Wednesday, October 5, 2016

ምን ስም ይሰጠዋል?

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ማክሰኞ መስከረም ፳፬ ቀን ፪ሺህ፱  ..              ቅፅ   ቁጥር 

በዓለም ላይ የነበሩና ያሉ ዘረኞች፣ ግፈኞችና አምባገነኖች የተለያዩ ምክንያቶች እየፈለጉ ሕዝብ ገድለዋል፣ አስረዋል፣ አሰቃይተዋል። በዚህም ተግባራቸው፣ « ናዚ፣ ፋሽስት፣ ጨፍጫፊ፣ አረመኔ» ወዘተርፈ ተብለዋል። ከእነዚህ እጅግ በከፋ ሁኔታ የዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በአጠቃላይ፣ በተናጠል ደግሞ በዐማራው፣ በኦሮሞው፣ በአኙዋኩ፣ በኑኤሩ፣ በሶማሊው፣ በአፋሩ፣ በሲዳማው ወዘተርፈ ነገዶች ላይ የሚፈጽመው ሁለንታናዊ ግፍ በምን ቃላት ሊገለጽ እንደሚችል የቋንቋ ሊቃውንት ሊያስቡበት የሚገባ ነው። ከላይ የተገለጹት የጭካኔ እና የአረመኔነት ስያሜዎች በፍፁም የወያኔን ማንነትና ዕውነተኛ ባሕሪ አይገልጹትም። ይገልጹታል ከተባለም ተለምዶአዊ በመሆኑ፣ የቃሎቹ የያዟቸው ጽንሰ ሀሳቦችና ድርጊቶቹ የሚጣጣሙ አይደሉም። በምንም ታምር ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የኖረ በዓልን ለማክበር ቄጤማ ይዘው በተቀመጡ ሽማግሌዎች፣ ሕፃናት፣ ሴቶችና ወንዶች ላይ ከሰማይ በአውሮፕላን፣ ከምድር በመትረየስ የሞት ዶፍ ማውረድ በምንም መመዘኛ ምክንያታዊነት የለውም። እገዛዋለሁ የሚለውን ሕዝብ፣ ያውም «ለብሔር/ብሔረሰቦች እኩልነት» ቆሜአለሁ እየለ ጧት ማታ በሚምል የገዛ ወገኑን የደበደበ አረመኔ የሚባል ቡድን በዓለም ታሪክ ስለመኖሩ በእርግጠኝነት ለመናገር አይቻልም።
የትግሬ ወያኔ ፣ በሀሰት ያሰራቸውን የኅሊና እስረኞች በራሱ የፍርድ ሂደት ቢያቀርባቸው አደረጉ ያላቸውን ስለማድረጋቸው ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ስለሆነም እስካሁንም የሚሠራው ትያትር ሕዝቡ ያወቀበት መሆኑን በመረዳቱ፣ በቂልንጦ፣ በጎንደርና በደብረታቦር እስር ቤቶች በቁጥጥሩ ሥር ያሉትን እስረኞች በእሳት ለኩሶ፣ ንፁሐን ዜጎችን አጠቃ፣ በአሰቃቂ ሁኔታ ጨረሰ። እስረኞችን የወባ መድኃኒት ነው ብሎ፣ ማላታይን አጠጥቶ ፈጀ። ኤች አይ ቪ ቫይረስን በመርፌ እየወጋ ሕዝብ ጨረሰ። የዐማራውን ነገድ ቁጥር ለመቀነስና ፈጽሞ ለማጥፋት ባለው ዕቅድ፣ ዐማራ ሴቶችን ለይቶ በወሊድ ቁጥጥር ስም ታማሚና መካን አደረገ። የዐማራ ወንዶችን የመራቢያ አካላቸውን እየቀጠቀጠ፣ ሰዎችን በቁማቸው ጉድጓድ ውስጥ ከቶ አሰቃየ። እንዲህ ዓይነት ፍፁም አረመኔና ፋሽስት የተባለ ቡድን ከወያኔ በቀር የኢትዮጵያ ታሪክ አያውቅም።
ግፈኛውና ዘረኛው የትግሬ ወያኔ ቡድን ባለፈው እሑድ ጥቅምት 22 ቀን 2009 ዓም በደብረ ዘይት ከተማ የእሬቻን የኦሮሞ ባህላዊ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተሰበሰቡ ንፁሐን ዜጎች ላይ የፈጸመው ቃላት ሊገልጹት የማይችሉት የጅምላ ግድያና ፍጅት ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በጽኑ ያወግዛል።
ግድያው ወያኔ ለ25 ዓመታት ካደረጋቸው የሚለየው፣ ላለፉት ዘጠኝና አሥር ወራት በተከታታይ በሐረርጌ፣ በወለጋ፣ በጅማ፣ በአርሲ፣ በኢሉባቡር፣ በሸዋ፣ በጎንደር፣ በጎጃምና መሰል ክፍለሀገሮች የዘለቀው ሕዝባዊ እንቢተኝነትና የዐማራው የማንነት ትግል ገዝፎና ገፍቶ ምኒልክ ቤተመንግሥት በራፍ ላይ በመድረሱ፣ በወያኔና አሽከሮቹ ላይ የፈጠረው የፍራት መጠን ከፍተኛ መሆን በአልሞት ባይ ፍርግጫ ያላቸውን የመጨረሻ ኃይል ያሳዩበት መሆኑ ነው። ነፃነትን የተጠማ፣ ማንነቱን ለማስከበር ቆርጦ የተነሳን ሕዝብ፣ ይህ ዓይነቱ የፈሪ በትር የታጋዩን ሕዝብ ወኔ ያጎለብታል እንጂ፣ እንደማይቀንሰው የኢትዮያ ሕዝብ ደጋግሞ ለዓለም ማኅበረሰብ አሳይቷል። በመሆኑም የትግሬ ወያኔ ፍርሀት በወለደው ስሜት በእሬቻ በዓል ተሳታፊዎቹ ላይ የወሰደው ዘግናኝና ሰቅጣጭ የጅምላ ፍጅት፣ የወያኔን በቃላት ሊገለጽ የማይችል ጭካኔ ከማሳየት በቀር፣ የሥልጣን ዕድሜውን ያራዝማል ተብሎ አይታሰብም። በአንፃሩ የወያኔን ዕድሜ በእጅጉ የሚያሳጥር፣ የሕዝቡን ነባር አንድነት ወደነበረበት ደረጃ የሚመልስ ነው። እንዲያውም የትግሬ ወያኔ ጠባብና አናሳ ቡድን ለሥልጣን ዕድሜው ማራዘሚያ በኦሮሞውና በዐማራው ነገዶች መካከል በሀሰት ገንብቶት የነበረው የጥላቻ፣ የመጠራጠርና የመገፋፋት ድልድይ ይሰብራል።
ሰሞኑን ደብረዘይት ላይ የፈሰሰው የኦሮሞው፣ የዐማራውና መሰል ነገዶች ልጆች ደም፣ ትናንት ጎንደር፣ ባሕርዳር፣ ደብረታቦር፣ ደብረማርቆስ፣ ነፋስ መውጫ፣ ወረታ፣ አምባ ጊዮርጊስ፣ ደባርቅ፣ ዳንግላ፣ ኮሶ በር፣ ቡሬ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ወዘተርፈ ላይ ከፈሰሰው የዐማሮች ደም የሚለየው አንዳችም ነገር የለም።  በሁሉም አካባቢዎች በወያኔ ነፍሰ ገዳዮች የፈሰሰው ደም የኢትዮጵያውያን ደም ነው። ወያኔ ከሁሉም በላይ የዐማራውንና የኦሮሞውን ልዩነት ሊያሰፋው የሚፈልገው ሁለቱ ነገዶች አንድ ከሆኑ ኢትዮጵያን ሊገዛና ሊዘርፋት እንደማይችል ስለሚያውቅ ነው። ይህንን የትግሬ-ወያኔን መሰሪ ሴራ፣ የኦሮሞውና የዐማራው ልጆች «አውቀንባችኋል» በማለት ወደ ነባሩ አንድነታችን በፍጥነት መመለስ ወያኔን አይሞቱ ሞት የሚገድለው እንደሆነ አይጠረጠርም። ስለሆነም የመከራ ጊዜአችን ለማሳጠር የሁለቱ ነገዶች አንድነት ፍቱን የወያኔ አገዛዝ ማርከሻ እንደሚሆን ተረድተን፣ ፍትሕ የተነፈጉ ፍትሕን እንዲያገኙ፣ በአረመኔዎች የተገደሉ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ እንዳይቀር፣ ኢትዮጵያውያን በነገድ ሳይሆን፣ በዕኩልነት ላይ በተመሠረተ ኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ እንድናተኩር ያሻል።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!

የኢትዮጵያ ትንሣዔ በትግላችን ዕውን ይሆናል!

Thursday, September 1, 2016

ሞረሽ ለዐማራ ሕዝብ!!!


ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ረቡዕ ነሐሴ ፳፭ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.              ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፮

ከሞረሽ  ወገኔ  የዐማራ ድርጅት የተሰጠ የነፍስ አድን ጥሪ!
የተከበርከውና ጀግናው የዐማራ ሕዝብ ሆይ!
የትግሬ ወያኔ አገዛዝ «ዐማራውን አከርካሪውን ሰብረነዋል»፣ «ዐማራው ላይመለስ ገድለን ቀብረነዋል» በማለት ይሳለቅብሃል። በእርግጥም ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ከአምስት ሚሊዮን በላይ ዐማሮችን ገድሎ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን ደግሞ አሰድዶ ከመኖሪያ ቀያቸው አፈናቅሏል። ሆኖም ግን ከሞቱት በላይ፣ ካሉት በታች ሆነህ የምትኖረው የቀረኸው ዐማራ፣ ከገባህበት የቁም መቃብር ለመውጣት ዘወትር ትግልህን እንዳላቋረጥክ እኛ አብረንህ የምንታገለው ልጆችህ ቀዳሚ ምሥክሮችህ ነን። በተለይም ከሐምሌ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ መግነዝህን ቀደህ እና በጣጥሰህ፣ የተጫነብህን  የመቃብር ድንጋይ እና አፈር ፈነቃቅለህ ከፈጽሞ ጥፋት ራስክን ለማዳን እያደረግኸው ላለው ተጋድሎ እና የጀግንነት ተግባር ያለን አድናቆት እናአክብሮት እጅግ ከፍ ያለ ነው። ለምታደርገው ራስክን  ከፈጽሞ ጥፋት የመታደግ ተፈጥሮአዊ የመከላከል ትግል፣ እኛ በስደት የምገኝ ልጆችህ ምንጊዜም ከጎንህ የማንለይ መሆኑን ስናረጋግጥልህ በታላቅ አክብሮት እና ወገናዊነት ነው።
ዛሬ ይህንን ጥሪ እንድናስተላልፍልህ የተገደድነው፣ ጨካኙ፣ አረመኔው እና ፀረ-ዐማራ የሆነው  የትግሬ ነፃ አውጪ ወራሪ ቡድን፣ በመላው የዐማራ ሕዝብ ላይ፣ ካለፉት ሁሉ በመጠኑና በስፋቱ የተለየ፣ ይፋ በሆነ ሁኔታ ጦርነት ማወጁ ነው። የጥቁር ናዚው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ በዐማራው ላይ እጅግ መጠነ-ሰፊ የሆነ የዘር ማጥፋት ዘመቻ መክፈቱን፣ በወያኔ ታዞ አዳሪ የሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ተብየው አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ፣ ለወታደሩና ለፀጥታ ኃይሉ ሙሉ የመግደልና የማሰር ሥልጣን መስጠቱን፣ በብዙኃን የመገናኛ መሣሪያዎች ሰምተናል። በዚህም መሠረት፣ የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን ለመጨፍጨፍ፣ እጅግ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ  ነፍሰ በላ ገዳዮቹን፣ በተለያዩ የትርንስፖርት መንገዶች ወደ ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረማርቆስ፣ ደሴ፣ ደብረ ታቦር፣ ደባርቅ፣ ወዘተርፈ በማጓጓዝ ላይ እንደሆነ አውቀናል።
እኛ በስምህ ተደራጅተን፣ በአረመኔው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ እየተፈጸመብህ ያለውን የዘር ጥቃት ለዓለም ማኅበረሰብ በማሰማት ላይ የምንገኝ ልጆችህ፣ የምናቀርብልህ ጥሪ አለን። ይኸውም፥ አንተን በደመኛ ጠላትነት ፈርጀው፣ ፕሮግራም አዘጋጅተው እና ተደራጅተው፣ ላለፉት 41 ዓመታት የዘር ፍጅት ሲፈጽሙብህ የኖሩት የትግሬ-ወያኔዎች ዛሬም የጥፋት በትራቸውን እንዳልሰበሰቡት አንተም አሳምረህ ታውቀዋለህ። እንዲያውም ከሌሎች ነገዶች ያልተቀላቀሉበት፣ የትግሬ-ወያኔ ብቻየሆኑ ነፍሰ-በላ ገዳዮች፣ የፌድራል ፖሊስ እና የመከላከያ ሠራዊት መለዮ ለብሰው፣ አንተን የዋሁን እና ደጉን የዐማራ ሕዝብ ለመጨፍጨፍ  ከፍ ሲል በተዘረዘሩት ከተሞች የተሰማሩ መሆናቸውን ዕለት በዕለት የምትመሰክረው ሃቅ ነው። ስለሆነም ሌላ ከውጪ የሚመጣ ደጋፊ ኃይል ሳትጠብቅ፣  ራስክንና ቤተሰብህን ከጥቃቱ መከላከል እንድትችል አስፈላጊውን መሰናዶ ታደርግ ዘንድ ለማሳሰብ እንወዳለን። ከታሪክም እንደምንገነዘበው፣ ዐማራው የራሱን እና የአገሩን ጠላቶች ከጓሮው ገብተውለት ቀርቶ፣ ከጉያቸው እየገባ የዶግ አመድ የማድረግ የቆየ የጀግንነት ታሪክ እና ባህል ባለቤት ነው። ስለሆነም ይህን በእብሪት ተወጥሮ፣ ከብብትህ የገባውን የትግሬ-ወያኔ መንጋ፣ በጎበዝ አለቆችህ በመመራት አስፈላጎውን መከላከል በማድረግ፣ ይህን የጣሊያን እንቁላል አቅራቢና አልጋ አንጣፊ የነበሩትን የባንዳ ልጆች ጥርቅም፣ በተለመደው ጀግንነትህ ፍላጎታቸውን የቀን ሕልም እንደምታደርገው እምነታችን ከፍ ያለ ነው።
በአሁኑ ሰዓት፣ አጥፊው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ በባሕር ዳር፣ በጎንደር፣ በደብረ ማርቆስ፣ በደሴ እና  በደብረ ታቦር በሚገኙ ሕንፃዎች ውስጥ አልሞ ተኳሽ ነፍሰ ገዳዮቹን አሰማርቶ ለጅምላ ግድያ ሙሉ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታውቋል።  ከዚህበተጨማሪም  ነፍሰ በላዎቹ የትግሬ-ወያኔዎች በከተሞች ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሚኒባሶች እና የሕዝብ ማመላሻዎች  መኪናዎች መትረየስ እና ላውንቸር ጠምደው ሕዝብ ለመጨፍጨፍ ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ላንተ መንገር «ለቀባሪው ማርዳት» ይሆንብናል። ስለሆነም፣ አንተ ጀግና እና ኩሩ የሆንከው የዐማራ ሕዝብ፣ ይህ የትግሬ-ወያኔ አጥፍቶህ ከመጥፋቱ በፊት፣ አጥፊውን ኃይል ቀድመህ ለማጥፋት ክንድህን አስተባብረህ ለመብትህና ለነፃነትህ ተዋደቅ። «ከዘላለም ባርነት እና ውርደት የአንድ ቀን ነፃነት» ይመረጣልና፣ አንተም እንደ አባቶችህ፣ ለልጆችህ እና ለልጅ ልጆችህ ኩራትን እና ነፃነትን ለማውረስ በወራሪው እና በዘረኛው ጠላትህ በትግሬ-ወያኔ ላይ የተባበረ ክንድህን አንሳ። «ጅብ ከሚበላህ፣ ጅቡን በልተህ ተቀደስ» ይባላልና፣ አንተን ሊያጠፋ የተፈጥሮ ድንበርክን ተከዜን ተሻግሮ የመጣውን፣ ይህ የሰከረ መርዘኛ እባብ እንዳያመልጥህ በር በሩን ዘግተህ መተናፈሻ በማሳጣት ለትውልዱ የማይረሳ ትምህርት ሰጥተህ እንደምትሸኘው እምነታችን ጽኑ ነው። የትግሬ-ወያኔ ያቀደልህን ሞት እና የዘር ዕልቂት ትውልድህን ከፈጽሞ ጥፋት እንድትታደግ ጥሪያችን ስናቀርብ፣ በእኛ በኩል ማድረግ የሚምንችለውን ሁሉ ለማድረግ የምንሰስተው አንዳችም ነገር አለመኖሩን ስናረጋግጥልህ በታላቅ አክብሮት ነው።
ለብአዴን አባላት እና አካላት!
ይድረስ «ለብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ» አካላትና አባላት! የቆየው እና መልካሙ ባህላችን፣ እንደሚያስገነዝበን «ከባዕዳ ቆርሰህ ወደ ወገንህ ዙረህ ጉረስ» የሚል ነው። የትግሬ-ወያኔ ለእናንተ ባዕድ እንጂ፣ ወገናችሁ እንዳልሆነ፣ በየቀኑ የሚፈጸምባችሁን አድልዖ እና በደል ከእናንተ የተሻለ የሚያውቀው የለም። የትግሬ-ወያኔ እናንተን የሚያያችሁ፣ የወገኖቻችሁ መቁረጫ እና መፍለጫ የምሣር እጀታ (ዛቢያ) አድርጎ እንጂ፣ እንደትግል አጋር አድርጎ አለመሆኑን ትስቱታላችሁ አንልም። ይህም በመሆኑ ምንጊዜም አያምናችሁም። ባለመታመናችሁ ደግሞ ዘወትር በስለላ እና በክትትል ውስጥ ያላችሁ ናችሁ። አሁን የወልቃይት-ጠገዴን የማንነት ጥያቄን ተከትሎ የተቀጣጠለው የሕዝባዊ እንቢተኝነት ማዕበል የትግሬ-ወያኔን ጠራርጎ አፈር ሳይቀላቅል ይቆማል ብላችሁ የምታስቡ እና የምታምኑ ከሆናችሁ፣ የምታስቡት በአዕምሮአችሁ ሳይሆን፣ እንደሚባለው በሆዳችሁ ነው ማለት ነው። በአዕምሮአችሁ የምታስቡ ከሆነ፣ የትግሬ-ወያኔ ላለፉት 41 ዓመታት በዐማራው እና በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍ ገደቡን አልፎ በመፍሰሱ፣ እንደጎርፍ የፈሰሰው የንፁሐን ዜጎች ዕንባ ከፈጣሪ ደጅ የደረሰ መሆኑን አምናችሁ ተቀበሉት። ስለዚህ ምንጊዜም ከተበዳዮች ጎን የሚቆመው የዕውነት አምላክ ፍርዱን የሚሰጥበት ቀን ላይ በመሆናችን፣ የትግሬ-ወያኔ እናንተንም ሆነ እናንተ የወጣችሁበትን የዐማራ ነገድ አጥፍቶ፣ ወደ ምሽጉ እንዳይሄድ፣ ከወገናችሁ ጎን የምትቆሙበት ወቅት ላይ መሆናችሁን ልብ እንድትሉ አደራ እንላለን።
ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የገዳዩ አካል ብትሆኑ፣ ሥራችሁ በምድርም በሰማይም ይቅር የማይባል ከፍተኛ ወንጀል እና ኃጥያት መሆኑን ከወዲሁ እንድትገነዘቡት እንሻለን። ዛሬ በድብቅ የሚቀር አንዳችም ነገር የለም። ዕድሜ ለዘመኑ ቴክኖሎጂ፣ የምትሠሩትን ማናቸውንም መልካምም ሆነ መጥፎ ሥራ በድምፅ፣ በምስል፣ በሰነድ ተቀርጾ፣ በደቂቃዎች ውስጥ ለእኛ ከጉዳዩ ባለቤቶች ቀርቶ ለዓለም ማኅበረሰብ የሚደርስ መሆኑን አታውቁም ለማለት አንደፍርም። በመሆኑም፣ የእያንዳንዳችሁ እንቅስቃሴ በሕዝቡ ዕይታ ውስጥ ያለ ስለሆነ፣ ከአይቀሬው የትግሬ-ወያኔ ውድቀት በኋላ፣ ተበዳዩ ሕዝብ ለሚያቀርብላችሁ ጥያቄ የምትሰጡት ምክንያት ዋጋ አይኖረውምና፣ ከወዲሁ ከወገናችሁ ጎን እንድትቆሙ በወገናችን በዐማራው ስም ጥሪአችን እናቀርብላችኋለን። በመሆኑም ወገናዊነታችሁ ለወገናችሁ እንጂ፣ ለቅኝ ገዣችሁ ወያኔ እንዳይሆን አደራ እንላለን።
በተቃራኒው ይህንን ጥሪ ተላልፋችሁ፣ ከዐማራው ደመኛ ቡድን ጋር ቆማችሁ የወገናችሁ መቁረጫ ምሣር እጀታ ከሆናችሁ፣ ሞታችሁ አካላዊ ብቻ ሳይሆን፣ መንፈሣዊምም ጭምር እነደሚሆን ልናሳስባችሁ እንወዳለን። ይህን ጥሪ ተላልፋችሁ በወገናችሁ ላይ አንዳች ጥፋት ብትፈጽሙ፣ በኋላ ላይ ለሚከተለው የከፋ እርምጃ፣ ሕዝባችን «እጄን በእጄ» የሚለው ፀፀት ተሸካሚ እንዳይሆን፣ ከወዲሁ ተገቢውን ጥንቃቄ እንድታደርጉ ጥሪያችን እናቀርባለን።
በፌደራል ፖሊስ እና በመከላከያ ውስጥ ያላችሁ የዐማራ ነገድ ልጆች፥
የፖሊስ ሠራዊት ዋና ተግባር የሕዝብን ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ እንጂ፣ ሕዝብን ሰላም መንሳት እና ማሸበር፣ አልፎም ዘር ማጥፋት አይደለም። የመከላከያ ሠራዊት ዋና ተግባርም የአገሩን ሉዓላዊነት እና አንድነት ከውጪ ወራሪዎች መከላከል እንጂ በሰላማዊው የገዛ ወገኑ ላይ ጥይት በመተኮስ መጨፍጨፍ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። ይህንን የምታደርጉ ከሆነ ግን ከዚያ በኋላ ለሚመጣው ሕዝባዊ ምላሽ ተጠያቂዎቹ እናንተው እንጂ ሕዝቡ አይሆንም። በመሆኑም አፈሙዛችሁን በአሸባሪው የወያኔ ቡድን ላይ በማዞር ሕዝባዊ ወገንተኝነታችሁን እንድታሳዩ ከወዲሁ ትጠየቃላችሁ።
ለትግራይ ሕዝብ!
አባቶቻችን እንደሚነግሩን ትግሬና ዐማራ አንድ ዓይነት ሃይማኖት የሚከተሉ፣ ከግዕዝ የተቀዳ ቋንቋ የሚናገሩ፣ በታሪክ እና በመልከዐ-ምድር አቀማመጥ የተቆራኙ፣ የተጋቡ እና የተዋለዱ፣ በዚህም ምክንያት የወል የሆነ ሥነልቦና የገነቡ መሆናቸውን ነው። ካለፉት 50 እና 60 ዓመታት በኋላ ግን ያ የቀድሞ ታሪክ መልኩን ለውጧል። በተለይም ደግሞ ከአብራክህ የወጣው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ ላለፉት 25 ዓመታት በጨበጠው የፖለቲካ ጡንቻ ተጠቅሞ፣ ዐማራውን በአውራ ጠላትነት ፈርጆ፣ በዐማራው ላይ የዘር ፍጅት መፈጸሙን መቼም ቢሆን፣ የለም አልተደረገም እንደማትለን ተስፋ አለን።
የትግሬ-ወያኔ ቡድን የኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ዋና ጠላቶች መሣሪያ በመሆን፣ ኤርትራን አስገንጥሎ፣ አገሪቱን ተፈጥሮአዊ የቀይ ባሕር ባለቤትነቷን በማሳጣት መተናፈሻ ያጣች፣ የበይ ተመልካች ያደረጋት መሆኑን ታውቃለህ። በዚህም የተነሳ፣ በትውልድ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በመከዐ-ምድር ወዘተርፈ አንድ ከሆነው የኤርትራ ሕዝብ ጋር ጥቁር ደም አቃብቶ ኑሮህ የሰቀቀን እንዲሆን ማድረጉን ትዘነጋዋለህ አንልም። ይህ ቡድን አንተን ማኅበራዊ መሠረቱ በማድረግ፣ በፈለገው ጊዜ የፈለገውን የሚያስፈጽምብህ ሁነኛ የጥፋት መሣሪያው እንደሆንክ በመቁጠር፣ ያለፈው አልበቃ ብሎት፣ ዛሬም በዐማራው ነገድ ላይ አጠቃላይ የሆነ የዘር ፍጅት ለመፈጸም በወታደርነት እና በደህንነት ሠራተኛነት የተሰለፉት ልጆችህ ዐማራውን እንደፈለጉ እንዲያስሩ እና እንዲገድሉ ትዕዛዝ አስተላልፏል።
የትግሬ-ወያኔ ባዘዘው ትዕዛዝ መሠረት የትግራይ ሕዝብ ዛሬም የወያኔ መሣሪያ ሆኖ በዐማራው ላይ ተከታታይ የዘር ፍጅት ከፈጸመ፣ በትግሬ ሕዝብ እና በዐማራ ሕዝብ መካከል በተከታታይ ትውልዶች ምንጊዜም ሊታረቅ ከማይችል የጠላትነት ስሜት ውስጥ የሚገባ መሆኑን ልብ ልትለው ይገባሃል። ስለሆነም ከጊዜአዊ ስሜት እና «ወያኔ የእኛ መንግሥት ነው» ከሚለው የጧት ጤዛ እምነት ወጥተህ፣ የትግሬ-ወያኔ ዐማራውን እንድታጠፋ የሰጠህን ትዕዛዝ ከመፈጸም እንድትታቀብ ወገናዊ ጥሪያችን እናቀርባለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ፣ የትግሬ-ወያኔ ዓላማ አስፈጻሚ መሆንክን ከቀጠልክ፣ ትውልዱ እንደ እስካሁኑ፣ በኢትዮጵያዊነቱ ኮርቶ እና ተንደላቆ በመላ አገሪቱ የመኖር ዕጣው የሚሟጠጥ መሆኑን ልናስገነዝብህ እንወዳለን። ዛሬ የትግሬ-ወያኔ የዘረጋው ዐማራን የማጥፋት ዘመቻ በሁሉም በትግራይ ልጆች ተቀባይነትን ካገኘ፣ በትግሬና በዐማራው መካከል ለዘመናት ተገንብተው የነበሩ ግንኙነቶች ድልድይ እስከ ወዲያኛው የማይጠግኑ መሆናቸውን መናገር ነቢይ መሆንን አይጠይቅም። ስለሆነም ለጊዜአዊ ጥቅም እና ለልጆችህ ገደብ የለሽ አምባገነናዊ ሥልጣን መራዘም ብለህ፣ ከቋሚው እና ዘላለማዊው ወንድምህ የዐማራ ነገድ ጋር የተቃባኸው ደም «ባለፈው ይብቃ»  ብለህ፣ ከሕዝቡ ጎን እንድትቆም የጠበቀ አደራችንን እናስተላልፍልሃለን። የዚህ ጥሪ ተቀባይነት ማግኘት፣ ጥቅሙ ለዐማራው ሳይሆን ፣ ለአሁኑም ሆነ ለወደፊቱ የትግሬ ትውልድ መሆኑን ልብ ብለህ፣ ከአጥፊው የትግሬ-ወያኔ ቡድን ራስክን እንድትለይ ጥሪያችን እናቀርባለን!
በዐማራነት እና በኢትዮጵያ አንድነት ለምታምኑ የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች!
የድርጅቶቹ መኖር ዋጋው ሕዝብን ከጥፋት ለመከላከልና ወደ ተሻለ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ሕይዎት ለመምራት መሆኑ ግልጽ ነው። ሕዝብ ከሌለ ድርጅቶች አይኖሩም። በመሆኑን የእነዚህ ድርጅቶች መኖር ፋይዳው፣ ቆምንለት ለሚሉት የኅብረተሰብ ክፍል ኅልውና መጠበቅ የሚችልበትን ሁሉ፣ ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር እያገናዘቡ ማድረግ ነው።  በዚህ ረገድ ዘረኛው የትግሬ-ወያኔ ቡድን የዐማራውን ነገድ ዘር ለማጥፋት ይፋ የሆነ የዘር ፍጅት አዋጅ አውጇል። ይህ የዘር ፍጅት በስፋት እንዳይቀጥል፣ ኢትዮጵያ ተብላ የምትታወቅ አገርም ታሪክ እንዳትሆን፣ ይህ አጥፊ ቡድን የተያያዘውን የጥፋት ጉዞ ማስቆም የግድ ከሚለው ወቅት ላይ ተደርሷል። የትግሬ-ወያኔን ከጥፋት መንገዱ ማስቆም የሚቻለውም፣ ከያዘው የፖለቲካ ሥልጣን፣ በተያያዘው ሕዝባዊ እንቢተኝነት ትግል አሽቀንጥሮ መወርወር ሲቻል ብቻ ነው። ለዚህም በመጀመሪያ የጥቃቱ ሰለባ የሆነው የዐማራው ነገድ ልጆ አንድነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ዛሬ አስፈላጊ ነው። ቀጥሎም በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ድርጅቶች፥ ልዩነቶቻቸውን አጣብበው፣ አንድ በሚያደርጓቸው ጉዳዮች ዙሪያ በመሰባሰብ፣ አጥፊው ቡድን አጥፍቶን ሳይጠፋ በቁርጠኝነት ልንታገለው ይገባል። ለዚህ ዕውን መሆንም፣ ማንንም ያላገለለ የዘመቻ ሥራ ሊሠራ የሚችል ግብረኃይ ተቋቁሞ፣ የሚከተሉት ሥራዎች  በአፋጣኝ እንዲሠሩ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።
አንደኛ፦ የዕለቱን የአገሪቱን ሁኔታ እየተከታተለ ዝርዝር መረጃዎችንና ዘገባዎችን ወጥነት እና ተከታታይነት ባለው መልኩ ለዓለም ማኅበረሰብ፣ ለዓለማቀፋዊ እና  አሕጉራዊ ድርጅቶች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የሚያቀርብ የመረጃ ሥርጭት አካል መሰየም።
ሁለተኛ፦ በዲፕሎማሲው መስክ መልካም ስም ያላቸውን ሰዎች በማቀናጀት ወያኔ አገሪቱንና ሕዝቡን ወደ ጥፋት ጎዳና እየወሰዳት መሆኑን ሳይሰለቹና ሳይዘናጉ መረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካሎች የሚሰጥና የሚያግባባ ቡድን መፍጠር፤
ሦስተኛ፦ በትግሬ-ወያኔ ግፈኛ ቡድን ለተገደሉ፣ ለታሰሩ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ የሚያሰባስብና የሚለግስ ቡድን መፍጠር፣
አራተኛ፦ ወያኔ አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ የኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖች ባስቸኳይ ተገናኝተው፣ መጭውን የአገራችን ዕጣ ፈንታ የሚወስን ወጥ እና ተደጋጋፊ የሆነ ሥራ በአስቸኳይ መጀመር ጊዜ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም።
በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ነፃነት ወዳዱ እና ጀግናው የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! «አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል» እንዲሉ፣ የዐማራው፣ የኦሮሞው፣ የሶማሌው፣ የአኙዋኩ ወዘተርፈ ችግር የእያንዳንዳችን ችግር ነው። የዐማራው ፍጅት ያንተም ፍጅት ነው። የትግሬ-ወያኔ በዐማራው ሕዝብ ላይ እንዳደረሰው በደል ሁሉ፣ የበደሉ መጠን በዓይነት እና ሁኔታ ይለያይ እንጂ፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን ላይ ላለፉት 25 ዓመታት ፈጽሞታል። ይህ የአገር፣ የታሪክ፣ የባህልና የማንነት ጠር የሆነ ቡድን፣ እስከ ዛሬ በዐማራው ላይ ያደረሰው በደልና ግፍ አልበቃ ብሎት፣ በግልጽና በይፋ በአዋጅ፣ የዐማራን ዘር ለማጥፋት ለወታደሩና ለጸጥታ ሠራተኛው ትዕዛዝ ሰጥቷል። ይህ ጥፋት በዐማራው ላይ ተፈጽሞ የማይቀር፣ ሁሉንም ለሥልጣኔ ያሰጉኛል የሚላቸውን ነገዶች ለማጥፋት ወደኋላ የማይል መሆኑን ባለፉት ዘመናት በተለያዩ ቦታዎች የወሰዳቸው አስከፊና ዘግናኚ ርምጃዎች ምንነቱን አሳይቷል። እሳትን ማጥፋት በሩቁ ነውና፣ ይህ በዐማራ ሕዝብ ላይ የታወጀው የዘር ፍጅት በእያንዳንዳችን ደጅ ከመድረሱ በፊት ከዐማራው ወገንህ ጋር በመቆም እሳቱን ከዚያው ላይ ለማጥፋት የተለመደ ኢትዮጵያዊ ትብብርህንና ጀግንነትክን ዳግም እንድታስመሰክር ጥሪአችን ስናቀርብልህ በታላቅ አክብሮት ነው። የዐማራው መዳን የኢትዮጵያ መድኅነት ነው። ሞትና ስደት ባለፈው ይብቃ! ናዚያዊው የትግሬ-ወያኔ አጥፊ ቡድን ነውና፣ አጥፍቶን ሳይጠፋ ቀድመን ለማጥፋት ከተቀጣጠለው የዐማራ ነገድ ሕዝባዊ እንቢተኝነት ጎን እንቁም!
በመጨረሻም፥ ከላይ የዘረዘርናቸውን ተግባሮች ካከናወንን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን የትግሬ-ወያኔ የጫነብንን የናዚ-ዓይነት አገዛዝ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አሽቀንጥረን ለመጣል እንደምንችል ጥርጥር የለንም። ለዚህም ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይርዳን።

ወያኔ አጥፍቶን ሳይጠፋ፣ እርሱን ለማጥፋት እንተባበር!
ድል ለሠፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት


Wednesday, August 17, 2016

የትግሬ-ወያኔ የዐማራ እና የኦሮሞ ነገዶችን ሕዝብ ጨርሶ ለማጥፋት ያቀደውሚስጢራዊ አዲስ ሤራ

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት             ማክሰኞ ነሐሴ ፲ ቀን ፪ሺህ፰  ዓ.ም.             ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፳፪

ላለፉት 25 ዓመታት የትግሬ-ወያኔ በሕዝብ ላይ የፈጸመው ግፍና በደል ከመጠን በላይ በመሆኑ፣ ሕዝቡን ለእምቢተኝነት አነሳስቷል። ይህ ግፍና በደል መጠን የለሽ በመሆኑ፣ በአገሪቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች፣ በተለይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በሐረርጌ፣ በአርሲና በወለጋ ክፍለ-ሀገሮች የሚኖረው ሕዝብ፣ የትግሬ-ወያኔ «ለብሔር ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ዕኩልነት» ሲል «አመጣሁት» ያለውን «ሕገ-መንግሥት» የማይቀበለው መሆኑንና፣ የዚሁ  «ሕገ-መንግሥት» ተብየ መገለጫ የሆነውን ሠንደቅ ከተሰቀለበት በማውረድ፣ ከጥንት ጀምሮ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት መገለጫ፣ የነፃነት ቀንዲል የሆነችው ሠንደቅ ከፍ-ብላ እንድትውለበልብ እያደረገ መሆኑ በግልጽ ተስተውሏል። ይህም የትግሬ-ወያኔ አመጣሁት ያለው ዕኩልነትና የነገዶች አንድነት ውሸት መሆኑን፣ ባንፃሩ ግን የትግሬ-ወያኔ የውስጥ ቅኝ ገዥ ኃይል እንደሆነ፣ በተከታታይ በተደረጉት የሕዝባዊ እንቢተኝነት ሰላማዊ ሰልፎች በግልጽ ታይቷል።
ይህ የሕዝብ አመጽ ያርበደበደው የትግሬ-ወያኔ ቡድን፣ የሚይዝ የሚጨብጠውን በማጣቱ፣ የእርሱ ምርኮኛ የሆነውንና በጥቅማጥቅም የገዛውን የትግራይ ትውልድ በነቂስ አስታጥቆ፣ በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ ለመዝመት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስተማማኝ ከሆኑ የውስጥ ምንጮቻችን ያገኘናቸው መረጃዎች ያሳያሉ። የትግሬ-ወያኔ ከሚያደርገው ሠፊ የጥፋት ዝግጅቶች ውስጥ፣ የትግራይን ትውልድ «በትግልህ ያገኘኸውን ልዩ መብትና ነፃነት፣ ትምክተኞች፣ ነፍጠኞች፣ የድሮው ሥርዓት አራማጆችና ዐማሮች ሊነጥቁህ ነውና ዐማራን ለማጥፋት ዝመት፣ ተንቀሳቀስ» በማለት፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በጠለምት፣ በአርማጭሆ ነዋሪዎች ላይ ክተት አውጇል። በአጠቃላይም በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም ሰሞኑን በጎጃምና በጎንደር የተለያዩ ከተሞችና ገጠሮች ቅጥር የነፍሰ ገዳይ ቡድኖችን በማሰማራት ሌሊት ሌሊት ወጣቱን እየፈነ ወደ ማሰቃያ እስር ቤቶቹ እያስገባ መሆኑ ታውቋል።
ይህ ድርጊቱ ፍላጎቱን ሙሉ በሙሉ ሊሳካለት እንደማይችል በመረዳት፣ በመላ ኢትዮጵያ የሚያካሂደው ሌላም ሠፊ የጥፋት ዕቅድ አቅዶ ለተግባራዊነቱ በጥድፊያ እየሠራ መሆኑ እየተሰማ ነው። ይህም መጠነ ሠፊ የሆነ ጥፋት ያነጣጠረው በዐማራና በኦሮሞ ነገዶች ሕዝብ ላይ እንደሆነ ታውቋል። የትግሬ-ወያኔ በእነዚህ ነገዶች ሕዝብ ላይ የጥፋት ተልዕኮውን ለመወጣት ያቀደው ዕቅድ፣ «በዐረብ ኢሚሪቶችና በሻዕቢያ የሚታገዙ አሸባሪዎች፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ እየተንቀሳቀሱ ነው» የሚለውን ሀሳብ የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ፣ በተለይም ሽብርተኝነት ለመዋጋት በሚል ሸሪክ የሆነውን የምዕራቡን ዓለምና የአሜሪካንን ልብ ለማማለል እንደሆነ ይገመታል። በዚህ ረገድ በቅርብ ቀናት ውስጥ የትግሬ-ወያኔ በሐረር፣ በድሬደዋ፣ በጎንደር፣ በባሕር ዳርና መሰል ከተሞች፣ የሕዝብ ክምችት በሚበዛባቸው ቦታዎች፣ በመንግሥታዊ ተቋሞች፣ በመገናኛ አውታሮች ወዘተርፈ ፈንጅ በማፈንዳት እኩይ ዓላማውን በተግባር እንደሚያውል ውስጥ አዋቂዎች አስጠንቅቀዋል። ፈንጂዎችን ራሱ አፈንድቶ፣ «የዐማራ እና የኦሮሞ ጽንፈኞች እንዲህ አደረጉ» በማለት ለደጋፊዎቹ  የተቀነባበረ የሤራ መረጃ በማቅረብ፣ «ሕገ-መንግሥት» ተብየውን አግዶ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ወታደራዊ አገዛዝ በማወጅ፣ በሁሉም ቦታዎች ለወያኔ ጄኔራሎች የመግደልና የማሰር ሥልጣን በመስጠት በዐማራውና በኦሮሞው ነገዶች ሕዝብ ላይ መጠነ ሠፊና አሰቃቂ ዕልቂት ለመፈጸም ቁርጠኛ አቋም መያዙ ታውቋል።
በሰኔ 1980 ዓ.ም. «ነፃ ላወጣህ መጣሁ» ባለውና በራሱ ነገድ በሆነው የሀውዜን ከተማ ነዋሪ ሕዝብ ላይ ያን የመሰለ የተቀነባበረ ሤራ ሠርቶ ሕዝብ ያስጨረሰ ድርጅት፣ «ጠላቶቼ ናቸው» ባላቸው የዐማራና የኦሮሞ ነገድ ሕዝብ ላይ ይህን ዓይነቱን ድርጊት አያቅድም፣ አይፈጽምም፣ አያደርጉትም፣ አይሆንም የሚያሰኝ አመክንዮ አይኖርም። ኢትዮጵያዊ የሆኑትንና «ለትግሬ-ወያኔ ዓላማ አንገዝም፣ አባልም አንሆንም» ያሉትን የትግራይ ልጆች፣ «አባሎቼ ናቸው» የሚል የተቀነባበረ የሐሰት መረጃ፣ ለደርግ የመረጃ አካላት እያቀበለ ወገኖቹን ያስጨፈጨፈ ድርጅት ይህን አያስብም አይባልም። በሂደት እንዳስተዋልነው፣ ወያኔ «አደርገዋለሁ፣ አጠፋዋለሁ» ብሎ ያቀደውንና ያለው በተግባር ከመፈጸም ወደ ኋላ ያለበት አንድም አጋጣሚ አላየንም። ይህንም እኩይ ድርጊት አያደርገውም ለማለት የሚያስችል ምክንያት ለማቅረብ አስቸጋሪ ነው።
የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን፣ ዐማራንና ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖትን አጠፋለሁ ብሎ አቅዶ መነሳቱ ይታወቃል። በዕቅዱ መሠረትም 5 ሚሊዮን ዐማራ አጠፋ። የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አመራርን ከሦሥት ከፈለ፥ የአገር ቤትና ስደተኛ ሲኖዶሶች እንዲሁም ገለልተኛ በሚል። የሃይማኖቱ ነባር ተቋሞችን፣ ለምሣሌ ያህል፥ የዋልድባን፣ የዝቋላ አቦን እና የማኅበረሥላሴን ገዳማትን አቃጠለ፤ ቅጥረ ግቢያቸውን መነጠረ። የሃይማኖት አባቶችን አሰደደ። ቱባ ባለሥልጣኖቹ ዐባይ ፀሐየ፤ ስብሃት ነጋ፣ መለስ ዜናዊ፣ ሣሞራ የኑስ ሌሎችም በአደባባይ፣ «ዐማራና ኦርቶዶክሱን አከርካሪውን ሰብረነዋል፣» «ገድለን ቀብረነዋል» ማለታቸውን አንዘነጋም። እናም ባለፉት 25 ዓመታት ገድለው ካልጨረሱት ውስጥ የቀረውን የዐማራና የኦሮሞን ነገዶች ሕዝብ «አስቸኳይ ወታደራዊ» አገዛዝ በማወጅ ሊጨርሱት ቁርጥ ሀሳብ ማድረጋቸውን የዐማራውና የኦሮሞው ነገድ አባሎች ለአፍታም መጠራጠር አይኖርባቸውም። ስለሆነም፣ የትግሬ-ወያኔ ዝግጅቱን አጠናቅቆ ወደ ጥፋት ተልዕኮው ሳይገባ፣ ዐማሮችና ኦሮሞዎች ዕቅዱን ለማክሸፍ መተባበር ይጠበቅባቸዋል።
ከሁሉም በላይ «ሺህ ጋን ቢታለብ ወይ በገሌ» እንዳለችው ድመት፣ ዐማራው በብሔርተኞቹ ድርጅቶች በቀና ስለማይታይ፣ ልጆቹ በመካከላቸው አለን የሚሏቸውን ጥቃቅን ልዩነቶች በማርገብ፣ በአንድነት በመቆም ለወገናችን መከታ መሆን ይጠበቅብናል። የዐማራው ምሁራንና ፖለቲካኞች በአንድነት መቆም፣ የአንድነት ኃይሉን ለተፈላጊው አጠቃላይ የኢትዮጵያውያን አንድነት ጽኑ መሠረት ስለሚሆን፣ የዐማራው ምሁራን በቅድሚያ የነገዳቸውን አንድነት ዕውን በማድረግ፣ በሌሎች አቻ ቡድኖችና ድርጅቶች ላይ መልካም ተጽዕኖ ማሳደር ይጠበቅባቸዋል። ይህን ለማድረግ ስበቦችን መደርደር አስፈላጊ አይደለም። በወገናችን አንገት ላይ ሳንጃ ተጥሏል፤ በግንባርና ደረቱ ላይ አፈሙዝ ተደግኗል። ስለዚህ ይህ ጊዜ አይሰጥምና በዐማራ ስም የተደራጃችሁ ድርጅቶች ከያላችሁበት «አለን» ብላችሁ በጋራ የምትሠሩበት መንገድ ካሁኑ ካልጀመራችሁ፣ ይህንም ለወገናችሁ በግልጽ ካላሳያችሁ፣ የጥፋቱ አካል እንጂ፣ የመፍትሔው አካል ናችሁ ብሎ ማኅበረሰቡም ሆነ ታሪክ  ሊያወሳችሁ እንደማይችል በእርግጠኝነት መናገር ድፍረት አይሆንም። ስለሆነም ሁላችንም ለዐማራው ኅብረትና አንድነት ኅሊናችን ከፍተን በቅንነት እንነሳ! በዚህ የመከራ ጊዜ የዐማራው ልሂቅ በአንድነት ቆሞ፣ ለወገኖቹ ቤዛ ካልሆነ ምንጊዜም ዐማራው አንድ ይሆናል ለማለት ያስቸግራል። እንኳን የአንድ ታላቅና ታሪካዊ ነገድ ልጆች ቀርቶ፣ በክረምት እባብና ጓጉንቼር በአንድ ጉድጓድ ይኖራሉ። ይህ ክፉ የወያኔ ዘመን ዐማራውን ቀርቶ፣ ዐማራና ኦሮሞውን በአንድ ካላሰላለፈ የኢትዮጵያ አንድነት ርቆ የተሰቀለ ባዶ ተስፋ ከመሆን አያልፍም።

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ዐማራነት ነፃነት፣ ዕኩልነት አንድነት ነው!

ኢትዮጵያ በቆራጥና ጀግና ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች!

መግለጫ በቶሮንቶና አካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሽዋ ከፍለ ሀገር ልጆች የተላለፈ ጥሪ


ላለፉት  ሃያ አምስት ዓመታት ዘረኛውና ክፋፋይ የወያኔ አገዛዝ በመላው  ኢትዮጵያውያን ላይ፤ በተለይ ደግሞ በአማራው ላይ በቃላት ሊገለጽ በማይችል ለሰው አይምሮ በጣም ከባድ በሚሆኑ የግድያ፣ ህዝብ የማፈናቀል፣ የግፍና የበደል ዶፍ ሲወርድበት  የቆየው የጎንደር- በጌምድር ክፍለ ሀገር ሕዝብ በሰላም እየታገለና በትእግስት ችሎ ችሎ ባለፉት 15 ቀናት ውስጥ ከሞት ውጭ የቀረኝ አማራጭ ስለሌለ፤ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ለማንነቴ፣ እንዲሁም የጎንደር ሕዝብ ለመብቴና ለኢትዮጵያዊነቴ የመጨረሻውን መስዋእትነት እከፍላለሁ ብሎ በመነሳቱ የወያኔ የጸጥታና የጦር ሃይል እንደለመደው ለመግደልና ለማሰር ሲሞክር ከሕዝቡ ጋር ግጭት አድርጓል፤ አሁንም ሕዝቡ በመፋለም ላይ ይገኛል። በመጀመሪያ የጎንደር ሕዝብ ቆራጥነቱ፣ ጀግንነቱና ወኔው አኩርቶናል፤ ጥንታዊቷንና ታሪካዊቷን የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን ማውለብለቡ ከልብ አስደስቶናል።  ኖር!  ኖር ! እንላለን።

 በጎጃምም የባህር ዳር ሕዝብ በሰላማዊ መንገድ ለጎንደር ሕዝብ ድጋፉን ሲያሳይ እና ለወያኔ አልገዛም ሲል  በመነሳቱ፤ በአግአዚ ጦር በጭካኔ መጨፍጨፉና መደብደቡ ቢያሳዝነንም፣ ቢያስቆጣንም የሕዝቡ ቆራጥነትና እምቢተኛነት እጅግ አኩርቶናል፤ ከጎንህም ነን አለንልህ እንላለን። ችግሩ ችግራችን፣ ስቃዩ ስቃያችን፣ ሞቱ ሞታችን ነውና  ክጎንደር - በጌምድር ክፍለ ሀገር ከተወለዱ ልጆቹ፣ ክጎጃም እና ከወሎ ከ/ሀገር ከተወለዱ ወንድሞቹና እህቶቹ ጋር በመወያየትና በመመካከር አስፈላጊውን ሁሉ እርዳታ ለመስጠት ነሐሴ 1 ቀን 2008 ( Aug 7, 2016) ባደረግነው አስቸኳይ ስብሰባ በአንድ ድምጽ ወስነናል፤ ቃል ገብተናል። ስለዚህ ይህን ታሪካዊና የአማራ ሕዝብ ኢትዮጵያዊ ትግል በምትችሉት መጠን እርዳታና ድጋፍ እንድታደርጉ የትግሉም አካል እንድትሆኑ የአገርና የሕዝብ አድን ጥሪ እናስተላልፋለን።


 ኢትዮጵያ በቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘላለም  ትኖራለች! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ! 

ቶሮንቶ፤ ካናዳ   እርዳታና ድጋፍ ለማድረግ ለምትፈልጉ፤ 647 219 2804  ይደውሉ