱን የሚያስጠላ ከመሆኑ የተነሣ፣ ልቦና ያለው ተመልካችም ሆነ ሰሚ፣ መንግሥት ነን ባዮቹ የወያኔ ገዢዎች በጀርመንና በኢጣሊያን ምድር ከታዩት ከናዚና ከፋሽስት መንግሥታት መሪዎች በምን ይለያሉ ብሎ ለመጠየቅ ይገደዳል።

በበኩሌ ጥላቻው ከየት መጣ ብዬ አውጥቼ አውርጄ ማሰላሰል ከጀመርሁ ዓመታት ቈጥሬአለሁ። ዕድል ቀንቶኝ ከብዙ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጋር ኑሬአለሁ፤ አድጌአለሁም። ስለዚህ ፍንጭ ይሰጠኝ ይሆናል ስል ወደልጅነት ሕይወቴ ወደኋላ ተመልሼ በዐይነ-መነጽሬ ሳይና ሳሰላስል፡ ሁሌዬ ተመላልሰው እፊቴ የሚደቀኑብኝ ሁለት ገጠመኞች ናቸው። አንደኛው በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ከምትባል ከተማ በሠላሳ ኪሎሜትር ያህል ርቀት የሚገኝ መንዲዳ የተባለ መንደር አለ። ባንድ የኢጣሊያን መሐንዲስ ለሕንፃ ሥራ ተቀጥረው ከሰሜን የመጡ ሠራተኞች ባካባቢው ዘመናዊ ምግብ ቤት ስለሌለ፣ ሁሌዬ የሚበሉት ከተማሪዎቹ ጋር አብረው ነበር።

የቀረውን ምግብ ሁሉ በልተው፣ ጠላዉን ብቻ መተው ልማዳቸው ሁኖ ስለነበር፣ አስተናጋጁ ገርሞት አንድ ቀን ምክንያቱን ሲጠይቃቸው አላንዳች ማፈር “ዐማሮች ናችሁ አሉን፤ ዐማራ ቂጥኝ አለውና እንዳይተላለፍባችሁ ምንም ዐይነት መጠጥ ቢሰጣችሁ እንዳትጠጡ ተብለን ስለተመከርን ፈርተን ነው” ብለው በጨዋነት መልስ ሰጡ። ሌላው በአሥመራ ከተማ በአንዳንድ አስተማሪዎች አነሣሽነት፣ ተማሪዎቹ እነዚህን ዐማሮች አታናግሯቸው ተብለው ስለተመከሩ፣ ከደቡብ የመጣነው በመጀመርያው ዓመት ምንም ብንጥር ጓደኛ ማፍራት ከባድ ሆነብን። እምብዛም ባይሆን ጥቂት ከምንቀርባቸው ጋር ችግሩ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተሰባሰብን። መልሱ እውነትም ‘ዐማሮች’ ስለሆነን እንደነበር ለማወቅ ብዙም አልፈጀንም። 

ከሁሉም የከፋብን ግን ዐማሮች አይደለንም ስንል፣ ቀጥሎ የመጣው ልውውጥ ነበር። “ዐማሮች ካልሆናችሁ፣ ታዲያ ጋላ ናችሁ እንዴ!” ተባልን። ለዚህም በአሉታ ስንመልስ፣ “ታዲያ ከጋላ በታች ሰው አለ እንዴ!” ሲሉን ክው አልን። እንግዴህ እነዚህ የልባቸውን የሚናገሩ ላቅመ አዳም እንኳን ያልደረሱ ልጆች ናቸው፤ በጭንቅላታቸው ውስጥ የሚያንሸራሽሩት አሳቦች ግን የአካባቢውን ስሜት የሚያንፀባርቁ ሊሆኑ አይችሉም ብዬ መከራከሩ የሚያዋጣ ስለማይመስለኝ አልፈዋለሁ። ሁኖም የገጠመኙ ወቅት የወያኔ መሪዎች ልክ ወደጫካ ያመሩበት ጊዜ ስለነበር፣ የዛሬውን ሥራቸውን እያየሁ የለም እነሱ በዚህ ዐይነት አስተሳሰብ የተበረዙ ሰዎች አልነበሩም ብዬ ማሰቡ ያዳግተኛል። በአፍሪቃ ቅኝ ገዢዎችና በፋሽስቶች እጅ ባካባቢዎቻቸው ይካሄድ የነበረው ኀይለኛ ስብከት፣ በዐማራ ላይ ጥላቻ፣ በተቀረው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ላይ ደግሞ ከፍተኛ ንቀት እንዳሳደረባቸው አይጠረጠርም ብል በሐሰት የምወነጀል መስሎ አይታየኝም።

በሁለተኛ ደረጃ መታወቅ ያለበት ወያኔዎች የቀዝቃዛ ጦርነት ፍጻሜው ውጤት መሆናቸው ነው። በዚህ ጦርነት መጨረሻ፣ በሕይወቱ ወቅት እንደመዥገርት የሕዝባቸውን ደም እየመጠጡ የደነደሱ መንግሥታት እምብዛም ሳይቈዩ ወዲያው ፈረጡ:: የሁለተኛው ዓለም መሪዎች ተራ በተራ ከሥልጣናቸው ሲወድቁ፣ ያልታደሉት ታረዱ፤ በለስ የቀናቸው ደግሞ ለፍርድቀርበው ሰለባቸው ከነበሩት ጋር ተፋጠጡ። በሦስተኛው ዓለም የሁለቱ

ኀያላን ባላንጣዎች መንግሥታት፣ ማለትም የአሜሪቃና የሶቭየት ኅብረት፣ ቱኪዎቻቸው የነበሩት ገዚዎች ግን፣ እንደሁለተኛው ዓለሙ መሪዎች በየአመዳቸው አልቀሩም። እንደኢትዮጵያው መንግሥቱ ኀይለማርያም፣ የሱማሌው ሲያድ ባሬና፣ የድሮዋ ዛይር የዛሬዋ ኮንጎ ሞቡቶ ሴሴኮ የመሳሰሉት፣ ያን ሁሉ የድሎታቸውና ያምባገነንታቸው ወቅት ድንፋታና ጉራ ረስተው ይሰብኩ ለነበሩት ለናት አገር ፍቅር እንደመቆም፣ ሁላቸውም ነፍሴ አውጭኝ እያሉ በደንገለላ ሳይሆን በሽምጥ ፈረጠጡ።

በጦርነቱ ድልና የበላይነት ያገኘችው አሜሪቃም በኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥቱ ኀይለማርያምና ጀሌዎቹ በጣር ላይ መሆናቸውን ስታይ፣ ዕድሉ ሳያመልጣት በራሷ ተላላኪዎች ልትተካቸው እንደተሟሟተች፣ ከደርግ መንግሥት ፍጻሜ ዋዜማ በተደረገው በአስችኳይ ስብሰባ ላይ ጥርት ብሎ ይታያል። በስብሰባው፣ አሜሪቃ ሥልጣን ቋማጩቹን ገለልተኛ አገላጋይ መስላ ብታደራደራቸውም፣ ኳሱንም ሜዳውንም ሙሉ በሙሉ በወያኔ እጅ እንደተወች ለመረዳት አብዛኛውን ተመልካች አያዳግትም ነበር ቢባል ሐቅ ይመስለኛል። ባሜሪቃና በዐረቦች ትብብር፣ የኅበረተሰባዊነትና የመደብ ጦርነት አንጋቢው ደርግ በመስኮት ሲሸመጥጥ፣የጐጥና የጐሣ አንጋቾቹ ወያኔዎች በበር አድርገው ብቅ አሉ። በአንድ አስተዋይ ጓደኛዬ አባባል፣ ጅሎቹ የሩሲያን አምባገነን ቡችሎች፣ ባሜሪቃ አፋኝ አደንዝዝ ማጅራት መቺዎች ተበሉ።

በጫካ ኑሮ ዘመናቸው ወያኔዎች የተራማጅነት ጨንበል እንዳጠለቀ ወረተኛ ሁሉ፣ በኅብረተሰብአዊነት የተኰተኰቱ፣ የቻይናው ማኦ ቲሰቱንግ ታማኝ ደቀመዛሙርት፣ የአልባኒያው ኤንቨር ሆሻ አድናቂዎችና አጨብጫቢዎች ሲሆኑ፣ አሜሪቃ ግን ለነሱ የበዝባዦች ቊንጮና ደመኛቸው ነበረች። ሁኖም በደማስቆ መንገድ ክርስቲያኖችን ድምጥማቸውን ሊያጠፋ ሲጓዝ እንደነበረው ሐዋርያዊው ጳውሎስ፣ እነሱም ባንዴ ከአሜሪቃን ጥልቅ ጥላቻ ወደጥብቅ ፍቅር ተለወጡ።

ሥልጣን ላይ እንደወጡ የተገበሩትም ልክ የአሜሪቃ መንግሥት ዋና ጸሓፊ የነበረው ክሲንጀር ጥቂት ቀደም ሲል ስለኢትዮጵያ አረቀቀ የተባለውን ነው ማለት ይቻላል። በቀዝቃዛ ጦርነትና በዐረብ-እስራኤል ግጭት ሰበብ ከ፲፱፻፷ዎቹ መጨረሻ ላይ ጀምሮ፣ አሜሪቃ ስለኢትዮጵያ የነበራት መምርያ ከድሮው ከቅኝ ገዢዎቹ ከአውሮጳውያን መርህብዙም የማይለይና የማይራራቅ ነበር ማለት ይቻላል። የአውሮጳ ቅኝ ገዢዎች ኢትዮጵያ ካልተበታተነች የአፍሪቃን ክፍለ አገር በዘለቄታ ከሥልጣናቸው ሥር ለመያዝ አስተማማኝ ዋስትና አይኖረንም ይሉ እንደነበር ሁሉ፣ አሜሪቃም በቀይ ባሕር አካባቢ ያላትን ጥቅሟን እስከሚቻል ጊዜ ድረስ ለማስከበር፣ ኢትዮጵያ እንደ ዐረብ አገሮች ተከፋፍላና ተነጣጥላ ካልጠፋች በስተቀር አይሳካም ወደሚል አቋም የደረሰች ይመስላል። ቅኝ ገዢዋ ኢጣልያ ኢትዮጵያን ለመቈጣጠር “የዐማራን አከርካሪ በማያዳግም ሁናቴ መስበር አለብን” ትል የነበረውን አባባል፣ የወያኔም ባለሥልጣኖች በየጊዜው አስተጋብተውታል1።

 ስለዚህም የወያኔና የአውሮጳውያን ቅኝ ገዢዎች ሕልም አንድ ነው ማለት ይቻላል። እንግዴህ አሜሪቃ የ“ትግራይን ረፓብሊክ” መፍጠር ዋና ግቡ ያደረገውን ወያኔን ለሥውር ዓላማዋ ብትመርጥ ምንም የሚገርም አይመስለኝም። አሜሪቃም እንደአውሮጳውያኖች ቅኝ ገዢዎች ዐማራ ቢጠፋ ደንታቢስ ብትሆን ምን ይገርማል።

 እንደተለመደው የወያኔ መንግሥት ሥራ ከዚህ በፊት በተለያዩ ጽሑፎቼ እንዳነሣሁ፣ በጥላቻና በድንቁርና ላይ የተመሠረተ ሁኖ ነው እንጂ እነሱና እነሱን የመሳሰሉ የጐጥና የጐሣ ምሁራንና ልሂቃን የሚነበንቡት ዐማራ

 1 . የወያኔ መሪዎች ስለዐማራ ተናግረዋል ከሚባሉት ንግግሮች አንዳንዱ ለጠላትም ጆሮ እንኳን ይቀፋል። እዚህ ጥቂቶቹን ከነተናጋሪያቸው ጋር ልጠቅስ እወዳለሁ። 
“ ዐማራ ጠላት ነው” (የሕ.ወ.አ.ት. ማእከላዊ አቋም - ሰነድ)። “ዐማራ መንገድ ላይ ቁጭ ብሎ ሲለምን ማየት እፈልጋለሁ” (መለስ ዜናዊ)። 
“ዐማራን እንደ ሲጋራ ረግጠን ጥለነዋል” (ስዬ አብርሃ)።
 “ገድለን የቀበርነውን ዐማራ አታንሱብን” (ሳሞራ ይኑስ)።
 “ዐማራውንና ኦርቶዶክሱን ሰብረን ጥለነዋል” (አቦይ ስብሃት)።
 “ዐማራ ትምክሕተኛ ነው” (ገብረኪዳን ደስታ)።


በሕይወት ኑሮም አያውቅም ማለት ይቻላል2። ዐማራ [በግእዝ ቋንቋ አምሐራ] ለመጀመርያ ጊዜ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ስሙ የሚነሣው፣ በተለያየ ስም “ድግናጃን፣” “ደጋዛን”ና “ግዳዣን” በመባል በሚታወቀው በአክሱም ንጉሥ የሐዋርያዊነት ሥራ በተያያዘ ጉዳይ ነው። ንጉሡ ከመናገሻ ከተማው ወደመቶ ዐምሳ ሰባኪዎችን “ደብተራ” ብሎ ከሠየማቸው በኋላ፣ ሕዝቡን እንዲያከረስትኑ ወደ “ዐማራ” ምድር እንደላካቸው ሰነዱ ይገልጣል። እንግዴህ በዚህ ሰነድ መሠረት “ዐማራ” የሚያመለክተው፣ የተወሰነ የመሬት ክልል መሆኑ አይካድም። የተለያዩና በየጊዜው የመጡት የውጭ አገርና ያገር ቤት ጸሓፊዎች አላንዳች ማዛባት እንደሚናገሩ፣ ክልሉ በምዕራብ በኩል በአባይና እሱን በሚመግበው የበሽሎ ወንዝ፣ በሰሜን በአንጎትና ላስታ፣ በደቡብ በወንጭት ወንዝ፣ በምሥራቅ ደግሞ ወደደንከል በረሃ በሚደርሰው ሰፋፊ ገደላገደል የተከበበውን ምድር ይዋሰናል። ይኸ ዝርዝር እንደማስረጃ ካገለገለን እንግዴህ፣ ዛሬ የወያኔ መንግሥት ዐማራ ብሎ የሚጠራቸውን እንደነጐጃም፣ በጌምድር፣ ሸዋ እንዲሁም የወሎን ከፊሉን አያካትትም።

የዚህ ክልል ነዋሪዎች አፈታሪክ የሚነግረን፣ “ዐማሮች” ምንጫቸው በቀጥታ ከአክሱም ሲሆን፣ “ዐማራ” የሚለው ቃል ትርጒሙ “ነፃ ሕዝብ3” ማለት እንደሆነ ነው። ሁኖም ዐማራ በሰፊውና በገነነ መልኩ በመቈራኘት የሚታየው ከገዢው መደብ ጋር በመያያዙ ይመስለኛል። የአክሱማውያን መንግሥት ከብዙ የጨለማና የድብልቅልቅ ዘመን በኋላ የተተካው፣ በታሪክ ዛጐ በመባል በሚታወቀው ሥርወመንግሥት ሲሆን፣ ከሱም ቀጥሎ የመጣው “ሰለሞናዊ’” እያልን የምንጠራው ነው። የዛጐ መንግሥት በአገዎች እንደተቋቋመ ሁሉ፣ በታሪክ መሠረት የሰለሞኖች ሥርወ መንግሥት ቈርቋሪ ደግሞ ግእዙ “ንጉሠ አምሐራ4” በሚለው በአፄ ይኩኖአምላክ እንደሆነ ይታወቃል። እዚህ በጣም መጠንቀቅ የሚገባን ነገር አለ። “ንጉሠ አምሐራ” የሚል ስያሜ ይኑራቸው እንጂ፣ ጐንደር የነገሥታቱ ቋሚ መናገሻ ከተማ ሁና እስከተቈረቈረችበት ማለትም እንደአውሮጳ አቈጣጠር [አ.አ.] እስከ ፲፮፻፴፪ ዓ. ም. ጊዜ ድረስ፣ ምናልባትም ከመጀመርያው “ንጉሠ አምሐራ” ውጭ፣ በዐማራ ምድር ውስጥ የነገሠ ሌላ ንጉሥ ነበር ማለት ያዳግታል። ግዛታቸው ሰፊ፣ ተራራማና ገደላገደል የሞላበት ስለነበር፣ ለቊጥጥር እንዲያመቻቸው ሲሉ፣ ነገሥታቱ የሚኖሩት በየጊዜው ሰፈር እየቀያየሩ “በዟሪ” ወይንም “በተሽከርካሪ ከተማ፡” ነበር። ሥልጣናቸውን በየጊዜው በመፈታተን እከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥሉት ሁናቴዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚፈጠሩት በአገራቸው ደቡብና ምሥራቅ ባሉት የእስላሞች ባላባቶች በኩል ስለነበር፣ ይኸንን በመገንዘብ የዟሪ ከተማቸው ዋና ዋናዎቹ ግዛቶች በደቡብ እንደነይፋትና ሸዋ፣ ደዋሮና ፈጠጋር የመሳሰሉት አገሮች ነበሩ። ከዘመነ-መሳፍንት በኋላም ቢሆን፣ በዐማራ ምድር ውስጥ የነገሠ ንጉሥ እንደሌለ ስለምናውቅ ወደዝርዝሩ መሄድ አስፈላጊ ሁኖ አይታየኝም።
ዐማራ የተባለው ክልል የ”ዐማራ” የነገሥታት መቀመጫ ሁኖ እንደማያውቅ ግልጽ ከሆነ፣ አገሩን የሚገዙት ነገሥታቱስ ከዐማራ ቤተሰብ ወይንም ክልል የተወለዱ ነበሩ ወይ ብሎ መጠየቁ ተገቢ መስሎ ይታየኛል። አፄ 2 . መጥሌነትና ድንቁርና ብዙውን ጊዜ ተያይዘው ናቸው የሚሄዱት። ኢጣሊያን አገር ተማሪ ሳለሁ፣ አንድ ከደቡቡ [በሥልጣኔ ወደኋላ ከመቅረቱ የተነሣ “mezzo-giorno” ወይንም “መንፈቀ-ዕለት” ይሉታል] በኩል የመጣ የደስደስ ከፊቱ ያለው ጓደኛችን ካገር ቤት የተላኩልንን የውብ ቤቶች ሥዕል (ፎቶግራፍ) እያየን ሲንጯጯህ ሰምቶ መጣና፣ ሥዕሎቹን ሲያይ ገርሞት፣ “እናንተ ጥቁርች፣ሥዕሎቹ ከየት ናቸው” ሲል ጠየቀን። “ካገራችን” ስንለው፣ ደጋግሞ ያየው የታርዛን ፊልም ትዝ ብሎት ነው መሰለኝ፣ “አፍሪቃ ውስጥ ሁሉም እዛፍ ላይ የሚኖር መስሎኝ! ታዲያ ቤትም አለ እንዴ” ሲለን ከኛ አንዱ፣ “እውነትህን ነው ሁላችንም የምንኖረው በዛፍ ላይ ነው። የኢጣሊያን አምባሳደር ደግሞ የሚኖረው ከሁሉም በረዘመው ዛፍ ላይ ነው” ብሎ ባሽሙር ሲያሽማጥጥበት ነገሩ ያነውኑ ገባው። 3 . ቃሉ መሻዘር “ዐም (ዕብራይስጥ)= ሕዝብ”፣ “ሐራ = ነፃ” 4 . ትርጒሙ “የዐማራ ንጉሥ” ማለት ነው። 4 ይኩኖ አምላክ “ንጉሠ አምሐራ” ቢባሉም፣ በመከታተል አልጋቸውን የወረሱት ነገሥታት ግን፣ ምናልባትም ከመጀመርያዎቹ ጥቂቶቹ በስተቀር፣የአብዛኞቹን የቅርብ ወላጆቻቸውን [ማለትም አባትና እናት] ብንመለከት፣ ሙሉ በሙሉም ሆኑ፣ በከፊል ከዐማራ ዘር ወይንም ምድር መሆናቸው እጅግ በጣም አጠያያቂ ነው ማለት ይቻላል። ለማንኛዉም እስኪ ወደጥልቅ ሳንገባ ለማስረጃ ያህል የሚከተሉትን እንያቸው። በ፲፮ኛ ዘመን የነገሡት ነገሥታት፣ ካፄ ልብነድንግል ባለቤት ከጐጃሜዋ5 ከእቴጌ ሰብለወንጌል በስተቀር፣ የሁሉም ሚስቶቻቸው የትግራይ ወይንም የሐዲያ ተወላጆች ነበሩ ማለት ይቻላል። የቄንጠኛዋ የጐንደር ከተማ መንግሥት ነገሥታት፣ የአፄ ሱስንዮስ ዝርያ ናቸው። እርሳቸው ደግሞ በእናታቸው ከቤተእስራኤል ሲሆኑ፣ ወልድ ሠዓላ ይባሉ የነበሩት ሚስታቸው እቴጌ ሥልጣን ሞገሳ በበኩላቸው ከኦሮሞ ብሔረሰብ መሆናቸው ይነገራል። እናታቸውም እስላም ነበሩ ይባላል። ከዚህ የምንማረው ነገር ቢኖር፣ ጐንደርን ከቈረቈረው ከልጇ ፋሲለደስ ጀምሮ እስከ ዘመነ-መሳፍንት ድረስ በኢትዮጵያ ዙፋን ይቀመጡ የነበሩት የኦሮሞ፣ የቤተእስራኤል ደም ካላቸው ብሔረሰብሶች የተወላለዱ ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሩ ማለት ነው።

የዘመነመሳፍንቱ ነገሥታት በደምገንቧቸው የነበረው ደም በግልጥ የቋራና የኦሮሞ ድብልቅ ነው። የገዛራሳቸውን “ርእስ መስፍን ዘኢትዮጲያ6” በሚል የማዕርግ ስም ሠይመው፣ነገሥታቱን በዘፈቀደ እንደጉልቻ እየቀያየሯቸው በበላይነት የሚመሩት ፈላጭቈራጮቹ መሪዎች ደግሞ ከመላ ጐደል የየጁ ኦሮሞች7 ነበሩ። ዘመኑም የሚታወቀው በሥርወመንግሥታቸው የ“ወረሼኮች8” በመባል ነው። ዘመነ መሳፍንት ማለት እንግዴህ የኦሮሞ ዝርያ ናቸው የተባሉት የየጁ መኳንንት ላንድ መቶ ዓመት ያህል የጐንደርን መንግሥት ሙሉ በሙሉ የተቈጣጠሩበት የኢትዮጵያ ታሪክ ዘመን ነው ማለቱ እውነትትን ያንፀባርቃል ብዬ አምናለሁ። ከዘመነመሳፍንት ባሻገር፣ ወደዛሬዋ ወደዘመናዊት ኢትዮጵያ ብንመጣ ሁናቴው ብዙም አይቀየርም።

 ሦስቱ አጼዎች (ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ9ና ምኒልክ) ከገዛ ራሳቸውም ሆኑ ከሚስቶቻቸው መካከል አንድም ጭንጩ ዐማራ በርግጥ የለም ማለት ይቻላል። አፄ ቴዎድሮስ 10 ከቋራ፣ አፄ ዮሐንስ ከትግራይ፣ አፄ ምኒልክ ከተለያየ ብሔረሰብናቸው። ልጅ ኢያሱና አፄ ኀይለሥላሴ
11 ደግሞ ያማራ ደም አለባቸው ቢባልና ቢለካ በርግጥካሥር የአንድ ግማሽ እጅ እንኳን ላይሞላ ይችላል ብል ሐሰት አይደለም።

 ከነገሥታቱ ወረድ ብለን በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙትን ባለሥልጣናት ብናይ፣ ደረጃው ሁሉንም አካባቢና ብሔረሰብ ያካተተ ሁኖ እናገኘዋለን። ሁኖም በገዢዎች ትውልድ አካባቢ ለሚመራመር ግለሰብ ታላቁ ችግር፣ ታሪክ ጸሓፊው በግልጥ ካልተናገረ በስተቀር በስም ብቻ ተመሥርቶ ባለሥልጣኑ ከየትኛው ብሔረሰብወይንም አካባቢ እንደመጣ መንገር በጣም ያዳግታል። ምክንያቱም በኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ ውስጥ አንድ ግልጥ ሁኖ የሚታይ ጉዳይ ቢኖር፣ ሥልጣንና ሹመት የግለ-ሰቡ የአገልግሎት ብቃትና ትጋት ፍሬ ውጤት እንጂ 
 5 . የጐጃም ነዋሪ አማራ እንዳልነበረ ዝቅ ብሎ ይታያል። 
6 . ትርጉሙ “የኢትዮጵያ የበላይ ገዢ”። 
7 . ትንሹ ራስ አሊ በመባል የሚታወቀው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በተፈራረመው የንግድ ውል የንጉሡንና የራሱን ማኅተም በሰነዱ ላይ ቢያኖርም፣ ራሱን “የኢትዮጵያ ንጉሥ” ብሎ ነው የፈረመው።

 8 ቃሉ ሙሻዘር ሲሆን ከኦሮሞኛ “ወረ = ቤተሰብ”፣ ከዐረብኛ “ሼኽ/ሸይኽ = ሼኽ”፣ ከአማርኛ “ኦች = የብዙ ምልክት” የተወጣጣ ነው። ባንድጋ ሲጋጠም “የሼይኽ/ሼኽ ቤት/ቤተሰብ” ሲሆን፣ ስሙ የሚያመለክተው ሥርወመንግሥታቸው የኦሮሞ፣ የአማራ ወይንም የአርጐባና የእስላም ቅልቅል መሆኑን ነው። 

9 . የአፄ ዮሐንስ ባለቤት እቴጌ ምሥጢረ ሥላሴ የአፋር ተወላጅ ነበሩ። አፄ ዮሐንስን ያገቡት ከከረስተኑ በኋላ ነው። 

10 . አፄ ቴዎድሮስ የቋራ ብሔረሰብ ሲሆኑ፣ ባለቤታቸው እቴጌ ተዋበች የታናሹ ራስ አሊ ልጅ ናቸው። 

11 ልጅ ኢያሱ የወሎው ገዢ የንጉሥ ሚካኤልና የወይዜሮ ሸዋረጋ ምኒልክ ልጅ ናቸው። አፄ ኀይለሥላሴ ባያታቸው ኦሮሞ ሲሆኑ እናታቸው ጉራጌ ናቸው ይባላል፣ ባለቤታቸው እቴጌ መነን አስፋው የልጅ ኢያሱ የእኅት ልጅ ናቸው። 5 በትውልዱ ዘርና አካባቢ የተገደበ አይደለም ማለት ይቻላል። ሿሚው በመጀመርያ ደረጃ እንደመስፈርት የሚጠቀማቸው የተሿሚውን ችሎታና ታማኝነት እንጂ ከየትኛው ቤተሰብና ብሔረሰብ ወይንም ቀዬ መምጣቱን አይደለም። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ አንድ በጥብቅ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር፣ ብዙ ጊዜ በተሳሳተ የአውሮጳውያን ታሪክ በመመሥረት ስለኢትዮጵያ የጉልተኛ ባላባት12 ሥርዐት የሚናገሩ በርካታ ጸሓፊዎች ቢኖሩም፣ ሐቁ ግን እውነትን ለማዛባትና ለማወናበድ ካልሆነ በስተቀር ሥርዐቱ ባገራችን በግልጥ የታየበት ጊዜ ከቶ የለም። መደብ፣ ወገንና አካባቢ ጠቃሚነታቸው በሁለተኛ ደረጃ ሊሆን ይችላል። ግን እንደችሎታና ታማኝነት ወሳኝ መስፈርቶች አይደሉም። ስለዚህም ነው እንግዴህ ከላይ እንደተባለው ስለባለሥልጣኖቹ ማንነትና አካባቢ ብዙም የማናውቀው። ሁኖም አንዳንዴ ካንድጉዳይ ጋር በማማያያዝ፣የጥቂቶች ማንነታቸው ሲጠቀስ ይታያል። እስኪ ከነዚህ መካከል ለወጉ ያህል ጥቂቶቹን እንመልከት። በአፄ ሱስንዮስ ዘመን ከሁሉም ታላቅ ሹመት ሁኖ የሚገመተውን የጐጃምን ግዛት፣ “ጐጃም ነጋሽ” የሚለውን ያገሩን ገዢ ማዕርግ ተከናንቦ ለብዙ ዓመታት ያስተዳደረው የጉራጌው ተወላጅ “ጐጃም ነጋሽ ክፍሎ” ነበር። ያፄ ሠርፀድንግልን ሁለት ልጆች አግብቶ፣ መላ ኢትዮጵያን በበላይነት ያስተዳድር የነበረው በጊዜው የመንግሥት ፈላጭ-ቈራጩ መኰንን፣ የወለጋው ተወላጅ ራስ ዘሥላሴ13 ነበር። በ “ዳሞት ጸሓፊላምነት” ማዕርግ፣ የኢትዮጵያን ሕዝብም ሆነ፣ ወሰንና ድንበር ለማስጠበቅ ሲል ብዙ ጦርነት በጀግንነት በመዋጋት፣ ንጉሠነገሥቱን እንደአ.አ. ከ፲፮፻፲፯ እስከ ፲፮፻፳፯ ዓ.ም. በታማኝነት አገልግሎ፣ በመጨረሻም የዳሞት ግዛቱን ከኦሮሞ ወረራ ሊከላከል ሲል በጦር ሜዳ ላይ ሕይወቱን የሠዋው ደጃዝማች ቡኮ፣ ከመጀመርያዎቹ የኦሮሞች ታላላቅ ገዢዎች አንዱ ነበር። እንዲሁም ንጉሠነገሥቱ “እንደልቤ ታማኝ” ይሉት የነበሩት፣ ዋናው አማካሪያቸውና፣ ከቁመታቸው ዕጥረት የተነሣ በኦሮሞኛ ቃል “ጢኖ” በመባል የሚታወቁት፣ ጸሓፈ ትእዛዙ አዛዥ ተክለሥላሴ፣ የኦሮሞ ብሔረሰብ ነበሩ።

ጽሑፋቸው እንደሚያመለክተው፣ አዛዥ ጢኖ ከኦሮሞ ቋንቋና ባህል በተጨማሪ፣ ዐማርኛና ግእዝ አሳምረው የሚያውቁ፣ ቅኔ የሚቀኙ፣ አንደበታቸው የተባ፣ ብዕራቸው የሰላ ጸሓፊ ናቸው። እነዚህ ለእንደዚህ ዐይነት ወግና ማዕርግ ሊበቁ፣ ዕውቀትንም ሊገበዩ የቻሉት፣ “ጋላ” በኢትዮጵያ ፈጸመ የተባለው ወረራ ግማሽ ዘመን ማለት ዐምሳ ዓመት እንኳን በማይሞላው ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ እስከኛ ጊዜ ድረስ ባሉት ዐራት መቶ ዓመታት ውስጥማ ምን ያኽል መቀራረብና መዋሐድ እንደተካሄደ መገንዘብ የሚያዳግት አይሆንም።

 ከላይ ስለልጅ ኢያሱና አፄ ኀይለሥላሴ አንሥቻለሁ። ከነዚህ ሁለቱ ጋር በተያያዘ፣ በቅርብ ጊዜ ባነበብሁት ባንድ ሊቅ ሕዝቅኤል ኢብሳ በተባሉ ያንድ ዩኒቬርሲቲ መምህር ተደርሶ በበርካታ የኢትዮጵያ ድረ-ገጾች በወጣ ጽሑፍ ላይ አንዳንድ ኂሶች መሰንዘሩ ተገቢ መስሎ ይታየኛል። ሊቁ “ኢትዮጵያ፤ የኦሮሞ እውከት፤ ስለብሔራዊ ጥያቄና ወደሕዝበ መንግሥት ሽግግር 14” በሚል ድርሰታቸው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ግንባር [ኢ.ሕ.ዴ.ግ] በመባል የሚታወቀው የወያኔ መንግሥት በዐዋጅ ኦሮሞ ብሎ በሠየመው ሕዝብ ላይ የጐሣው አቀንቃኞች ደርሶበታል የሚሉትን ግፍና ሰቈቃ ይተርካሉ። ታሪክን በገለልተኛነት ለሚመራመርና የኦሮሞን ሕዝብ ታሪክ ለሚያውቅ ምሁር፣ የሊቁ ንግግር የተለመደውን ደጋግሞ ከመወሸከት ውጭ ምንም አዲስ ነገር ስለማያፈነጭ ጊዜ ላለመፍጀትና የጽሑፌን አቅጣጫ ላለመለወጥ ስል አልፈዋአለሁ። ሁኖም ላነሣ የፈለግኋቸው ሁለት አውራ ነገሮች አሉ። 

12 . በ እንግሊዝኛ ፊውዳሊዝም [feudalism] በመባል የሚታወቀው ሥርዐት ነው። 13 . ጸሓፊው የራስ ዘሥላሴ አባቱ ከወረብ እናቱ ከጐናን ምድር ሲሆኑ የተወለደው በመጤነት በደርኀ ምድር ነው ይላል። አንዳንድ ጸሓፊዎች ቦታዎቹ በወለጋ ውስጥ ይገኛሉ ቢሉም የተረጋገጠ ነገር የለም። 14 . Ethiopia: An Oromo Dilemma. The National Question and Democratic Transition” 6 አንደኛ፣ እንዴት ሁለቱ የሴማውያን ዘሮች ማለትም ትግሬዎችና ዐማሮች፣ ኦሮሞችን አገልለውና ካስፈለገም የሥልጣን ፍርፋሪ ብቻ በመወርወር ያስተዳደሩን ሥልጣን የግላቸው ሀብት እንዳደረጉ፣ ምሁሩ አበክረው ይናገራሉ።

እንዲህም ሲሉ፣ ሊቁ በጽሑፋቸው የሚጠቅሱትን የእንደነጆን ማርካኪስ [John Markakis15] ዐይነቶቹን የግራዘመም ጸሓፊዎችን አሳብ ከማንሸራሸር በስተቀር፣ ከማንም ታሪክ ጸሓፊ የሚጠበቁትን አመዛዛኝ ልቡናና የማያዳላ አእምሮ በመጠቀም የኢትዮጵያን ታሪክ ያገናዘቡት አይመስሉም። በመጀመርያ ደረጃ ከላይ ያየነው በዘመነ መሳፍንት አገሩን ይገዛ የነበረው የወረሼኮቹ ሥርወ መንግሥትም ሆነ፣ ነጋሾቹ መሳፍንት እንደፍላጎታቸው የሚለዋዉጧቸው ነገሥታት በስም ሰለሞናውያን ይሁኑ እንጂ፣ ከመላ ጐደል የኦሮሞ ዝርያ መሆናቸውን አይተናል።

ስለዚህም በኢትዮጵያ እየተፈራረቁ ከፍተኛ ሥልጣን ይዘው የነበሩት ትግሬዎችና ዐማሮች እንጂ ኦሮሞች ለዚህ አልበቁም ማለት በጠራራ ቀን ፀሐይ የለችም ብሎ እንደመሟገት የሚቈጠር መስሎ ይታየኛል። በሁለተኛ ደረጃ የገረመኝ ነገር ቢኖር፣ ምሁሩ በምዕራባውያን ኀይሎች አነሣሽነትና በሥልጣን ሽኩቻ፣ ባንድ በኩል በልጅ ኢያሱና በአባታቸው ንጉሥ ሚካኤል፣ በሌላው ደግሞ በልጅ ተፈሪና (ኋላ አፄ ኀይለሥላሴ) በደጋፊዎቻቸው መካከል፣ እንደኢትዮጵያ አቈጣጠር [ኢ.አ.] በመስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም. የተካሄደውን የሰገሌን ጦርነት በሚያስደንቅ ሁናቴ በመተርጐም፣ በወሎ ኦሮሞችና በሸዋ ዐማሮች እንደሆነ አድርጎ ማቅረባቸው ነው።

በሁለቱም በኩል የሚዋጉትም ሆነ፣ ጦሩን በበላይነት የሚመሩት፣ አብዛኞቹ ኦሮሞች ወይንም የኦሮሞ ደም ያላቸው ሲሆኑ፣ ምሁሩ እንዴት አድርገው እንደዚህ ለመደምደም እንደበቁ አይናገሩም። ምናልባት ኦሮሞ ሲሉ፣ እንደነፃ አውጪ ነን ባዮቹ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የተወሰነ መስፈርት ካላቸው ደግሞ ምሁሩ በጽሑፋቸው ውስጥ ይኸንን ግልጥ አያደርጉም። አባባላቸው ደግሞ ኦሮሞች እርስበርሳቸው አይዋጉም የሚል ከሆነ፣ በጣም ሩቅም ሳይሄዱ የእረኝነትን ሥርዐት ትተው፣ በኦሞ ወንዝ አካባቢ በመንግሥትነት ተቋቁመው የነበሩትን፣ የጅማ አባጅፋርን፣ የጉማንና የጐማን ከዚያም ባሻግር የለቃ-ነቀምትንና የለቃ-እናርያን ንጉሦች፣ እንዲሁም በወሎ ውስጥ የየጁዎች ባላንጦች የነበሩትን የማመዶችን ሥርወ መንግሥት ማየት ይበቃል። በአገዛዛቸው ጨካኝነት፣ በኦሮሞም ሆነ መሬታቸውን ከነጠቁ በኋላ “ባዕዳን” ብለው በፈረጁባቸው ባገሩ ተወላጆች ላይ ያደርሱባቸው የነበረው ግፍና ሰቈቃ፣የጐሣው ልሂቃን ’የአበሻ” ነገሥታት በሕዝባችን ላይ ፈጸሙበት ከሚሉት እጅግ ይከፋል እንጂ በምንም ረገድ አያንስም ብዬ እገምታለሁ።

ሊቅ ሕዝቅኤል በዚህ ድርሰትና በሌሎችም ጽሑፎቻቸው ይልቁንም በጀርመን አገር ታትሞ በወጣው በEncyclopedia Aethiopiaca ኦሮሞ-ነክ ዐምዶች [vol. 4 O-X] ላይ ከፖለቲከኞች እንጂ ካንድ ገለልተኛ የታሪክ ምሁር የማይጠበቁ አያሌ የተዛቡ አስተያየቶች አስቀምጠዋል። እንደዚህ ዐይነቱ የታሪክ አተረጓጐም ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ምሁራን ታሪክን የፖለቲካ ደንገጡር እንዳደረጓት ነው ብል ሐሰት አይመስለኝም። በዚህ ረገድ ሊቅ ሕዝቅኤል ብቸኛ አይደሉም16፤ እንደጊዜው ፖለቲካ የሚቀያየሩ የወረት-በላ ምሁራን የበዙበት ዘመን ስለሆነ፣ ነገሩ የሚገርም መስሎ አይታየኝም በማለት አሳቤን ልቋጭና ወደዛሬው ጥያቄዬ ልመለስ። 15 . ጆን ማርካኪስም ሆኑ ብዙዎች እሳቸውን የመሰሉ የውጭ አገር ጸሓፊዎች እንደሊቅ ሕዝቅኤል በኢትዮጵያ ምድር አልተወለዱም ብቻ ሳይሆን ቋንቋውንም አይናገሩም፤ ላገሩና ለባህሉ ባዳ ናቸው፤ ግንኙነታቸው ደግሞ ከተማሪዎቻቸውና እንደነሱ በአውሮጳውያን ተቋማት ከተማሩት ኢትዮጵያውያን የማያልፍ ስለሆነ ሕዝቡንም በቅርብ አያውቁትም። ስለዚህም ለኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ታሪክና ባህል ያላቸው ግንዛቤ የሚያንፀባርቀው በትርጒም ካነበቡትና በአካባቢያቸው ካሉት የቀሰሙት መሆኑ መካድ ያለበት አይመስለኝም። 16 . በጣም የሚገርመው አብዛኞቹ የኦሮሞ ምሁራን ነን ባዮች እንደፖለቲካ ልሂቃኖቻቸው በታሪክና ተረት መካከል ያለውን ልዩነት የተገነዘቡ አይመስሉም። በኦሮሞ ታሪክ ውስጥ ብዙ ምናቦች አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የቦረንና የበርይቱማ ዝምድና እንደሐቅ አድርጎ መውሰድ ሮማውያን ገናናዋን የሮም ከተማ የቈረቈሩት ሮሙሉስና ረሙስ በጤግሮስ ወንዝ ከተጣሉ በኋላ ተኲላ እያጠባቻቸው አሳደገቻቸው የሚለውን ምናብ ሐቅ አድርጎ እንደመቀበል ነው። በሌላው ደግሞ በኦሮሞ ላይ የተፈጸመውን ግፍና ሰቈቃ ሲወሽክቱ፣ ኦሮሞች በሌሎቹ ላይ የፈጸሙትን አያነሡም። አፄ ምኒልክ የገባር ሥርዐት በሕዝባችን ላይ ጣሉብን እያሉ ንጉሠነገሥቱን በግፍ ሲወቅሱ፣ “ሕዝባቸው” በየወረረበት ሰፋሪውን ያገሩን ተወላጅ 7 ዐማራን በተመለከተ በቂ ያልሁ ስለሚመስለኝ፣ ልቀጥልና ወደዐማርኛ ልሻገር። የዐማርኛ ቋንቋ ምንጩና መነሻው ዐማራ ከተባለው ክልል እንደሆነ አይካድም። ልክ እንደዐማራ እሱም በዘተለምዶ ተቈራኝቶ የሚገኘው ከገዢው መደብ ጋር ቢሆንም፣ ሐቁ ግን ቋንቋው በደምቡ ያደገውና የዳበረው የኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረገው ያልተቈጠበና ሰፊ አስተዋፅኦ ነው ማለት ይቻላል። ስሙ ከተወለደበት ምድር ጋር ተያይዞ ቢቀርም፣ እውነቱ ግን በየአካባቢው የሚገኙትን የተለያዩ ቋንቋዎች ቃላትንም ሆነ አገባብ በመከለስ፣ በማዳበልና በማቀያየጥ አዋህዷቸውና አመሳስሏቸው ይገኛል። የቋንቋ ጥናት ምሁራን ሴማዊ ብለው ፈርጀውታል። በኔ አመለካከት ይኸ ዐይነቱ አከፋፈል በርካታ ታሪካዊ ጥላሸት የለበሰ በመሆኑ እንደአስተያየት እንጂ እንደዐምደ ሃይማኖት ሁኖ መወሰድ የለበትም።

ያም ሁኖ ግን፣ ሐቁ ዐማርኛ በኩሳውያንና በሌሎችም ባካባቢው ካሉት ቋንቋዎች ቃላትና አገባብ በሰፊው ከመደባለቁ የተነሣ ሴማዊ ብሎ መጥራቱ ፋይዳ ያለው አይመስለኝም። የራሱን ስያሜ ሰጥቶ፣“ኢትዮጵያዊ” ወይንም “አፍሪቃዊ” ማለቱ የሚቀል ይመስለኛል። በፊደልም ሆነ በአነባብከማንኛውም ያለም ቋንቋ የተሻለ ነው ብዬ አምናለሁ። ብዙዎች ቋንቋዎች ንባባቸው በጽሑፍ ተቀርጾ ካለው ፊደል ጋር በፍጹም አይጣጣምም። ለምሳሌ በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሰበብ ባለም እየተሰራጨ በመጣው የእንግሊዝኛ፣ አንድ ቊጥር ወይንም “One” ሲነበብ “ዋን” ብሎ እንጂ እንደጽሑፉ “ዖንእ” አይደለም። እንዲሁም ከአውሮጳዉያን ቋንቋዎች መካከል ጽሑፉና አነባቡ አገባቡን ተከትሎ ይሄዳል ከሚባሉት ቋንቋዎች መካከል ኢጣሊያንኛ አንዱ መሆኑ ይታወቃል። አባባሉ እውነትነት ቢኖረውም፣ ሐቁ ግን እሱም ቢሆን መጠነኛ ሕገወጥነት ያጠቀዋል። ለምሳሌ ያህል ኢጣሊያንኛ የዐማርኛ “ሸ” የሚል ፊደል ስለሌለው፣ የሚጻፈው ቢያንስ ሦስት ፊደላትን በማቈራኘት ነው። “ሻ-ካሎ17” ለማለት “scia-callo” መጻፍ ይኖርበታል። በዚህ መልክ ስናየው ያማርኛ ፊደል የተራቀቀና ዘመናዊነትን ያሟላ ነው ማለት ይቻላል።

ፊደሎቹ በዛ በማለታቸው፣ ለጥናት መጠነኛ ጊዜ ቢፈጁም፣ አንዴ ጠንቅቋቸው ላወቀ ግን በቅልጥፈት፣ በቀላልነትና በይዘት ደረጃ ወደር የሚገኝለት ቋንቋ አይደለም ሊባል ይችላል። በኮምፑቴር አገላለጽ “የሚነበበው እንደተጻፈው ነው18”የሚለው አባባል የሚገባው ከማንኛዉም ቋንቋ ይልቅ ለዐማርኛ ነው ቢባል እውነትነት አለው:: ዐማርኛ ባገሪቷ ውስጥ ያሉትን የልዩ ልዩ ብሔረ-ሰቦችን ድምፅ ሊያስተናግድ ሲል፣ ጥንት ከአባቱ ግእዝ በወረሳቸው ፊደላት ላይ እንዳስፈላጊነቱ አዳዲስ ፊደል ሊፈጥርና ሊጨምር በቅቷል። አብዛኛውም የቋንቋው ተናጋሪ የሚገኘው ከጥንት ትውልዱ ክልል ውጭ ነው። የተለያዩ ማስረጃዎች እንደሚገልጹ ከሆነ፣ በሁሉም ዘንድ ባይሆን እንኳን በተወሰኑት በዛሬዎቹ ሱማሌዎችም አካባቢ ተስፋፍቶ እንደነበር አል-ፋቂህ በመባል የሚታወቀው የግራኝ ታሪክ ጸሓፊ እስላሙ ዐረብ በ“የአበሻ ወረራ” በሚል መጽሐፉ ከመዘገበው ፍንጭ እናገኛለን። አፄ ልብነድንግልን በድንገት በሰፈሩበት ዐምባ ላይ ለመያዝ ዐቅዶ፣ ግራኝ ለወታደሮቹ በዐማርኛ ብቻ እንዲናገሩ ጥብቅ ትእዛዝ ሰጠ። 

ወታደሩም እንደታዘዘው አድርጎ፣ ሳይጠረጠር የደኅንነቱን ጠባቂዎች ዐልፎ ንጉሥ ነገሥቱን ለመያዝ ምንም አልቀረውም ነበር። አፄውን ሊያስመልጣቸው ያበቃው ምናልባት ግራኝ ራሱ ሳይታወቀው በራሱ [አደርኛ?] ቋንቋ መናገሩ ይመስላል። ዐማርኛ ለተለያየ ብሔረሰብና አካባቢ የኢትዮጵያዊነቱ መግለጫ መሆኑ አይካድም። ከላይ የጠቀስናቸው እንደነጐጃም ነጋሽ ክፍሎ፣ ጸሓፈላም ቡኮና ራስ ዘሥላሴ የዐማራ ተወላጆች እንዳልሆኑ ይታወቃል። አጭር በመሆኔ “ጢኖ” የሚል የኦሮሞኛ ስም ተስጥቶኛል ባዩ ጸሓፌ ትእዛዝ አዛዥ ተክለሥላሴም በጽሑፋቸው ስለቋንቋው ሲገልጡ፣ “ዐማርኛ ቋንቋችን” እያሉ ኩራት በተሞላበት ስሜት ሲናገሩ ይታያሉ። በላስታና በሸዋ፣ በአረመኔ መልክ እንደጨፈጨፈ፣ ለባርነት እንደዳረገ፣ የባላይነቱን በተቀበለው ደግሞ የሃበታ፣ ጠለታ፣ ሞጋሳ/ⶁአሳ፣ ገበሮ እያለ የተለያዩ የጭቆና ሥርዐቶች እንደጫነባቸው ሊናገሩ አይፈልጉም።

 17 . ‘Sciacallo = ቀበሮ” 18 . የእንግሊዝኛው፣ “What you read is what you see.” 8 በበጌምድርና በወሎ፣ እንዲህም በጐጃም ግዛቶች አማርኛ የኩሳውያንን ቋንቋዎች ተክቶ ይገኛል። በአርጐባና ጋፋት በመሳሰሉት አገሮች ደግሞ የሴማውያንን ቋንቋዎች ቦታ ወስዷል። አማርኛ ያፋቸው መክፈቻ ቋንቋቸው ቢሆንም፣ እነዚህ እላይ የተጠቀሱ አገሮች እንደአ.አ. በ፲፱፻፺ዎቹ ዓ.ም. ላይ፣ ዐማሮች ናችሁ የሚል ስያሜ በሥልጣን ላይ ባለው መንግሥት በግድ በላያቸው ላይ እስከተለጠፈባቸው ጊዜ ድረስ፣ “ዐማራ” በመባል አይታወቁም። ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩት በሚኖሩበት አገርና ቦታ ስም ጐንደሬ፣ ጐጃሜ፣ መንዜ በመባል እንጂ በፈጠራ በተሰጣቸው ዐማራ በሚል ብሔረሰብነታቸው አልነበረም። ታሪክም ራሱ የሚያመለክተው ይኸንኑ ሐቅ ነው። ከ፲፬ኛ እስከ፲፰ኛ አዝማን ድረስ በተከትታይ ድረስ የተጻፉት የነገሥታቱ የታሪክ ሰነዶች ዐማራ የሚለውን ቃል ከቦታ እንጂ ከብሔረሰብ ጋር አያቈራኙም።

 እንዲሁም እስከ፲፱ኛ ዘመን ድረስ በተጻፉት የክርስቲያኖቹም ሆኑ የእስላሞቹ ዜና መዋዕል ውስጥ “ዐማራ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው፣ በአሁን ጊዜ በወሎ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የቦታ ስም እንጂ ብሔረሰብን አይደለም19። ጽሑፌ የሚያስረዳው አንድ መሠረታዊ ነገር ቢኖር፣ ኢትዮጵያውያን ከገዢው መደብ ጀምሮ እስከ ተራው ሕዝብ በጋብቻና በአምቻ የተሳሰሩ መሆናቸውን ነው። ያገሩ አስተዳደሩም ሆነ ቋንቋው በተለምዶ ዐማራና ዐማርኛ ቢባልም ሁሉም ኅብረተሰብ በባለቤትነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አድርጎባቸው ያስመዘገባቸውና የገነባቸው መሆኑን የታሪክ ሰነዶች ይመሰክራሉ። ዐማራ የሚያመለክተው የዚህ አስደናቂ ግንብ አሳቡንና መሠረቱን የጣለው ሕዝብ የሚኖርበትን በጣም የተወሰነ ክልል እንጂ አሁን በሥልጣን ያለው መንግሥት ለጥቅሙ ሲል አብዛኛውን የኢትዮጵያን ሕዝብ በገፍ በማግለል ጭብጥ የማይሞሉና ማንንም የማይወክሉ መሰሎቹን ብቻ አሰባስቦ የፈጠረውን ኅብረተሰብ አይደለም። 

19 . እንዲሁም ከዚሁ ጋር በማያያዝ የምጨምር ነገር ቢኖር፣ ባሁኑ አጠራር ኦሮሞ፣ ድሮ ደግሞ ጋላ በመባል የሚታወቀው ሕዝብ ሁናቴም ልክ ይኸንኑ የዐማራን ይመስላል። ጥንት ቦረን፣ ሜጫ፣ ቱለማ፣ ኢቱና ጉጂ በመሳሰሉት ስሞች ራሳቸውን ይጠሩ የነበሩትን ብሔረ-ሰቦች ፣ ኦሮሞ በሚባል በጋራ መጠርያ ስም ሥር እንዲካተቱ አስገድዷቸዋል19። ጉዳዩ ራሱን የቻለ ሰፋ ያለ ጽሑፍ ስለሚፈልግ ቦታው ስላልሆነ፣ አሁን ልለፈው። ሁኖም አንድ መሰመር የሚገባ የማይካድ ሐቅ አለ።

Wednesday, July 27, 2016

It is immoral to ignore the horrifying atrocities committed by TPLF on the Amara people


It is something to hear about atrocities in general but it is altogether shocking when someone tells you about the atrocities in gruesome detail that raises the hair on your back. 

Journalist Muluken Tesfaw has done a very detailed investigation on the atrocities committed on Amara people funded and directed by TPLF.  He went in all part of the country and interviewed eye witnesses who either saw the crime committed or have first-hand information about the atrocities.

It is difficult and downright immoral to hear these horrific killings and NOT do anything about it. These well investigated and documented crimes should be filed to open legal proceedings. This obligation to organize and to bring the perpetrators of these crimes in NOT only the duty of activists but it is also the moral responsibility of those who practice law for a living here in the Diaspora. 

Some of the perpetrators of this horrifying crimes are now living in the US and Europe including Tamrat Layne who was a disgraced former prime minister of TPLF. This horror was committed under his watch while the killings were carried out through out the country. 

These crimes should be reported to ICC and other human rights organizations around the world to bring TPLF and its collaborators to justice. We should all help accomplish this mission of bringing this genocidal crime to light for the whole world.

የሕዝብን ጥያቄ በሃይል ማንበርከክ ክቶዉንም ኣይቻልም


(ከጠለምት ተወላጆች ዓለም ኣቀፍ ትብብር የተሰጠ መግለጫ)

ሰሞኑን ፀረ ሕዝቡ የወያኔ ገዢ ቡድን በወልቃይት፥ ጠገዴና በጠለምት የማንነት ጥያቄ ኣስተባባሪ ኮሚቴ የኣመራር ኣባላትን ጨለማን ተገን በማድረግ በድብቅ ኣፍኖ ወደትግራይ ለመውሰድ ጎንደር ከተማ ኣድፍጦ የቆየው ኣፋኝ ነብሰ ገዳይ ቡድን እነዚህን ብርቅየ የሕዝብ ልጆች የወሰደዉ ኢስብኣዊና አረመኒያዊ ተግባር ኣጥብቀን እንቃወማለን።
መሳሪያ ሳይዝ ህጋዊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ በደሉንና ብሶቱን ላቀረበ ሕዝብ የሚሰጥ ምላሽ ኣፈና፥ እስራትና ግድያ ሊሆን አይገባዉም ነበር። ይሁን እንጂ ገና ከጅምሩ ሕዝብን ለስቃይ ሃገርን ለጥፋት ለማብቃት ሽንጡን ገትሮ ከሚታገለው ኣረመኒያዊ የወያኔ ቡድን ይህ እንደሚጠበቅ ላፍታ እንኩዋን ኣንዘነጋዉም።
የሃያ ዓምስት ዓመታት የመከራና የሰቆቃ ስቃይ ተወልዶ ባደገበት ፥ ልጅ ወልዶ ባስተማረበትና ለሃገሩ ኣርሶ በጠቀመበት ምድሩ፥ እንደሰዉ መኖር ተነፍጎ በግፍ ላይ ግፍ በየቀኑ ኣረመኔ በሆኑ የስርዓቱ ኣሽከሮች እየተፈፀመበት፥ ግፍና በደሉ ሲበዛበት ሕግና ስርዓትን ተከትሎ ኣቤት በማለቱ፥ የሚደርስበት፥ ስቃይ መሸከም በቅቶት በቆራጥንትና በኣንድ ልብ ይህን የሃገርና የሕዝብ ጠላት የሆነን ሥርዓት ለመታገል ዛሬ ኣደባባይ መውጣት የደረሰበት ወቅትና ለነፃነቱ ወደሗላ ላይመለስ ለትግል ዝግጁ ሆኖ ይገኛል።
ይህ ብሶትና በደል ገፋፍቶት የተነሳ ሕዝባዊ ቁጣ በበሰለና በሰከነ መንገድ የሕዝብን ጥያቄ መልስ ካልተሰጠ በቀር በሃይልና በመሣሪያ ጋጋታ ጥያቄዉን ለማፈን መሞከር ሊያመጣ የሚችለዉን መዘዝ ከወዲሁ ልናስጠነቅቅ እንወዳለን። በሃይል ታፍኖ በመሣሪያ ብዛት ተቀብሮ ፀጥ ለጥ ያለ የሕዝብ ቁጣ በየትኛዉም ዓለም ኣልታየም። ጊዜ ይወስድ እንደሆን እንጂ ሁሉም የሕዝብን ቁጣ በየደረጃቸው ይቀምሱታልና። ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ!
ይህ የሃገርና የሕዝብ ጠላት የሆነን ኣገዛዝ ለኣንዴና ለመጨረሻ ለማስወገድ ኣንዱ ኣከባቢ ሲነሳ ሌላው ዝም እያለ ሳይሆን ሁላችንም በኣንድነት በሁሉም የሃገራችን ኣቅጣጫ በጋራ መንቀሳቀስ ካልቻልን የግፉና የመከራዉን ፅዋ በየተራ እየተቀበልን እንኖራለን። በኣንድ ኣከባቢ የሚነሳን ሕዝባዊ እንቅስቃሴ በሌላው ኣክከባቢ ያለዉ ሕዝብ ሊደግፈዉና እሱም ኣብሮ ሊነሳ ይገባዋል። በመሆኑም ዛሬ ይህን ኣስከፊ ሥርዓት ፊት ለፊት እየታጋፈጠ ካለዉ የወልቃይት፥ የጠገዴ፥ የጠለምትና የጎንደር ሕዝብ በኣጠቃላይ ከኣማራው፥ ከኦሮሞውና ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር በመሰለፍ ሃገራችን ከከፍተኛ ኣደጋ ለማዳን ነገን ሳንል ዛሬ በጋራ እንድንነሳ በኣክብሮት እንጠይቃለን።
ቆራጡና ጀግናው የጎንደር ክ/ሃገር ሕዝብ ሆይ! ለበርካታ ዓመታት የተፈፀመብህን ግፍና ስቃይ ሞልቶ ተሸክሞ መኖር በቃኝ ብለህ ለማንነትህና ለመብትህ የምታደርገው የጀግና ሕዝባዊ ትግል እኛ በዉጭ ሃገር የምንገኝ ልጆችህ የምንደግፈዉና ከጎንህ የምንቆም መሆናችንን በኩራት ለመግለፅ እንወዳለን። ዛሬ የምትከፍለው የደም ዋጋ ለወገንህና ለምትወዳት እናት ሃገርህ ኢትዮጵያ በመሆኑ እንደ ቀደምቱ ዛሬም ገድልህ ህያው ሆኖ ይኖራል።
ላለፉት ሃያ ኣምስት ዓመታት የፈፀማችሁት ግፍና ሰቆቃ ኣልበቃ ብሎኣችሁ ይሄውና ዛሬም በኦሮሞ፥ በጋምቤላ፥ በኮንሶና ሰሞኑን ለማንነቱና ለመብቱ የሚታገለዉን የጎንደር ሕዝብ በሃይል ለመደፍጠጥ የምትጥሩ የስርዓቱ መሪዎችና ጀሌዎች ሰሞኑ በጎንደር በተነሳው ሕዝባዊ ዓመፅ እንደተመለከታችሁት ዛሬዉኑ የምትፈፅሙት ግፍና በደል ካላቆማችሁ የሚደርስባችሁን የሕዝብ ቅጣት የሚሸከም ትክሻ እንደማይኖራችሁ ልናስገነዝባችሁ እንወዳለን።
በመጨረሻም በተናጥል የምናደርገዉን ሕዝባዊ ኣመፅ በጋራ ኣድርገን ሃገራችንን ከመበታተን ሕዝባችንን ከመከራና ከግፍ ለማዳን ከወልቃይት፥ ጠገዴና ጠለምት፥ በጠቅላላው ከጎንደር፥ ከኣማራ፥ ከኦሮሞ፥ ከጋምቤላ፥ ከኮንሶና ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር በጋራ ሆነን ኢትዮጵያን እንድናድን ሃገራዊ ጥሪ እናቀርባለን። ሰሞኑን በቆራጥነትና በጀግንነት ይህን ሃገር በቀል ከሃዲ ሥርዓትን ለማስወገድ እየታገለ ካለዉ የጎንደር ክ/ሃገር ሕዝብ ጎን ሁላችንም እንድንቆም እናሳስባለን። ሕዝባዊ ቁጣን ብሃይል ማፈን ኣይቻልም! ኢትዮጵያ በልጆቻ ተጠብቃ ለዘላለም ትኖራለች !! የጀግናው የጎንደር ክ/ሃገር ሕዝብ ትግል እናደንቃለን ከጎኑም እንቆማለን!!!

Tuesday, July 26, 2016

«የማይመቱት ልጅ፣ ሲቆጡት ያለቅሳል!»

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             እሑድ ሐምሌ ፲፯ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.            ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፲፰
 


·          የጐንደሩ ጉዳይ የዐማራውን ኅልውና የማስከበሩ ትግል የመጀመሪያው ምዕራፍ እንጂ የመጨረሻው እንዳልሆነ ይታወቅ!

ሰሞኑን የሞሶሎኒ ዓላማ አራማጅ የሆነው ዘረኛው የትግሬ ወያኔ አረመኔአዊ አገዛዝ፤ ባለፉት 40 ዓመታት በወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ በተናጠል፤ በዐማራው ነገድ በጥቅል፤ የሚፈጽመው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋርሯል። በቅርቡም ባካሄደው ዘግናኝና ሰቅጣጭ ግድያና ሥቃይ፣ እስራት፣ እንግልትና የማንነት ነጠቃ፣ የጥቃቱ ሰላባና ዒላማ የሆነውን የወልቃይት፣ የጠገዴና የጠለምት ሕዝብ ትዕግሥት አሟጦ ወደለየለት ሕዝባዊ አመጽ መሸጋገሩን የብዙኃን መገናኛ መሣሪያዎች መዘገባቸው ይታወሳል። የሕዝባዊ አመጹ አነሳስም ሕዝቡ አስቦና አቅዶ ያደረገው ሳይሆን፣ በአባይ ወልዱ የሚመራው የትግራይ ገዥ እና «የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር ሊቀመንበር»፣ «የዐማራ ክልል አስተዳደር» ተብየው ሳያውቅና ሳይፈቅድ፣ አፋኝ ነፍሰ ገዳዮቹን በማን አለብኝነት ወደ ጎንደር ከተማ ልኮ፣ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ሕጋዊና ሰላማዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባሎችን  በደረቁ ሌሊት፣ ሰርቆና አፍኖ ለመውሰድ ባደረገው የአሸባሪነትና የውንብድና ሥራ፣ ጀግናው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ «የአገዛዝ ሥርዓቱ ያወጣው ሕግ ከሚፈቅደውና ከሚያዘው ውጭ፣ በሌሊት ማንም እንደሌባ አፍኖ ሊወስደኝ አይችልም» በማለት በወሰደው ሕጋዊ የተከላካይነት ርምጃ፣ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ፣ በቋፍ ላይ ለነበረው የሕዝብ ብሶት፣ አሸባሪውና ወንበዴው ወያኔ ቤንዚን በማርከፍከፉ የተነሳ የተፈጠረ ሕዝባዊ ማዕበል ነው።
የጎንደር ሕዝብ፣ አስተዋይ፣ ጨዋና የአብሮነት ስሜቱ የጠነከረ በመሆኑ እንጂ፣ ወያኔ ሆን ብሎ በቀሰቀሰው ሕዝባዊ ቁጣ ከወያኔ ጋር ንክኪ ብቻ ሳይሆን፣ የዘር ትስስር ባላቸው ላይ ይደርስ የነበረው ጥፋት መጠነ ሠፊ ሊሆን ይችል እንደነበር ብዙዎች ያምናሉ። በመሆኑም ሕዝቡ ቁጣውን የገለጸው፣ በሁሉም የትግሬ ተወላጆች ላይ ሳይሆን፣ የሥርዓቱ ተጠቃሚዎች እና ሰላይ አሰላዮችን መርጦና ለይቶ ነው። ቁጣውን የገለጸውና ክንዱን ያነሳው፣ ትምህርት ሰጭ በሆነ መልኩ፣ ላለፉት 40 ዓመታት የወያኔ ሰላዮች፣ ተላላኪዎች፣ ገዳዮችና አስገዳዮች በመሆን ሕዝቡን ሲያሰቃዩ በነበሩና፣ ለወያኔ በሰጡት አገልግሎትና ሁለንተናዊ ድጋፍ፣ የልዩ ልዩ ጥቅሞች ተጠቃሚዎች በሆኑት ወያኔዎች ላይ ነው።
«ለሕዝብ ጥቅም፣ ለሰዎች ዕኩልነት፣ መብትና ነፃነት፣ ከሁሉም በላይ ለኢትዮጵያ አንድነት ቆመናል» ለሚሉና «በሕዝብ የበላይነት እናምናለን» ለሚሉ፣ «ወያኔ ዘረኛና አጥፊ ድርጅት ነው ብለው ከልብ ለሚያምኑ፣» የጎንደር ሕዝብ የወሰደው ራስን የመከላከል ርምጃ ተገቢና ለሌሎችም በአርኣያነቱ የሚጠቀስ እንጂ፣ የሚያስወግዝ አልነበረም። ሆኖም፣ «የማይመቱት ልጅ፣ ሲቆጡት ያለቅሳል፣» ዓይነት የሆኑት በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ የትግሬ ተወላጆች፣ አንዳንዶቹም ወያኔን አምጠው ወልደው፣ የትግሬ ዘር በነቂስ ዐማራውን በዘር ደመኛ ጠላትነት እንዲያይ፣ ፕሮግራም ጽፈው፣ አደራጅተውና መርተው ከዚህ አጥፊ ደረጃ ያደረሱ ቡድኖችና ግለሰቦች፣ የጎንደር ሕዝብ ራሱን የመከላከል ሰብአዊና ፖለቲካዊ ተፈጥሮአዊ መብቱን ተጠቅሞ በወያኔ አፋኝ ቡድኖች ተጎትቶ ላለመታረ,ድ ያደረገውን የመከላከል ርምጃ በማውገዝ፣ የባዶ በርሜል ጩኸት ሲጮኹ ተሰምተዋል። በዚህም የማስመሰል ተቃዋሚነታቸው ዕርቃኑን እንዲቆም አድርገዋል። የወያኔ አጋርነታቸውንና የዐማራው ነገድ ጠላትነታቸውንም ዳግም አሳይተዋል። የሚገርመውና የሚደንቀው እነዚህ ወገኖች ወያኔ ባለፉት 40 ዓመታት፦
o      የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብን ማንነት ነጥቆ «ትግሬ ናችሁ» ከማለት ያለፈ፣ አጽመ እርስቱን በመንጠቅ ከሰባት መቶ ሺ በላይ ትግሬዎችንና የወያኔ ታጋዮችን አስፍሮ ሕዝቡን ለልመና ሲዳርግ፣
o      በአስር ሺዎች የሚቆጠሩትን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብን ንብረታቸውን ወርሶ ሲገድል፣
o      በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩትን የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብን ሲያሰድድ፣
o      1985 ዓ.ም. በአደባባይ ኢየሱስ ቤተክርስቲያ ላይ ለፀሎት በተሰበሰቡት ምዕመናን ላይ በመትረየስ ሩምታ ከ60 በላይ ገድሎ፣ በመቶ የሚቆጠሩትን ሲያቆስል፤
o      በደደቢት ሠራዊት ከተማዋን አስከብቦ የጎንደርን ሕዝብ የደም ካሣ የመብራት ኃይል ማመንጫ ጄኔሬተር ነቅሎ ብዘት ከተማ ሲተክል፣
o      የጎንደርን ሕዝብ የሚንቀሳቀስ ንብረት ነቅሎ ወደ ትግራይና ኤርትራ ሲያጉዝ፣
o      1983 እስከ 1985 ዓ.ም. ባሉት ዓመታት በበደኖ፣ በአሰቦት ገዳም፣ በወተር፣ በመቻሬ፣ በአርባጉጉ፣ ዐማራውና ክርስቲያኑ ከነሕይዎቱ ገደል ሲጣል፣ በገጀራ አንገቱን ሲቀላ፣ ነፍሰጡሮች ሆዳቸው በሳንጃ ሲቀደድ፣ እናቶች ጡታቸው ሲቆረጥ፣
o      በወለጋ፣ በከፋ፣ በኢሉባቡር፣ በመተክል፣ ለዘመናት ይኖሩ የነበሩ ዐማሮች፣ ዐማራ በመሆናቸው ብቻ፣ ቤት ንብረታቸውን ተነጥቀው ሲባረሩ፣ ሲገደሉ፣ ታርደው ሲበሉ፣
o      የዐማራውን ተፈጥሮአዊ የመራባት መብቱን በመግፈፍ በወሊድ ቁጥጥር ስም እንዲመክን ሲደረግ፣
o      በአጠቃላይ ባለፉት 25 ዓመታት የወያኔ አገዛዝ 5 ሚሊዮን ዐማራ ከምድረ ገጽ ሲያጠፋ፣
o      በጋምቤላ ሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት ሲፈጽም፣
o      በቴፒና በአዋሳ ንፁሐን ዜጎችን ሲገድልና ሲያሰቃይ፣
o      በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያላቋረጠ ግድያ፣ እስራትና መሬት ነጠቃ ሲያደርግ፣
o      በሱርማ ተወላጆች ላይ እንደ ጥንቱ የባርነት ዘመን እንደ በቅሎ ቀይዶ፣ እንደ በሬ ጠምዶ፣ የምድር ሥቃይ ሲያሳያቸው፣
o      1997 ዓ.ም. የብሔራዊና ክልላዊ ምርጫ ወያኔ በሕዝብ ድምፅ ተሸናፊ በመሆኑ፣ ሥልጣኑን ላለመልቀቅ በወሰደው የኃይል እርምጃ ባስከተለው ሕዝባዊ አመጽ፣ በአዲስ አበባ ከተማ በአጋዚ ሠራዊት ንፁሐን ዜጎች ጭንቅላትና ልባቸውን ተመትተው ለሞቱና ለቆሰሉ ኢትዮጵያውያን፣ «ለምን?» ብለው ያልጠየቁ ወገኖች ዛሬ፣ «ለምን ወያኔ ይደፈራል? እንዴት ተብሎ ወያኔ ይቆነጠጣል?» በሚል ስሜት፣ ወያኔና አጋሮቹ በጎንደር ሕዝብ ላይ የተለመደ የጥፋት ክንዱን እንዲያነሳ ጥሪ አቅርበዋል።
እስካሁን ይፋ ከተደረጉት መግለጫዎቻቸው፣ ወያኔ የባሕሪው የሆነውን የጥፋት ክንዱን፣ በተናጠል በጎንደር ሕዝብ ላይ፣ በጥቅል ደግሞ በዐማራው ነገድ ላይ እንዲያነሳና የዘር ፍጅት እንዲፈጽም ጥሪ ያቀረቡትና ለጥፋቱም ተባባሪ መሆናቸውን የገለጹት የትግራይ ተወላጆች የሚከተሉት ናቸው።
አንደኛ፦ «የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር - ዴሞክራሲያዊ ምትሕብብር ትግራይ» የተሰኘው የፖለቲካ ድርጅት፦
ይህ ድርጅት የወያኔ መሥራች አባሎች ብቻ ሳይሆኑ፣ የድርጅቱን ፕሮግራም ባዘጋጁ፣ በመሩና ባደራጁት አረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርዓጽዮን የተመሠረተና የሚመራ መሆኑ ይታወቃል። እነዚህ ሰዎች በየግል የሥልጣን ሽኩቻ ከድርጅቱ ከሕወሓት እስከተባረሩበት 1977-78 ዓ.ም. ድረስ፣ ወያኔ በኢትዮጵያ አንድነት፣ ብሔራዊ ጥቅም፣ በሕዝቡ ሉዐላዊነትና ነፃነት ላይ ለፈጸው አገራዊ ክሕደት፣ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂዎች ከሚሆኑት መካከል ናቸው። ከሁሉም በላይ «ዐማራው የትግሬ ሕዝብ ደመኛ ጠላት ነው! በመሆኑም የትግሬ ዘር ተደራጅቶ ዐማራውን ማጥፋት አለበት፤» የሚለውን የወያኔ ፕሮግራም በመጀመሪያ ደረጃ እንዲይዝ አንድ አድርገው የጻፉና በዚህም በወልቃይት፣ ጠገዴ እና ጠለምት ሕዝብ በተናጠል፣ በጥቅል በጎንደሬውና በዐማራው ነገድ ላይ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል እንዲፈጸምበት መመሪያ ያዘጋጁ፣ መመሪያ የሰጡ፣ ሕዝቡን ለጥፋት የቀሰቀሱ፣ ያደራጁና የመሩ መሆናቸው በግልጽ ይታወቃል። አረጋዊና ግደይ ከድርጅቱ እስከተባረሩበት ጊዜ ድረስ፣ ድርጅቱን በሊቀመንበርነትና በምክትል ሊቀመንበርነት የመሩ፣ የድርጅቱን ፕሮግራም አርቅቀው ያጸደቁ፣ ወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምት፣ እንዲሁም ከወሎ የነጠቁት ራያና ቆቦ፣ ሰቆጣ ወደ ትግራይ ግዛት እንዲካለል ካርታ ያዘጋጁ መሆናቸው ይታወቃል። ይህን «አናውቅም፣ አልሰማንም» የሚል ካለ፣ የአቶ ገብረመድኅን አርኣያን ቃለምልልሶችና ጽሑፎች እንዲያዳምጥና እንዲያነብ ይጋበዛል። ወዳጅና ጠላቱን ለይቶ የማያውቀው «ተቃዋሚ ነኝ» የሚለው ወገን፣ የእነዚህን መሠሪ ሰዎች ዓላማና ሤራ በቅጡ ሳያውቅ፣ ከነርሱ ጋር የፖለቲካ ሽርክና መግጠሙ ከማሳዘን አልፎ ያሳፍራል። የተቃዋሚው ጎራ ትግል ለድል አልበቃ ያለውም እነዚህን የመሰሉ ሰዎች ከማግለል አልፎ፣ ትግሉን እንዲመሩ እድል በመስጠቱ ነው።
የአረጋዊ በርሄ ቦርሳ ተሸካሚ የሆነውና የዚሁ ድርጅት አባል የሆነው፣ ወላጆቹ ባወጡለት ስም ዮሴፍ ዘለለው፣ ወያኔ ባወጣለት የጥፋት ስሙ ደግሞ መኮንን ዘለለው የተባለው ባንዳ፣ ከኤስ.ቢ.ኤስ. ሬዲዮ ጋር ባደረገው ቃለምልልስ፣ « አማርኛ ወደ ወልቃይት ሄደ እንጂ፣ ወልቃት ትግሬ ነው» ብሎ መናገሩን የምናስታውሰው በከፍተኛ ቁጭት ነው። ተቃዋሚውን ለመሰለልና ለመከፋፈል የቆሙትን እነዚህን የመሰሉ ሰዎች በተቃዋሚው ጎራ ማሰለፍ፣ አንድም ወያኔንና ባሕሪውን አለመረዳት፣ ሁለትም እያንዳንዱ የትግሬ ትውልድ ለወያኔ ያለው አመለካከት ስስ መሆኑን አለመገንዘብ ነው። ይህ ደግሞ ራስን በራስ ከመግደል ተለይቶ የሚታይ አይደለም። (ይህ አባባል ግን ሁለቱን የዕውነተኞቹ የጥንቶቹ የትግራይ ሕዝብ ዓላማና ፍላጎት አራማጅ የሆኑትን በግልጽ ለወያኔ የጉረሮ አጥንት የሆኑትን አቶ ጌታቸው ረዳንና አቶ ገብረመድኅን አርኣያን አይመለከትም።)
ተቃዋሚው ዕውነት በቁርጠኝነት ወያኔን ለመታገል ከቆረጠ፣ ከእንደነዚህ ዓይነት ሰዎች ራሱን ማጽዳት አለበት እንላለን። ይህን እንድንል ያስገደደን፣ «በአረጋዊ በርሄና ግደይ ዘርአጽዮን የሚመራው «የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር» በ18/7/2016 «ጎንደር፣ የህዝቡ ትግል ሲግል-የኢህአዴግ ውድቀት ሲቀላጠፍ» በሚል ርዕስ ባሰራጨው መግለጫ፣ ወያኔን አጥብቀው የሚቃወሙ፣ የወያኔን ተልዕኮና ግብ ምን እንደሆነ በቅጡ የተረዱ ግለሰቦችና ድርጅቶችን፣ ከሁሉም በላይ ወያኔ የትግራይን ሕዝብ በነቂስ አደራጅቶ በኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያዊነትና በዐማራው ነገድ ላይ እያደረሰ ያለውን የዘር ፍጅት አጥብቀው የሚቃወሙ ወገኖችን፣ «የትግራይን ሕዝብ ከወያኔ ባለመለየት ሊያጠቁት ነው» በማለት፥ ለወያኔ መረጃ አቅራቢ፣ ሰላይ፣ ገዳይና አስገዳይ በሆኑት የትግራይ ተወላጆች ላይ የሚሰነዘረውን በሐቅ ላይ የተመሠረተ ክስና ወቀሳ በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እንደሆነ በማስመሰል ወያኔአዊ ተልዕኮውን ሊጭንብን ሞክሯል። እንዲህም ሲል ሊያስፈራራን ይሞክራል።
«የትግራይ ህዝብን የአምባገነኑ መደብ አጋር አድርጎ የሚያይ ሽባ አመለካከት ከሽባነቱ አልፎ የጋራ ትግሉን አደናቃፊ በመሆኑ አጥብቆ ይቃወመዋል። የኢሕአዴግ ገዥ ቱጃሮችን በማንበርከክ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን ትንቅንቅ ለመበረዝና የሚካሄደው ትግልን ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል አንዳንድ ቡድኖች ለፕሮፓጋንዳ፣ ለፖለቲካና ለንብረት ፍጆታ ሲሉ ትግሉን ጥላሸት ሊቀቡት የሚዳዱ አደናቃፊዎችም በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል።»ሲል ያስጠነቅቃል።
እነዚህን ሁለት አረፍተ ነገሮች አፍታትተን የያዙትን ፍሬ ነገር ከገለባው አበጥረን እንመርምር። «የትግራይ ህዝብን የአምባገነኑ መደብ አጋር አድርጎ የሚያይ ሽባ አመለካከት ከሽባነቱ አልፎ የጋራ ትግሉን አደናቃፊ በመሆኑ አጥብቆ ይቃወመዋል።» በመጀመሪያ ደረጃ ወያኔ የተደራጀው በዘር እንጂ፣ በመደብ ወይም በሀብት ክፍፍል ልዩነት ላይ አይደለም። በመሆኑም ደጋፊዎቹ፣ የሰው ኃይል ምንጩ፣ የገንዘብ ምንጩ፣ የመረጃ አቅራቢው፣ የሀሳብ ደጋፊው ትግሬ ነው። አባሎቹም በነቂስ ትግሬዎች ናቸው። ይህን አረጋዊ እና ግደይ ሊክዱን አይችሉም። ከካዱም «ክህደት የዘር ነው እንዴ?» ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል። ወያኔ አዲስ አበባን ሲቆጣጠር ይፋ እንደሆነው፣ በትግራይ ክፍለሀገር ውስጥና ውጭ ከሚኖረው ትግሬ የወያኔ አባል ያልሆኑት ከሃያና ኃምሣ አይበልጡም። እነዚህም መውጫ ያገኙት ሲሰደዱ፣ መውጣት ያልቻሉት ኃብት ንብረታቸውን ተወርሰው ለዘመናት በትግራይ እስር ቤቶች እንዲማቅቁ ተደርገዋል። አቶ አብርሃ በላቸው፣ አቶ ኃይሌ ኪሮስ አሰግድ፣ ወይዘሮ ዙፋን፣ ወይዘሮ ኤልሳ ተስፋየ ወዘተርፈ ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው።
ድርጅቱ ከምሥረታው ጀምሮ ዘረኛና ጎጠኛ ከመሆኑ የተነሳ፣ ለመጀመሪያዎች አምስትና ስድስት ዓመታት ምልመላ የሚያካሂደው ከአድዋ፣ አክሱምና ሽሬ ተወላጆች ብቻ ነበር። በዚህም የተነሳ ድርጅቱ ዐሽአ (ዐድዋ፣ ሽሬ አክሱም) በሚል ተለዋዋጭ ስም ይታወቅ ነበር። ይኸም ሆኖ የምልመላ ቅድሚያ የሚሰጣቸው በእናት በአባታቸው ትግሬ ለሆኑት ነበር። የነዚህን አውጃራ ተወላጆች መልምሎና በዓላማው ሥር ካሰለፈ በኋላ ወደሌሎቹ አውራጃዎች ሲጓዝ የምልመላ ቅድሚያ የተሰጠው አሁንም በእናትም በአባትም ትግሬ ለሆኑ፣ ቀጥሎ በአባታቸው ወገን ትግሬ ለሆኑ፣ እነዚህን የጥፋት ዓላማቸው ተሸካሚዎች አድርገው ሲጨርሱ፣ በእናት ወገን ትግሬ የሆኑትን መመልመላቸው ይታወቃል። ከዚህ አንፃር ወያኔ ከዘረኝነት አልፎ ለሴቶች ያለውን ዝቅተኛ አመለካከትና ልዩነት በግልጽ ያሳያል። በዚህ ሂደትም «ድፍን የትግሬ ተወላጅ፣ ወዶም ይሁን ተገዶ የወያኔ ዓላማ አራማጅ አልነበረም፣ አልሆነም» የሚሉ ካሉ ከዕውነት በተቃራኒ የቆሙ የጥፋት መልዕክተኞች ብቻ ናቸው።
የትግሬ ዘር ለወያኔ የሰው ኃይል፣ የገንዘብ፣ የመረጃና መሰል ጉዳዮች ምንጭ ባይሆን ኖሮ፣ ወያኔ ከዚህ ደረጃ መድረስ አይችልም ነበር። ይህን በተመለከተ ወያኔ ስልጣንበያዘ ማግስት መለስ ዜናዊ ለትግራይ ሕዝብ በመቀሌ አደባባይ «ከእናንተ በመወለዳችን ኮርተናል፣ ወርቆች ነን» ሲል የገለጸው ከሕዝቡ ያገኘው ድጋፍ ሠፊ እንደሆነያረጋግጣል። ከዚህም በተጨማሪ፣ የአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር በመግለጫው ይፋ እንዳደረገው፣ በ17 ዓመቱ የወያኔ ትግል 60,000(ስድሣ ሺህ) የትግራይ ወጣቶች በጦርነቱ መሞታቸውን፣ 170,000(አንድ መቶ ሰባ ሺህ) መቁሰላቸውን ይፋ አድርገዋል። እንግዲህ በሕይዎት ያሉትን ስንጨምር ነገዱ አለው ከሚባለው 5 ሚሊዮኑ ውስጥ አንድ ሚሊዮኑ በቀጥታ በትጥቅ ትግል መሳተፉንና ቀሪው በልዩ ልዩ መስኮች ድርጅቱን ይረዳ እንደነበር የማይሞተው ታሪካችን እያሳየን ነው። እና «የትግራይ ሕዝብ ለወያኔ አልረዳም» የሚለው አባባል ተራ ማጭበርበርና በሕዝብ ስም ድብቅ ዓላማን ለማራመድ ከመጣር ተለይቶ አይታይም። መባል ያለበት፣ «የትግራይ ሕዝብ ወዶም ሆነ ተገዶ፣ አምኖም ሆነ በጊዜው ስሕተት ለወያኔ መሣሪያ መሆኑ ዕውነት ነው። ይህ ደረቅ ሐቅ ነው። ግን ሕዝብን እንደሕዝብ በጠላትነት መፈረጁ ለፖለቲካዊ ትክክለኝነትና ለወደፊቱም የአብሮነት ጉዞ መልካም ስለማይሆን ሕዝቡን ከዋነኞቹ አጥፊዎቹ ልጆቹና የድርጅቱ አመራሮች እንለይ» የሚለው ነው። ይህን ለመለየት ደግሞ፣ ሕዝቡ ራሱ የልጆቹን ዕኩይና አጥፊ ተግባር ከምክር ጀምሮ እስከ ውግዘት ከዚያም በአካልና በሀሳብ ልክ እንደ ጌታቸው ረዳና ገብረመድኅን አርኣያ በይፋ ተቃውሞውን ማሳየት ይጠበቅበታል። ይህ በሌለበት ሁኔታ ሕዝቡን ከወያኔ ለይቶ ለማየት ከማስቸገሩም በላይ፤ ሕዝቡ በወያኔና ተባባሪዎቹ ላይ ቁጣውን ሲገልጽ «የትግራይን ሕዝብ ለማጥፋት ነው» ብሎ መፈረጅ፣ ከወያኔነት የተለየ አድራጎት አይደለም።
በሌላ በኩል «ወያኔ ኢትዮጵያን አጠፋ፣ ሕዝቡን በዘር ለያይቶ አገሪቱን በተነ፤ በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በጋምቤላውና በሱማሌው ነገዶች ላይ የዘር ፍጅት ፈጸመ» ብለው የሚጮኹትን ግለሰቦችና ቡድኖች የሚያራምዱትን አመለካከት «ሽባ » ከማለት አልፎ፣ «የጋራ ትግሉን ያደናቅፋል» በማለት የአዞ እንባ «ለጋራ ትግሉ ያነባል።» የእነዚህ ወገኖች አቋም በገሐድ የሚታይን የጥፋት እርምጃ መቃወም እንጂ፣ ጎጂ አመለካከት ወይም አጥፊ ርዕዮተ-ዓለም አይደለም። በነባራዊ ዓለም በገሐድ የሚታይን የጥፋት ጉዞ መቃወም «ሽባ» ካስባለ፣ አረጋዊና ግደይ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ በመቶ ኦመት በመገደብ፣ «ኤርትራ በኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት የተያዘችና ናት፤ በመሆኑም መገንጠል አለባት፤ የትግራይ ሕዝብ ራሱን ችሎ ይስተዳደር ነበር፣ ስለሆነም ከኢትዮጵያ መገንጠል አለበት፤» ብለው የጻፉና የተናገሩ ምን ሊባሉ ይሆን? ትውልድ ይታዘብ። በወያኔ ድርጊት ላይ የተቃውሞ ድምፅ ያሰሙትን ወገኖች በሽባ አመለካከት የፈረጁ ሰዎችና ድርጅቶች አቋም ስንመረምር፣ «ዝንጀሮ የራሱን ጠባሳ ሳያይ፣ በጓደኛው ይስቃል» የሚለውን አባባል ያስታውሰናል። እናም በሽባ አመለካከት የዘር ፖለቲካ ተወልደው ያደጉት አረጋዊና ግደይ ሌሎችን «ሽባ» ሲሉ፣ የራሳቸውን ማንነት ሕዝቡ የማያውቅ መስሏቸው ስለሚሆን ልካቸውን እንዲያውቁ ማድረግ ተገቢ ይመስለናል። ይህ አባባላችሁ ሕዝቡ የከረረ አቋም እንዲይዝ የምትገፋፉት እንጂ እንዲለዝብ የማያደርግ ስለሆን እንድታስቡበት ግድ ይላችኋል። ይህ አባባላቸው ሕዝቡ የከረረ አቋም እንዲይዝየሚገፋፋ እንጂ፣ እንዲለዝብ የማያደርግ ስለሆነ፣ በወያኔዎችና በተላላኪዎቻቸው ላይ የሚወሰደው ርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። «የማን ቤት ፈርሶ የማን ይበጅ፤ ያውሬመውለጃ ይሆናል ኢንጂ!» የሚለውን የቆየ የአባቶቻችን ይትባህል ልብ እንድትሉ ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ፋሲል ደመወዝ «አረሱት ሁመራን፣ አረሱት መተማን፣ ያውም የእኛንዕጣ፣ እነርሱ ምን ያርጉ ከእኛ ሰው ሲታጣ» ሲል ያዜመው ዜማ ባዶ ሰሚ ያጣ ሙዚቃ እንዳይመስላችሁ። ከእኛም ሰው መኖሩን የሰሞኑ የጎንደር ሕዝብ ነውጥ፣ ያሳያችሁይመስለናል። ወያኔና ተከታዮቹ ምን ቢደረግ ልትሰሙ ብቻ ሳይሆን፣ ልትፈሩ እንደምትችሉ የሰሞኑ የትግሬዎች ማኅበራትና ድርጅቶች ውካታ እና እሪታ ከበቂ በላይ ማሳያአያስፈልገውም። ስለሆነም የተነጠቅነው መብታችን፣ መሬታችን፣ ማንነታችን እስኪመለስ ድረስ በሚገባችሁ ቋንቋ ለማነጋገር እንደሚቻል ሕዝቡ ቁርጠኝነቱን አሳይቷችኋል፣ ለወደፊትም ይቀጥላል።
ሁለተኛው ሀሳብ «የኢሕአዴግ ገዥ ቱጃሮችን በማንበርከክ የሥልጣን ባለቤት ለመሆን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚያደርገውን ትንቅንቅ ለመበረዝና የሚካሄደው ትግልን ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል አንዳንድ ቡድኖች ለፕሮፓጋንዳ፣ ለፖለቲካና ለንብረት ፍጆታ ሲሉ ትግሉን ጥላሸት ሊቀቡት የሚዳዱ አደናቃፊዎችም በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል።» የሚለው የተጥመለመለ ሀሳብ ነው። በመጀመሪያ ደረጃ ኢሕአዴግ የሚባል ድርጅት የለም። ኢሕአዴግ የሚባል ድርጅት አለመኖሩን ሥብሃት ነጋ በተለያዩ ሬዲዮ ጣቢያዎች ባደረገው ቃለ ምልልስ ነግሮናል። በመሆኑም ኢሕአዴግ የወያኔ የሕዝባዊ ድርጅቶች ስብስብ የሆነ መሣሪያ እንጂ፣ ገዥው ድርጅት ሕወሓት/ወያኔ ነው። ይህን አረጋዊና ግደይ ይጠፋቸዋል ተብሎ አይጠረጠረም። የልጅነት ዕድሜአቸውን ያሳለፉበት የወያኔ ድርጅትና በዚህም ተጠቃሚ የሆነው ብዙኃኑ የትግራይ ሕዝብ እንዲነካባቸው ስላልፈለጉ፣ የጥፋቱን የአንበሣ ድርሻ ለአሽከሮቹ ለማሸከም በማቀድ የተጠቀሙበት የማታለያ ዘዴ ነው። የሚታለል ካለ! በነአረጋዊ አገላለጽ የሚያሳዝነውና እነርሱንም ከከፍተኛ ግምት ውስጥ የሚጥላቸው «--የሚካሄደውን ትግል ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል አንዳንድ ቡድኖች ለፕሮፓጋንዳና ለንብረት ፍጆታ ሲሉ ትግሉን ጥላሸት ሊቀቡት የሚዳዱ አደናቃፊዎች በጊዜ ሃይ ሊባሉ ይገባል፤» የሚለው ነው።
አረጋዊ በርሔና አጋሩ ግደይ ዘርኣጽዮን የሚመሩት ድርጅት ሮማን ፕሮቻስካ የተባለው የኦስትሪያ-ሐንጋሪ ቆንሲል የሞሶሎኒ መልዕክተኛ ሆኖ፣ እኤአ በ1935 ባሳተመው መጽሐፍ «ኢትዮጵያ የብሔረሰቦች እስር ቤት» እንደሆነች፣ አሳሪውም «ዐማራው» እንደሆነ፣ «ለእያንዳንዱ ብሔር የመገንጠል መብት ቢሰጠው ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንደማትኖር» የጻፈውን፣ ዋለልኝ መኮንን እንደ ደረቅ ሐቅ ተቀብሎ፣ በተማሪው እንቅስቃሴ ውስጥ ነዝቶ ዛሬ በአገራችንና በዐማራው ነገድ ላይ የደረሰውን ጥፋት የወለደ መሆኑ ይታወቃል። የዚህ ዓላማ አራማጅ የሆነው ወያኔና መሥራቹ አረጋዊ፣ «የኢትዮጵያ መሠታዊ ችግር የብሔር ጭቆና ነው። ጨቋኙም ዐማራ ነው። የትግሬ ብሔር በነቂስ ተደራጅቶ ዐማራውን ማጥፋት አለበት» የሚል ፕሮግራም አዘጋጅቶ፣ በአገሪቱና በዐማራው ነገድ ላይ ከፍተኛ የጥፋት ተግባር ከፈጸሙ በኋላ፣ ሕዝቡ የጥፋት ጉዞውን ለመግታት ሲንቀሳቀስ፣ እንቅስቃሴው በጥፋት ኃይሎችና ቡድኖች ላይ ትኩረቱን ሲጥል፣ በብሔሮች መካከል ያልነበረውን ቅራኔ እንደነበር አድርገው ስለው በዐማራውና በሌሎች ነገዶች ላይ የዘር ፍጅት ከተፈጸመ በኋላ፣ «የሚካሄደው ትግል ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል» የሚለው አገላለጽ፣ ፍፁም ክህደት ከመሆኑም በላይ ተራ ማጭበርበር ነው። ፍረዱ ወገኖቼ፣ ዛሬ በአገራችን ውስጥ ከወያኔ ጋር የሚደረገው ግብግብና ትንቅንቅ የመደብ ትግል ነው? የርዕዮተ ዓለም ነው ፍትጊያ ወይ? ትንቅንቁና ግብግቡ በነገዶች መካከል አይደለም ወይ? ወያኔ የትግሬን ዘር አደራጅቶና አስታጥቆ በአጋዚ ሠራዊት የሚጨፈጭፈው ዐማራ፣ ኦሮሞ፣ ሶማሊ፣ አኙዋክ፣ ኑኤር፣ ወዘተርፈ የመደብ ጠላት ነው? መቼም አረጋዊና መሰሎቹ «አዎ!» እንደሚሉን አንጠራጠርም። ገና ጧት ወያኔ በረሃ ሳይገባ ትግሉን «በብሔሮች መካከል ማድረግ እንዳለበት» አምኖና ወስኖ፣ በዚህም «የትግራይ ነፃ አውጭ ግንባር» የሚል ስም ሰጥቶ ነገዱን በዙሪያው አሰልፎ በሌሎች ነገዶች ላይ ጦርነት አውጆ፣ የዘር ፍጅት ከፈጸመ በኋላ፣ ፍጅቱ እሳቱን ወዳነደዱት ክፍሎች ሲዞር፣ ከቅራኔ አልፎ ተፃራሪ ደረጃ ሲደርስ፣ «ትግሉን ተራ የብሔሮች ቅራኔ በማስመሰል» ማለት ምን ማለት ነው። ዐማራው፣ ኦሮሞው፣ ሶማሌውና መሰሉ ሲሞት ለነገ አረጋዊ የጽድቅ ሥራ ነው። እነዚህን የገደሉ ሰዎች «ተው! ግድያችሁን አቁሙ፤ በልክ ሁኑ፣ ሕግ ይዳኛችሁ!» ሲባሉ፣ ወንጀል እና በትግሬ ዘር ላይ እንደተዘመተ ዕኩይ ተግባር ሊቆጠር ነው። ይህ ዓይነቱ አቋም ነው የትግሬን ትውልድ የሌሎች ነገዶች ተወላጆች ከጥርጣሬ አልፈው «ሁሉም የወያኔ አባሎችና ተባባሪዎች ናቸው» ብለው እንዲያስቡ የሚያስገድደው።
በመሆኑም በነአረጋዊ በርሔ ድርጅት የወጣውን የመግለጫ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ ለጎንደር ሕዝብ ድጋፍ የወጣ ሳይሆን፣ አጥፊውን የወያኔ ቡድን ሕዝቡ እንዳይቃወም ለማስፈራራት፣ «ወያኔን ከነካችሁ እኛ አለንባችሁ» በሚል ስሜት እንድንገነዘበው አድርጎናል። ስለሆነም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ፣ ከሁሉም በላይ ወጣቱ የዐማራ ትውልድ «የትግራይ ዴሞክራሲዊ ትብብር» የተሰኘው ድርጅትና መሪዎች ከመለስ፣ ከስብሐት፣ ከዐባይ ፀሐየ እና መሰሎቻቸው የማይለዩ፣ የወያኔ አገዛዝ እንዲቀጥል በአማራጭነት የተሰለፉ መሆኑን አውቆ እንዲታገላቸው ጥሪአችን እናቀርባለን። በተለይ «ሸንጎ» የተሰኘው የድርጅቶች ስብስብ ይህንም ድርጅት አቅፎ የያዘ በመሆኑ ቆም ብሎ ራሱን በመፈተሽ ትብብሩን ከዕውነትኛ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶችና ግለሰቦች ጋር እንዲያደርግ እንጠይቃለን።
ሁለተኛ፦ በአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር፦
ይህ ማኅበር የጎንደሩን ሕዝባዊ አመጽ በመቃወምና ወያኔ በሕዝቡ ላይ የጥፋት ክንዱን እንዲያነሳ፣ ንብረታቸው ለወደመባቸው የወያኔ አባሎችና ሰላዮች አስተዳደሩ ካሣ እንዲከፍል ጥሪ ያደረገውና ለዚህም ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ ያሳወቀ ነው። ይህ ዘረኛ የትግሬዎች ማኅበር Friday, 15th of July 2016 በተጻፈና «በቅርቡ በጎንደር ከተማና አካባቢዋ በተከሰተው አውዳሚ ሁከት አስመክቶ (አስመልክቶ ለማለት ይመስላል) የተሰጠ መግለጫ፣» በሚል ርዕስ ባወጣው የእሪታ መግለጫ፣ የወያኔ ቱባ ባለሥልጣኖችና ተማርን የሚሉ ልጆቹ በብዙኃን መገናኛ መሣሪያዎች ፊት እየቆሙ፣ «ሕወሓትን እና የትግራይን ሕዝብ» መለየት አይቻልም እያሉ የነገሩን ደረቅ ሀቅ መሆኑን እንድንገነዘብ፣ በወያኔና በሕዝቡ መካከል ልዩነት እንደሌለ እንድንረዳ አድርጎናል። ይህ ማኅበር ባወጣው በዚህ መግለጫው እንዲህ ይለናል፦
«----ኩሩና ታጋሽ የትግራይ ህዝብ ለዓመታት ሲጠነሰስ የቆየ ጥላቻ በቅርቡ በጎንደርና አካባቢዋ በሂወቱና ንብረቱ አሳፋሪና አሳዛኝ የሆነ ከባድ የጥፋት ድርጊት ሲከናወን ለመመልከት በቅተናል። ስልጣን እንጂ የሃገር፤ የሕዝቦች ሰላምና ዕድገት ግድ የማይሰጣቸው ሐይሎች ለተንጋደደ የፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ተጠቃሚ እንደሆነና የችግሮች ሁሉ ምንጭ እንደሆነ አድርገው በማቅረብና በመስበክ የጥቃቱ ሰላባ እንዲሆን አድርገውታል።»
ቀጥሎም
«በመራራው የ17 ዓመታት ትግል የትግራይ ህዝብ ከ60,000 በላይ የሂወት ከ170,000 በላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ከፍሎ ውድ ልጆቹን እንደ አብርሃም በግ ለመስዋዕትነት ያቀረበውን ሕዝብ ፍፁም ዘረኛ በሆነ የትምክህት ሃይሎች የተደጋጋሚ ጥቃቶች ሰለባ መሆኑ በጣም ያሳፍራል።»
በማለት የወያኔ ሰላዮች በመደፈራቸው የተሰማውን ቁጭት ገልፆ፣ ተጎጂዎች ላላቸው ወያኔዎች ካሣ እንዲከፈሉ፣ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸምባቸው ጥበቃ እንዲደረግላቸው፣ በጥፋቱ ተሳትፈዋል የሚባሉት ወገኖች ለሕግ እንዲቀርቡና የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድባቸው ይጠይቃል። «መንግሥት» ለሚወስደው ርምጃም «ከጎኑ እንደሚቆሙ» ገልጸዋል።
ከላይ የአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር (የአውሮፓ የወያኔ ቅርንጫፍ ማለቱ ይቀላልከፍ ሲል የተጠቀሱትን ሀሳቦች እንፈትሽ። « ለዓመታት ሲጠነሰስ የቆየ ጥላቻ»የሚለውን ሐረግ ምን ለማለት እንደሆነ እንመርምር። ምርምራችን ትክክለኛ ውሳኔ ላይ እንዲያደርሰን «ጥላቻውን ማን ፈጠረውለምንስ ተፈጠረእንዴትስ ተፈጠረየሚሉትን ጥያቄዎች አንስተን ተገቢና ትክክለኛ መልስ ማግኘት አለብን። በኢትዮጵያ ነገዶች መካከል ጥላቻና መጠራጠር እንዲፈጠር ያደረገው የትግሬ-ወያኔ ነው። ይህ አጥፊ ቡድን 1968 ዓ.ም. ባውጣው ፕሮግራም «ዐማራው የትግራይ ሕዝብ ጠላት ስለሆነ ትግሬ ተደራጅቶ ዐማራውን ማጥፋት አለበት» በማለት ሕዝቡን የሰበከ፣ ያደራጀ፣ የመራናየፈጀ መሆኑ ግልጽ ነው። ወያኔ ከትግራይ ምድር ሲወጣ፣ ሌሎችን ነገዶች አደራጅቶ በዐማራው ላይ እንዲዘምቱ ማድረጉን የኢሕዲን(ብአዴን)፣ ኦሕዴድ፣ ደሕዴግ እና መሰሎቹቋሚ ነቃሾች ናቸው። በነዚህ ትብብር የአገሪቱን አስተዳደር በነገድ ሸንሽኖ ሕዝቡን ሆድና ጀርባ ያደረገው ወያኔ ነው። የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምትን ሕዝብ የፈጀ ወያኔ ነው።ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ በጉልበት ጠቅሎ ሕዝቡን ጦም አዳሪ ያደረገው ወያኔ ነው። በወልቃይት ጠገዴ ለም መሬቶችን ከዐማራዎቹ ነጥቆ ያሰፈረው ትግሬዎችን ነው። እናንተ ሰዎች፣ የለየላችሁ ከሃዲዎች ካልሆናችሁ በስተቀረ «አልተደረገም» አትሉንም። ዳሩ ግን ክህደት የዘር ይመስል፣ የወያኔ ሰዎች ፍፁም ከሃዲዎች ናችሁና ከእናንተ ዕውነትአንጠብቅም። እነዚህ የሕይዎት፣ የመብት፣ የኢኮኖሚ፣ የባህልና የማንነት ነጠቃዎች ጥላቻን መፍጠራቸው የታወቀ ነው። ጥላቻ ደግሞ አመጽን መፍጠሩ ዲያሌክቲካዊ ሂደቱነው። ጎንደርም የሆነው ይኸው ነው። « አሸዋ ላይ ፈሶ ጤፍ አይታፈስም፣ ምን ጊዜ ቢረዝም ቂም አይበሰብስም» ነውና ባህላችን ተጀመረ እንጂ፣ ሒሣብ ገና አልተወራረደምናበዚህ ሊገርማችሁ አይገባም። «ወንድ ልጅ፣ መቼ ይሞታል ቢሉት፣ የሠራውን የረሳ ዕለት» እንደተባለው በጎንደር ሕዝብ ላይ በተናጠል፣ በዐማራው ነገድ ላይ በጥቅልየሠራችሁትን ሁሉ አቀፍ በደል ረሳችሁት እንዴእናንተ ብትረሱት እኛ የችግሩ ሰላባዎች ምንጊዜም አንረሳውም። የወያኔ አረመኔአዊ ሥራ እንርሳህ ብንለውም አይረሳምና!
ሌላው አሳዛኙ ነገር ይህ የአውሮፓ የትግሬዎች ማኅበር የገለጠው፣ እነርሱ በዘረፉት የአገርና የሕዝብ ሀብት ቁንጣን ይዟቸው ሲያገሱ፣ ብዙኃኑ የኢትዮጵያ ሕዝብከቆሻሻ ገንዳዎች የተጣለ ትርፍራፊ በወረፋ እንደሚበላ፤ ምሳ፣ ቁርስና እራት በቤተሰብ በወረፋ የሚመገብ፤ ያም «ትንሽ አላቸው» በሚባሉ ቤተሰቦች ነው። ከሁሉም በላይ 15ሚሊዮን በላይ የሆነው ሕዝብ ለርሃብ ተጋልጦ ለልመና ተዳርጎ ባለበት ወቅት፣ «ስልጣን እንጂ የሃገር፤ የሕዝቦች ሰላምና ዕድገት ግድ የማይሰጣቸው ሐይሎች ለተንጋደደየፖለቲካ ፍጆታ ሲሉ የትግራይ ሕዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለየ ተጠቃሚ እንደሆነና የችግሮች ሁሉ ምንጭ እንደሆነ አድርገው በማቅረብና በመስበክ የጥቃቱ ሰለባእንዲሆን አድርገውታል።» በማለት ያሰፈሩት ሀሳብ ወያኔዎች የቱን ያህል ካለራሳቸው ጥቅም በቀር ለአገርና ለሕዝብ መብትና ጥቅም ደንታ ቢስ ስግብግብ ፍጡሮች መሆናቸውንያሳያል። ለመሆኑ ከመንጋደድ አልፎ የወደቀ ፖለቲካ የሚያራምደው ማነው21ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን ላይ ሆኖ፣ የጎሣ ፖለቲካ አባቱ ማነውለዘር የበላይነት የሞተውማነውከላይ «ስድሣ ሺህ ሞቱ፣ መቶ ሰባ ሺህ ቆሰሉ» የተባሉት እኮ፣ የትግሬን ጥቅም ለማስከበር ነው። የምናየውም ይኸው ነው። ወያኔ ወይም ትግሬ ኢትዮጵያን፣ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጥፍቶ፣ የትግሬን የበላይነት ለማንገሥ የተደራጀና ያለ እንጂ፣ ለሕዝብ ነፃነት፣ ዕኩልነት፣ አንድነትና ብልጽግና የቆመድርጅት አለመሆኑ፣ ከጅቡቲ መቀሌ፣ ከሱዳን መቀሌ የሚገነባው የባቡር ሐዲድ፣ ትግራይ ውስጥ የተገነቡት ዩኒቨርስቲዎች፣ ኮሌጆች፣ ሆስፒታሎች፣ ክሊኒኮች፣ ፋብሪካዎች፣የተዘረጉት አውራ መንገዶች፣ የተገነቡት ከተሞች ወዘተርፈ አፍ አውጥተው ይናገራሉ። «የትግራይ ሕዝብ በወያኔ አልተጠቀመም» የሚሉ ወገኖች «ተጨፈኑ እናሞኛችሁ» የሚሉብቻ ናቸው። ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ የደህንነትና የፋይናንስ ተቋሞቹ በነቂስ በትግሬ ልጆች የተያዙ ናቸው። ባጭሩ የአገሪቱ ቢሮክራሲ ከዘበኛ እና የጽዳት ሠራተኛ ጀምሮ እስከ ሚኒስተር ያሉት ቦታዎች በወያኔ አባሎች የተሞሉ ናቸው። አገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው 65 ጄኔራል መኮንኖች መካከል 61 ትግሬዎች ናቸው። ከዚህ ወዲያለሥልጣንና ለጥቅም መስገብገብ ምን አለማለት ያለባችሁ ደረቁ ሐቅ፣ «ወያኔ የሞተውና የተደራጀው ለትግራይ ሕዝብ ሁለንተናዊ ጥቅም ነው» ብትሉ ተፈርታችሁ ዕውነትምበመናገራችሁ ተወዳችሁ ትከበሩ ነበር። ውሸት ያስንቃል፣ ያዋርዳል እንጂ፣ አስከብሮም አስፈርቶም አያውቅም።
ሦስተኛ፦ የሰሜን አሜሪካ የትግሬዎች ማኅበር 
ይህ ማኅበር በበኩሉ በጁላይ 14/ 2016 «በጎንደር ከተማ በተፈጠረው ረብሻ በማስመልከት ከትግራይ ተወላጆች ማሕበር በሰሜን አሜሪካ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ» በሚልርዕስ በተጻፈ፣ በጎንደር ከተማ የተከሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ በቁጥጥር ሥር ለማዋል «መንግሥት» የወሰደውን የተቀናጀ የአፈና እርምጃ አሞግሶ፦
«--ቀጣይ እና ውጤታማ እንዲኾን የፌደራል እና የክልሉ መንግሥቶች የህዝባችንን ሰላም ለማስፈን አበርትተው እንዲሰሩ ጥሪአችን እናቀርባለን። መንግስትእየወሰደ ያለውን እርምጃ እንዲቀጥልና የሁከትና ብጥብጡ መሪ ተዋናዮች--ማለትም ``በሕጋዊ ጥያቄ`` ሽፋን እና ስም ሕገወጥ ድርጊት ሲያከናውኑ መንግሥትየደረሰባቸው አካላትበቁጥጥር ስር ውለው በአፋጣኝ ወደ ፍርድ እንዲያቀርባቸው እንጠይቃለን።» ይላል።
ይህ መግለጫ ከላይኞቹ የሚለየው፣ በቀጥታ የወያኔው አፈቀላጤ የጌታቸው ረዳ አባባል ግልባጭ መሆኑ ነው። በዚህ  የትግሬዎች ማኅበር አገላለጽ፣ የሕዝብ ሰላም ማለት የወያኔ ሰላም ማግኘት ነው። አጥፊዎች ከተነኩ፣ ገዳዮች ከተገደሉ፣ በዝባዦችና ሌቦች ንብረታቸው ከወደመ «ሰላም ተናጋ» ይሉናል። የአምስት ሚሊዮን ዐማሮች ሕይዎት ሲጠፋ፣ ንብረታቸውን ተዘርፈው ሲባረሩ ለነርሱ ሰላም ነው። ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ «ወያኔ አገር እያጠፋና ሕዝብ እየበደለ ይኑር» የሚል በመሆኑ፣ በየትኛውም መልኩ የዐማራው ነገድ የሚገዛው አይሆንም። መግለጫው ግን አንድን ሐቅ ፍንትው ብሎ እንዲታይ ያደረገ በመሆኑ ይበል የሚባል ነው። «ትግሬና ወያኔን ለዩ» ለሚሉ ወገኖች፣ በማያሻማ መልኩ ወያኔ ማለት ትግሬ፣ ትግሬ ማለት ወያኔ እንደሆነ ሁነኛ መልስ ሰጥቷል።
አራተኛ፦ አብርሃ ደስታ፣ አስራት አብርሃም እና ሙሉዓለም ገብረመድኅን የተባሉት፦
እኒህ ሰዎች በየግላቸው «ለምን ወያኔ ይነካል» በሚል ስሜት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ያሰሙት ስሞታ ከፍ ሲል በተጠቀሱት መግለጫዎች በተሰጡት መልሶች የሚካተት በመሆኑ ዝርዝር ውስጥ መግባቱ መደጋገም ስለሚሆን ማለፉን መርጠናል። ሆኖም ግን «የወያኔ ተቃዋሚ ነው» የሚባለው አብርሃ ደስታ ያሰማው ተቃውሞ ማንነቱን በጥብቅ እንድንፈትሽ የሚገፋፋ ሆኖ አገኝተነዋል። ይህ ሰው ለሁለት ዓመት ታሥሯል። ባጭር ጊዜ መፈታቱ በራሱ ጥርጣሬ ላይ የሚጥል ነው። ምክንያቱም ከእርሱ የከፋ ያልጻፉትና ያልተናገሩት አንዱዓለም አራጌና እንስክንድር ነጋ ዐማሮች በመሆናቸው ብቻ የ18 ዓመታትና የዕድሜ ልክ እስረኛ ሲሆኑ፣ እርሱ ከሁለት ዓመት እሥራት በኋላ መፈታቱ ለወያኔ ባለው ቀረቤታና ስስ ልብ እንደሆን እንድናጤን አድርጎናል። በጥንቃቄ ከመረመርነው፥ መታሰር በራሱ የቁርጠኛ ተቃዋሚነት መስፈርት አይደለም። ለስለላና ለተለያዩ ሥራዎች ሰዎች በተቃዋሚነት ስም ይታሰራሉና። በሌላም በኩል ትክክለኛ ተቃዋሚው፣ ከዳዊት ከበደ፣ ከአብርሃም ያየህ፣ ከስየ አብርሃ እና ከነጋሶ ጊዳዳ ትምህርት መውሰድ ያሻዋል እንላለን።
የጎንደር ሕዝብ ጭቆናው፣ አፈናው፣ እስራቱ፣ እንግልቱ፣ ውርደቱ ከሚሸከመው በላይ በመሆኑ፣ ክንዱን በጨቋኞች ላይ አንስቷል። ይህ ክንድ፣ በአሉባልታና በዛቻ አይዝልም፤ አይታጠፍምም። የሚዝለውና የሚታጠፈው፣ ዕውነተኞቹ የትግራይ ልጆች፣ በጎንደር ሕዝብና በዐማራው ላይ ወያኔ የፈጸመውን ይህ ቀረው ያልተባለ ግፍና በደል አምነው፣ ዳግም እንዳይደገም ወያኔን በማውገዝ፣ ከጎኑ ሲቆሙ ብቻ ነው። ይን ሲሆን፣ ጎንደሬው፣ ከሁሉም በላይ ዐማራው፣ የይቅርታ ባህሉ እጅግ የዳበረ በመሆኑ፣ «ባለፈው ይብቃ» የማለት አቅሙ የጎለበተ ስለሆነ፣ ዕምነቱም ስለሆነ፣ በዳዮቹ የሠሩትን ጥፋት ከልብ ካመኑ፣ በይቅርታ አብሮ ለመኖር አይቸገርም። በዛቻና በማስፈራራት ግን፣ ከእንግዲህ ወዲያ ጎንደሬው «አፈርኩ» ብሏልና ባለፈው መልኩ ክብሩና መብቱ ተገፎና ተረግጦ መኖር የማይችል መሆኑን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። በማስጠንቀቂያው መሠረት ከጎኑ መቆም፣ ካልሆነም የሚሰነዝረውን ለመቀበል መዘጋጀት ነው። ምርጫው የወያኔና የትግራይ ሕዝብ ነው።
በዚህ ረገድ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት፣ እስካሁን እንዳደረገው ሁሉ፣ ዐማራው በአንድ አዕምሮ አስቦ እንደሠራዊት በመትመም፣ ሊያጠፉት የተሰለፉትን ኃይሎች እንዳመጣጣቸው በመመከት፣ ወያኔና አጫፋሪዎቹ እንደሚሉት «ፈሪ፣ እና ሽንታም» አለመሆንክን በተባበረው ክንድህ የጎንደርን ምሳሌ በመከተል ወያኔና አጋሮቹን ልታሳያቸው ግድ ከሚልህ ምዕራፍ ላይ የደረስክ መሆንክን አውቀህ፣ ለማይቀረው የነፃነት ጉዞ ትጥቅህን እንድታበረታ ጥሪ እናቀርባለን!
 
የወልቃይት ጠገዴ፣ የጠለምት፣ የሑመራ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ የመላው ዐማራ ሕዝብ ጥያቄ ነው
ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ጠለምት፣ ሑመራ ዐማራ ነው!
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!