Solomon Derzie, Sun 23Aug2015
ምንጭ፦ https://www.facebook.com/solomon.derzie/posts/10206336938917867·
ብዙዎቻችሁ ንጹህ ኢትዮጵያውያኖች እንደሆናችሁ እናውቃለን። ወያኔ የሚባል የእፉኝት ልጆች ጥርቅም ባንድ ለሊት እንደጭስ በነው፤ ወይም ደግሞ በተአምር ዶጋመድ ሆነው ቢያድሩና እፎይታ ብናገኝ የናንተም የኛም ምኞታችን ነው። ያ ግን እንደማይሆን አውቀን ሁሉም በየፊናው እነዚህን ካንሰሮች ከህዝባችን ጫንቃ ላይ አሽቀንጥረን ለመጣል በየመሰለንና ባመንንበት የበኩላችንን አስተዋጾ ለማበርከት የምናደርገውን ጥረት በመከባበርና በመቻቻል ማድረግ ሲገባን ዛሬም እንደትላንቱ "የኔ ካልሆንክ እንደ ጉም ተነህ ጥፋ"የሚል አውዳሚ ባህላችን እስካልተላቀቅን ድረስ ማንም ማንንም አያሸንፍም።
አማራው ከማንኛውም የሃገሪቷ ዜጎች በተለዬ ሁኔታ የጥቃት ኢላማ ተነጣትሮበት ከሃያ አራት አመት በላይ የዘለቀ ሰቆቃ እየተፈጸመበት እንዳለ ሁሉም የሚያውቀው ጉዳይ መሆኑ እየታወቀና ወያኔም ራሱ ምንም ባለማፈር በማን አለብኝነት በራሳቸው ፓርላማ ውስጥ በእብሪት ከ2.5 ሚሊዮን በላይ አማራ ከምድረገጽ ተኖ እንደጠፋ አምነዋል። ለአቅመ ሄዋን የደረሱ የአማራ ተወላጅ ልጃገረዶች የሚያመክን መርፌ መወጋታቸውን በቪዲዮ መረጃ እየታዬ ሌላው ደንታም ባልሰጠው ሁኔታ፤ ይህ ጉዳይ ያስደነገጣቸውና ያንገበገባቸው አማሮች የተቻላቸውን ሁሉ ለማድረግ ደፋ ቀና ቢሉ ምኑ ላይ ነው ጥፋቱ? ለምንድን ነው ሌላው ኢትዮጵያዊ ያላንገበገበው? አማራዎች እኮ ከጉራፋርዳ በተባረሩ ወቅት አንድነት አባል የነበረበት "መድረክ" ለምን መግለጫ አታወጡም ተብለው ሲጠየቁ የሰጡት መልስ እያጣራን ነው ብለው ነበር መልስ የሰጡት። እስከዛሬም አላወጡም ዝንተ አለምም አያወጡም። አንድነት ውስጥ ከነበሩ የአማራ ተወላጆች ጋርም የነበረው ግጭት አንዱ ይኸው ይመስለኛል። አንድነትም በዚህና በመሳሰሉት ጉዳዮች ከእንደ በየነ ጴጥሮስ አይነቶቹ የወያኔ የውስጥ አርበኛና የለየለት ጸረ አማራ ግለሰቦች የሚመሩ ድርጅቶች ምንም ሳይነኩ አማሮች ያሉበት የኢትዮጵያ ጠበቃው የነበረው"አንድነት"ፈረሰ ወይም ለባንዳዎች ተሰጠ።የመኢአድም እጣፋንታ ተመሳሳይ ነበር።
ወደዋናው ነጥቤ ልመለስና፤አሁን እንኳን በቅርብ በጋምቤላ ከ542 በላይ አማራዎች በተገደሉና በሺዎች የሚቆጠሩ በተባረሩበት ወቅት አሁን ከግንቦት 7 ጋር የተወዳጀው እንደ ወንድሜ እወደው የነበረውና ያቅሜን ያህል እረዳው የነበረ ኦባንግ ሜቶ እንኳን በሚመራው ድርጅት በአዲሲቱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ስም መግለጫ ለምን እንዳላወጣ ስጠይቀው የሰጠኝ መልስ ከሚታመኑ የዜና አውታሮች ወይም ድርጅቶች መረጃ እፈልጋለሁ ነበር ያለኝ። ልብ በሉ፤ይህ ሰው የጋምቤላ ተወላጅ ነው። ጋምቤላ የምትበር ወፍ እንኳ ስትሞት የሚያውቅ ንቁና ታታሪ ሰው ነው እንዳልሰማ ይናገር የነበረው። ነገር ግን የጀርመንም በሉት በተለይም የአሜሪካ ድምጽ የአማረኛ ራዲዮ ፕሮግራም ከመዘገብም አልፎ ተጎጅዎችን ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው ባለበት ሁኔታ ነው አቶ ኦባንግ መግለጫ አለማውጣትን የመረጠው። ይቺ ደግሞ የግንቦት ሰባት ስራ እንደሆነች ጠንቅቀን እናውቃለን። ኦባንግ ጥሩ ሰው ነበር፤ ከክፉዎች ተጠግቶ በተሳሳተ መንገድ እየሄደ መሆኑን ልጠቁመው እወዳለሁ በዚህ አጋጣሚ። የምለው ነገር ውሸት ከሆነ ስልኬን ያውቀዋል በአደባባይ መነጋገር እንችላለን።ያን ጊዜ ስጠይቀው ምስክር ስለነበረኝ ለማለት ነው። ለነገሩ በኢን ቦክሳችንም የተመላለስናቸው ነጥቦች መረጃ ስላለኝ እንዳመጣጡ አስተናግደዋለሁ።
እሱ የሚመራው ድርጅት ውስጥ ቁልፍ ቦታ ያላቸው የአማራ ተወላጆችም ኦባንግን መግለጫ እንዲያወጣ የገፋፉት አይመስለኝም ጉዳዩ ከበላይ አለቃቸው ከለየላቸው ጸረ አማሮች ስለሆነ የሚሰፈርላቸው ድርጎ እንዳይቆም መሆኑን አውቃለሁ። ኢሳትም ያንጊዜ በስሷ ነው የዘገባት 542 ሰው ተገድሎ። ብዙ ሌላም ማለት ይቻላል ግንቦት ሰባት በጉልበት እየነጠቀን እየወሰደ የግሉ ስላደረጋቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ኢሳትን ጨምሮ።
አሁንም የዚህ ድርጅት አመራሮች አምላኪዎች ካላረፋችሁ ወያኔዎች ደስ እንዳይላቸው በማለት እንጂ አምቀን የያዝነው ሊፈነዳ የደረሰ ብዙ ጉድ ስላለ የማይነካካ አትነካኩ መሳቂያ እንዳንሆን፤ የፈነዳ ጊዜ ሸክሙን እናንተም አለቆቻችሁም አትችሉትም። ከኢሳትም ሆነ ከግንቦት ደጋፊነት በሉት አባልነት ተገፍትረን የተባረርነው ለምን የአማራውን መደራጀት ደገፋችሁ ተብለን ነው።የተሰጠን ምርጫ ሁለት ነበር። አንድም አርፈን መቀመጥ ያለበለዚያ በግንቦት ሰባት መሰናበት። ምርጫዬ ለወላድ መሃኑ ወገኔ የበኩሌን ማድረግ ነበረ። ይህ ሁሉ እብሪት ከየት የመጣ ነው ብዬ እጥይቅ ነበር ራሴን። እያደር ነው የገባኝ። ይህ ቅጥ ያጣ ጥላቻ ከወደ አስመራ የሚወነጨፍ አረንዛ መሆኑን። እኛ በየወሩ የምናዋጣትና አክቲቪስቶች በአመት ሁለት ወይም ሶስት ጊዜ እየዞሩ የሚለምኗት ገንዘብ ፕሮፌሰ መስፍን እንዳሉት የትም ስለማታደርስ የግብጾችንና የኢሳያስን ቅድመሁኔታወች ተቀብለው ድርጎ ማግኘት ነበረባቸው የኢሳት ባለቤቶች። ይህን ሁሉ ጉድ በሆዳችን አምቀን ዝም ባልንና ጥቂት የአማራ ልጆች ተሰባስበን የተቻለንን በማድረግ ለዚህ ለተገፋ ህዝብ ድምጽ ለመሆን ደፋ ቀና ብንል ምንድን ላይ ነው ጥፋቱና ወንጀሉ? እነበቀለ ገርባ እኮ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ከመድረኩ እያስነሱ ከአንድም ሁለት ጊዜ በኢስት ላይ ኢንተርቪው ሲደረጉ (ይህንን ደግሞ ሄኖክ ነው የነገረን ፈጥራችሁ ነው እንዳትሉ) ለምን ኢትዮጵያን የሚጠሉ የኦሮሞ ጽንፈኞች እንደፈለጉ ይፈነጩበታል ብላችሁ የመጠየቅ ድፍረቱ የሌላችሁ ጉዶች ለምንድን ነው ለአማራው ተቆርቋሪዎች ላይ ክንዳችሁና ምላሳችሁ የሚበረታው? ምን ሰራችሁ እያላችሁ የምታብጠለጥሏቸው የአማራ ልሂቃንን ስራ ለማዬት ምን ጥረት አድርጋችሁ ነበር?
ኢሳትን እኮ በጥራራ ጸሃይ ነው የኢትዮጵያ ህዝብ በጉልበት የተቀማው። እንዴት እንደተቋቋመ እኮ እናውቃለን። በዳኛ ወልደሚካኤል የሚመራ 13 የቦርድ አባልት የነበሩ ተቃም ነበር እኮ ነአምን አማካኝነት ሻቢያ እስኪነጥቀን ድረስ። ለዚህ ያበቃን ድህነታችን እንደሆነ አውቀን ነበር ዝም ያልነው።ኢሳትንማ ፍጹም ለማድረግ አትሞክሩ። እናንተም በዚሁ ልሳን ከመለፍለፍ ሌላ ምን የምትሰሩት ነገር የለም? ኤርትራ የወረዱት መሪዎቻችሁም እግዜር ከረዳቸው ተመልሰው ይመጣሉ አይሆንም እንጂ ከሆነም በጦርነቱም ከተጀመረ እንዲማገድ የተደገሰለት ያው የፈረደበት የአማራው ተወላጅ ነውና ብዙም አትመጻደቁ የኛው ልጆች ናቸው።ዝም ብላችሁ በየመድረኩ እየዞራችሁ ነጻነት የናፈቀውን ወገኔን እያማለላችሁ ቦጥቡጡት።
ዱሮ "አይንህን ጨፍንና ላምኝ''ነበር ተረቱ፤ አሁን ደግሞ "አይኔን ጨፍኑኝና አሞኙኝ"ሆኗል ነገሩና እንደፈለጋችሁ ጋጡት አያገባንም። እኛ አልደረስንባችሁም አትንኩን። ዙሪያ ገባውን ከካታር በሚለገስ ዳጎስ ባለ ብር እየገዛችሁ ስላሳደማችሁብን ነው እንጂ የኛማ ድንቅዬ ልሂቃኖች ሳይተኙና ደከመን ሳይሉ ህዝቡን በማንቃትና የነ ኦነግን ተረት ተረት እንደ ጉድ እየናዱት ነው ድርጊቱ ለናንተ አለቆች የቂጥ ቁስል ቢሆኑባቸውም። ለነጁሃርና አቶ በቀለ ገርባ እንጂ ኢሳት ለአማራው ልጆች አይሆንም ትዛዙ ከአስመራ በቀጭኗ ሽቦ እንከፈሰሰ ድረስ። እናንተ ስለወያኔ አፈና እያወራችሁ አፈናን ታወድሳላችሁ ፈረንጆች "ደብል ስታንዳርድ" እንደሚሉት ማለት ነው። የኛ ምሁሮች ለአማራው ደፋ ቀና ከማለት አልቦዘኑም በሁሉም መስክ የአማራውን ድምጽ ከማሰማት ታልፎ መረጃን እስከመሰብሰብ የሚቻላቸውን እያደረጉ ነው። ለናንተ የማይታያችሁ ሁሉም የዜና አውታር ማለት ይቻላል ከኢትዮ ፓትሪዬትና ወልቃይት ዳት ካም በስተቀር ስላደሙባቸው በነ
3
ኢካዲኤፍና ኢትዮጵያን ሪቪው እንዲሁም የስዬ እህት ልጅ በነ አብራህም በላይ ድህረ ገጸች ላይ አታገኟቸውም። ይህን ያልኩበት ምክንያት አበበ ገላውም ይቺኑ እናንተ የምትሏትን ምን ሰራችሁን ስለደገማት ነው። ይህን ከየት አመጣኸው ብላችህ ደግሞ አይናችሁን እንዳታጉረጥርጡብኝ፤ ኢካዲኤፍ የሚባለው ድህረገጻችሁ ፌስ ቡክ ላይ ለጥፎት አይቼው ነው። አቤንማ ማን ይነካል መለስን ገሎልን። ለማንኛውም መከባበር ደግ ነው። የናንተ ኢሳትም አፈናውን ይቀጥል እኛም ባለችን ጉልበትና ቀዳዳ እንፍጨርጨር አትንኩን።
በተለይ የአማራ ተወላጆች የሆናችሁ ዛሬም እኛን ብታብጠለጥሉንና የኛው እዳ ብትሆኑም እንወዳችኋለን። "ስጋችሁን በጎመን ለዋጭ" ከመሆን ብትቆጠቡ ደህና ይመስለኛል። አማራው ቢሸሽ እስከ ኢትዮጵያ ድረስ ነውና እዘኑለት ነው እያልን ያለነው። ያለ አማራ ኢትዮጵያ ማሰርያ የሌለው የማገዶ ሸክም እንደማለት ነው። አማራው የኢትዮጵያ ድርና ማግ ነውና አትጥሉት። አማራ ከጠፋ የምትንገበገቡላት ኢትዮጵያም አትኖርም።አማራን ማዳን ኢትዮጵያን ማዳን ነው። ጠባቦችም አትበሉን ትንሽ እፈሩ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰንደቅ አላማችንና መገለጫችን አረንጓዴ ቢጫና ቀዩ ሰንደቃላማችን ነው።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!!! አሜን!!!!!!!
No comments:
Post a Comment