ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ዘረኛውና ክፋፋይ የወያኔ አገዛዝ በመላው ኢትዮጵያውያን ላይ፤ በተለይ ደግሞ በአማራው ላይ በቃላት ሊገለጽ በማይችል ለሰው አይምሮ በጣም ከባድ በሚሆኑ የግድያ፣ ህዝብ የማፈናቀል፣ የግፍና የበደል ዶፍ ሲወርድበት የቆየው የጎንደር- በጌምድር ክፍለ ሀገር ሕዝብ በሰላም እየታገለና በትእግስት ችሎ ችሎ ባለፉት 15 ቀናት ውስጥ ከሞት ውጭ የቀረኝ አማራጭ ስለሌለ፤ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ለማንነቴ፣ እንዲሁም የጎንደር ሕዝብ ለመብቴና ለኢትዮጵያዊነቴ የመጨረሻውን መስዋእትነት እከፍላለሁ ብሎ በመነሳቱ የወያኔ የጸጥታና የጦር ሃይል እንደለመደው ለመግደልና ለማሰር ሲሞክር ከሕዝቡ ጋር ግጭት አድርጓል፤ አሁንም ሕዝቡ በመፋለም ላይ ይገኛል። በመጀመሪያ የጎንደር ሕዝብ ቆራጥነቱ፣ ጀግንነቱና ወኔው አኩርቶናል፤ ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ማውለብለቡ ከልብ አስደስቶናል። ኖር! ኖር ! እንላለን።
በጎጃምም የባህር ዳር ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ለጎንደር ሕዝብ ድጋፉን ሲያሳይ እና ለወያኔ አልገዛም ሲል በመነሳቱ፤ በአግአዚ ጦር በጭካኔ መጨፍጨፉና መደብደቡ ቢያሳዝነንም፣ ቢያስቆጣንም የሕዝቡ ቆራጥነትና እምቢተኛነት እጅግ አኩርቶናል፤ ከጎንህም ነን አለንልህ እንላለን። ችግሩ ችግራችን፣ ስቃዩ ስቃያችን፣ ሞቱ ሞታችን ነውና ክጎንደር - በጌምድር ክፍለ ሀገር ከተወለዱ ልጆቹ፣ ክጎጃም እና ከወሎ ከ/ሀገር ከተወለዱ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመወያየትና በመመካከር አስፈላጊውን ሁሉ እርዳታ ለመስጠት ነሐሴ 1 ቀን 2008 ( Aug 7, 2016) ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባ በአንድ ድምጽ ወስነናል፤ ቃል ገብተናል። ስለዚህ ይህን ታሪካዊና የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ትግል በምትችሉት መጠን እርዳታና ድጋፍ እንድታደርጉ የትግሉም አካል እንድትሆኑ የአገርና የሕዝብ አድን ጥሪ እናስተላልፋለን።
ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘላለም ትኖራለች! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ቶሮንቶ፤ ካናዳ እርዳታና ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ፤ 647 219 2804 ይደውሉ
No comments:
Post a Comment