አክሊሉ ወንድአፈረው
ሜይ 22፣ 2015
በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው አስመራ ላይ የተሰየመው የሻአቢያ መንግሥት ለ 23 ዓመታት የተከተለውን አካሄድ
እንዳላዋጣው በመገንዘብ ይመስላል በተወሰነ ደረጃ ለየት ያለ ገጽታን ለማሳየት እና ራሱን አለሳልሶና የሰላም አባወራ ሆኖ
ለመቅረብ በመሯሯጥ ላይ ይገኛል። ይህ ምን መልክ ይዞ ነው የሚራመደው? ለሀገራችን ኢትዮጵያስ ምን እንደምታ አለው?
የሚለው የዚህ ጽሑፍ ዋና ዐላማው ነው።
የአቶ ኢሳያስ አፈወርቂና የሸአቢያ የኩርፊያና የማን አለብኝ ዓመታት
አቶ ኢሳአስ አፈወርቂ እና ድርጅታቸው ሸአቢያ አስመራ ላይ እንደመንግሥት ከተሰየሙ በሁዋላ ስለራሳቸው እጅግ የተጋነነ
እይታ ይዘው ነው ያካባቢውንም ሆነ አለም አቀፉን ህብርተሰብ የተቀላቀሉት። በዚህም መሰረት በየሄዱበት በሽክላ ዕቃ
የተሞላ መደብር ውስጥ እንደገባ እንሰሳ በግራም በቀኝም ያገኙትን ሁሉ እያተረማመሱ ቆይተዋል። በዚህም መሰረት ባጭር
ጊዜ ውስጥ፣
እንደ አውሮፓ አቆጣጠር ከየመን ጋር በ 19961
ከጅቡቲ ጋር ከ 1994 እስከ 20082
ከሱዳን ጋር ደግሞ ከ1994 እስከ 200 ድረስ ዲፕሎማቲክ ግንኙነትን እሰከማቋረጥ የደረሰ ውዝግብ ውስት
ገብተው ነበር3
ከኢትዮጵያ ጋር ደግሞ በ1998 ጦርነት ውስጥ ገብቷል።
ይህ ብቻ ሳይሆን አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ድርጅታቸው ሸአቢያ ከተለያዩ ሀገሮች ጋር የሚያጋጥማቸውን አለመግባባት
በኩርፊያና ቶሎ ብለው በማካረር ዲፕሎማቲካ ግንኙነትን እስከማቋረጥ በሚደርስ አካሄድ ለመቋጩት ሲሞክሩ ደግሞ
ደጋግሞ ታይቷል። ይህ አያያዛቸው ባንድ በኩል ለራሳቸው ከሚሰጡት እጅግ ተፈላጊ ነኝ፣ ታላቅ አርበኛ ነኝ፣ ታላቅ
የፖለቲካ ሊቅ ነኝ ወዘተ ከሚል እጅግ የተጋነነ ግምት የሚመነጭ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ ያስተሳሰብ ደካማነታቸውን
እና ስሜትን የመቆጣጠር ችሎታቸው እጅግ ዝቅተኛ እንደሆነ የሚወስዱትም እርምጃ ሊያሰከትልባቸው የሚችለውን ጉዳት
ማገናዘብ አለመቻላቸውን ያመለክታል።
በዚህ ድንገተኛ ኩርፊያ እና ነገርን ቶሎ የማካረር ባህሪይና እርምጃ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ድርጅታቸው ሸአቢያ ራሳቸውን
እጅግ የከፋ ችግር ውስጥ የጣሉበት (ከኢትዮጵያ ጋር ከነበረው የ 998ቱ ጦርነት ውጭ) አንድ ምሳሌ እንዳውሮፓውያኑ
አቆጣጠር በ 2007 ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት የልማት ድርጅት (ኢጋድ) ውስጥ ኤርትራ ራሷን ድንገት ማግለሏን
በጽሁፍ ባስታወቀች ጊዜ ነበር4።
ይህ እጅግ ድንገተኛ ያልተለመደና በዲፕሎማቲክ አለምም እንደ በሳል እርምጃ የማይታየው አካሄድ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂን ፣
ድርጅታቸውንና እወካላታለሁ የሚሏት ኤርትራን ከአካባቢያዊ፣ አህጉራዊውና አለም አቀፋዊ መድረክ አግልሏቸው
በምንም መልኩ ድምጻቸው እንዳይሰማ አድርጓቸው ከእለት ወደ እለት የተነጠሉ ብቸኛ ሆነው ቆይተዋል።
ይህ ብቻ አይደለም፣ ኢሳያስ አፈወርቂ እንዳውሮፓውያን አቆጣጠር በ2008 አመተ ምህረት ድንገት ተነስቶ አለም አቀፍ
የእርዳታ ድርጅች ሁሉ ጠቅልላችሁ ከኤርትራ ውጡልኝ ኣሉ፡፡ በወቅቱ የኤርትራ ህዝብ ችግር አለበት፣ በረሀብም
የሚሰቃየው ህዝብ ቁጥር ሰፊ ነው፣ ይህን ጉዳይ ለመታደግ እርዳታው ያግዛል ቢባሉም፣” ነገሩን ሁሉ አጡዘው
1
http://www.ipsnews.net/1996/08/yemen-eritrea-hanish-islands-conflict-ends-questionsremain/
2 http://military.wikia.com/wiki/Djiboutian%E2%80%93Eritrean_border_conflict
3 http://news.bbc.co.uk/2/hi/africa/590910.stm
4 http://reliefweb.int/report/eritrea/eritrea-suspends-membership-igad
“እርደታችሁን ረሀብተኛ ለሆኑት ስድስት እና ሰባት ሚሊዮን ኢትዮጳያውያን ሕጻናት ወይም በቅኝ ግዛት ለተያዙት
(ኦኪፔሽን ) የኦጋዴን ሶማሌ ህዝብ ስጡት ነበር ያሉት” 5
ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ የእርዳታ ድርጅቶችን ድንገት ተነስተው በጅምላ ማባረራቸው ያሰከተለው
ትዝብት ሳይቀዘቅዝ፣ በሜይ 2008 ከአልጀዚራ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ፣ ተመልካችን ሁሉ
በሚያሰደነግጥ ሁኔታ ራሳቸውን ለመቆጣጠር አቅቷቸው የተሳከረ እና ካንድ “የሀገር መሪ” የማይጠበቅ አቀራረባቸው ሲታይ
በሌሎች ዘንድ የነበራቸውን ጥቂት ከበሬታ ያሳጣቸው ይመስለኛል።6
ከላይ ከተጠቀሰው በተጨማሪ፤ “አንችው ታመጭው አንችው ታሮጭው” እንደሚባለው በ2007 ድንገት ተነስተው
በኩርፊያ ከኢጋድ ለቅቄ ወጥቻለሁ እንዳላሉ ሁሉ በ2011 ደግሞ ድንገት ወደ ድርጅቱ አባልነት ልመለስ ብለው የኢጋድን
በር ያንኳኩት ያው አቶ ኢሳያስ ነበሩ። ይህ ብቻ ሳይሆን ወደ ኢጋድ ለመመለስ ያቀረቡት ጥያቄ ደርሶናል ሆኖም የዚህ
አይነቱ ጉዳይ ውሳኔ የሚሰጠው በድርጅቱ የመሪወች ጉባኤ ስለሆነ በትእግስት ይጠብቁ ተብሎ ቢነገርም እንዴት ይሆናል
አሁኑኑ ካላስገባችሁኝ ብለው በዲፕሎማሲው አለም እጅግ ባልተለመደና አሳፋሪ በሆነ መልክ ሳይጋበዙ መልክተኛ ልከው
በስብሰባው ጉባኤ ላይ ካልተሳተፍኩ ብለው ግርግር የፈጸመት ያው አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ነበሩ።78
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት መረጃወች እንደሚያሳዩት፣ የአቶ ኢሳያስ መንግስት ከምስረታው ጀምሮ እኔ ያልኩት ካልሆነ በሚል
ዘዬ ፣ ባካባቢው የራሳቸውን የበላይነት ለማስፈን ባደረጉት ሙከራ እጅግ አጥፊ የሆነ ባህሪን ሲያንጸባርቁ ለረጅም ጊዜ
ቆይተዋል። ይህ ሁኔታም፤ በስርአቱ ላይ እጅግ ብዙ ተቃውሞ አስነስቶባቸዋል፣ ከአካባቢውም ሆነ ከአለም አቀፉ
ህብረተሰብ ነጥሏቸው ቆይቷል።
አዲሱ የሸአቢያ አካሄድ
አቶ ኢሳያሰ ወደስልጣን ሲመጡ ዴሞካራሲያዊ ብቻ ሳይሆን አብዮታዊም ተብሎ ሰለተገመቱ እሳቸውም ቢሆኑ
ዴሞካራሲን እውን ለማድረግ እችላለሁ በማለት አለም አቀፉን ህብረተሰብ ለተወሰነ ጊዜ ከጎናቸው ለማሰለፍ ችለው ነበር።
አሁን ከ 20 አመታትን ያስቆጠረው ተግባራቸው ግን ዴሞክራሲያዊም፣ ዘመናዊም መሪ እንዳልሆኑ በተግባር ሰላሳየ
ባካባቢው የሚከሰቱ ቀውሶችን እንደእግር ማስገቢያ በመጠቀም ታላላቆቹን መንግስታት መልሶ ለመወዳጀት ከፍተኛ
መገለባበጥ ለማድረግ ሲጣጣሩ ይታያል። ይህን ሲያደርጉ ግን ቀደም ሲል ይዘዋቸው የሚጓዟቸውን ፍላጎቶች ፣ ለምሳሌ
በሀገር ውስጥ ስልጣንን በብቸኛነት ይዞ መቀጠሉን፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ ድንበሩን በሚፈልገው መልክ ማስከለል እና
ከ1998 ጦርነት በሐላ የተቋረጠበትን ጥቅም መልሶ መመስረት በዋናት ሳይቀየር ነው።
የአቶ ኢያሳያስ አዲሱ አካሄድ በዋናነት የተጀመረው ባውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2011 አምባሳደር ግርማ አስመሮምን ባፍሪካ
አንድነት ድርጅት አምባሳደር አድርገው በሾሙበት ጊዜ ነበር። የአቶ ግርማ ሹመት ተራ አምባሳደርነት ሙያ መጫወት ብቻ
ሳይሆን የአቶ ኢያሳያስን አዲሱን ዲፕሎማቲክ አካሄድ በዋናነት እንዲመሩም ነበር። አምባሳደር ግርማ በሀይለስላሴ ዘመን
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የነበሩና ሁዋላም በኢትዮጵያ ውስጥ የአቶ ኢሳያስ መንግስት አምባሳደር
ሆነው ያገለገሉ ናቸው ። በዚህም የተነሳ የኢትዮጵያን ፖለቲከኞችና የዜጎችንም ባህሪይ “ ጠንቅቄ አውቃቸዋለሁ” ባይ
ናቸው። አምባሳደር ግርማ በቀጣይነት ይህንኑ የአቶ ኢሳያስን አጀንዳ በዋናነት ለማስፈጸም በተባበሩት መንግስታት ዋና
አምባሳደር ተደርገው በ2014 መሾማቸው ይታወሳል።9
5 https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=UAXKsZ8OsWo
(ከ12ተኛው ደቂቃ ጀምሮ ያለውን ያዳምጡ)
6 https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=UAXKsZ8OsWo
7 http://www.diretube.com/ethiopian-news/eritrean-representative-thrown-out-of-igad-meeting-inethiopia-
video_e219074e8.html
8 http://www.africareview.com/News/IGAD+bars+Eritrea+from+Addis+Ababa+mee
ting/-/979180/1224476/-/5wmtfkz/-/index.html
9 http://www.caperi.com/new-permanent-representative-of-eritrea-to-un-presentscredentials/
ፈረንጆች “ብዙ ትንኞችን ከኮምጣጤ ይልቅ ማርን በመጠቀም ማጥመድ ትችላለህ” “ You can catch more flies with
honey than with vinegar “ እንደሚሉት የአቶ ኢሳያስ መንግስትም አላማውን፣ ራእዩን ወዘተ ሳይለውጥ ተቀባይነት
ያሰገኛል ብሎ በገመተው ሰላም እና መረጋጋትን ባካባቢው ለማሰፈን፤ በግንባር ቀደምነት አስተግባሪ መስሎ መሯሯጥን
መርጠወል። ለዚህም የሚከተሉትን እንመልከት
በየመንና መካከለኛው ምስራቅ
ኤርትራን “ከኢትዮጵያ ግኝ ገዥነት ነጻ ለማውጣት” አቶ ኢሳያስና ድርጅታቸው ባካሄዱት ትግል የአረቡ አለም በሁሉም
መልኩ ግንባር ቀደም አጋር እንደነበር ይታወሳል። በገንዘብና በዲፕሎማቲካ ብቻ ሳይሆን ለምሳሌ የኢራኑ አያቶላ ኮሚኒ
በሳምንታዊ የእለተ አርብ (የጁምአ) ሳይቀር ለኤርትራ ነጻነት ተከታታይ ጸሎት ያደርጉ ነበር።10
ከ“ነጻነት” በሁዋላ ግን እንደተመኙት እንክብካቤው አልቀጠለም። በአረቡ አለምና በመካከለኛው ምስራቅ ቦታ ተነፍጓቸው
የቆየት አቶ ኢሳያስ የየመን ግጭትና የሳውዲ የሚመራው ትብብር ጣልቃገብነት ሲከሰት በግንባር ቀደምትነት ነው
“ሁኔታውን ለማረጋጋትና ሰላም ለማውረድ” በሚል ሰበብ ዘለው የገቡት። በዚህም መሰረት በአፕሪል 2015 በሳውዲ አረቢያ
ጉብኛት አድርገው በዚሁ ጉዳይ ላይ ከሳውዲ ንጉሰ እና ሌሎችም ባለስልጣናት ጋር ተወያይተው አንዳንድ ስምምነትም ላይ
እንደደረሱ ተዘገቧል።11
በማስከተልም “ባካባቢው ሰላምን ለማምጣት” በሚል ሰበብ ቀደም ሲል ይረዷቸው ነበር እየተባለ በሚጠረጠረው የሁቲ
አማጽያን ላይ ጀርባቸውን አዙረው በሳውዲ ለሚመራው ጸረ ሁቲ ወታደራዊ ዘመቻ እግረኛ ጦር ለመላክ እንደሚፍልጉ
ተናግረዋል።12
የአቶ ኢሳያስ መንግስት በአንድ እስላማዊ ሀገር የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ መገኘቱ በራሱ በኤርትራ የእስልምና ሀይማኖት
ተከታዮች ዘንድ ሊያስከትለው የሚችለው እንደምታ ምን እንደሚሆን ወደፊት የሚታይ ይሆናል። አሁን ባለው ሁኔታ ግን፣
በውስጥ የሚመጣን የህዝብ ቁጣ ለሳውዲ አረብያና አጋሮቿ ድጋፍ በመስጠት ሊመጣ ከሚችለው ጠቀሜታ ጋር ሲወዳደር
ሚዛን አይደፋም ተብሎ እንደተደመደመና ሊመጣ የሚችለውንም ግፊት ለመቋቋም ቆርጠው እንደተነሱ ያመለክታል።
በደቡብ ሱዳን
ቀደም ባሉት አመታት ኤርትራ የደቡብ ሱዳን ነጻነት ደጋፊ ሆና መኖሯ ይታወቃል። ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ከተቀናጀች
በሁዋላ ግን አቶ የኢሳያስ ተጽእኖ እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡ በቅርቡ የደቡብ ሱዳን ድርጅቶች የእርስበርስ ግጭት
ሲከሰትም አቶ ኢሳያስ ችግሩን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ ምንም ቦታ አላገኙም ነበር።
በኢጋድ አጋፋሪነት ተይዞ በነበረው የደቡብ ሱዳን ተፋላሚዎች እርቅ ጉዳይ በወያኔ/ኢህአዴግ ሊቀመንበርነት እና በሌሎች
የምሰራቅ አፍሪካ መንግስታት ተባባሪነት እየተካሄደ ቆይቷል። በዚህ ሂደትም ኤርትራ ሙሉ በሙሉ ተገልላ ቆያታለች።
በማርች 2015 የእርቅ ሂደቱ እንደተደናቀፈ ግልጽ ሲሆን ነበር ኤርትራ ድንገት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ዋና ተዋናይ ሁና
ለመቅረብ የሞከረችው። በዚህም መሰረት የደቡብ ሱዳኑን መሪ አስመራ ድረስ በመጋበዝ ላካባቢው ችግር ኤርትራ ዋና
ተጫዋች ነች የሚለውን ማስጨበጥ ነበር የሞከሩት። ዋና ምክራቸውም “ሊበጠብጢአችሁ ከሚፈልጉ መንግስታት
ተጠንቀቁ” የሚል ነበር።13
በአለም አቀፍና ያካባቢ ድርጅቶች ውስጥ (ኢጋድ)
ኤርትራ በ2007 ድንገት በቃኝ ብላ ከኢጋድ እንዳልወጣች እና በወቅቱ ይህ እርምጃችሁ ትክክል አይደለምእና አስቡበት
ቢባሉም አሻፈረኝ ብሎ የቆየው የአቶ ኢሳያስ መንግሰት ማንም ሳይጠይቀው ነበር ድንገት ተነስቶ በ2011 መልሶ ለመቀላቀል
ጥያቄ ያቀረው።14
10 https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v (ከሰባተኛው ደቂቃ ጀምረው ያዳምጡ)
11 https://www.middleeastmonitor.com/news/middle-east/18347-saudi-arabia-eritreaagree-
to-boost-red-sea-security http://www.madote.com/2015/04/pictures-eritreanpresident-
visits.html
12 http://ethiomedia.com/100leads/4825.html
13 http://sudantribune.com/spip.php?article54751
14 http://stesfamariam.com/2014/04/10/eritreas-igad-suspension-and-reactivation-decisionssacrosanct-
and-legal/
ይህ ጥረት አቶ ኢሳያስ ቀደም ሲል ያጡትን ቦታ መልሶ ለመያዝ የሚደረገው ሙከራ አንድ አካል ለመሆኑ ምንም ጥርጥር
የለውም።
ከኢትዮጰያ ጋር
ኢትዮጰያን በተመለከተ ኢሳያስ አፈወርቂ አሁን የሚከተሉት አካሄድ
መሰረታዊ መስሎ የሚታያቸውን የድንበር ጉዳይ እሳቸው በሚፈልጉት መንገድ እንዲደመደም ማድረግ
ተቃዋሚውን በማግባባት፣ በመሞት ላይ ካለው የወያኔ ስርአት ጋር ማበር ሳይሆን የመጭው ጊዜ ባለስላጣናት ጋር
መወዳጀት
ከኢትዮጵያዊ ተቃዋሚዎች ጋር በማበር የቆሽሽውን የራሳቸውን ገጽታ ማደስና፣ ተቀባይነት ማግኘት
ጥቂቶቹ ናቸው።
ለኢሳት ሰራተኞች በፌብሯሪ 2015 በኤርትራ ውስጥ የሰጡት እጅግ ረጅም ቃለምልልስ ተቃዋሚውን ለማግባባት ያዘጋጁት
እቅድ አንድ ገጽታ ይመስላል። በዚያ ቃለ ምልልስ ውስጥ አቶ ኢሳያስ፤ የ ኤርትራና ኢትዮጵያን ጉዳይ የተመለከተ ስብሰባ
በያካባቢው መደረግ ያገባዋል “ በማለት የሰነዘሩት ምክር መሰል መመሪያ ፤ በቅርቡ ደግሞ በማይ 9 እና 10 በዋሽንግተን
ዲሲ “ ያፍሪካ ቀንድ ሁኔታን” የመረመረው ስብሰባ ይዘት በከፊልም ቢሆን ከአቶ ኢሳያስንና ከሻአቢያን የተሀድሶ ስትራተጂ
ጋር እጅግ እንደሚጣጣም ይታያል።
አቶ ኢሳያስ በኢሳት ቃለመጠቅ ላይ አበክረው የገለጹት ለኢትዮጵያ አንድነት የቆሙ፣ ለኢትዮጵያ ከመልካም ነገር ውጭ
የሚመኙት ነገር እንደሌለ ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ መብት አለመከበር እንቅልፍ እንደነሳቸው እና እንዲያውም ኢትዮጳያ
መፈራረስ አለበት ተብሎ በተለያዩ መንግስታት ሲሰነዘር እርሳቸው አይሆንም ብለው እንዳስቆሙ ወዘተ ነበር።
ይሀ ሁሉ ግን ኢትዮጰያውያን ለአመታት ከምናውቀው የኢሳያስ አፈወርቂ ንግግሮች እና ተግባር ጋር እጅግ የሚጋጭ ነው።
ሰበብ ፈልገው በኢሳያስ አፈወርቂ ለመጭበርበር በተጠንቀቅ ከሚጠባበቁት ወይም በኢትዮጵያ ኪሳራ ላይ ወዳጅነትን
ለመመስረት ከሚፈልጉት በስተቀር ሁኔታውን በትክክል ለመረዳት ለሚሞክር ሁሉ የአቶ ኢሳያስ አቋም አሁንም ቀድም ሲል
ከነበረበት ቦታ ፈቀቅ እንዳላለ መገንዘብ ያቻላል። ለዚህም በዚያው በኢሳት ቃለምልልስ እና በተለያዩ የዜና አውታሮች
ውስጥ ደግመው ደጋግመው የ ኤርትራና የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ያለቀለት እንደሆነና ኢትዮጵያም “ከወረረችው የኤርትራ
ግዛት መውጣት እንዳለባት መናገራቸውን ማስተዋል በራሱ በቂ መረጃ ነው” ባለፈው አመት (2014) አምባሳደር ግርማ
አሰመሮም ለ ገለልተኛ አገራት ስብሰባ ካደረጉት ንግግር ውስጥ ደግመው ደጋግመው ያሰመሩበትም ይህንዩ ነበር።
http://www.madote.com/2014/05/ambassador-girma-asmeroms-speech-at.html
በመጨረሻም በቅርብ በሜይ 9 እና 10 የተካሄደው የዋሸንግተኑ የሰብአዊ መብት ስብሰባ ጉዳዩ ስለ አፍሪቃ ቀንድ ነው
እየተባለ፣ በመላው አፍሪካ በመብት ረገጣ ያፋሪካዋ ሰሜን ኮርያ (the north Korea of Africa) እየተባለች
የምትታወቀውን ኤርትራ የምታካሂደው ግፍ በጨረፍታ እንኳ አለመናገሩ (አንዳንድ ጠቃሚ የውይይት ዶክመንቶች
መቅረባቸው እንዳለ ሆኖ) ጉባኢውን ከሰብአዊ መብት ጉባኤነት ይልቅ የሻቢያ የህዝብ ግንኙነት መሳሪያ አስመስሎታል። ስለ
ኤርትራ መናገር ካላሰፈለገ፣ ስብሰባውን የምስራቅ አፍሪካ ብሎ አለመሰየም ነበር። የምስራቅ አፍሪካ ከተባለ በሁዋላ
ዋናዋን ሰብአዊ መብት ረጋጭ አለመተቸት ግን እጅግ አሰተዛዛቢ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያውያንን እና ያርትራ ወገኖቻችንንም
ቁስል አለመረዳት ነው።
የዚህ አይነቱ አያያዝ ደግሞ ለኤርትራም ሆነ ለቀሪው ኢትዮጵያ ህዝብ የሚሰጠው ጠቀሜታ የለውም። የአቶ ኢሳያስ ዘግናኛ
አገዛዝ እንኳንስ የኤርትራ ነዋሪዎች አለም አቀፉ ህብረተሰብም በያደባባዩ የሚናገረው እና አበክሮ የሚታገለውም ነው።
ቢያንስ ቢያንስ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ዋቢ እየጠቀስን የምንሟገትባቸው ድርጅቶች ማለትም ሂውማን ራይትስ ዋች፣15
አምንስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎቹም ስለ አቶ ኢሳያስ አገዛዝ እና የኤርትራ ነዋሪዎች ሰቆቃ የዘገቡትን በጥቂቱ ማየት በቂ
ግንዛቤን ይሰጣል።
የህዝቡን ትግልም ሆነ ነጻነት ማንም ሀይል አያግደውም። የሌላው መብት ሲረገጥ የሁሉም መብት እንደተረገጠ ማሰታወስ
ለሁሉም ተገቢ ነው። ሰለኤርትራ ነዋሪዎች መብት መረገጥ እኔ ምን አገባኝ የሚል ሰው ደግሞ፣ የኔ መብት ስለተረገጠ
ለመብቴ በማደርገው ትግል ሌሎች እርዳታ ይስጡኝ ብሎ መጠየቁ መሰረት የሌለው ነው16
15 http://www.hrw.org/world-report/2014/country-chapters/Eritrea
16 https://www.youtube.com/watch?feature=player_detailpage&v=e2rP5alopBE
በመጨረሻም የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ ብዙ እጅግ ብዙ የሚያነጋግሩ ጉዳዮች እንዳሉ መረዳት ተገቢ ነው፡ ይህን
ለመረዳት ደግሞ በሀገር ቤት የሚነቃነቁ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲወች (አድርባይ የሚባሉት ሳይቀሩ) የሚሉትን ማዳመጥ
በቂ ነው። በዚህ ውስጥ ያልተዘጋውን የሀገራችንን አጀንዳ ወደጎን ከማለት አልፎ ለአቶ ኢሳያስና ለመንግስታቸው
ፕሮፓጋንዳ፤ የህዝብ ግንኙነትና አገዛዙን የማጠናከር ስራ ተባባሪ መሆን ግን ሀላፊነት የጎደለው ብቻ ሳይሆን መስመር
ማለፍም ጭምር ይሆናል።
ማጠቃለያ
የአቶ ኢሳያስ ያለፉት ጥቂት አመታት የተሀድሶ እንቅስቃሴ አገዛዛቸውን ከደረሰበት የውስጥም የውጭም መገለል እና
የፖለቲካ ግፊት፣ አላቅቆ እንደገና ለማንሰራራት የሚደረገው ጥረት አካል ነው።
አለም አቀፍ ሁኔታው ያመቸኛል ባሉት መንገድ አቶ ኢሳያስ ራሳቸውን እንደገና አጠናክረው እየተንገዳገደ ያለው አገዛዛቸውን
መልሰው ለማጥናከር፣ ኢትዮጵያን በተመለከተ ደግሞ ነባር አቋማቸውን ለማስፈጸም ያልተዘጉና በእንጥልጥል የሚገኙ
አጀንዳወችንም በአለም አቀፍ ግፊትና በተባባሪ ኢትዮጵያውያን ለማስፈጸም ሁኔታውን አያመቻቹ ይገኛል።
አንድ የአለም አቀፍ ሁኔታዎችን የሚተነትን ጸሀፊ የዩክሬን ነጻነት ከየትኛውም ሀያል መንግስት በላይ በደካማዋና ትንሿ
ቡልጋሪያ መዳፍ ስር ሊሆን እንደሚችል ገልጦ ነበር። ይህን ያለውም፣ ራሽያ የኢኮኖሚዋ መሰረት የሆነው የነዳጅ ምርቷን
ወደውጭ ለማስተላለፍ እየሰራችው ያለችው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ በቡልጋርያ በኩል ስለሆነ ደካማዋ ቡላጋሪያ
የቧኒቧውን ስራ አልደግፍም ብትልና ብታቋርጠው ምን ያህል ታላቋን ራሽያን ለማሽመድመድ እንደምትቸል ለማሳየት
ነበር።
የእኛም የነጻነት ትግላችንና ሀገራዊ ነጻነታችን በመሞት ላይ ለሚገኝ ጨካኝ ጸረ ኢትዮጵያ ሀይል ማንሰራሪያ ብቻ
ሳይሆን በዚሁ ቡድን መዳፍ ስር በድጋሜ እንዳይወድቅ በጥንቃቄ ማሰተዋል ይገባል። ለዚህም በሬ ሆይ ሳሩን አይተህ
ገደሉን ሳታይ የሚለውን የአበውን ብሂል እናሰታውስ። ጎበዝ ነገሩ ሁሉ እየተስተዋለ ቢሆን መልካም ነው።
አስተያየት ethioandenet@bell.net
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
May 24, 2015
No comments:
Post a Comment