ሙሉቀን ተስፋዉ (Muluken Tesfaw), August 20 at 10:13pm · Edited ·
ምንጭ፦ https://www.facebook.com/muluken.tesfaw
Criticism may not be agreeable, but it is necessary. It fulfils the same function as pain in the human body. It calls attention to an unhealthy state of things.
Winston Churchill
የአማራን ሕዝብና የተማሩ ሰዎች ‹ልሂቃን› በተመለከተ የጻፍካቸውን ሁለት ጽሁፎች በደንብ ደግሜ ደጋግሜ
አነበብኳቸዉ፡፡ የመጀመሪያዉን ጽሁፍ ሳነብ በፍጹም በአንተ እጅ የተጻፈ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ተጽፎም ከሆነ በስሜት እንጅ
በአስተዉሎት የከተብከዉ ነዉ ብዬ ለማሰብ ትንሽ ጊዜ ወሰደብኝ፡፡ ፈጽሞም የመጸጸትም ይቅርታም የመጠየቅ ፍላጎት
እንደሌለህ ተረዳዉ፡፡ ቢሆንም በጨዋ ደንብ ይህን ደብዳቤ ልጽፍልህ ፈለግኩ፡፡
አንዳንዴ ዝምታ ፍርሐት ላይሆን ይችላል፤ ድፍረትም እዉቀት አይደለም፡፡ መሳሳትም የሰዉ ልጆች ሁሉ
ሊያደርጉት የሚችሉት ነዉ፤ ሆኖም ከስህተት ለመማር መሞከር ደግሞ ትልቅነት ይሆናል፡፡ በመጀመሪያ ማወቅ የሚገባህ ነገር
‹አማራነት ደሜ ውስጥ አለ› ብሎ በማሰብህ ብቻ በአማራ ላይ መጨፈር አሊያም የወጣበትን ሕዝብ መሳደብ ከአመክንዮም
ከእውቀትም ውጭ ‹የበሉበትን ወጪት› ሰባሪነት ነዉ፡፡
ቀጥታ ወደ ጉዳዩ ስገባ ሄኖክ ‹የአማራ ምሁራን (ዘግይቶ አንዳንድ በሚል ተስተካክሏል) ዶክተር ብርሐኑን
የማይወዱበት ምክንያት› ያልከዉ እነማንን ነዉ? እነማን ናቸዉ የአንተን አለቃ የሚጠሉት? የጽሁፍህ አላማ እነማንን መሰረት
በማድረግ የተጻፈ እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡
ሁለተኛዉ ምናልባትም አንድ ወይም ሁለት ሰዎች ዶክተሩን ተቃውመዉ
ቢጽፉ አሊያም ቢናገሩ የግለሰቦቹን ስም ጠቅሰህ ለምን መጻፍ አልፈለግክም? ግለሰብን ከመዉቀስና ሕዝብን በጅምላ
ከመሳደብ የትኛዉ ይቀላል?
ስድብህን ‹‹አንዳንድ የአማራ ምሁራን ብርሐኑ ነጋን የሚጠሉት ዋነኛ ምክንያታቸዉ ቆሻሻቸዉን ስላሳያቸዉ
ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ላለፉት 25 ዓመታት በገበየሁ ታሪክ ማኪያቶ ሲጠጡ የኖሩ፣ በገብርዬ ጀግንነት ዘር ሲቆጥሩ
የኖሩት፣ በበላይ ሲፍክሩ የኖሩት እነርሱ ግን አንዳቸዉም መሆን የማይችሉ እንደሆኑ በይበልጥም ደካሞችና አቅመ ቢሶች
እንደሆነ ፍንትዉ አድርጎ ስላሳያቸዉ ይመስለኛል፤…›› በማለት ትቀጥላለህ፡፡
ይህ ስድብህን ሕወሓት በ1968 ዓ.ም.
ካወጣው ማንፌስቶ አማራዉን ካየበት አይን ጋር አይሄድ አይመጣ አንድ ሆኖ አግኝቸዋለሁ፡፡
ሕወሓት ‹‹አሁን ያለዉ የትህምከተኞችና የአድሓሪያን የዐማራ ባህል ሙሉ በሙሉ መጥፋት አለበት›› ብሎ አዉጆ
ነበር (አዉጇል)፡፡ ቆይቶ ግን የፈለገዉን ያክል አማራ ካሳደደ በኋላ የሸዋ አማራን ብቻ ብሎ አንተ አንዳንድ አማራ ልሂቃን
ብለህ እንዳሻሻልከዉ ሕወሓትም አሻሻለዉ፡፡
አማራማ አዲሱ ለገሰም፣ ተፈራ ዋልዋም፣ ታምራት ላይኔም አማራ ነኝ ብለዋል፡፡ ከዚህ ላይ መድገም ባልፈልግም
አለምነዉ መኮነን ያለዉም ከአንተ የተለየ አይደለም፡፡ አለምነዉም ከተሳደበ በኋላ ‹‹ትምህምከተኞችን›› ብቻ ነዉ ብሎ
አስተካክሎታል፡፡
ኧረ ለመሆኑ በአለቃህ ምክንያት በየቦታዉ እየተለቀሙ እየተሰቃዩ ያሉት የአማራ ወጣቶች አይደሉምን? የአማራ
ምሁራን ከዚህ ሲታሰሩ ከብርሐኑ ጋር ትገናኛላችሁ በሚል እንደሆነ አንተ ታጠዋለህ? የአማራ ሕዝብን እያስፈጁ ‹‹ቆሻሻ››
2
ብሎ መሳደብ ምን የሚሉት ፈሊጥ ነዉ? ለምንድን ነዉ በሚሞት ሕዝብ ቁስል ላይ እንጨት ለመስደድ እርህራሄ ያላሳየህ?
ስለምንስ የሞቱ ወገኖችህ ደም ሳይደርቅ፣ አርባቸዉ እንኳ ሳይወጣ ልጆቻቸዉን ‹‹እድፋም›› የምትልባቸዉ? ስለምን
ቁስላችን ታመረቅዘዋለህ?
‹አማራዎች በጅምላ ሞቱ› የሚለዉን ዜና እንደሰማህ ይባስ ብለህ መሳደብህ በእዉነት የጨዋ ልጅ ደንብ ነዉ?
አሜሪካ የምትባለዋ ሐገር ‹ምን አይነት ሰደዴ› አድርጋ ብትቀርጽህ ነዉ እንደዚህ ድፍረትህ?
እስኪ የእዉነት እናዉራና የብርሀኑ ጀግንነት የትኛዉ ነዉ? በዚህ ሰባት አመት ውስጥ ባስጨረሳቸዉ የዐማራ ልጆች
ደም ‹ኒሻን› ይሸለም ካልሆነ የእርሱ ጀግንነት የትኛዉ ነዉ? ስለምን ብሶታችንን ትቆሰቆሱታላችሁ?
እንደ ሰለጠነ ሰዉ የተጣላሃቸዉን ግለሰቦች በተናጥል ማብጠልጠል ትችላለህ፡፡ ነገር ግን አማራን እባክህ ተወዉ፡፡
የአማራ ሕዝብን ለቀቅ አድርገዉ፡፡
እነ ፕሮፌሰር አስራት የአማራ ምሁራን አይደሉምን? እነ እስክንድር ነጋስ? እነ አንዷለም
አራጌ ከየት የተገኙ ናቸዉ? አለቃህን የሚጠሉ የምትላቸዉን ሰዎች በግልጽ አናግራቸዉ፡፡ Gashaw Mersha ZGondar
Gashaw ZeAmhara
No comments:
Post a Comment