Wednesday, December 3, 2014

ከ5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ?

የትግሬ-ወያኔ ለ17 ዓመታት በሽፍትነት፣ ለ23 ዓመታት ደግሞ በገዢነት ተፈናጦ በዐማራ ሕዝብ ባደረሰው የዘር ማጽዳት
እና የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምን ያህል ንፁሃን ዐማሮች እንደተጨፈጨፉ የተለያዩ አስተያዬቶች ሲደመጡ ቆይተዋል። ሞረሽ ወገኔ
ባደረገው ዝርዝር የሕዝብ ብዛት ቆጠራ ትንተና መሠረት ከ1983 ዓ.ም. ወዲህ ደብዛቸው ከምድረ-ገፅ እንዲጠፉ የተደረጉት ዐማሮች ብዛት ከ5 ሚሊዮን እንደማያንስ ይጠቁማል። ይህ ምንን ያመለክታል? ከጥናቱ ውጤት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ጎልተው ይወጣሉ።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው አገር አቀፍ ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ የተካሄደው በ1976 ዓ.ም. ነበር። በወቅቱ ኤርትራን እና
የአሰብ አስተዳደርን ጨምሮ ጠቅላላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት 42,616,876 ያህል ነበር። በኤርትራ እና በአሰብ አስተዳደር ኗሪ
የነበሩት ዜጎች ቁጥር ሲቀነስ በቀሪዋ ኢትዮጵያ ይኖር የነበረው ሕዝብ ብዛት 39,868,572 ይሆናል። በወቅቱ በሕዝብ ብዛት አንደኛ የነበረው የኦሮሞ ነገድ ብዛቱም 12,387,664 ሲሆን፤ እንዲሁም ዐማራ በሁለተኛ ደረጃ 12,055,250 ያህል ተወላጆች ነበሯቸው።

ስለሆነም በወቅቱ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች ብዛት መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት 332,414 ይሆናል ማለት ነው። የመጀመሪያው
የሕዝብ ቆጠራ ከተደረገ ከ23 ዓመታት በኋላ፣ ማለትም በ1999 ዓ.ም. በተደረገው ሦሥተኛው የሕዝብ ቆጠራ ውጤት መሠረት
ዐማራው ቁጥሩ በአዝጋሚ ሁኔታ ወደ 19,867,817 ሲጨምር የኦሮሞዎቹ ብዛት ግን ከእጥፍ በላይ አድጎ ወደ 25,488,344
ደርሷል። ስለዚህ በኦሮሞ እና ዐማራ ተወላጆች ብዛት መካከል ያለው የቁጥር ልዩነት 5,620,527 አሻቅቧል ማለት ነው። በዐማራው እና በኦሮሞው መካከል የነበረው የቁጥር ልዩነት ተመጣጣኝነት እንዳለ እንደተጠበቀ ይቀጥል ቢባል እንኳን ከ23 ዓመታት በኋላ ሊኖር የሚችለው ልዩነት ከ664,828 አይበልጥም። በመሆኑም ከ5ሚሊዮን የማያንሰውን ዐማራ ዬት እንዳደረሱት የሚያውቁት የትግሬ- ወያኔዎች እና ሎሌዎቻቸው ናቸው።
ባለፉት 23 ዓመታት ከ4,751,333 በላይ የዐማራ ነገድ ተወላጅ የጠፋው ወያኔ ገና የትጥቅ ትግል ሲጀምር «የትግራይ ሕዝብ
ደመኛ ጠላት ዐማራ ነው፤» « ዐማራን፣ የአማርኛ ቋንቋን እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን ማጥፋት አለብን!» ብለው የተሰለፉ
በመሆናቸው የዐማራውን ነገድ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በመግደላቸው ነው። በግልፅ እንደሚታወቀው ወያኔ የዐማራውን ነገድ
በሚከተሉት ሥልቶች አጥፍቷል። እያጠፋም ነው፥
 በተለያዩ ሰበቦች በጅምላ በመግደል፦ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በሠቲት፣ በአርማጭሆ፣ በራያ ሕዝብ ላይ
የፈፀሙት የግፍ ግድያ፣
 በአሰቦት ገዳም፣ በአርባ ጉጉ፣ በወተር፣ በበደኖ በሌሎችም የሐረርጌ እና አርሲ አካባቢዎች ይኖሩ በነበሩ ዐማሮች ላይ
የፈፀሙት የግፍ ጭፍጨፋ፤
 በወለጋ፣ በኢሉባቡር፣ በጅማ ያካሄዷቸው ዐማራን በጅምላ የመግደል ዘመቻዎች፤
 ከ1983 -1987 ዓ.ም. ድረስ በሕወሓት ሠራዊት አማካይነት በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃም እና በጎንደር ኗሪ በሆኑ ዐማሮች ላይ
የ«ሽፍታ ምንጠራ» እና «ብረት ማስፈታት» የሚሉ የሽፋን ዘመቻዎች በማካሄድ በፈፀሟቸው ጭፍጨፋዎች፤
 ዐማራውን በተለያዩ ተፅዕኖዎች በማስፈራራት ዐማራነቱን ክዶ የሌላ የነገድ ማንነት እንዲቀበል በማስገደዳቸው፤
ከ5 ሚሊዮን የማያንሰው ዐማራ ዬት ደረሰ?
2
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ረቡዕ ኅዳር ፳፬ ቀን ፪ሺህ፯ ዓ.ም. ቅፅ ፫ ፣ ቁጥር ፮
 ዐማራውን እየለዩ ከሥራ በማባረር በርሃብ በመጨረሳቸው፤
 «የመሬት ድልድል» በሚሉት እና ዐማራን «መሬት አልባ የትግሬ-ወያኔ ጭሰኛ» ለማድረግ በቀየሱት ፖሊሲ ዐማራው ከሁሉም ኢትዮጵያዊ ተለይቶ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል አርሶ እና ሠርቶ እንዳይኖር በማድረጋቸው፤
 ነባሩን የወባ መከላከያ ድርጅት ዘግቶ ድርጅቱን ወደ ትግራይ በማዛወር የዐማራውን ነገድ ተወላጆች የወባ መከላካያ አገልግሎት በማሳጣት አያሌ ዜጎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፣ በተለይም በጎጃም ሕዝብ ላይ ከ1985-1989 ዓ.ም. ያደረሱት እልቂት በምሣሌነት ይጠቀሣል፤
 የዐማራውን ነገድ ተወላጆች በዘር ጠላትነት ፈርጀው የኤች.አይ.ቪ./ኤድስ ቫይረስን በመርፌ በማስተላለፍ በገፍ እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
 የዐማራውን ተወላጆች መሠረታዊ የጤና አገልግሎት በመንፈግ በተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች እንዲያልቁ በማድረጋቸው፤
 በወሊድ ቁጥጥር ስም የነገዱን አባሎች መካንና ታማሚ በማድረጋቸው፤
 ከዐማራ የጸዱ ክልሎችን ለመፍጠር በተያያዙት የዘር ማፅዳት ዘመቻ «ኦሮሚያ፣ ደቡብ ብሔር-ብሔረሰቦች፣ ቤንሻንጉል-ጉምዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር እና ሶማሌ» ብለው በከለሏቸው «ባንቱስታን-መሠል» ግዛቶች ይኖሩ የነበሩት ዐማሮችን በግፍ እና በገፍ በማባረር፣ በመግደልና በመደብደብ ለተደራራቢ ችግሮች በማጋለጣቸው፤
ለዐማራው ነገድ ቁጥር መቀነስ ዋና እና ተያያዥ ምክንያቶች ናቸው። ስለሆነም ያለምንም ማወላወል የዐማራው ነገድ በትግሬ-ወያኔ በተከፈተበት የማያባራ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ሰለባ መሆኑን ትውልዱ ሊገነዘበው ይገባል።
በተለይ ለዐማራው ነገድ ተወላጆች እና ለሃቀኛ ኢትዮጵያውያን የቀረበ ጥሪ፦
ይህን መረጃ በማባዛት ለዓለም ሕዝብ ባሉት የመገናኛ መሣሪያዎች በመጠቀም በማሰራጨት፣ ሆን ተብሎ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለተፈጸመበት የዐማራ ነገድ ድምፅ ልንሆን ይገባል። ለተበደሉ እና የመኖር ሰብአዊ መብት ለተነፈጋቸው ሰብአዊ ፍጡሮች ድምፅ መሆን ዘረኝነት ወይም ጠባብነት አይደለም። በመሆኑም የዐማራው ተወላጆች ብቻ ሣይሆኑ፤ ለሰብአዊነት የቆሙ ሁሉ ለዚህ ነገድ ድምፅ ከመሆን አልፈው፣ በኢትዮጵያውያን ላይ ይህን ዓይነት የከፋ ወንጀል የሚፈፅሙትን ለፍትኅ አደባባይ ለማቅረብ ለተያያዝነው ትግል፥ የመረጃ፣ የምክር፣ የዕውቀት እና የገንዘብ ልገሣ እንድታደርጉልን በዚህ አጋጣሚ ጥሪያችን እናቀርባለን።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ አሥራት የትውልዳችን ቃል ኪዳን ነው!
የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ዳግም ትንሣዔ በቆራጥ ልጆቿ ተጋድሎ ዕውን ይሆናል!


ፕ/ር መስፍን " ከባለቤቱ ያወቀ ምንትስ ነው" ሲባል አልሰሙ ይሆን?

ሠሞኑን በአማራ ተወላጆች ዙሪያ ብዙ እየተባለ ነው። አማራ አለ፣የለም እና የመሳሰሉት። እኔም በግሌ የሚሰማኅኝን ለማለት ካሰብኩ የሰነባበትኩ ቢሆንም እስከአሁን የቆየሁት በዚሁ አወዛርጋቢ በሆነው የአማራ ጉዳይ በዋናነት የሚጠቀሱት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም እኔ ወደምኖርበት ምእራብ አውስትራሊያ ፐርዝ እንደሚመጡ በመስማቴ እና ስለሁኔታው በይበልጥ ለመረዳት ከዚህ የበለጠም አጋጣሚም ሥላልነበረ ነው። ወደዝርዝሩ ከመግባቴ በፊት ግን አንባቢያን ሁለት ነገሮችን እንዲገነዘቡልኝ በልዑል እግዚአብሔር ስም እጠይቃለሁ። ይሄውም አንደኛ እውነታውን ውድ ኢትዮጵያውያን እንዲያውቁት ከሚል ቀና መንፈስ እንጅ እኔ አንድ ተራ ሰው የእሳቸውን አመለካከትም ሆነ ንግግር የመተቸት ብቃቱም ሆነ ፍላግጎቱ የሌለንኝ መሆኑን ሲሆን ሌላው ደግሞ ከዚህ በታች እሳቸው እንደተናገሩት አድርጌ የምጠቅሰው ነገር ተራ የአሉባልታ ወሬ ሳይሆን ለታሪክም በሚል በድምጽ ተቀድቶ የሚገኝ መሆኑን ነው።

1፦ቀደም ብለው ከተናገሩት በመነሳት ለምን በደፈናው ኢትዮጽያውያን በብዛት እና በግዳጅ ከኖሩበት አካባቢ ይፈናቀላሉ ይላሉ?የዘር ግንዳቸው እየተጠና የሚፈናቀሉት አብዛኛዎቹ አማራዎች ናቸው።ስለሆነም የኢትዮጵያ ምሁራን እውነታውን የመጋፈጥ ድፍረቱ ሊኖራችሁ ይገባል የሚል መንፈስ ያዘለ ጥያቄ ከአንድ የስብሰባው ታዳሚ ሲጠየቁ፦ "በኢትዮጵያ ውስጥአማራውም፣ኦሮሞውም፣ጋምቤላውም፣አፋሩም....ይፈናቀላል።ስለዚህ ለሁሉም አዝናለሁ እንጂ ለአንድ ወገን ብቻ ለይቼ አላዝንም " የሚል ነው።
እዚህ ላይ ግን መታወቅ ያለበት አንድ መሰረታዊ ሃቅ " ከባልሽ ባሌ ይበልጣል " እንዳለችው ዘመናይ ሳይሆን በአማራውና በሌሎች ነገድ ላይ የሚደርሰውን በደል አንድ አድርጎ ማየት ለእኔ ሚዛናዊ የሆነ የህሊና ዳኝነትን ትዝብት ውስጥ የሚጥል ከመሆኑም በላይ የወያኔን ታሪካዊ ማንነትንም ጠንቅቆ ካለማወቅ ወይም ማወቅ ካለመፈለግ የመነጨ ይመስስለኛል። ወያኔ ገና ጫካ ሲገባ ጀምሮ የትግራይ ህዝብ ጠላት አማራ ነው ብለው በግልፅ በሰነድ አስቀምጠዋል ። ሥለዚህ ሀብትን ብቻ ዒላማ ያደረገ ዘረፋንና በተራ ቂም በቀል በመነሳሳት ሆን ብሎ በመግደል ንብረቱን መዝረፉ ጉዳቱ አንድ አይነት ነው ብሎ መናገር በጣም ያስተዛዝባል። የህወሃት ወንበዴ የማፍያ ቡድን በአማራ ላይ ያለውን ጥላቻ ያስጠኑት የውጭ ባዕዳን ኃይሎች እና ለጊዚያዊ ፍርፋሪ ብለው ለጣሊያን ያደሩ ባንዳ የወያኔዎቹ ወላጆቻቸው ናቸው። ይህንን ደግሞ እነታማኝ በየነ ጣሊያኖች ኢትዮጵያን ከመውረራቸው በፊት በትግራይ ክልል ከአውሮፕላን ላይ የበተኑትን ፀረ አማራ የሆነ የቅስቀሳ በራሪ ወረቀት በማስረጃ ማቅረቡ የሚታወስ ነው።

ስለሆነም ለም መሬትንና ማዕድንን ስለፈለጉ ብቻ ማፈናቀልን እና ታሪካዊ ጠላታችን ነው ብለው በአደባባይ ያለይሉኝታ የሚገልፁትን ነገድ በአገሪቱ በአራቱም አቅጣጫ ሲመቻቸው በመግደል፣ሳይመቻቸው በሌሎች ነገድ በማስገደል እና የተረፈውን በብዛት ማፈናቀል በጣም የተለያዮ ናቸው። ሥለእውነት እንነጋገር ከተባለ ከአማራ ውጭ የትኛው ነገድ ነው ሆን ተብሎ ኤችአይቪ(HIV) እየተወጋ እንደቅጠል የሚረግፈው? ከበሽታው የተረፉትን የአማራ ሴቶች እህቶቻችን እስከወዲያኛው እንዳይወልዱ ያለፈቃዳቸው ክትባት እተሰጣቸው መውለድ ያልቻሉ እስኪ ንገሩን እነማን ናቸው? የሚወለዱ ህፃናት ሥለሌሉ ትምህርት ቤቶች የሚዘጉበት ክልል የቱ ይሆን? እንደነ ዶ/ር አሰፋ ነጋሽ ጥናት የአማራውን ቁጥር ለመቀነስ ከየትኛውም ክልል በይበልጥ እንደሜሪ ስቶፕስ(Mary stops) የመሳሰሉ ስለቤተሰብ እቅድ የሚያስተምሩ ድርጅቶች በአማራው ክልል በየሰፈሩ የበዙበት ምክንያት ከቶ ለምን ይሆን? ወያኔ በራሱ የመገናኛ ብዙሀን በህዝብ ቆጠራ ሪፓርት ላይ እንዳመነው 2.5 ሚሊዮን አማራ የት እንደደረሱ አልታወቀም የተባለለት ነገድ ከቶ የትኛው ይሆን? እራሱን እንደ እንጨት እየማገደ በደምና በአጥንቱ የአገሩን ዳር ድንበር አስከብሮ ሌሎችንምእንዳላስከበረ፣ከሌሎች ነገዶች ጋር እየተጋባ እንዳልተዋለደ በፈጠራ የውሸት ታሪክ በተለያዮ ክልሎች " አማራ ያየህ ጠላት አየህ " እየተባለ የሚዘመትበት ሌላ የትኛው ነገድ ነው? ፍርዱን ለእነፕሮፌሰር ሳይሄን በአለም መጨረሻ ሥለእውነት ለሚፈርደው ብቻ ሳይሆን እራሱም እውነት ለሆነው ለአብ ልጅ፣ ለድንግል ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ክርስቶስ እተዋለሁ።

2፦የአማራን ጉዳይ በሚመለከት በተደጋጋሚ ለቀረበላቸው ጥያቄ በተለያዮ የኢትዮጵያ ቦታዎች እየተዘዋወሩ በቂ ጥናት እንዳካሄዲና ወሎ አካባቢ አንዱን የእስልምና እምነት ተከታይ አማራ ነህ ወይ? ብትሉት አይደለሁም ብሎ ይሸሻል። በተለያየ አካባቢም ያገኙት መልስም ተመሳሳይ ስለሆነ አማራ ማለት ክርስትያን ማለት ነው ካሉ በኃላ ይህንን በሚመለከት ያልተረጋገጠ ወሬ ይዞ ከመሮጥ " የክህደት ቁልቁለት " የሚለው መጽሐፋቸውን ህዝቡ ቢያነበው በቂ መልስ ያገኝ ነበር ብለዋል።

በመጀመሪያ መጽሐፉን የማንበቡ እድል ላልገጠመን " የክህደት ቁልቁለት "በሚለው መጽሐፋቸው ላይ አማራን በሚመለከት ምን እንዳሉ ሲጠየቁ ቢነግሩን ኖሮ በቂ መልስ በሆነ ነበር። ሆኖም ፈልጉና አንብቡት ከማለት ውጭ ሊነግሩን ፈቃደኛ አልነበሩም። ሌላው አሁን ላይ ሆኖ " ድሮ አማራ ማለት ክርስትያን ማለት ነበር " ማለት ለእኔ ለተፈጠረው ወይም ለሚፈጠረው ችግር እራስን ለመሸንገል ካልሆነ በስተቀር ለችግሩ መፍትሄም አይሆንም ባይ ነኝ። ዛሬ የበሬን ቆዳ ሸጠን ዶሮ እንክዋን መግዛት በማንችልበት ዘመን ላይ ተቀምጠን " ድሮ እኮ በግ በአንድ ብር ገዝተን፤ መልሰን ቆዳውን በአንድ ብር በመሸጥ ስጋ በነፃ እንበላ ነበር " እንደማለት ነው። እውነታው አማራ ምንም ይሁን ምን፣ ነበረም ተባለ አለ በወረንጦ እየተለቀመ እየታደነ በመገደል ላይ ይገኛልና ገዳዮቹ ፈልገው ያላጡትን ነገድ፤ በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ግድያን እቃወማለሁ የሚለው ወገን የሚገደለውን አጣሁት ማለቱ ከቶ ሚስጢሩ ምን ይሆን? ለዚያውም የሚገደለው ወገን አለቅን እያለ እየተጣራ። ከዚህበተጨማሪ እኔ በእድሜዬ ትግራይ ውስጥ ያለን ክርስትያን አማራ ነው ሲባል ሰምቼአላውቅም።ኦሮሞውም፣ጉራጌውም፣ሌላው ሌላውም በነገዱ ስም ይጠራል እንጂ ክርስትያን ስለሆኑ ብቻ አማራ ተብለው ሲጠሩ አልሰማንም። በይበልጥ ግልፅ ለማድረግ እንዲረዳን ትግራይ ውሰጥ ያለ ክርስትያን አፉን የሚፈታው በትግርኛ ሲሆን በተጨማሪ አማርኛ ይናገራል። በሌሎችም አካባቢ የሚገኙ ክርስትያኖችም የሚናገሩት የራሳቸውን ነገድ እና አማርኛም ጭምር ነው። አሁን ግን በግንባር ቀደምትነት ዒላማ እየሆነ ያለው አማርኛ የአፉ መፍቻ ተናጋሪ የሆኑት ላይ ነው። ይህ እውነታ እንዳለ ሆኖ እነ መለስ ዜናዊ፣አቦይ ሥብሃት፣ተፈራ ዋልዋ፣ታምራት ላይኔ.....ወዘተ ለአማራ ያላቸውን ጥላቻ ከልባቸው ሞልቶ ስለተትረፈረፈ መቆጣጠር አቅቶአቸው በመገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ሲደነፉ እየሰማን አማራ ማለት ክርስትያን ማለት ነው ማለት በተለዬ መልኩ በዚህ ነገድ ላይ የሚደርስን ግፍ ለማዳፈን የሚደረግ ጥረት ያስመስላል።

3፦በጣም የገረመኝና እስካሁንም ድረስ ለማመን የከበደኝ ነገር ከኢትዮጵያ ተቆርሶ ለሱዳን ስለተሰጠው ለም መሬት የሚያውቁት ነገር እንዳለ ፕሮፌሰሩ ተጠይቀው የሰጡት አስደንጋጭ መልስ ነው " ይሄን በሚመለከት አሜሪካን አገር የሚኖሩ ጎንደሬዋች እኔን ስለጉዳዮ ጥናት ስላደረክ ማስረጃ ካለህ ብለውኝ ነበር ግን ያደረጉት ነገር የለም። አሁንም ይሄ ለጎንደሬዎቹ ቀላል ነው። ቁጭ ብሎ ድንበሩ ለሱዳን ተሰጥቶዋል ወይስ አልተሰጠም ከማለት እያንዳንዱ ጎንደሬ አምስት፣አምስት ዶላር አዋጥተው አንድ ሰው ቢልኩ ማረጋገጥ ይቻሉ ነበር " ሲሉን የተወሰንን ሰዎች ስሜታችንን መቆጣጠር ስላቃተን "በመሠረቱ ድንበሩ የኢትዮጵያ ነው፣ የተወሰደውም ከጎንደር ብቻ ሳይሆን ከጎጃምና ከጋምቤላም ጭምር ነው፣ ግን እርስዎ እንዳሉት ለምን ጎንደሬው ብቻ ያዋጣል?ለምን እርስዎም ጭምር አያዋጡም?ለምን ጉራጌው፣ ኦሮሞው.....ወዘተ አያዋጣም? "ሲባሉ "ከረጠበው ላይ ሸናችበት" እንዲሉ እንደቀልድ አሁንም እደግመዋለሁ ብለው ያንኑ ቃል በቃል ደግመውታል።
እዚህ ላይ ሳልገልፅ የማላልፈው ነገር ይህን ድንበር በሚመለከት በአፄ ኃይለሥላሴ ጊዜም ንጉሱ ድንበሩን ለሱዳን ሰጡ እየተባለ ይወራ ስለነበር አንድ የቡልጋ አካባቢ ሰው መጥተው ስለጉዳዮ ሲጠይቁኝ " እርስዎ የቡልጋ ሰው ታዲያ ምን አሳሰበዎ "እንዳልዋቸውና እሳቸውም " ዳሩ ሲነካ መሃሉ ዳር ይሆናል " ብለው እንደመለሱላቸው ለተሰብሳቢው ገልፀውልናል። እንደእኔ አስተያየት ይሄንን ንግግር የተናገሩት ሳያስቡት ነው። ምክንያቱም ፕሮፌሰር መስፍን ለቡልጋው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የመለሱላቸው መልስ ፤ ፕሮፌሰሩ ዛሬ ለእኛ የነገሩን እቅዋማቸው የዛሬ አርባ አመት ጀምሮ በልባቸው ተቀብሮ አብሮዋቸው እንደነበረ የሚያመለክት ስለሆነ ነው። እንደፕሮፌሰሩ አባባል የጎንደሬው የድንበርም ሆነ ሌላ ችግር የሌላውም ሁሉ ኢትዮጵያዊ ችግር ካልሆነ፤ ከሞተው የወያኔ ጠቅላይ ሚ/ር መልስ ዜናዊ "የአክሱም ሀውልት ለወላይታው ምኑ ነው?......" ንግግር ፕሮፌሰሩ በምን ተለዮ? በባድሜ የድንበር ቸግር ሆን ተብሎ ፈንጅ ጠራጊ እንዲሆኑ ከፊት ግንባር ያሰለፉዋቸው 80,000 ኢትዮጵያውያን የኦሮሞ፣አማራ እና የሌሎች አካባቢ ተወላጆች መሆናቸውን እውን ፕሮፌሰሩ ሳያውቁ ቀርተው ነው? እኔ እንደራሴ አመለካከት ፕ/ር መስፍን ከአማራ ነገድ ጋር በተያያዘ የፈጠራቸው አምላክና እራሳቸው ብቻ ወይም ደግሞ በአስተዳዳጋቸው ዙሪያ አብረው የነበሩም ጭምር የሚያውቁት የሆነ ነገር እንዳለ ይሰማኛል።
በአጠቃላይ የፕ/ር መስፍን የፐርዝ ጉብኝት ሲገመገም የመጡበት አላማ ያልታወቀበት እና ከመድረክ ለሚነሱ ጥያቄዎችም አጥጋቢ መልስ ያልተሰጠበት ነበር ስል በርግጠኝነት ነው።ሌላው ቀርቶ የጋምቤላ ተወላጅ የሆነች እህት ተንስታ " የኢትዩጵያ ሁኔታ ስለሚያስፈራ ወደፊት ስለኢትዮጵያ ምን ቪዥን(vision) አለዎት? ስትላቸው ምንም የለኝም ብለው የሌሎቹን ባላውቅም እኔን ግን በጣም ስላስገረሙኝ " የጉዞዎት እላማ ምንድን ነው? ቢባሉ መልስዎት ምን ይሆናል? በውጭ አገር የምንገኘውን ኢትዮጵያውያንን ተስፋ ለማስቆረጥ ነው ወይ የሚል አንድምታ አያሰጥቦዎትም ወይ?"ብዬ ጠይቂያቸው ነበር ግን እንደተለመደው መልስ አልሰጡኝም። ማጠቃሊያ በኢትዮጵያ እንድነት ለምታምኑ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ አማራ እንደማንኛውም ሌሎች ነገዶች ሁሉ ነበረ፤ እስከአለም ፍፃሜም እግዚአብሔር እንደፈቀደለት እንደሌሎች ወንድሞቹ ይኖራል። ሌሎቹ ውንድሞቹ እንዳይደርሱለት ወይም የሚደርስበትን ችግር ለማደብዘዝ እያለ የለህም፤ በተለዬ መልኩ እየተገደለ ችግርህ እኩል ነው እየተባለ እየሰማን ነው። አንድ ሰው በተሰጠው የዘመኑ ህገመንግስታዊ መብቱ ተጠቅሞ እኔ ስለሌለሁ ከዛሬ ጀምሮ እንዳሌለሁ ቁጠሩኝ ማለት እየቻለ፤ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠርን አንድ ባለታሪክ ህዝብ ፈፅሞ የለህም ማለት የአመቱ ብቻ ሳይሆን የሚሊኒዮሙም ታላቅ ድፍረት ይመስለኛል። በኮሚኒዝም ማቆጥቆጥ ዋዜማ የራሺያ ኦርቶዶክስ ካህናት ነጭ እና ቀይ ለባሽ በሚል ተለያይተው ሲናቆሩ በስተመጨረሻ ሌኒን ከነተከታዮቹ መጣና አንተም ነጭ እትለብስም፤አንተም ቀይ አትለብስም ብሎ ቤተክርስትይንን እስከማዘጋት ደርሰው እንደነበር አንድ ሰባኪ ያስተማረውን አስታወሰኝ። ዛሬ ያለን ነገር አለ ፤ የለም እያባባሉን ስያጨቃጭቁን ጠላቶቻችን ግን እኩይ ሥራቸውን ለሰክንድ እንኩዋን አላቆሙም። የተከበሩ ውድ ፕ/ር እርስዎ የማይወዱት ነገር ካለ አልወድም ይባላል እንጂ የለም አይባልም። እየተገደልኩና እየተፈናቀልኩ ነው እባካችሁ ድረሱልኝ እያለ የለህም ማለዎ" ከባለቤቱ ያወቀ ምንትስ ነው " የተባለውን ያስመስልብዎታልና አንድ እና ሁለት የወሎ እስላም ብቻ ጠይቀው
በእርግጠኝነት ከመናገር ይልቅ ወይ በሰፊው እየተዘዋወሩ በድጋሚ ጥናት ያልድርጉ፤ ወይም ደግሞ ንግግሮዎት ብዙዎችን ስላስቀየመን ደፍረው እንኩዋን ይቅርታ ባይጠይቁን ዝምታም እኮ ወርቅ ነው ። እንደአባቶቻችን ዘወትር ስምህን የምንጠራው ፤ አልፋና ኦሜጋ የሆንክ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እንደኛ ሃጢያት ሳይሆን ስለቅዱሳን አባቶቻችን ብለህ፤ከሁሉም በላይ ከሰው ወገን ሁሉ መርጠህ ስላከበርካት ስለእናትህ ስለቅድስት ፤ድንግል ማርያም ብለህ ከዚህ ሁሉ መዓት ታደገን፤ አሜን መላከፀሐይ ኃይሌ ከምዕራብ አውስትራሊያ ፐርዝ

TPLF shockingly admits failures in Ethiopia


By Admasu Belay 
December 2, 2014

Since it came to power over 20 years ago, the TPLF regime has always declared its achievements in Ethiopia's political and economic sectors. Everybody knows the state media ETV and its daily nonstop propaganda of how much better Ethiopia has become over the years. Not only that, TPLF has been telling the international community about how it changed and transformed Ethiopia. So much so that it had even deceived some Bush and Obama adminstration officials to believe its lies. But after over 20 years, the London-based Financial Times (FT) reported today that TPLF has finally admitted its massive failures in Ethiopia.

Shockingly, the TPLF admitted its disasterous policy of landlocking Ethiopia and its economic impact as well as the risk of another famine in Ethiopia.

For the last two decades, this "F word," was banned by Meles and all his TPLF disciples. In the past, If any foreign officials dared to use the words "famine" and "Ethiopia" in the same sentence, the wrath of TPLF's "ministry of foreign affairs (mfa)" would attack and humiliate them with endless MFA press releases. Meles himself told Ethiopians to forget about famine and promised that even our poorer people "will eat three times a day very soon." That promise was made in 1994! Ironically today, the TPLF government sent a document to international investors, admitting another “risk of famine, the high level of poverty" in Ethiopia, according to the Financial Times.

Not only has Ethiopia lost most of its hard currency reserves but the "steadily depreciating exchange rate may adversely affect Ethiopia’s economy?," according to the TPLF documentThat is not all. TPLF also admitted the chance of "resumption" of the war with Eritrea and more unrest from "political turmoil" as well as bad relations with Djibouti causing the "blocking of the country's only access to the sea." It is about time TPLF accepted its failures! Out of TPLF's top five policy changes since it removed Mengistu regime in 1991, it has now admitted four policies have failed already.
  1. On Eritrea policy and access to the sea. (ADMITTED FAILURE)
  2. Avoiding drought and famine (ADMITTED FAILURE)
  3. On Improving Ethiopian economy/fiscal policies (ADMITTED FAILURE)
  4. Political reform and democratization (ADMITTED FAILURE)
  5. Ethnic federalism (No admission yet)
Regarding the 5th TPLF policy, everybody knows TPLF has failed. Soon it will admit this failure too.
In 1995, TPLF claimed its "ethnic federalism" system will empower tribes without dividing Ethiopians. But today, Ethiopia is the most ethnically divided country in the world. Ethnic hatred, propaganda and tensions today are the highest ever in history. Just like the 1990s Rwanda, tribalism has destroyed Ethiopian nationalism and humanity. Sooner or later, TPLF will be forced to admit its last and final failure.

Regardless, Today will go down in history as the day TPLF admitted that it has achieved almost nothing (other than a few tall buildings) since it removed the DERG regime in 1991. It has failed Ethiopia in every way possible. The only reason TPLF is still in power is because Ethiopians are peaceful people, unlike the warmongering and hate-filled TPLF.

For all those EPRDF ruling party supporters and TPLF foot soldiers worldwide, this must be the most embarrassing day. One single TPLF document has virtually dismissed over 20 years of ETV propaganda.