አስራትን የካዱ ድረገፆች፤ “በግ” እና “አህያው” አበሻ!
ጌታቸው ረዳ (Editor Ethiopian Semay)
ባለፈው ሰሞን “ተቃዋሚ ሚዲያዎች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የቆሙ ናቸው? እሳቶቹ ፋሲል የኔአለም እና የደረጀ ሃብተወልድ ምስጢር” በሚል ያቀረብኩት ሳምንታዊ ትችት ንኡስ ከበርቴ/ ምሁራን በሚሳተፉበት EEDN (Ethiopian Electronic DistributionNetwork) እና በመሳሰሉት መድረኮች መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱን በአንዳንድ ወዳጆቼ በደረሱኝ መረጃዎች አውቅያለሁ። በዚህ አጋጣሚ በርከት ያሉ ደብዳቤዎች/ቴክስቶች እና ስልክ ጥሪ በማድረግ ያበረታታችሁኝ ወገኖቼ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
ድንገት ሳልመልስላችሁ የቀረሁ ወገኖች ካላችሁ በደብዳቤ ብዛት እና ባንዳንድ ጫናዎች የተነሳ ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ይቅርታ እጠይቃለሁ። ባጋጣሚ ሞረሽ ወገኔ ፓልቶክ ከዶ/ር አበባ እና ዶ/ር ተስፋዬ ደምመላሽ ጋር የፕሮፌሰር አስራት የሙት መታሰቢያ ቀን ለማክበር፤ በእንግዳነት ተጋብዤ፤ ከአቅሜ በላይ በሆነ ምክንያት ለመገኘት ባለመቻሌ “ምነው ደህና ነህ?” ብለው ለጠየቁኝና የኔን ሃሳብ ለማድመጥ የመጣችሁ ወገኖቼ ሁሉ ባለመገኘቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
2
በዛው ርዕስ በሚቀጥለው ሰሞን ወይንም በጥቂት ቀናት እለጥፈዋለሁ። ለዛሬ ግን ልንነጋገርበት የምፈልገው አብይ ጉዳይ አለ። ፕሮፌሰር አስራት “አንፀባራቂው ኰከብ” በሚል ስያሜ ባንጋፋ ምጽሄቶች ላይ ሲሰየሙ የነበሩት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ህይወታቸው የሰውት የቀዶ ጥገና ሐኪም የነበሩት ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ በአገርም ሆነ በውስጥ አገር በሚገኙ ድረገፆች ካለ Ethiopatriots.com, welkait.com, http://www.moreshwegenie.org/ ድረገጽ በቀር አንድም የድረገጽ አዘጋጅም ሆነ ጸሃፊዎች ለመታሰቢያቸው የለጠፉት ነገር ባለመኖሩ እጅግ ያሳዝናል። ልጆቻቸውም (ውጭ አገር የሚኖሩ ካልዋቸው) ለምን ቅሬታቸው እንዳላሰሙ ለኔም አግርሞኛል። ልጆቻቸው በአባታቸው ፈለግ እየተከተሉ ነው? የሚለው በዚህ ላይ ሌላ ቀን እመለስበታለሁ ይሆናል።
እስኪ በአቶ አምሃ አስፋው ግጥም ልጀምር፡
በጎች ይግጣሉ ከሜዳ
ነገ ፋሲካ መሆኑን እረስተው
እህዮችም እንዲሁ
ቁስላቸውን ለዝንብ አጋልጠው!
ከላይ ያለው ግጥም የተቀነጨበው ከላይ ከፎቶግራፉ ላይ ከሚነበበው ኢትዮጵያን ረጅስተር መጽሄት ለአስራት ማስታወሻ የተጻፈ ነው።
ተቀወሚው ድረገጽ ቡድንተኛ እና ሚዛን የማይጠብቅ መሆኑን የሚያያከራክር አይደለም።ቡድንተኛ መሆኑን የሚጠበቅ ቢሆንም፤ ሚዛን ያጣ ሲሆን ‘አክራሪ” ይሆናል ማለት ነው። ይህ ቡድንተኛነት ያጠቃው በፖለቲካ ሰዎች የሚመራ የተቃዋሚ ድረገጾች እና ጋዜጠኞች (ነን ባዮች) ክስተት ደግሞ በተቃዋሚ ድረገጾች የተለመደው ጸረ አማራነት፤ጸረ ኢትዮጵያ፤ጸረ አርበኛነት ባሕሪው እየባሰበት መምጣቱ አስገራሚ ነው።
አገር ወዳዶችን ለሕዝብ እንዳይታዩ፤እንዳይደመጡ፤እንዳይታወቁ፤ትግላቸው እንዲታፈን ማድረግ ባሕሪያቸው መሆኑን ደጋግሜ ገልጫለሁ። እነዚህ ተቃዋሚ ነን ባይ ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎቻቸው ለሕዝብ የተሰው ሰማዕታት ብለው
3
የሚያስቡዋቸው ግለሰቦች አሉዋቸው። እነሱም እንደ በኬጂቢ ስለላ መንገድ የተካነው ሻዕቢያ፤ አስመራ ውስጥ ሻዕቢያ ለስለላ ካሰማራቸው
(ሻዕቢያ የደርግ ጀኔራሎችን ሳይቀሩ በሰላይ ሴቶች ምስጢር ያስለፈለፈ እና ያስገደለ መሆኑን የምታውቁ ይመስለኛል። ወያኔዎችም ሰላይ ሴቶች እንደተጠቀመ የሚታወስ ነው። ለምሰሌ ትግራይ ውስጥ የሕዝብ ድርጅት ሃላፊ የነበረው በሗላ በደርግ አዲስ አበባ የተረሸነው የመቶአለቃ ደስታ ታደሰን ታሪክ ልብ ይለዋል።)
ለእነ አንዳርጋቸው ፅጌ በተስፋዬ ገብረአብ በኩል የተጠመደለትን ከእነ ሰሚራ የመሳሰሉት የሻዕቢያ ኮረዳ ልጃገረዶች ጋር ሲቀብጥ ከነበረውና ለነብሰገዳዩ ለፋሺስት ኢሳያስ አፈወርቂ አፈቀላጤነት ሲቆም ለነበረው ለእንደ እነ አንዳርጋቸው ጽጌ የመሳሰሉትን “በማንዴላነት” እየሰየሙ በኢትዮጵያ ሰንደቃላማ መሃል ፎቶግራፉን እየለጠፉ፤ ግጥም እየለቀቁ፤ አሁንም በድረገጾቻቸው አምድ ለጥፈው ከላይ እያስዋቡ ሲያሸበርቁዋቸው፤ ለማንም ፋሺሰት ወገባቸው ላለጠፉ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ አርማ የሆኑትን አስራትን ግን እንኳን እንደ ባንዳው ከሃዲ አንዳርጋቸው ጽጌ በድረገጻቸው ሊያስውቧቸው ቀርቶ አንዲት የመዘክር መስመር አንኳ ነፍገዋቸዋል።
ይህ ክስተት ብቻ አይደለም በዚህ ሁለት ሰሞን የታየው። ለምሳሌ The Monitor የሚባል ጋዜጣ የዘገበውና EEDN ላይ የተለጠፈው ኢትዮጵያ ውስጥ ክርስትያኖች በጽንፈኛ እስላሞችና የወያኔ ወከሎች በኢትዮጵያ ክረስትያኖች ሰሞኑን እየተፈጸመ ያለው ግድያ እና የውጡ መፈናቀል፤ ድረገፆች ትኩረት ሰጥተው እንደሊቢያው አልዘገቡትም አልተረባረቡበትም። አልደረሳቸውም አንዳይባል እንኳ ኢ ኢ ዲ ኤን ውስጥ የድረገጽ አዘጋጆች እንደማይጠፉ የታወቀ ነው። እዛው አስተላልፉት ብሎ ሳኖዜ ካሊፎረኒያ የሚኖሮው ወዳጄ አቶ ግርማ በቀለ አስተላልፎላቸዋል። ለምን አላስተጋቡትም?
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክስርስትያን በሆዲ እና ከስልጤ ሐገረስብከት የተላለፈ የድረሱልን ጥሪ “እስላማዊ ጽንፈኞች” በየቤታቸው እየዞሩ ሃይላንድ ቤንዚን በማርከፍከፍ ቤቶቻቸውን በማቃጠል፤ ወደ አገራችሁ ሂዱ እያሉ በመስደብና
4
በመገፍተር የእስላመዊ ጽንፈኛው ግፍ በክርስትያኑ ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው በማለት “ሞኒትር’ እንዲህ ሲል ዘግቦታል።
“አዘርነት በርበሬ ወረዳ ክርስትያኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፡ ሓላፊነት በማይሰማቸው ጽንፈኛ ባለሥልጣናት በደል “ወረዳው ሊቢያ ሆኖብናል፤ለእኛም አልቅሱልን” እያሉ ነው። (By Monitor Ethiopian News) ይላል።
ክርስትያኖች ኢትዮጵያ አገራቸው ውስጥም “ሊቢያ ሆኖብናል” በማለት የድረሱልን ጥሪ ሲያደርጉ፤ ሚዲያዎች በሊቢያ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ሲያተኩሩ፤ አገራቸው ውስጥ ግን በአማራው እና በክሰርስትያኑ ላይ ምን ጥቃት እየተፈጸመ እንዳለ አላወቁም/ ወይንም ሆን ብለው ቸል ብለውታል (የዘገቡት ካሉም በስፋት አልተዘገበም) ለምን? የክርስትያኖቹ ሰቆቃ እና የድረሱልን ኡኡታ ቁጥር ቁ/ጉ/ቅ/ማ/42/07 ቀን 02/09/07 ይላል። ተቃዋሚው ድረገጽ ብቻ ሳይሆን፤ ውጭ አገር ያለው የክርስያኖች ሲኖዶስም ሕዝቡን አስተባብሮ በወያኔ አምባሲ ላይ ሰላማዊ ሰልፍ አድርጎ ክርሰትያኖች በገዛ አገራቸው በወያኔ ስርዓት ምንም ዓይነት ከለላ ሳይደረግላቸው ለጥቃት እየተጋለጡ መሆናቸውን ለዓለም መንግሥታት እና ለዓለም ቤተክርስትያናት እንዲያውቁት ማድረግ ይገባቸው ነበር።ግን አላደረጉም። ለምን?
እነኚህ አባቶች ሚዲያዎች እና ፖለቲከኞቹ በሰለማዊው ሰልፍ እንዲያግዟቸው አያውቁዋቸውም እንዳይባል አንዳንድ ካሕናት አባቶች ከሻዕቢያ ቅጥረኞች ከግንቦትና ከኢሳት አፈቀላጤዎች ጋር በየቦታው እየዞሩ ፖለቲካውን ሲያኝኩ ሲያላምጡ ሲያደምጡ እና ሲሳተፉ አይተናቸዋል። ታዲያ በራሳቸው አባሎች ግፍ ሲደርስ ምን ዋጣቸው?
ውጭ ያለው የእስላምና ተጋዮች/ ድምፃችን ይሰማ አጋር ማሕበር “ሸንጎ” ከተባለው የፖለቲካ ማሕበር ሲቀናጅ፤ክርስትያን ማሕበራት የምትቀናጁበት ባይኖራችሁም፤ ምዕመናኖቻችሁን በያገሩ ያሉ ምዕመናኖች አሰባስባስባችሁ ዓለም እንዲያውቀው ማድረግ በተገባችሁ ነበር።ለዚህ ነው አስራት ወልደየስ የሚታወሰው። አስራትን ከገደሉት በሗላ፤ ግድያው ቀጠለ። ጥቃቱን የሚያቆመው መሪ፤ ሃይልና ድምፅ ጠፋ። ተቃዋሚ አማራ ምሁር ተብየውም፤ ወያኔዎች ጋር ከሚሞዳሞዱት “ሆዳም
5
አማራዎች” አልተሻለም። አማራን አደራጅቶ ከጥቃት መከላከል ማለት “ጐሰኝነት ነው” እያለ ወደ “በግነት” እና “አህያነት” እየተለወጠ ነው።
ተቃዋሚውም ቢሆን ትኩረቱ የጦዘው፤ ለተቃዋሚው ዝገባ የሚቀናው “የዞን 9 ጦማሪያን”፤ “ለእስልምና የሚታገሉ የድምፃችን ይሰማ ታሳሪዎች” እና “ የኢሳያስ ወዳጅ አንዳርጋቸው ጽጌ” ብቻ ናቸው። በየ ዕለቱ የሚዘገበው ዘገባ ቢያንስ በቀን አንዳንዴ ሁለት ጊዜ ይዘገብላቸዋል። ለነሱ አገር ወዳዶች እና አርበኞቻቸው እነኚህ ብቻ ናቸው። የነዚህ ታሳሪዎች ፎቶግራፎቻቸው በድረገጾቻቸው ብቻ ሳይሆን በፓልቶክ ክፍሎችም ተለጥፎ በሕዝብ እንዲታወሱ ተደርጓል። አማራና ክርስትያን ወይንም አስራትን የሚያክል ዓለም ያስገረመ ታላቁ ጉሬዛ እና ታጋይ ከነዚህ ዞን 9 ተብለው ከሚታወቁ ‘ጦማሪዎች” እና እስላም ታጋዮች ወይንም ከተስፋዬ ገብረአብ ሁነኛ ወዳጅ ከአንዳርጋቸው ጽጌ እንዴት ሲያንሱ ነው ላንድ ቀን እንኳ ክብር የተነፈጉት? እስኪ ምሁራን ተወያዩበት (የሚያመዛዝን ትንሽ የቀረች ሕሊና ከቀረቻችሁ ማለቴ ነው)።
አስታውሱ ለማንም እስረኛ በኢትዮጵያ ታሪክ (በወያኔ ጊዜ!!!) ተደርጎ የማያውቅ አንዳርጋቸው ጽጌ ሚስቱን እና ልጆቹን ከአዲስ አበባ እስር ቤት ለንደን ድረስ በስልክ እንዲያነጋገር ሲፈቀድለት፤ አስራት ወልደየስ፤ በዝግ ክፍል በጨለማ ታስረው ብርሃን በማጣታቸው የዓይናቸው ብርሃን (ረቲና) ተጋርዶ ማየት አቅቷቸው ‘ታውረው” እንደነበር የሚታወስ ነው። እንዲህ ላለው ጀግና የሙት ቀን ማስታወሻ መዘገብ አቅቷቸው ዓለም ስለጣመቻቸው ስለ ሰረገኞች ዜና ሲዘግቡ ይውላሉ። ስለሆነም ነው አቶ አምሃ አስፋው፤ የፕሮፌሰር እስራትን ስቃይ ያልተሰማው “የበጉ እና የአህያው አበሻ” ዝምታ በመገረማቸው ነው “የእስረቤቱን መስኮት ተጠግተው አበሻን አዩ በመስኮት….”፡ ብለው ግጥም የገጠሙት። አበሻው ምንኛ ወደ በግነት እና አህያነት ባሕሪ መለወጡ ሲገልጹ ነው ። ‘ብቅ ብለው በመስኮቱ በጉ እና አህያውን አበሻን በአግራሞት አዩ’ የሚሏቸው ታዛቢው ፕሮፌሰሩ በጠባብ እስር ቤት ታስረው በነበሩበት ወቅት ማለታቸው ነው።
እርግጠኛ ነኝ በሐኪም አስራት ከዚህ ዓለም መሰወር የተደሰቱት ወያኔዎች እና ኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ ባዩ ወንጀለኛው “ኦነግ” እና በምስራቅ/በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢ በድርጅት ተሰግስገው የሚገኙ የተንሰራፉት እስላማዊ ጽንፈኞች ብቻ መሆናቸውን በእርግጠኛነት መናገር እችላለሁ። ተቃዋሚ ነኝ ባይ ጸሐፊዎች እና
6
ድረገጾች ግን ‘በሞታቸው’ ቢያዝኑም፤ ማዘን ብቻ በቂ ነው ወይ? አርበኞች፤አገር ወዳዶች ከሕዝቡ ትውስታ ለምን እንዲሰውሩ ይፈለጋል? ሌላ ቢቀር በአመት አንድ ጊዜ ማስታወስ ለምን ተሳናቸው? የምርጫ ጊዜ ነው አንኳ እንዳይባል፤ ምርጫው ከልቦናችን የፋቅነው በመሆኑ ከማንም ልቦና ትኩረት በፍጥነት የበነነ ጤዛ ስለሆነ ጊዜ አይሻማም።
ቢሆንስ አስራትን ከማንም “ኤቨንት/ከሳቴ” ቅድሚያ ቢገባው እንጂ እንዴት ሊረሳ ይችላል? ዓድዋና የካቲት 12 እንዲሁም ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ስንዘክር አስራትን በየዓመቱ መዘከር ተመሳሳይነት አለው።
ለፋሺስቶች ግምባር ሰጥቶ በፋሺስት ፓርላማ ወገብን ቀጥ አደርጎ መከራከር ምንኛ አኩሪ አርበኛነት መሆኑን እንዴት ረሳችሁት? በግ እና አህያው መቃወም ፈርቶ አንድ ብቸኛው ድምፅ በፋሺስቶች አዳራሽ ያስተጋባው ጀግና ማን ነበር? ኢትዮጵያ በጎሳ አትሸነሸንም፤ አትበታተንም፤ብሔራዊ ሰንደቃለማችን በናንተ ምላስ ስትዋረድ ዝም አልልም ብለው የተከራከሩት ማን ናቸው? ሆዳሞች ንገሩን እንጂ! በተለይ አሁን የምናገረው ሆዳም አማራ ጋዜጠኞችን ፤ድረገፅ አዘጋጆችን፤ምሁራኖች፤ አማራ ዘፋኞች ፤ አማራ ቀልድ ነጋሪዎች /ኮመዲያኖች አማራ ጸሐፊዎችን ነው። ሆዳም አማራ ብለው ስለሰደብዋችሁ ነው? ወይስ ምን ምክንያት አላችሁ ለዝምታችሁ? ንገሩን እንጂ?
ይህ እንደ ጣሊያን 44 ባንዴራ ተሰፍቶለት እንዲአውለበልብ፤ ትርጉም የታጣለት ትርጉመቢስ የሕዘብ አጣራር “ብሔር ፤ብሔረሰብ፤ ሕዘቦች” እያለ ኢትዮጵያን እንዲጠራ ለ24 አመት በወያኔ ፕሮፓጋንዳ የተወለወለው ምስኪኑ አዲሱ ትውልድ ኢትዮጵያን ያስረኩበት አርበኞቻችን እንዴት ይወቃቸው? ማንስ ይዘግብላቸው? ለመሆኑ አዲስ ትውልድ ታየ ወልድሰማያትን አስራትን መኮንን ዶሪን፤የኢህአፓው መሪ ጸጋዬ ገብረመድህንን….ያውቃቸዋል? ሚዲያ ስራው ምንድ ነው? ናጄሪያዊ አገረገዥ ኢትዮጵያዊቷን አገባ፤ ቁርጥ ስጋ መብላት ካቆምኩኝ በሗላ ‘ቦርጭ” ቀነስኩ” (ዘ-ሓበሻ)፤ ቢቢኪንግ ሞተ (ኢትዮ-ሚዲያ) ……እያሉ ሲዘግቡ ለሚሊዮኖች ድምፅ ቆሞ አንድ ኢትዮጵያ፤ አንድ ሰንደቅዓላማ ለአንድ ሕዝብ “ኢትዮጵያ” ቤዛ ለሆነው ሐኪም አስራት እንዴት ከአዘጋጂዎቹ አንዲት ዘለላ ዓረፍተነገር ለማስታወሻ ተነፈገው?
7
ለመሆኑ የዞን 9 እና የነ አንዳርጋቸው አስታዋሾች እነ ፕሮፌሰር አል ማርያም የት ገቡ? አል ማርያም ወደ ፖለቲካው ዘው ብሎ የገባው ከምርጫ 97 በሗላ መሆኑን እናውቃለን። አስራት ሲታገል ጊዜ ባለመኖሩ አንይያዝለትም ፤ ነገር ግን ምሁር አንደመሆኑ መጠን “አስራትን” የሚያክል ዝሆን የአል ማርያም ዓይን ይስተዋል ብዬ አልጠረጥርም። ታዲያ ምነዋ ስለ አስራት የሙት ቀን በዓል መዘከር ለገመ? የምሁራኖቹ ሕሊና ምን ዓይነት ብል እየበላው ይሆን እስከዚህ ድረስ ታላለቅ ዝሆን የሚያክሉ አርበኞች ከብዕሮቻቸው ትውስታ የሚሰወሩት? ስቀጥል አንጀቴ ስለሚያር፤ እዚህ ላቁም። በዚህ አጋጣሚ አርበኛዋ፤ተከራክራ የማሸነፍ ችሎታዋ የላቀ፤አንደበተ ርቱዕዋ ደ/ር አበባ ፈቃደን እና ደ/ር ተስፋዬ ደምመላሽ፤ እና የሞረሽ ፓልቶክ አዘጋጆች “ፈለገ አስራት” እና እህቴ “ቃጠሎ” በዚህ አጋጣሚ አመሰግናቸዋለሁ። በማዘጋጀው ሐተታ እና ክርክር፤ በደብዳቤና በስልክ ለምታበረታቱኝ ሁሉ እንዲሁ አመሰግናችሗለሁ፡ የአስራት ፈለግ እንከተል። አመሰግናለሁ:: ለወጣቱ ትውልድ፤ ፕሮፌሰር አስራት ማንነት ለማወቅ ይህንን ተጭናችሁ አርአያነታቸውን እሰሙ።Professor Asrat vs Meles and Isayas July 1991- peace and Democracy conference in Addis Abeba https://www.youtube.com/watch?v=-SikAw7Djk8 The funeral service of the late Professor Asrat Woldeyes https://www.youtube.com/watch?v=ay7fAK8fXew Professor Getatachew Haile remembered long time friend Dr Asrat https://www.youtube.com/watch?v=2q7MRDQqCWk አመሰግናለሁ።ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማየ አዘጋጅ) getachre@aol.com
No comments:
Post a Comment