Sunday, November 29, 2015

ገሃዱ አሰቃቂ ረሃብ እና የማወናበጃው «የልማት ዕድገት» በኢትዮጵያ

በያዝነው ዓመት በአገራችን በኢትዮጵያ አስከፊ የርሃብ አደጋ እንደተስፋፋ ከተለያዩ የዜና አውታሮች ይደመጣል። በተቃራኒው ደግሞ የትግሬ-ወያኔ የሚቆጣጠራቸው የመገናኛ ብዙሃን በአገዛዙ ጥረት ስለተገኘው የልማት ትሩፋት ይለፍፋሉ። በአንድ አገር በአንድ ጊዜ ሁለት እጅግ ተቃራኒ ሁኔታን የሚያንጸባርቁ ዜናዎች ሲደመጡ እውነቱን አንጥሮ ማሣዬት ተገቢ ነው። ስለሆነም በዚህ መግለጫ ዕውነቱ የትኛው እንደሆነ ብቻ ሣይሆን የመፍትሔ ኃሣቦችንም ለማመልከት ተሞክሯል።

በአገራችን በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ጊዜያት ከፍተኛ የርሃብ አደጋዎች ተከስተዋል። በዚሁ ሳቢያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን አልቀዋል፤ አሁንም እያለቁ ነው። ለአብነት ያህል በንጉሡ ዘመን በ1958 ዓ.ም. እና በ1965-66 ዓ.ም. እንዲሁም በደርግ ጊዜ በ1977 ዓ.ም. የተከሰቱት የርሃብ አደጋዎች በአስከፊነታቸው እና በሕዝብ ጨራሽነታቸው የሚጠቀሱ ናቸው። በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን ርሃብ አልፎ አልፎ የሚመጣ ሣይሆን በየዓመቱ ከ7 እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያንን ለችጋር ማጋለጡ እና የሰው እጅ ተመልካች እንዳደረጋቸው ይታወቃል። ይህም ሆኖ እንደ ዘንድሮው እጅግ የከፋ አልነበረም። በመሆኑም በዚህ ዘመን ርሃብ በኢትዮጵያውያን ላይ ቤቱን ሠርቷል ለማለት ያስደፍራል። ስለሆነም ሦሥቱም ተከታታይ አገዛዞች አንዱ ካለፈው ገዢ ስህተት ሊማር ባለመቻሉ ችግሩ እየተባባሰ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም።

በሦሥቱም የአገዛዝ ዘመኖች ለርሃቡ መንስኤ ተደርጎ የሚቀርበው ድርቅ ነው። ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ሲከሰት ድርቅ ይፈጠራል። ስለዚህ ድርቅ የተፈጥሮ ክስተት በመሆኑ ምንጊዜም የአየር ንብረት አካል ነው። ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወንዞች እና ሐይቆች ያሏት፣ በተፈጥሮ ኃብት የታደለች አገር ናት። ስለሆነም ሕዝብን የሚወክል እና ሕዝባዊ ተሳትፎ ያለው ሥርዓት ካለ፤ የድርቁን ተፅዕኖ ለመቋቋም ይቻላል። ይኽውም፥ ወንዞችን በመገደብ እና የሐይቆችን ውኃ በመጠቀም ከፍተኛ የመስኖ እርሻ ማስፋፋት ይቻላል። እንደሚታወቀው ከ85% የማያነሰው የአገራችን ሕዝብ ከእጅ-ወደ-አፍ በሆነ የግብርና ኢኮኖሚ ዘርፍ የተሰማራ ነው። ይኽ የአገራችን ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው ዘርፍ እስካሁን ድረስ የሚዘወረው ከጥንት ጀምሮ ባልተቀየረ ኋላቀር የበሬ እርሻ ነው። «ይህ ኋላቀር የእርሻ ዘይቤ ሣይቀየር አገሪቱ እንዴት በልማት ትሩፋት ልተምነሸነሽ ትችላለች?» ብሎ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።

አሁን በአስከፊ ሁኔታ የተከሰተው ርሃብ በሥልጣን ላይ ያለው ፀረ-ሕዝቡ እና ፋሽስቱ የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ የፈጠረው ነው። እንዴትስ ፈጠረው? ምክንያቶቹ፥

  • የኢትዮጵያ መሬት ብቸኛ ባለቤት የሆነው የትግሬ-ወያኔ ገዥ ኃይል ገበሬውን እጅግ አነስተኛ በሆነ የእርሻ መሬት ስለወሰነው፣ ገበሬው በቂ ምርት ማምረት አልቻለም።

  • ገበሬው የተበላሸ እና ጊዜው ያለፈበት ማዳበሪያ በግድ እንዲገዛ በመደረጉ መሬቱ ተጎድቷል፣ ለምነቱም ቀንሷል።

  • ገበሬው በቀላሉ ገንዘብ የሚገኝበት ሰብል (cash crop)፥ እንደ ጫት፣ አበባ ወዘተርፈ .... እንዲያመርት በሥርዓቱ በመገፋፋቱ የምግብ እህል ምርት አሽቆልቁሏል።

  • በወያኔ የዘር ማጽዳት ፖሊሲ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ገበሬዎች፣ በተለይም ዐማሮች፣ ከነቤተሰቦቻቸው ከቀያቸው በመፈናቀላቸው ምክንያት አምራቾች ሣይሆኑ የዕለት ምግብ የሚመፀወቱ ምንዱባን ሆነዋል።

  • በፍጥነት እያደገ የመጣው የሕዝብ ብዛት የእርሻ መሬት ጥበት በማስከተሉ፣ ሥራ ለመፈለግ ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሰውን ገበሬ ቁጥር እንዲያሻቅብ አድርጎታል። ይህም በእርሻው ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ውድቀት አስከትሏል።

  •  የትግሬ-ወያኔ ሆን ብሎ ከፍተኛ የደን ክምችት ያላቸውን ቦታዎች በየጊዜው በእሳት በማጋየቱ ምክንያት የአገራችንን የተፈጥሮ ሚዛን እና የአካባቢ አየር ንብረት በማዛነፉ ድርቅ በተደጋጋሚ እንዲከሰት አድርጓል።

  • የትግሬ-ወያኔ ከፍተኛ ለምነት ያላቸውን የእርሻ መሬቶች እስከ መቶ ዓመት በሚደርስ የጊዜ ገደብ በሊዝ መልክ ቸብችቧል። መሬት በሊዝ የሚገዙት ራሱ የፈጠራቸው የአገር ውስጥ ከበርቴዎች እንዲሁም የውጭ አገር ከበርቴ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች ናቸው። እነዚህም ከበርቴዎች እና ኩባንያዎች የሚያመርቷቸውን ምርቶች የሚያቀርቡት ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሳይሆን በቀጥታ ለውጭ አገሮች ገበያ እና ሸማች ይልካሉ። ስለሆነም ኢትዮጵያውያን በእጅ-አዙር ቅኝ አገዛዝ ሥር ወድቀው የበይ

ገሃዱ አሰቃቂ ረሃብ እና የማወናበጃው «የልማት ዕድገት» በኢትዮጵያ


ተመልካቾች በመሆናቸው እና በአገራቸው ውስጥ የሥራ እድል ሊያገኙ ስለአልቻሉ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣት አምራች ኃይሎች ለሥራ እድል ፍለጋ ወደ አረብ አገሮች ለመሰደድ ተገድደዋል።

  •  ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተብሎ በእርዳታ እና በብድር መልክ ከውጭ የሚገባው ብዙ ቢሊዮን ዶላር፤ እንዲሁም የአገራችን አንጡራ ኃብት በትግሬ-ወያኔዎች ያለማቋረጥ ይዘረፋል። ይህም ድህነት እንዲሠራፋ አድርጓል።

  • የድርቅን አደጋ ተቋቁሞ ርሃብን በዘላቂነት ለመግታት ሠፋፊ የመሠረተ-ልማት ግንባታዎች ማከናወን ወሣኝ ነው። ሆኖም ባለፉ አገዛዞች ከነበረው አዝጋሚ የመሠረተ-ልማት ግንባታ በከፋ ሁኔታ በዘረኝነት መንፈስ የትግራይ ክልል የተባለው ብቻ ተጠቃሚ እንዲሆን ይደረጋል። ከዚህ በተጨማሪም የአገዛዙ ሥርዓት ዕድሜውን ለማራዘም ከአገሪቱ በጀት ከግማሽ የማያንሰውን ለስለላ ሥራ ያውላል። ስለዚህ በርሃብ ወቅት ሕዝቡን ከአደጋ ለመታደግ የሚያስችሉ ከፍተኛ የእህል ጎተራዎች አልተሠሩም፤ ጤና ለመጠበቅ የሚያስችሉ ተቋሞች አልተገነቡም፣ እንዲሁም ወደ ገጠሩ እንደልብ ለመግባት የሚያስችሉ የገጠር መንገዶች አልተዘረጉም።

  • የትግሬ-ወያኔ በሚከተለው የከፋፍለህ-ግዛው ፖሊሲ ምክንያት ሕዝባችንን በዘር፣ በጎሣ እና በኃይማኖት እየለያየ ያጫርሳል። የእርስ በርስ ግጭቶች እና ጦርነቶች በተለያዩ አካባቢዎች በመከሰት ላይ ናቸው። ለአብነት ያህል፥ በጎንደር፣ በወሎ፣ በሸዋ፣ በጎጃም፣ በአርሲ፣ በወለጋ፣ በባሌ፣ በኦጋዴን፣ በጋምቤላ፣ በሲዳሞ፣ በጋሙ-ጎፋ፣ በከፋ፣ ወዘተርፈ …. በተደጋጋሚ ጊዜያት ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዲጫረስ ተደርጓል። ይህም የአምራቹን ኃይል ቁጥር የሚያመናምን፣ በተቃራኒው ለርሃብ አደጋ የሚጋለጠውን ዜጋ የሚያበዛ ነው።
ርሃብ እና ችጋር እንደ ደራሽ ጎርፍ በድንገት አይመጡም። በመጀመሪያ ድርቅ ሲከሰት ሰብሎች ይጠወልጋሉ፣ ምርትም አይገኝም፤ ይህ በትንሹ ከሦሥት ወራት ያላነሰ ጊዜ ይወስዳል። በድርቅ ጊዜ ከብቶች በግጦሽ ሣር እና በውኃ እጦት ይኮሰምናሉ፣ ከዚያም በገፍ ያልቃሉ። ይህ ሁሉ በአንድ ቀን ጊዜ አይከሰትም። ስለዚህ ከድርቅ ጋር የተያያዘን ችጋር ለመቋቋም በአንድ አገር የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ እና የዝግጁነት ሥርዓት ካለ ሕዝብ ለርሃብ አይጋለጥም። ይህ ተሞክሮ ረሃብን ታሪክ ለማድረግ በበቁ አገሮች በተግባር ታይቷል። በእኛም አገር ለአጭር ጊዜም ቢሆን ምልክቱ ታይቶ ነበር። በትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ግን የሚደረገው ሆን ተብሎ የዚህ ተቃራኒ ነው። በአፄ ኃይለሥላሤ ዘመን «የድርቅ ኮሚሽን» በመባል የተቋቋመው መሥሪያቤት በደርግ ዘመን እጅግ ጎልብቶ የአገሪቱን ሕዝብ ከከፍተኛ የርሃብ መቅሰፍት ለመታደግ የሚያስችል ተቋም ለመሆን በቅቶ ነበር። በተደጋጋሚ በርሃብ ሲጠቁ የነበሩ ዜጎችን ለም እና ለኑሮ ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት ባላቸው አካባቢዎች በማስፈር ከተረጂነት ወደተትረፈረፈ ምርት አምራችነት ለመቀየር ተችሎ ነበር። ዛሬ ግን በኢትዮጵያ ውስጥ ከገጠር እስከ ከተማ፣ በሁሉም ሥፍራ የዕርዳታ እህል የማይሠፈርለት ዜጋ በቁጥር ነው። ያም ቢሆን ውጭ አገር ያሉ ዘመዶቹ ገንዘብ የሚልኩለት፤ አልያም የወያኔ ሹመኛ ከሆነ ብቻ ነው። በተለይ ደግሞ ዐማራውን ለይተው ከሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በዘር ማጽዳት ዘመቻ በማፈናቀል በርሃብ እና በችጋር ይፈጁታል። «ለወያኔ አገዛዝ አንንበረከክም» ያሉትን አፋሮችን እና ሶማሌዎችን በርሃብ ይቆላሉ። በአጠቃላይ ለርሃብ እና ለችጋር የሚያጋልጠው ብልሹ እና ኃላፊነት የጎደላቸው አገዛዞች የሚፈጥሩት ችግር እንጂ ድርቅ ብቻውን ሊሆን አይችልም። ድርቅ ብቻውን ርሃብ የሚያመጣ ቢሆን ኖሮ የዝናብ ጠብታ የማያውቁ አገሮች ዜጎች ገና ጥንት ከምድረ-ገፅ ይጠፉ ነበር።

አንዳንድ ጸሐፊዎች «ፖለቲካ እና ሰብዓዊነት መያያዝ የለበትም» የሚለውን ኃይለ-ቃል ደጋግመው ይናገራሉ። ሆኖም ይህን የሚናገሩት በአፄ ኃይለሥላሤም ሆነ በደርግ የአገዛዝ ዘመኖች ለተከሰቱት የርሃብ ችግሮች ምንጮቹ የአገዛዝ ሥርዓቶቹ መሆናቸውን ሲያስተጋቡ የኖሩት ናቸው። ዛሬ ታዲያ ካለፉት ሁለት የአገዛዝ ሥርዓቶች እጅግ በከፋ ሁኔታ ኢትዮጵያውያንን ለማያባራ የርሃብ ችግር የዳረጋቸው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ሆኖ ሳለ ከዚህ ፍርድ እንዴት ሊያመልጥ ይችላል? የትግሬ-ወያኔዎች ኢትዮጵያውያንን በርሃብ እያቆራመዱ ዶላር ለመሰብሰብ የበሰለ ምግብ ወደ ውጪ አገሮች ይልካሉ። በአገር ቤት ግን ዜጎች የሚጣል የምግብ ትርፍራፊ በጉርሻ መልክ እየገዙ ሕይዎታቸውን ለማቆየት ይፍገመገማሉ። በየዓመቱ በርሃብተኛው ስም በቢሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ በዕርዳታ መልክ ከውጪ የሚለገሣቸው ወያኔዎች ገንዘቡን ወደ ውጪ አገሮች መልሰው እያሸሹ እነርሱ ቢሊዬኔሮች ሆነዋል፤ አሁንም ግን በርሃብተኛው ስም ከውጪ ዕርዳታ ይለመናል። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን በማንኛውም የአገር ውስጥም ሆነ ዓለም-አቀፍ ድርጅት አማካይነት በርሃብተኞች ስም የሚደረገውን ዕርዳታ ፋይዳው ምን እንደሆነ ቆም ብለን ልናስብብት ይገባናል። ለወገን ደራሹ ወገን ነውና ለርሃብተኛ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ካለማንም ጣልቃ ገብነት በቀጥታ የዕርዳታ እጃችንን እንዘርጋላቸው። ሞረሽ-ወገኔም ለዚህ የተቀደሰ ተግባር አስፈላጊውን መሠናዶ ያደረገ ስለሆነ ዕርዳታችሁን በተገቢው ሁኔታ ለማድረስ ዝግጁዎች ነን፤ በአድራሻችን ጠይቁን። ሆኖም ምንጊዜም ማስታወስ ያለብን ዘለቄታዊ መፍትሔ የሚመጣበትን መንገድ ነው። የትግሬ-ወያኔ ካለ፣ ርሃብ እና ችጋር ይቀጥላል። ስለሆነም ለዚህ ዓይነቱ ሁኔታ የዳረገን የችግራችን ሁሉ ምንጭ የሆነው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ መወገድ አለበት። ስለዚህ ኢትዮጵያውያን ከአጽናፍ እስከ አጽናፍ በአንድነት ተንቀሳቅሰን የችግሮቻችን ሁሉ ምንጭ የሆነውን የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ ለማስወገድ ቆርጠን እንነሣ።

ርሃብን ታሪክ ለማድረግ ቆርጠን እንነሣ!

የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ በተባበረ ክንድ እናስወግድ!

ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማክሰኞ ኅዳር ፲፬ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር ፫2

Thursday, November 5, 2015

ላጲሶን ለማወቅ በትዕግስት ያንብቡት!!!

መሰለ ተሬቻ ከበደ፣ ሐሙስ ጥቅምት ፳፭ ቀን ፪ሺህ፰ ዓም

 ምንጭ፦ https://www.facebook.com/amanuel.abinet/posts/773206409456281

 ዶክተር ላጲሶ ለኢትዮጵያ መሀበራዊ፣ ባህላዊና ፖለቲካዊ እሴቶች ምንም ክብር የሌላቸው፤ የኢትዮጵያንም ታሪክም ሆነ የታሪክ ምሁራንን እንደው እንዳሻቸው ለመጠልሸት ሳይታክቱ ከአርባ አመታት በላይ የተጉ፤ ይህንንም የሚያደርጉበትን ምክንያት “እኔ ብቻ ነኝ አዋቂ” ከሚለው ትዕቢታቸው በሻገር ለማወቅ የሚያዳግት ሰው ናቸው፡፡ ከልጅነቴ አንስቶ እኚህን ሰው ሳወቃቸው የኢትዮጵያን ታሪክ እና የታሪክ ሊቃውንት ሲያጠለሹ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትግር፣ አማራ፣ ሀድያ፣ ሀርላ፣ … ወዘተ እያሉ ሲከፋፍሉ ሲሆን እጅግ በሚያስደንቅ ሀፍረተ-ቢስ በሆነ መንግድ እየተገለባበጡ ከመጣው ስርዓት ጋር እንደ ኮሶ ተውሳክ እየተጣቡ በዚህ መያዣ መጨበጫ በሌለው ትንታኔያቸው/አሉባልታቸው ሲያታልሉበት ኖረዋል፡፡ ደረግ ስልጣን ላይ በነበረ ዘመን ከማርክስ በላይ ማርክሲስት ሆነው ያልዘላበዱት የማርክሲስት ርዕዮታለም አልነበረም፡፡ እኔ አንደኛ ክፍል እያለሁ አንስቶ የእርሳቸውን ህልመኛ ርዕዮት-አለም ስጋት አድጋለሁ፡፡ ዛሬ ታዲያ የዛን ግዜ ስብከታቸውን ባስታወስኩ ቁጥር ለብቻዬ የምስቅበት ግዜ ብዙ ነው፡፡ በኋላ መቶ ሰማንንያ ድግሪ ተሸከርክረው የጎሳ ብሄርተኝነት አቀንቃኝ ሆነው ስናይ እኔና ጓደኞቼ እጅግ ነበር የተደናገርነው፡፡ ይህ ተውልድ እኝህን ሰው እኩይ ስራ አበክሮ መርምሮ ወግድ ወዲያ ሊላቸው የተገባ ነው፡፡ 

አሁን እዚህ የሰጡትን ቃለ ምልልስ አብክሮ ላደመጠው እንኳን ከእጅግ ተራ የቦታና የግዜ የእውነታ/fact ስህተት እስከ ከፍተኛ የሀሳብ ፍልሰት በግድፈት የተሞላ እንደ ሆነ ለማወቅ አያዳግተውም፡፡ አሁን በቅርብ በሰጡት ቃለ-ምልልስ የኢትዮጵያ የደብተራ አሉባልታ የኢትዮጵያን ታሪክ ያጠኑት ምሁረን ማለትም ስርገው ሀብለስላሴ፣ ታደስ ታምራት፣ መርድ ወልደ አረጋይ፣ ባህሩ ዘውዴ … እና ሌሎችም ደብተራዎች ናቸው፡፡ የኢትዮጵያም ታሪክ በደብተራነት ጉድፍ የተሞላ ነው፤ ተስተካክሎ መፃፍ ይኖርበታል ብለው ነበር። አሁን በዚህ ቃለምልልስ ደግሞ አዋቂ መስለው የእነኚህኑ ምሁራን ስራ እያዛቡ መልሰው ሊተርኩት ሲዋጁ ይስተዋላሉ፡፡

«አማራ የአገው ወታደር የነበረ ነው» ይሉና መልሰው እራሱን የቻለ፣ የሰለሞን ስረው መንግስትን የተከል እና ከግብፃውያን እየዶለተ ሌሎችን ጎሳዎች እያረደ የገዛ ነው ይላሉ፡፡ ንግስት እሌኒ የሐድያ ሙስሊም ነበሩ፣ እጅግም ተፈርተው 75 አመታት ከልጅ ልጆቻቸው ጋር አንቀጥቅጠው ገዝተዋል ይሉና፤ የሰለሞን ስረው መንግስት የአማራዎች ነበር ይላሉ፡፡ እንደ አማራ ፈርጀው ያቀረቡትን አፄ ዘርዓ ያቆብን መልሰው አክሱምን እየሩሳሌም አደረገ ይሉታል፡፡ አፄ ዘርዓ ያቆብ በ1416 ዓ.ም ሞተ ይሉና መልሰው ደግሞ በ1550 ዓ.ም የደብረ ምጥማቅን የአበው ስብሰባ ጠርቶ በቅዱስ ኢዎስጣጤዎስ እና በቅዱስ ተክለ ሐይማኖት ሀይማኖተ ቀኖናን በተመለከተ ለዘመናት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ-ክሰርስቲያን የነበረውን መከፋፈል አስወገደ ይላሉ፡፡ በኢትዮጵያ የብሉይ ኪዳንን፣ የታቦት ስርዓትን፣ አምልኮ ማርያምን… ወዘተ የደነገገው ዘርዓ ያቆብ ነው … ወዲያም ሲል ክብረ-ነገስት እና ፍትሀ ነገስት በአንድ ወቅት ተተረጉመው የሰለሞን ስረው መንግስት መለኮታዊ ስልጣን ማስጠበቂያ ሆኑ … ውዳሴ ማርያም መጀመሪያ በፈረንሳይ ተፃፈ ብለው ያበቁና መልሰው ደግሞ ከአረብኛ ተተረጎመ ይላሉ፡፡ … እነኚህ ሁሉ አንድ ታሪክን አነበብኩ ከሚል ሰው የማይጠበቁ ለይቅርታም እጅግ የሚያስቸግሩ ስህተቶች ናቸው፡፡

የብሉይ እመነት በኢትዮጵያ እና በአረቢያ ገልፍ ከክርስትና በፊት የነበረ ሀይማኖት ስለመሆኑ እጅግ ብዙ ተመራማሪዎች አረጋግጠዋል፡፡ የታቦትንም ስርዓት አፄ ዘርዓ ያቆብ አልደነገጉም፡፡ ከከሳቴ ብርሀን ዘመን እንስቶ የነበረ ነው፡፡ ክብረ ነገስት በዓረብኛ እና በሌሎች ቋንቋዎች ከተፃፉ ልዩ ልዩ ታሪኮች ተወጣጥቶ የተቀናበረ ሲሆን የተፃፈውም በ13ኛው መ.ክ.ዘ እንደሆነ ይታመናል፡፡ ፍተሃ ነገስት ግን መጀመሪያ የተፃፈው አንድ አብድ አል-አሳል በተባለ ግብፃዊ ስሆን በ15ኛው መ.ክ.ዘ እንደ ተተረጎመ ያታመናል፡፡ ከ16ኛው መ.ክ.ዘ መባቻ በፊት ግን ስራ ላይ ስለመዋል ምንም የተገኘ ማስረጃ የለም፡፡ በአፄ ዳዊት ዘመን የተተረጎመው ታምረ ማርያም እንጂ ውደሴ ማርይም አይደለም፡፡ ዘርዓ ያቆብ የነገሱት እ.ኤ.አ ከ1434 እስክ 1468 ዓ.ም ሲሆን የደብረ ምጥማቅ ጉባኤም የተካሄደው እ.ኤ.አ በ1450 ዓ.ም ነበር፡፡ የኢዎስጣጤዎስ የሀይማኖት ንቅናቄ ከብሄርም ሆነ ከደቂቀ አስጢፋኖሶች ጋር ምንም የማይያያዝ መሰረቱን በደብረ ቢዘን ያደረገ የስርዓተ ቀኖና አጠባበቅ አለመግባባት ነበር፡፡ … ንግስት እሌኒ ሀድያ ይሁኑ የደዋሮ ተወላጅ እስከ ዛሬ ምሁራን ሙሉ ለሙሉ አልተግባቡትም፡፡ ነገር ግን ብዙሀን ምሁራን ግን የደዋሮ ተወላጅ እንደነበሩ ይስማማሉ ።

ዶ/ር ጌታሁን ዴሊቦ የከምባታ እና ሀድያ ተወላጅ ሲሆኑ የአንደኛ ደረጃ ትምህረታቸውን የሱዳን ኢንቴሪየር ሚሲዎን አቋቁሞት በነበረው የኩየራ የስጋ ደዌ ተጠቂ ሰፋሪዎች ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በናዝሬት ባይብል አካዳሚ እና የዶክትሬት ትምህርታቸውን በሆዋርድ በተባለ የአሜሪካን ጥቁሮች ዩንቨርስቲ ስለመከታተላቸው ይታወቅ እንጂ፤ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ድግሪያቸውን የት እና እንዴት ባለ ሁኔታ እንደተከታተሉ አይታወቅም፡፡ የዶክተሬት ድግሪ የሟሟያ ስራቸውን ለመረመረው፤ ከታሪክ አጠናን መንገድ እስከ መረጃ አሰባሰብ በበርካታ ግድፈቶች የተሞላ፣ እንኳን ለዶክተራል ለመጀመሪያ ድግሪ ሟሟየነት የማይመጥን፣ ከዚህ የተነሳ ምራቅ በዋጡ ምሁራን ለማጣቀሻነት ያልዋለ/የማይውል በሚሲዎኖች የዘመናት አትዮጵያን የማፍረስ የአሉባልታ ሴራ የተሞላ የሴራ ድርሳን ስለመሆኑ ለመረዳት አያዳግተውም፡፡ የእርሳቸውን ስራ ሲጠቅሱ ያየሁት ከመረጃ ይልቅ በስሜት ሞገድ የሚናጡ ጎሰኛ የታሪክ ፀሀፊዎችን ብቻ ነው፡፡ ቀድሞ ነገር ለግዕዝ ቋናቋ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው ሰው እንደሆኑ እየተዋቅ የታሪክ መረጃዎች በግዕዝ ቋንቋ ስለተያዙበት የመሐከለኛው ዘመን እና የቤተ-ክርስቲያን ጉዳይ እርሳቸውን ማናገር ተገቢ ነገር መስሎ አይታይም።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉበትን ሁኔታ ለሚመረምር ግን የእኝህን ሰው የአመታት የአትዮጵያን ታሪክ የማጠልሽት አባዜ ለመረዳት ከባድ አይሆንበትም፡፡ የከንባታና የሀድያ ማህበረሰብ ለሚሲዎን ሐይማኖታዊ ተልዕኮ የተመቸነው ከሚል እሳቤ በተሰራ አፍትሀዊ መድሎ፤ በእነ አቶ የሀንስ በኪሶ አቅራቢነት በእነ ሙላቱ ባፋ አስተኝታኝነት፤ የስጋ ደዌ ተጠቂ ያልሆኑት የከምባታ-ሀድያ ተወላጆችን በኩየራና በአከባቢው ከመስከረም 1944ዓ.ም ጀምሮ ሀገሬውን ከመሬቱ እየገፉ እንዲሁም የሌላ ብሄር ሰፋሪን ወደ ጎን እየከሉ እንዲሰፍሩ የህክምና አገልግሎቱም የበተለይ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተደረገብት ሁኔታ ውሎ አድሮ በ1966 እና 1983 ዓ.ም የስርዓት ለውጦች ወቅት ምን እነዳስከተለ በተጨባጭ ይታወቃል፡፡ በትንሹ በ1983 ዓ.ም የፖለቲካ ለውጥ ወቅት ከ2000 በላይ የከንባታና የሀድያ በሀገሬው የኦሮሞ ብሄር ተወለጆች ጥቃት እንዲፈናቀሉና ሀብት ንብረታቸው ለዝርፊያ እንዲዳረግ የተደረገበት መሰረታዊ ምክንያት ደ/ር ጌታሁን ዴሊቦን ከልጅነት በመድሎ ኮትኩቶ ያደረጀ የሚሲዎኖች ኢፍትሀዊ ስራ ነበር፡፡ 

ይህን እርሳቸውን የፈጠረ የሚሲዮን መድሎአዊ አሰራር ለማየት የማይዳዱት የዶ/ር ጌታሁን ምሁራዊ እይታ፤ “የአማራን መድሎ” ለማየት ሲተጋ፤ “አያ ጅቦ በማያውቁት ሀገር ቁረበት አንጥፉልኝ አለ” ሚለውን ተረታዊ ምሳሌ ያሳስባል፡፡ ታዲያ ይህ የሚሲዎኖች መድሎአዊ አሰራር ከመሬት ስሪት ጋር ተቆራኝቶ የፈጠረውን መሀበራዊ ቀውስ፤ ሌላኛው የተደናገረ የጎሳ ብሄርተኛ የታሪክ ተመራማሪ ነኝ ባይ ጌታሁን በንቲ የአማሮች ነፍጠኞች ኢፍትሀዊ ሴራ እንደሆነ አድርጎ በሁለኛ የድግሪ የሟሟያው አቀረበው፡፡ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስስ አይመለስ እንዲሉ ይህንኑ የተንሸዋረረ የታሪክ አረዳዱን፤ ጌታሁን በንቲ ለዶክተራል ድግሪው የአዲስ አበባን ታሪክ ሲፅፍ ደገመና አረፈው፡፡ የዛሬው ለጲሶ፤ ቅድመ 66 ዓብዮት ጌታሁን ዲሌቦ፤ ሀፍረትን የማያውቁ… ሀገር ለማፍረስ የተጉ የምሁርነትን ካባ በተግባር ሳይሆን በአስመሳይነት የተጎናፀፉ ሰው እንደሆኑ ማወቁ እጅግ ጠቀሚ ነው፡፡ 

”የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ” ከድጡ ወደ ማጡ

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔአለም ለፕሮፈሰር ጌታቸው ሀይሌና ለሌሎችም በማለት ያስነበበውን ይቅርታ መሰል መጣጥፍ በፌስቡክ ተለቆ ስላየሁት ደጋግሜ አነበብኩት። በመጀመሪያ ”ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ እለት” እንዲሉ የፕሮፌሰር ጌታቸው ሀይሌ ምርጥና አፋጣኝ ፅሁፍ ምን ይህል ቅጥፈት ቢበዛም ቁጥራቸው ትንሽም ቢሆን ውነተኞች እንዳሉ አስመስክረዋልና ምስጋናየ ይድረሳቸው። አንባቢዋቼ ለነገሩ ግንዛቤ እንዲኖራችሁ በማሰብ መንስዔውን ለመጠቆም እሞክራለሁ።

ባለፈው የሳምንቱ እንግዳ በተባለ የኢሳት ፕሮግራም የታሪክ ተመራማሪ በሚል ሽፋን ጋዜጠኛ ፋሲል ዶክተር ላጲሶን በቃለ መጠይቅ አቅርቦ አማራን እንዳይበላ እንዳይዘራ አድርገው ይዘልፋሉ ያጣጥላሉ። እሳቸውም እንደ ታሪክ ምሁር ሳይሆን እንደ አንድ አማራን አጥብቆ የሚጠላ ጎጠኛ አማራው የሰራውን፣ ታሪኩን፣ የፃፈውን ሁሉ በማዋደቅና በማናናቅ ታሪክ አልባ ከማድረጋቸውም በላይ አዲስ ታሪክ ሊሰሩ እንዳሰቡ አሳውቀውናል። እንግዲህ የሄ የቀረበው ”የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ነኝ” በሚለው ኢሳት ነው። ያኔ ታዲያ ጋዜጠኛ ፋሲል ተጠያቂው የተጠየቁትን ትተው ማለት የፈለጉትን ሲቀባጥሩ ሁሉንም በፀጋ ተቀብሏል። ኢሳትም እንደልማዱ አማራና ኢትዮጵያዊነት ሲወቀጥ በጀ ብሎ አለፈው። ምክንያቱም እራሱን የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ነኝ የሚለው ኢሳት የግንቦት ሰባት ልሳን ብሎም በዘር የተደራጁና ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ አጥብቀው የሚተጉ ቡድኖች ጠበቃ በመሆኑ ነው። 

ስለሆነም በኢትዮጵያ አንድነት የማያምኑና አማራውን በሀሰት በጡት ቆራጭነት በበዳይነት የሚወነጅሉት እነ ተስፋየ ገብረ አብና አያሌ አገር አጥፊዎች ሲስተናገዱ ለሀገርና ለወገን የሚያስቡ ውነቱን ውነት ሀሰቱን ሀሰት በማለት የሚታወቁት እነ አቶ ጌታቸው ረዳና ዶክተር አሰፋ ነጋሽ ፕሮፌሰር ሀይሌ ላሬቦ ወዘተ የመሰሉ ምርጥ የቁርጥ ቀን ልጆች በኢሳት አካባቢ ዝር እንዳይሉ በጥብቅ ይከለከላሉ። 

ለዚህም በቂ መረጃ እንዲሆነኝ ከራሱ ከፋሲል ፅሁፍ ብነሳ፣ ፋሲል በፅሁፉ ላይ ፕሮፌሰር ጌታቸው በኢሳት የሚፈፀመውን በደል ታዝበው ትክክል አለመሆናቸውን ሲገልፁ ከታሪክ በማጣቀስ ከታሪክ ማህደር ያገኙትና በፅሁፋቸው ላይ ያሰፈሩት ” "አረሚዎች ኦሮሞዎች) የክርስቲያኑን ሀገር (ዋካትን፣ ጠጠራን፣ ምድረ በረሐን፣ መቅደላን) ሊያወድሙ ተመካክረው ከብዙ ቦታ ዋጃ ላይ ከተቱ። ምክንያቱም፣ አረሚዎች፣ (አዲስ ንጉሥ) ሲያንግሡ የነገሠው አገር የማውደም ልምድ አላቸው። በዚያን ጊዜም ዳዩ ዳባ የሚሉት ነግሦ ነበረ። አገር የሚያወድሙበትና ጦር የሚያውጁት በኅዳር ወር በሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዐል ዕለት ነበር። . . . እመቤታችን ማርያም አረመኔዎቹ አገሯን ለማጥፋት ጨክነው እንደተነሡ ስታይ፥ሳያስቡት፣ ወደምድረ አዳል መርታ ጠላቶቻቸው (ሙስሊሞቹ) እጅ ላይ ጣለቻቸው። ከ12 ነገሥታት የጎሳ መሪዎች) አንድ ንጉሥ ብቻ ተረፈ፤ ከሠራዊቱም አንዳንድ ለወሬ ነጋሪ ተርፎ ይሆናል።" የሚል ይገኝበታል።

ፋሲል ታዲያ አሁንም ይህ ጽሁፍ ፕሮፌሰር ጌታቸው.ኢሳት ላይ ልናገረው ቢሉ የሚፈጥረውን አደጋ ተመልከቱ ባማለት ያስፈራራናል። ነገሩም በሁላችንም ዘንድ ሰርፆ ገብቶ እንዲዘገንነን ለማድረግ ይሞክራል። ውነተኛ ታሪክ ምኑ ነው የሚያሳፍረው? ምኑስ ነው የሚያስፈራው? አንዳንዴ ታሪክን እንደታሪክ ተቀብሎ ማለፍ የተሳነው ሁሉ ተሰብስቦ ውነት አይተንፈስ፣ ተበደልን የሚሉት ውሸትም ቢሆን ይውጣላቸው ብሎ ማጃጃል አለበለዚያም የኦሮሞ ነፃ አውጭ ነን ባይ ምሁር ተገዝቻለሁ ጠላቴ አማራ ገዝቶኛል ስላለ ሀይለኛ ንጉስ ነበራችሁ ብሎ መንገሩ የማያውቁትን መንገር አላዋቂነታቸውን ስለሚያሳይ ይቅር ማለት ይሆን? ለማንኛውም በነጋ በጠባ ምስኪን አማራ ሲፈናቀል ሲገደል ሲታረድ ከገደል ሲወረወር ገዳዩን ወዳጅ ከማድረግ ባለፈ ውነት ተድበስብሶ አጥፊዎች ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የሚንቆለጳጰሱበት መድረክ ማመቻቸት የጥፋት መልክተኛ መሆን ይመስለኛል።

ወደጭብጤ ልመለስና ዶ/ር ላጲሶ ውነትም እንደ ስማቸው ላጲስ በመሆን ታሪኩን ሁሉ ”ራሳቸው የፃፉትን ሳይቀር” የሚፃረር የማጥፋት ዘመቻ በማካሄዳቸው ኢሳት ከውነት አንፃር ሌላ ታሪክ አዋቂ ለማቅረብ ባይሞክርም ፋሲል እንዳስነበበው ከሆነ የሚረሽ ወገኔ ሊቀመንበር አቶ ተክሌ የሻው እባካችሁ ፕሮፌሰሩ አውቀው ይሁን ሳያውቁ የሳቱዋቸው ጉዳዮች ስላሉ እነዚያ እንዲስተካከሉ ሃሳብ ልስጥ ብለው ለኢሳት የኢሜል ማመልከቻ ይልካሉ። ቀጥለውም ደግሞ የኢሳትን መልካም ፈቃደኛነት ሲያገኙ በምን በምን ላይ መልስ መስጠት እንደሚፈልጉ የሚያብራራ መልእክት ይልካሉ። 

ጋዜጠጠኛ ፋሲል የአቶ ተክሌን ፅሁፍ አስመልክትቶ የሚከተለው ይለናል። 

”ጽሁፉን አነበብኩትና የተሰማኝን ጻፍኩላቸው። አንደኛውን አስተያየት ተቀበሉት፣ ሁለተኛውን ግን " እርሱን ለኔ ተወው " አሉኝ። ይሄ ነገር አደገኛ መሆኑን ከኢዲቶሪያል ፖሊሲያችንም አንጻር ማስተላለፍ እንደማይቻል ጻፍኩላቸው። ይህንን አደገኛ የተባለውን ጽሁፍ እዚህ ላይ የማልጠቅሰው ለእርሳቸው ካለኝ አክብሮት አንጻርና እሳቸው ይፋ አድርገው ያላሉትን ማድረግ ስለሌብኝ ነው። ባልደረቦቼን አማከርኳቸው። "ቃለምልልሱን መሰረዝ" የሚለው አንድ አማራጭ ነበር፤ ይህ ደግሞ ፈጽሞ የማይሞከር ነው፤ ለሃሳብ ነጻነት የሚታገሉ ሰዎች ፣ የሰዎች ሃሳብ የሚያፍኑ ከሆነ ትግላቸው የውሸት ነው ማለት ነው ። ይህንን ንግግር ቆርጬ ባስቀረው ደግሞ "ኢሳት ሃሳባችንን አፈነ፣ ቆርጦ አስቀረ" የሚል የአፈና ዘመቻ ይከፈትበታል። ይህም ሌላ ፈተና ነውስለዚህ የነበረኝ አማራጭ በተቻለኝ መጠን ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ ነገር እንዳይናገሩ መቆጣጠር ነበር። አውቀው ያደርጉታል ብዬ ባላምንም < ይህን ባይናገሩት ይሻላል" ስላቸው፣ እሱን በኔ ተወው ማለታቸው ፍርሃት ለቀቀብኝ። እውነት ለመናገር ወደ መጨረሻ አካባቢ ጣልቃ እገባ የነበረው በመጨረሻ ቅደም ተከተል ያስቀመጡትን እንዳይናገሩ እና በዋና ዋና ቅሬታዎች ላይ ብቻ አትኩረው የተነገረው ሁሉ ከውነት የራቀ ነውና መልስ ልስጥበት ስሜታዊ ወይም አነሳሽ የሆኑት ቃላትን እንዳይጠቀሙ ለማድረግ እንጅ ለሌላ አይደለም። አቶ ተክሌ ያን ጽሁፍ አስቀድመው ባይልኩልኝ ኖሮ እኔም ስጨነቅ ባልሰነበትኩ፤ እሳቸውም ያሰቡትን ተናግረው፣ እዳውን ለእኔ ትተው፣ ይጨርሱ ነበር። ዞሮ ዞሮ አደገኛ ያልኩትን ሃሳብ ቆርጨ ማስቀረቴ ስለማይቀር፣ ኢሳትም "ሃሳባቸውን ቆረጠባቸው በሚል ከመተቼት አያመልጥም ነበር ። ለነገሩ፣ ጽሁፍ አዘጋጅቶ በዚህ ቅደም ተከተል ቢሆንልኝ እመርጣለሁ የሚል መልዕክት መላኩም ትክክል አልነበረም። እንዲያውም "አቶ ተክሌ ኢሳትን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ብለው ነው ይህን ያጻፉት ወይስ ሌላ ምክንያት ይኖራቸው ይሆን እያልኩ ብዙ አውጥቼ አውርጃለሁ።”

 እንግዲህ ወገኖቼ ልብ በሉልኝ እኔ ከዚህ ከፋሲል ፅሁፍ የምረዳው እነ ኢሳያስ አፈወርቂን እነ ላጲሶን ሲጠይቅ ትህትና የተላበሰው ጋዜጠኛ ”ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን እውጭ ታሳድራለች እንዲሉ” የአቶ ተክሌ ባላንጣ ሆኖ መቅረቡ እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው መሆኑን ነው። ይህ ደግሞ የአማራ ጠላት በሌላ አነጋገር ”የእውነት ጠላት” አፉን በከፈተ ቁጥር ያለምንም ማስረጃ ማብጠልጠልና መወንጀል በሚፈቀድበት ኢሳት እንደ አቶ ተክሌ አይነት ይቆሙለት አላማ አማራው ከተነጣጠረበት የጥፋት ዘመቻ ለመከላከል በመሆኑ እባካችሁ ውነቱ ይኸ ነው የሚል ሰው ከኢሳት ኢዲቶሪያል ፖሊሲ አንጻር አደገኛ ከየተወገዘ መሆኑን ነው። በዚያ ቃለ ንዝንዝ ላይ ግን በጣም አስደናቂው ነገር የአቶ ተክሌ ትዕግስትና ፅናት ”ተውማ ፋሲል በዚህ ላይ ዶክተር ላጲሶ መልስ ይስጡበት አንተ የጋዜጠኛ ስራ ስራ” እያሉ በተደጋጋሚ ሲማፀኑት መስማት የአቶ ተክሌን ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እውቀታቸው ጥልቅና ሁለገብ መሆኑን በብቃት ያስመሰከረ ድል መሆኑ ነው። 

በአንፃሩ ደግሞ ፋሲል እንደዛ አላስተነፍስ ብሎ የጋዜጠኝነት ስነምግባር በጎደለው መልኩ ሲነተርካቸውና ካፋቸው ሲቀማቸው የነበረው ጠፋት ሳያንስ ጥፋቱን ማረም ሲገባው ፅሁፍ አሽሞንሙኖ ማቅረቡና ልክ መሆኑን መግለፁ ቁሜለታለሁ ከሚለው ኢትዮጵያዊነት ጋር የማይጣጣም ሆኖ አግኝቸዋለሁ።
 ምክንያቴም የሚከተለው ይሆናል።

  • ፋሲል በጥያቄው “የሠርቶአደር ጋዜጣ አዘጋጅ ነበሩ ይባላል። እውነት ይሁን ውሸት አላውቅም “ ብሎ የጠየቀው በቀጣይነት ከሚያቀርበው ጥያቄ ጋር ግንኙነት ስለነበረው ሳይሆን ”ደርግ” ብሎ አቶ ተክሌን ለማሸማቀቅ ነበር። ለዚህም ነው ከማስተካከያ ተብየ ፅሁፉ ውስጥ ያላካተተው። ለነገሩ ኢሳትም በአማራ ጉዳይ ይበረታል እንጅ የኢሳት እንግዶች እነ ካሳ ከበደ፥ ዳዊት ወ/ጊዮርጊስ፣ ዶር ላጶሶ ደርግ አልነበሩምን። ወያኔስ የነበሩት የኢሳት አባል አይደሉምን። አማራን የገደሉትና ያስገደሉት የኦነግ ባለስልጣናት፣ አሁንም አማራና ክርስቲያን በሜጫ አንገት እንቆርጣለን የሚሉት እነ ጁሀር ሙሀመድ መምነሽነሻ አደለምን! በኢሳት የደርግና የወያኔ ስራ አስፈጻሚ የነበሩ ግለሰቦች በክብርና በነፃነት በሚስተናገዱበት ኢሳት አቶ ተክሌ የሻውን የኋላ ታሪካቸውን ያለቦታው በመጎተት መጥፎና አሳፋሪ ለማስመሰል መጣር ግን ያማል። ፣

  • ፋሲል በፅሁፉ እንደገለፀው ”ይህንን ንግግር ቆርጬ ባስቀረው ደግሞ "ኢሳት ሃሳባችንን አፈነ፣ ቆርጦ አስቀረ" የሚል የአፈና ዘመቻ ይከፈትበታል። ይህም ሌላ ፈተና ነው። ስለዚህ የነበረኝ አማራጭ በተቻለኝ መጠን ህዝብን ለግጭት የሚያነሳሳ ነገር እንዳይናገሩ መቆጣጠር ነበር።” ይለናል። ይህ የሚያሳየው መልዕክቱ እንዲተላለፍ የተደረገው የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ስለሆኑ ትክክለኛውን ለማቅረብ በመፈለግ ሳይሆን ሀሜትን በመፍራትና ለኢሳት የሚገፈግፉት አማሮች ቅር እንዳይላቸውና ጥቅማጥቅሙ እንዳይቋረጥ ይመስላል። 

  •  ፋሲል ”ለነገሩ፣ ጽሁፍ አዘጋጅቶ በዚህ ቅደም ተከተል ቢሆንልኝ እመርጣለሁ የሚል መልዕክት መላኩም ትክክል አልነበረም። እንዲያውም "አቶ ተክሌ ኢሳትን አጣብቂኝ ውስጥ ለመክተት ብለው ነው ይህን ያጻፉት ወይስ ሌላ ምክንያት ይኖራቸው ይሆን እያልኩ ብዙ አውጥቼ አውርጃለሁ።” ይለናል። አቶ ተክሌ የሚመልሱት ዶ/ሩ በተናገሩት ጭብጥ ላይ ተመርኩዘው ስለሆነ ቅደም ተከተል ማስያዝ ግድ ይላቸዋል። ታዲያ በቅደም ተከተል አስቀምጠው የሚፈልጉትን ነጥብ ቢያሳውቁ ስተቱ ከምን ላይ ነው? በፋሲል አገላለፅ ግን ሁሉንም ነገር ሲያካብደው ጦርሜዳ ገብቻለሁ ያለው ግንቦት ሰባትም የአቶ ተክሌን ንግግር ያህል ጠላት የሚያርበደብድ አይመስልም። ይሄ ደግሞ ወያኔዎች የአማራን አከርካሪ መታን ከሚሉት ብዙም ልዩነት አላየሁበትም። 

  • አቶ ተክሌ በፅሁፍ የላኩለትን ነገር ምን እንደሆነ ሳይገልጽ ሾላ አድፍን አደገኛና ሕዝብ ከሕዝብ የሚያጋጭ በማስመሰል ቃለንዝንዙም የተደረገበት ምክንያት ከእርሳቸው ፅሁፍ እንደተረዳው መርዙ ከአፋቸው እንዳያመልጥ ነው ብሎ መቀባጠሩ ከታማኒነቱ ይልቅ በቃላት የተጠቀለለ ጥበባዊ መርዝ መርጨቱን ያሳያል።

  •  ሌላውና መዘንጋት የሌለበት የግል ማስታወሻ በሚል ርዕስ ከስር ያሰፈረው ፅሁፍ ደግሞ እራሱን እንደ ጲላጦስ ንፁህ አድርጎ አቶ ተክሌን ዘረኛ ለማስመሰል የጣረ ያስመስለዋል። ምክንያቱም እንደዛ ባያደርግ ኖሮ አቶ ተክሌ ከሞቀበት ሳያጨበጭቡ ለሚፈናቀለው ለሚታረደው ለሚሰደደው ዘር እንዳይተካ ለሚደረገውና ታዛቢ ላጣው አማራ ጠበቃ ሆኖ በስቪክ መደራጀትና መደገፋቸው ሊያስወቅሳቸው አይገባም ነበር።


 የኢትዮጵያ ህዝብ መቸስ ካጋጠመው የከፋ የወያኔ ቀንበር ለመላቀቅ የማያደርገው ጥረት የማይከፍለው መሰዋትነት የለውምና ተስፋን ስንቅ አድርጎ ቆርጨ ተነስቻለሁ ያለውን ሁሉ ለመደገፍ እውቀቱንም ገንዘቡንም ጉልበቱንም በቅንነት ይለግሳል። ከነዚህም ተስፋ ከተጣለባቸው ድርጅቶች መካከል አንዱ ”የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ”የተባለለት ኢሳት አንዱ ነው::

 ኢሳት ደግሞ አንዱን ልጅ አንዱን የእንጀራ ልጅ በማድረግ የሚያደርገው አድሎ ከወዲሁ ከልታረመ መቸም ቢሆን የኢትዮጵያ ህዝብ አይንና ጆሮ ለመሆን ከማስመሰል ባለፈ አይንና ጆሮ ሆኖ አይዘልቅም። ያው እንደተለመደው የተንሸዋረረ አይንና መስማት የተሳነው አጣርቶ የማይሰማ ጆሮ እንደሆነ ይቀራል። ኢሳቶች ደግሞ አማራን ያላካተተ ኢትዮጵያዊነት የትም አያደርስምና ከአማራው ላይ የጥፋት በትራቸውን ሊያቆሙ፣ በአማራው ላይ ጫና የሚያሳድር የተሳሳተና ከውነት የራቀ መልዕክት መተላለፉን ሊገቱ ግድ ይላል። አማራው ችሎ ችሎ በቃኝ ብሎ ፊቱን ከኢሳት ላይ እንዳያዞር ከተፈለገ መታረም ያለበት ፋሲል ብቻ ሳይሆን ኢሳት ነው። የኢሳት የጭፈን ደጋፊዎችም ያስተላለፍኩትን መልዕክት በጥሞና ተከታትላችሁ ሳትጨርሱ ለፍርድ አትቸኩሉ።

 ቸር እንሰንብት ነፃነት ናፈቀ 2015-11-03
 netsanetnafeke@hotmail.com

Monday, November 2, 2015

ሻቢያዎች ለምን ታገሉ?

ለማ ኃይሌ
 ጥቅምት ወር 2013 በፈረንጆች አቆጣጠር አምስት መቶ አካባቢ ኤርትራውያን ያሳፈረች መርከብ ሜዲትራንያን ባህር ባለችው ላምፔዱሳ ወደብ አካባቢ ሰጥማ 350 ኤርትራውያን በሞቱ ጊዜ ጉድ አያልቅበት የአቶ ኢሳያስ መንግሥት “የአፍሪካ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ሊሻገር ሲሉ ጀልባቸው ተገልብጦ በሜዲትራኒያ ባህር አለቁ” በማለት የራሱ ዜጎች መሆናቸውን ሽምጥጥ አድርጎ በመካድ አለምን ጉድ ያሰኘ ዜና በቴሌቪዥኑ አስተጋባ። ድርጊቱ የተፈጸመው በአውሮጳ ክልል በመሆኑ ግን ዜናው ሰፊ የስርጭት ሽፋን አገኘ። ትራጄዲው አለምን አናወጠ። ይሄኔ ሳይወድ በግድ የራሱ ዜጎች መሆናቸውን ለመቀበል ተገደደ። ያም ሆኖ ጲላጦሳዊነት የሚያጠቃው ይሄ መንግስት ሌላ ጉድ ይዞ ብቅ አለ፤- “ለኤርትራ ወጣቶች ፍልሰትና እልቂት ግንባር ቀደም ተጠያቂው የአሜሪካ መንግስት ነው” በማለት ኃላፊነቱን ከራሱ አወረደ።

 እስኪ አስቡት! አሜሪካን የሚያህል ታላቅ መንግሥት አንዲት የወጠጤ ግንባር እምታክል፤ የለት ጉርስዋን ያመት ልብስዋን እንኳን ለመሸፈን ዳገት የሆነባት፤ በዘመናችን የአፍሪካ ኖርዝ ኮርያ ተብላ እምትጠራ አገር ምን ጋሬጣ ልትፈጥርበት ትችላለችና ነው አሜሪካ እንቅልፍ አጥታ፤ የሰው ሃይልና በጀት መድባ የኤርትራ ወጣቶች አገራቸውን እየጣሉ እንዲወጡ እምትደክመው? ሰው ለጥልም ሆነ ለፍቅር እኩያውን ይፈልጋል። ፤ምነው እኚህ ሰዎች እኩያቸውን ቢፈልጉ? እነዚህ መሪዎች ዘጠና ዘጠኝ ፐርሰንት አሜሪካውያን ኤርትራ የምትባል አገር ከነመፈጠርዋ እንኳን እንደማያውቁ ይረዳሉ? ኤርትራ ኩዌት አይደለች ዘይት የላት፤ ኖርዝ ኮሪያ አይደለች ኑክሌር ቦምብ የላት ደቡብ ኮሪያ አይደለች ቴክኖሎጂ የላት በምንዋ ነው የአምስት ሚልዮን ምስኪኖች አገር ኤርትራ የነጮቹ ቀልብ ልትስብ እምትችለው?። ጂኦ- ፖለቲካ፤ ጦር ሠፈር ቅብርጥሴ…ወዘተ እንኳን እንዳይባል ያ ከቀዝቃዛው ጦርነት አብሮ የቀዘቀዘ ጉዳይ ነው። ፍሎሪዳ ላይ ቁጭ ተብሎ አፍጋኒስታን ላይ ያለ አሸባሪ በላፕቶፕ በአንድ ክሊክ አፈርድሜ እምታበላበት ዘመን ላይ ሆነህ ስለ ቃኘው ስቴሽን ማሰብ ተላላነት ብቻ ነው ሊሆን እሚችለው። በዛሬ ዘመን አገሮች አሜሪካ ጦር ሰፈሯን እንድትሰራ እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ውድድር የገቡበት መሆኑ ሳይረሳ።

 ለመሆኑ ኢሳያስ ለዚህ ትራጄዲ አሜሪካንን በተጠያቂነት እንዴት ሊመርጡ ቻሉ? እውነት ኤርትራ ባላት ጂኦግራፊያዊ ስፍራ ለአሜሪካ ብሔራዊ ጥቅም ወሳኝ ሆና ነው? በኔ እምነት ከዚህ አስተሳሰብ በስተጀርባ ያለው ታሪክ አንድ መፅሃፍ እሚወጣው ይመስለኛል። ይህ አሜሪካ ጠላታችን የሚባለው ፤ አመራሩ ያለበትን ትልቅ የማንነትና ቁመትህን ልክ ያለማወቅ ቀውስ እሚያመለክት ነው ። የፀጥታና የድንበር ውዝግቡ ያለው ሰላሳ አመት ከተዋጉዋት ኢትዮጵያ ጋራ ሆኖ እያለ ዘሎ በቦታው የሌለውን አሜሪካን መክሰስ ሳይካትሪስት እሚያስፈልገው ጉዳይ ነው። እንደሚባለው ከሆነ ኢትዮጵያን በቅኝ ገዢነት ሲከሱ እንዳልነበሩ ሁሉ ከቅርብ ጊዜ ወድህ ቋንቋው ተለውጦ ከፈደሬሽን እስከ ውድቀተ-ደርግ ያለውን ጊዜ “የአሜሪካ ቅኝ አገዛዝ በኢትዮጵያ እጅ” እየተባለ መፃፍና መናገርም ተጀምሮአል።

የዛሬ አመት ተኩል ገደማ የተላለፈው የፕረዚደንቱ እንተርቪው፤ “ኢትዮጵያ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በሁዋላ የተፈጠረች አገር ናት” የሚለው ትንተና፤ ከዚሁ ጋራ አጣምረህ ስታየው እነዚህ ሰዎች ለራሳቸው የሰጡት የጦዘ ግምት ያሳያል። አሜሪካንን በጠላትነት የመረጡበት ምክንያት የኢትዮጵያ ጠላትነት ለእነሱ ዝና አይመጥንም ብለው ስለሚያምኑ ነው። ስለዚህ አለም እነሱ እንደ ቬትናሞች አሜሪካንን በሠላሳ አመት ትግል አሸነፉ ብሎ እንዲያምን ይፈልጋሉ። ይህ እንግዲህ የነሱ የሰላሳ አመት ትግል ተመጣጣኝ ዋጋ (ጠላት) እንዲያገኝ ማለት ነው። በቅኝ የገዛችንና ሠላሳ አመት የተዋጋናት፤ ያቺ በስንዴ ልመና ባንድ ወቅት አለምን ያስቸገረች ኢትዮጵያ ናት ቢሉ ግን ትግላቸውና የትግላቸው ውጤት ሚዛኑ ይቀንሳል፤ ዋጋውም ያሽቆለቁላል። በአጭሩ ኢትዮጵያ እነሱ ላስቀመጡት -በምጣኔ ሃብት አዋቂዎች አነጋገር inflated price- አትመጥንም። በነሱ ቤት አሜሪካ ባትኖር ኤርትራም ከኢትዮጵያ ጋር በፈዴሬሽን አትዋሃድም ነበር፤ የነፃነት ትግላቸውም እንደዛ መራራ የሆነው በአሜሪካ ምክንያት ነው። ከባድሜ የወጡትም አሜሪካ ወያኔዎችን ስለረዱ ነው። 

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህልውና የተመሰረተው በአሜሪካ ነው። በአሁኑ አያያዛቸው ወደፊት ግንቦት 24 የናጽነት ቀናቸውን “ኤርትራ ከአሜሪካ ቅን አገዛዝ የወጣችበት” ተብሎ እንዳይከበር እሚያሰጋ ነው። አንዳንዴ ሳስበው ሻቢያዎች በቅዝቃዛው ጦርነት ወቅት የነበረውን የአሜሪካ ተወዳዳሪ ሶቭዬት ህብረትን በዚህ ዘመን የተካነው እኛ ነን እሚሉ ይመስላሉ። አሜሪካ እምትጠላን ይላሉ ገራገሮቹ ወንድሞቻችን - ለአፍሪካ መጥፎ ምሳሌ ስለሆንን ነው። እንዴት? የሚል ጥያቄ ስታስከትል “ምክንያቱም በራስ መተማመን የሚለውና ብድርን የማይፈቅደው ፖሊሲያችን ለተቀሩት አፍሪካውያን ምሳሌ እንዳይሆንና በዚህም የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዛቸው እንዳያከትም አሜሪካና አውሮፓ ብርቱ ስጋት ስለአላቸው ነው።” በማለት ያብራራሉ። በቅርቡ በአልጀዚራ የቀረበ ፊልሞን የተባለ የሻቢያ ወጣት ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች በተለዬ ችግር እየደረሰብን ያለው የመንግስታችን ፖሊሲ በራሳችን ስለሚቃኝ፤ለአለም ገንዘብ ተቋም፤ ለአለም ባንክ እማናጎነብስ፤ በትክክል ነፃ መንግስት ስለሆን ነው” በማለት ጋዜጠኛዋን አስደምሞአል። በነሱ አመለካከት ስድሳ ወደ የሚጠጉ የአፍሪካ ሃገራት ብሄራዊ ጥቅማቸውን ለአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም አስልፈው ሰጥተው አንዲት ሃገር ኤርትራ ብቻ በጽናት መቆምዋን ነው። ሁኔታው ያስቃልም ያሳዝናልም አንድ ያስመራ ወዳጄ ያጫወተኝ እዚህ ላይ ታወሰኝ። አልበሽርና ኢሳያስ ሲገናኙ ይተራረባሉ አሉ-የዛሬው አያርገውና። አልበሽር የወያኔዎችን የቁጥር እድገት ሲነግረው ያ ፊቱን ጨምድዶ” ታያለህ! ኢትዮጵያን በእድገት ሩጫው ብቻ አይደለም በቅርቡ አልፈናት እንሄዳለን “ ይለዋል። ጨዋታ አዋቂው በሽር “ድረሱባት እንጂ አልፋችሁ መሄዱስ ይቅርባችሁ” ይለዋል።

 አቶ ኢሳያስ “ለምን” ይላል፤ አልበሽርም መልሶ “አይ እናንተ ከፊት ስትሮጡ እነሱ ከኋላ ሆነው በተቀደደው ሱሪያችሁ መስኮት መቀመጫችሁን እያዩ እንዳይስቁባችሁ ብዬ ነው” አለው ይባላል። አሉ ነው አልነበርኩም። ወደ ራስችን እንመለስ። ነፍሳቸውን ይማርና ዘውዴ ረታ የኤርትራ ጉዳይ በሚለው መጽሃፋቸው ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ፍፃሜ ማግሥት ጀምሮ በማህበረ-አንድነት መሪነት የባህረ ነጋሽ ኢትዮጵያውያን ከናት አገራቸው ለመቀላቀል ስላደረጉት ተጋድሎ፤ የአፄ ሃይለሥላሴ መንግሥትም የባህረ ነጋሽ ህዝብ ወደናት አገሩ ለመመለስ ያደረገውን ተጋድሎ መሰረት በማድረግ በአለም ሸንጎ ፊት በስመ ጥሩዎቹ የአገራችን ዲፕሎማቶች በነአቶ አክሊሉ ሃብተወልድ፤ ሌሬንሶ ታእዛዝና ሌሎችም አማካይነት ስላካሄደው ዲፕሎማሲያዊ ትግል በስፋት አሳይተውናል። ኢትዮጵያውያንም እንደ ህዝብ በጉዳዩ የጠራ ግንዛቤ እንድንይዝ ረድቶናል። ምክንያቱም በራሳችን መንግሥትም የተፈፀሙ ስህተቶችም አሳይተውናል። በዚህም በደርግ ጊዜ ከነበረው የድንቁርና አካሄድ፤ በዚህኛው መንግሥት ካየነው የተዛባ ታሪክ ትንተና ወጥተን ሚዛናዊ የሆነ ግንዛቤ ለመጨበጥ ችለናል። ነገር ግን ከነጻነታቸው ወድህ ባለው ጊዜ በሃማሴን ጽንፈኞች በኩል እሚነገረውና እሚተረተረው ውሸት ሁሉ ደምረን ቀንሰን ስናዬው፤ የኤርትራ ችግር ከግንጠላው በኋላም በፊት ከነበረው ብሶበት እየቀጠለ መሆኑ ሲታይ፤ የዚች አገር የግንጠላ ተጋድሎ መነሻ ታሪክ ከሌላ አንግል በጥልቅ መመርመር ያለበት ጉዳይ መሆኑ ነው። ኤርትራ ተገነጠለች ማለት ተነስታ ህንድ ወይም ሰላማዊ ውቅያኖስ ውስጥ ተተከለች ማለት አይደለም። ያው በቦታዋ ነው ያለችው። የዚች አገር መሪዎች ስለራሳቸው የሚኖራቸው አመለካከት የተጣመመ ከሆነ ለጎረቤቶቻቸው የሚኖራቸው ፖሊሲም ጤናማ አይሆንም። ስለራሳቸው የጦዘ እና ያበጠ አመለካከት የነበራቸው እንደነሂትለር የመሳሰሉ እብዶች በታሪክ ምን ሰርተው እንዳለፉ ማስታወሱ ጠቃሚ ነው። ስለሆነም አሁን የሻቢያ መሪዎች የያዙት አሜሪካን እኩያህን አድርገህ እስከ መቁጠር የሚያደርስ እብደትና ኢትዮጵያንና ሌሎች የአካባቢው አገሮችንም ቁልቁል የማዬት አባዜ ምንጩን ለማወቅ ትግሉ የተካሄደበትን ምክንያት እስካሁን ሲነገረን ከነበረው በተጨማሪ ምርምር ተካሂዶ ልንደርስበት ይገባል።


 የዛሬይቱ ኤርትራ መሪዎች ፤የደጋ ክርስቲያኖች በንጉሱ ዘመን አባቶቻቸው አንድነትን ሲመርጡ እነሱ መገንጠልን የመረጡበት ምክንያት ኢትዮጵያውያን በውል ማወቅ ያለብን ይመስልኛል። አባቶቻቸው የታገሉት ለፈደሬሽን ወይ ለኮንፈደሬሽን ለካፒታሊዝም ወይ ለሶሻሊዝም ሳይሆን ኢትዮጵያ አገራቸውን ለማግኘት ነበር። ታገሉ አገኙም። ነገር ግን ልጆቻቸው ኢትዮጵያዊነትን ተጠየፉት። በአባቶቻቸው የነበረው ኢትዮጵያዊነት ወዴት ሄደ? እውን እነዚህ ሰዎች በረሃ የወጡት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋራ ከፍላጎትዋ ውጭ በመዋሃድዋ ወይም ፈዴሬሽኑ በመፍረሱ ነው? ፌደሬሽኑ ባይፈርሥ መሸፈታቸው ይቀር ነበር? ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድሃኒዬ በአንድ ወቅት እንደገለጡት ፌደሬሽኑ የቆላ ሞስሊሞች ወደ ክርስቲያን ኢትዮጵያ በመግባቱ የነበራቸውን ፍራቻ ለማስወገድ የተቀመጠ የጋራ አካፋይ ነው።

ክርስቲያኖቹ የታገሉት በኦሪትም በሃዲስም ይዘዉት ለኖሩት ማንነት-ለኢትዮጵያዊነት ነበር። ፌደሬሽን ይሁን አሃዳዊ ለነሱ ጉዳያቸው አልነበረም። እንዲያውም ንጉሱ እንደ መሲህ ይታዩ የነበሩት ይበልጥ በነዚህ ወገኖች አካባቢ እንደነበረ ይታወቃል። በንጉሰ ነገሥቱ ዘመን በአሥመራ ማህበረ ሀዋርያት ይታተም የነበረው መዝሙረ ዳዊት ፈልጋችሁ ብታነቡ በመግቢያው ለአምላክ የሚሰጠውን ውዳሴ ለጃንሆይ ሲያዥጎደጉዱት እንደነበረ፤ ንጉሱ አስመራ ለመጎብኘት ሲገቡ የህዝቡ አቀባበል በመጽሃፍ ቅዱስ ታሪክ ኢየሱስ ክርስቶስ ኢየሩሳሌም ሲገባ የነበረውን ትእይንት የሚያስታውስ እንደነበር ነው። ታዲያ የነዛ በኢትዮጵያ ብሔረትኝነት እና በንጉሰ ነገሥቱ ፍቅር ልባቸው ይነድ የነበሩት አባቶች ዘመናዊ አስኳላ የተማሩ ልጆቻቸው የአንድነቱ መንገድ ትተው የግንጠላውን ለመከተላቸው መሰረታዊው ምክንያቱ ምን ይሆን? በመሰረቱ የአንድ አገር ኢኮኖሚ የተቆጣጠሩ፤ ከሌሎች ዜጎች የተሻለ የኑሮ ደረጃ የነበራቸው ማህበረሰቦች ተጨቁነናል፤ ተበድለናል ብለው በረሃ ሲወጡ በታሪክ እሚታወቅ ነገር አይደለም። የደርግ ግፍ አስበርግጎት በገፍ በረሃ የገባው ወጣት ትተን በንጉሱ ዘመን የኢሳያስና ስብሃት ኤፍሬም የደጋው ክርስቲያን ትውልድ የበረሃ ትግሉን የተቀላቀሉበት ዋና ምክንያት ግን የሰለጠነች ኤርትራ ኋላ ቀር ከሆነች ኢትዮጵያ መዋሃድ ያሳደረባቸው ቁጭት ነው። በሌላ አነጋገር ሰዎቹ በረሃ የወጡት ያስመራ ስልጣኔን ከኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት ለመታደግ ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጽሁፎቹ ጥልቅ ትንታኔ ገናና እየሆነ የመጣው ኤርትራዊው ዮሴፍ ገብረህይወት

 The Eritrean Oblomov-loving-Asmara the superfluous way በሚል ርእስ ያቀረብው አስገራሚ ትንተና እና ሊሎች ጽሁፎቹ የኤርትራን ችግር ከሌላ አንግል ለማዬት እሚረዱ ናቸው። http://asmarino.com/articles/2046-the-eritrean-oblomovloving-asmara-the-superfluous-way

ዮሴፍ እንዲህ ይላል፡ Here is a fact that the nationalists would undoubtedly have a hard time to swallow: the golden age of Asmara happens to be neither in the Italian era nor in the Independence era; those g those g those golden years happen to fall exactly on the re olden years happen to fall exactly on the reign of Haile Selassie, starting to build up in the 50s to reach Selassie its apex in the 60s, only to abruptly end in the early 70s when ghedli (ታጋዮች ለማለት ነው) showed up at the doorsteps of Asmara in full force.

What then explains this riddle, since it doesn’t fit at all with the narrative that the nationalists have been telling the masses? This question has special relevance because the ghedli generation’s concept of modernity was entirely shaped from the impressions that this colonial city had left on them. In fact, it was with the saving of “Asmara ci In fact, it was with the saving of “Asmara civilization” in their tion” in their mind that they went through hell for 50 years. Wher mind that they went through hell for 50 years. e from came this perceived threat? Did Asmara have it so bad during the Haile Selassie era to warrant 50 years of insanity? To begin with, why can’t we say that Asmara’s golden age was during the Italian colonial era, given that it was after all the Italians that built it? There are two major reasons: First and foremost, as pointed above, 

Asmara remained a small Asmara remained a small sleepy little town for much of the colonial sleepy little town for much of the colonial era sleepy little town for much of the colonial era; it was only when Italy decided to invade Ethiopia that Asmara abruptly mushroomed five folds in the last six years. If there was no vibrant Asmara for much of the colonial era to begin with, one cannot talk of a “golden age” of a city that was never there. And, second, if we are to confine ourselves to the last six years, there were three things bedsides its brief “age” that would make a mockery out of these perceived golden years. ዮሴፍ የሚለውን እንደገና ልብ ብለን እናስተውለው! In fact, it was wi In fact, it was with the saving of “Asmara civilization” in their mind that they went through hell for 50 years. ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎችና የፖለቲካ ሰዎች አትኩሮት ሊሰ for 50 years. ጡት እሚገባ ጉዳይ ነው። ይህንን የምለው ያለምክንያት አይደለም።

 ዛሬም ብዙ ፖለቲከኞቻችን የምእራባውያኑን ቋንቋ ተከትለው የኤርትራ ችግር “Annexation” ወይም በኃይል የመያዝ ነው ሲሉ ይደመጣሉ። ከያትውልድ መሪዎች አንዱ ያሬድ ጥበቡ በቅርቡ በፌስቡክ አምዱ ያወጣው ጽሁፍ እንዲህ ይላል፡ “የኤርትራ ጉዳይ የannexation ወይም አስገድዶ የመያዝ ጥያቄ ነው የሚለው የምሁሩ ትንተና ተገቢው ትኩረት ያልተሰጠው ሩቅ ጠማችና ሃገር አደላዳይ አመለካከት ነበር ። በሚገርም አጋጣሚ፣ እኔ ለኢህዴን አንደኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ካዘጋጀሁት ጥናታዊ ሰነድ ጋር ተመሳሳይ ነው ። በህዳር 1976 ለሚካሄደው ጉባኤ "የኤርትራ ጉዳይ በተባበሩት መንግስታት የተሰጣቸውን የፌዴሬሽን መብት በመግሰስ ከኢትዮጵያ ጋር አንድ እንዲሆኑ የተደረገበት ሂደት በመሆኑ፣ የannexation ጥያቄ ነው፣ መፍትሄውም ሪፍሬንደም ማካሄድ ነው" የሚል ሰነድ ነበር ያዘጋጀሁት ። ይህን ሰነድ የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ለነበሩት ለነታደሰ ጥንቅሹ አስረክቤ ወደ ደቡብ ወሎ ለመስፋፋት ላቀድነው ወታደራዊ ዘመቻ ለመሳተፍ የኢህዴንን ታጋዮች ይዤ ከቤዝ አምባችን የሳምንታት የእግር መንገድ ጉዞ ርቀን ሄድን ። ከሁለት ወራት በላይ የፈጀውን ወታደራዊ ስምሪት አጠናቀን ወደ ሰቆጣ ከተማ ስመለስ ፣ እነ ታደሰ ጥንቅሹ የኔን ጥናት ለአባላት እንዳይሰራጭ አፍነው ፣ በረከት ሌላ "የኤርትራ ጉዳይ የቅኝ ግዛት ጥያቄ ነው" የሚል ሰነድ አቅርቦ፣ አባላትን በዚያ ሰነድ ላይ ብቻ ሲያወያዩ ደረስኩ ። ለጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴው የመረረ ተቃውሞዬን ከማቅረብ ውጪ፣ በዚያ በረፈደ ሰአት (ጉባኤው መከፈቻ ቀርቦ ስለነበር) ማድረግ የምችለው አልነበረም ። በተጨማሪም የበረከትም የጥናት ፅሁፍም ቢሆን ፣ በአፈታቱ ላይ "ነፃነት አሁኑኑ" የሚል ሳይሆን ፣ ከኔው አመለካከት ጋር የሚስማማ በሪፍሬንደም እንዲፈታ የሚጠይቅ ስለነበር ፣ ጉዳዩን አለዝቤ ለመያዝ ወሰንኩ ።”

የያሬድ ጥበቡ ትውልድ በዘመኑ የኢትዮጵያን ችግር የተነተነበት መንገድና ለችግሮቹም መፍትሔ ብሎ ያቀረባቸው ከግራ ዘመም አይዲኦሎጂው እሚመነጩ ነበሩ። ትውልዱ የነበረው የአገርና የወገን ፍቅር የማያሻማ ቢሆንም የኢትዮጵያ ትልቁ ችግር የህልውና ችግር ሆኖ እያለ ታሪኩን በአግባቡ ያላጠናው ትውልድ መሰረታዊ ያገራችን ችግር “የመድብና የብሔር” ብሎ በመደምደም ለለፉት አርባ አመታት ለገባንበት ችግር ምክንያት ሆኖአል። ትውልዱ የኤርትራ ችግርም ቢሆን ከሞላ ጎደል የተሟላ ስእል ያገኘው በዘውዴ ረታ መጽሐፍ እንደመሆኑ መጠን በፋኖነት ዘመኑ የኤርትራን ችግር አስመልክቶ የነበረው እውቀቱና ትንተናው ውሃ እሚቋጥር አይሆንም። እንደሚታወቀው በእንግሊዞች ዘመን የኤርትራ መፃኢ እድል ለመወሰን ሲንሸራሸሩ የነበሩ ሁለቱ አመለካከቶች (ነጻ መንግስት ወይም ከኢትዮጵያ መዋሃድ) ሃይማኖት ላይ የተመሰረቱ ነበሩ። ቆላ ሙስሊሞች ሙሉ ለሙሉ ነፃነት ሲሉ እጅግ ብዙሃኑ ደጋ ክርስቲያኖች ኢትዮጵያ ወይም ሞት አሉ።

ፌደሬሽን ሁለቱን እሚያስታርቅ ሆኖ ተገኘና ኤርትራ በፈደሬሽን ከኢትዮጵያ ጋራ ተዋሃደች። የመጀመሪያ የሸንጎ ምርጫም ሃይማኖትን መሰረት በማድረግ 35 ክርስቲያኖች እና 35 ሞስሊሞች የምክር ቤት አባላት፤ ክርስቲያን ፕረዚዴንት ሙስሊም አፈጉባኤ ሆነው ተዋቀሩ። ብዙም ሳይቆይ በዋናነት በደጋ ክርስቲያኖች ትግልና በንጉሰ ነገስቱ ድጋፍ ፌዴሪሽን ፈረሰ። እስላሞች የፈራነው ደረሰ አሉ። የነአዋተ የበረሃ የነፃነት ትግልም ተጀመረ። ከውህደት በኋላ ለኤርትራ በተሰጠው ልዩ ጥቅም ከሌላው ጠቅላይ ግዛት በበለጠ በብዛት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጎረፉት የደጋ ኤርትራ ወጣቶች መሃል አገሩን ካዩ በሁዋላ ካደጉባት አስመራ ጋራ በማወዳደር ኋላ ቀርዋ ኢትዮጵያ ያስመራን እድገት የምታጨናግፍ አድርገው ይቆጥርዋት ጀመር። ንጉሰ ነገስቱ “በቅኝ አገዛዝ ቅስሙ የተሰበረ ህዝብ ነው” በማለት ሞራሉን ለማደስ ያደረጉት ሁሉ ከመጤፍ የቆጠረው አልነበረም። ለወጣቶቹ በጊዜው የታያቸው ባለ እንዱስትሪዋ ኤርትራ ከ”ኋላቀርዋ አገር” ከተላቀቀች ከወደቦችዋ ጋር በአፍሪካ በእድገትዋ ከአውሮፓ አገሮች የምትስተካከል አገር ልትሆን እንደምትችል ነበር።

ወጣቶቹ የዩኒቨርስቲ ቆይታቸውን ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋራ ለመቀራረብና ለመዋሃድ አላዋሉትም በአንጻሩ ራሳቸውን የተለዩና በስልጣኔ ከፍ ያሉ አድርገው በመቁጠር “የተባበሩት መንግስታት አንዲት በእንዱስትሪ የበለፀገች አገር እጅግ ፊውዳልና ኋላ ቀር ከሆነች አገር አቆራኛት” የሚል ቁጭት ነበር እሚያንገበግባቸው። ይህንን በማስረጃ እንይ። ኪዳኔ ሐጎስ ካናዳ አገር የሚኖር በንጉሱ ዘመን የቀዳማዊ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበረ እንደ ያኒዎቹ ወጣቶችም ለኤርትራ ነጻነት በውቅቱ በረሃ የገባ ሰው ነው። ባለፈው መጋቢት ወር ሃሊፋክስ ካናዳ ለሚገኘው ቮይስ ኦፍ ኤሪትሪያ በሰጠው ኢንተርቪው https://www.youtube.com/watch?v=5267XGueEUA እንዲህ ይላል” የኤርትራ ህዝብ ከአካባቢው ህዝብ የሚለየው ነገር ቢኖር መተጣጠፍ የሚችል፤ የፈጠራ ጥበብ የተላበሰ ብልሃተኛ ህዝብ መሆኑ ነው።

ሞደርን ኢትዮጵያን የፈጠራት የኤርትራ ህዝብ ነው። ገብረሚካኤል አምባዬ የሚባል ኤርትራዊ እሸት የምትባል አውሮፕላን ሰራላቸው። እንዲያውም ከተጋድሎአችን አላማ አንዱ የነበረው የኢትዮጵያ መንግስት ወደፊት እንዳንራመድ አስሮ ስለያዘን የራሳችን መንግስት መስርተን ወደፊት ለመወንጨፍ ነበር” አስምሮም ለገሰ የተባለ አንትሮፖሎጂስት ይሄ “እኛ የተሻልን ነን” ለሚለው እሳቤ ሁነኛ ኢዲኦሎግ ነው። በ1988 እኤአ በጆን ሃፕኪን ዩኒቨርስቲ ሰለ ኤርትራ በኢኮኖሚ ራስን የመቻል ብቃት አስመልክቶ በሰጠው ዲስኩር ለዚሁ ማስረጃ ብሎ ያቀረበው ምክንያት “ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ” ያስባለ ነበር። “ስፖርት ብቻ ሳይሆን ኤርትራውያን ቴክኖሎጂ ከሰውነታቸው የተዋሃደ ነው፤ ስለሆነም አገራችን የእንዱስትሪ እኮኖሚ ለመገንባት አይቸግራትም።” ብሎ የጀመረው የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ ለማስረጃ ብሎ ያቀረበው ነገር ትንሽነቱን በሰው መሃል ያጋለጠ ጉዳይ ነበር። እንዲህ ነበር ያለው፡ “ለዩኒቨርስቲ ትምህርት አስመራን ለቅቄ ወደ አዲስ አበባ በሄድኩበት ወቅት ይዤአት የሄድኩኝ ካቻቪቴ ነበረችኝ። አማራዎቹ የክፍል ጓደኞቼ ስምዋን ስለማያውቁ ጠበንጃ መፍቻ ይሉዋት ነበር።” ይህ ለፕሮፌሰሩ የኤርትራውያን ከኢትዮጵያውያን በተሻለ ቴክኖሎጂ ማወቅን የሚያረጋግጥ ነበር።

ዳሩ ምን ይሆናል በቦታው ከነበሩ ፓናሊስቶች አንዱ የሆነው ጄምስ ማካን የተባለ ፕሮፌሰር“ ካቻቬታ ጣልያንኛ ነው በትግርኛ ምንድነው እምትሉት?” በማለት ላቀረበው ምፀታዊ ጥያቄ፤ ፕሮ/ለገሰ በመሸማቀቅ “የትግርኛ ቃል የለውም ያው ካቻቪቴ ነው እምንለው” ከማለት ውጭ አማራጭ አልነበረውም። የፕሮ/ለገሰ አመለካከት የዛሬዎቹ የኤርትራ መሪዎች መሰረታዊ እምነት ነው። በረሃ የወጡበት አላማ ዞሮ ዞሮ የሚያርፈው እዚሁ ነው። ከ30 አመታት ጦርነት በኋላ በድል አስመራ የገቡት እኒያ ዮሴፍ፤ “ያስመራ ስልጣኔ ተከላካዮች” በማለት ያጠመቃቸው ታጋዮች፤ ያገር መሪነት ሚና ሲጨብጡ ያሳዩት ባህርይ ይህንኑ ሲወጡ የነበራቸው እምነት የሚያሳይ ነበር። አሥመራ በገቡ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ያን ሁሉ ጠራርገው ያስወጡት ለፍቶ አደር ኢትዮጵያዊ ያቺ ሰወጡ የነበረችውን አሥመራ ውበት ለመጠበቅ ሲሉ ነበር።

ኢትዮጵያን የተመለከትዋት በቅኝ ገዥዎች አይን እንደ ጥሬ ሃብት አቅራቢ ሲሆን በአረቦች ላይ ሽርደዳ በአፍሪካ መሪዎች ላይ ማሾፍ የየቀኑ ሥራ አድርገዉት ነበር። የመከላከያ ኃይል ብቃታቸው ማነጻጸሪያ እስራኤልን ሲመርጡ በኢኮኖሚው እቅዳቸው ሲንጋፖርን በአጭር ጊዜ ለመድረስ አቅደው ነበር። ኤርትራ ከ”ናጽነት” በኋላ ያስየችው እብደት ቀረሽ ባህርይ ሌሎቹ፤ ነጻነታቸውን ከኮለንያሊስቶቹ እንግሊዝና ፈረንሳይ ካገኙ አገሮች የተለዬ የሆነበት ምክንያት ትግሉ የተካሄደበት ምክንያት የተለዬ በመሆኑ ነው። ዛሬም ከ25 አመት በኋላ በጦርነት ተሸንፈው፤ በኢኮኖሚውም ተንክታኩተው፤ 4ኤም ተነስተህ የዳቦ ወረፋ እምትይዝባት አገር ይዘው እንኳን ሻቢያዎች ዛሬም ከቁመታቸው ልክ የማሰብ አባዜ አልተዋቸውም። ማርች 28-2015 በአዋተ.ኮም ሰለ አቶ ኢሳያስ የወጣው ጽሁፍ ዝሆን አክላለሁኝ ብላ የፈነዳችውን እንቁራሪት ታሪክ እሚያስታውስ ነው፡፡ ጉዳዩ ኢሳያስ አረቦችንና እስራኤልን ለማስታረቅ ራሳቸውን በእጩነት ስለማቅረባቸው ይመለከታል። 

A diplomat from the region informed Gedab News that the Eritrean president, “either thinks highly of himself or underestimates the Arab leaders to consider brokering any deal between the Arab countries and Israel, a feat countries with leverage failed to ac Israel, a feat countries with leverage failed to achieve.” hieve.” http://awate.com/isaias- http://awate.com/isaias-wants-a-bigger-role-in-the-yemeni-crisis/ crisis/ ሻቢያዎች ሰላሳ አመታት የታገሉለትን ነፃነትን ካገኙ በኋላ ዛሬም ቢሆን ከኢትዮጵያ ጋራ ከቅድመ ነፃነት በበለጠ ችግር ውስጥ የገቡበት ምክንያት ከመጀመሪያው የወጡበት አላማ ተፈፃሚ ሊሆን አለመቻሉ ነው።

የወጡበት አላማ ነፃ አገርን በመመስረት ብቻ የሚፈጸም ቢሆን አስመራ ከገቡበት አንስቶ ይህንን ለማሳካት ይችሉ ነበር። ነገር ግን እነሱ ከሌሎቹ በቅኝ ተገዥነት ከቆዩ ህዝቦች እሚለያቸው ይሄ ካከባቢው እኛ እንሻላለን የሚለው የበላይነት ስሜት ሲሆን ነገር ግን የሄ እሱነታቸው የአካባቢው ጌታ መሆን ስላላስቻላቸው እረፍት፤ እርካታና ሰኩሪቲ ሊሰማቸው አልቻለም። እነሱ ሲወጡ ቁልቁል ያዩዋት ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ባይኖራትም ቢያንስ እዛም እዚህም በበቀሉ ህንጻዎች ምክንያት ዛሬ አንጋጠው የሚመለከትዋት አገር ሆናለች። እንደተመኙላትም አልፈረስችም። በረሃ ሲወጡ “ወደባት አዴይ” እያሉ የዘፈኑላቸው ምጽዋና አሰብም ጄነራል ኤልትሪክና ጄኔራል ሞተርስ ሆነው አልተገኙም፤ የወደብ ባለቤትነት በራሱ ኢኮኖሚ አለመሆኑ የገባቸው 50ሺ ዜጎቻቸውን በትግሉ ካጡ በኋላ ነው። ገብሩ አሥራት “ሉዓላዊነትና ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ” በሚል መጽሐፉ በገጽ 153 “የሻቢያ ኢትዮጵያን የመቆጣጠር ውጥን’ በሚለው ክፍል ሐምሌ 1983 ዓ/ም አስመራ ላይ በተደረገውና 40 ጥናቶች በቀረቡበት የኢኮኖሚ ኮንፈረስ ላይ የተነገረውና የተተነተነው ሁሉ በወቅቱ ምን ያህል እንዳስቆጣው ይናገራል።

ኮንፈረንሱ አንድ ቀኝ ገዥ ሃይል ቅኝ በያዘው አገር ለማድረግ ያቀደውን የሚገልጽበት እስኪምስል ድረስ ጥናት አቅራቢዎች ነጻ አወጣን በሚሉት አገራቸው ስለሚመሰርቱት የኢኮኖሚ ስራት ሳይሆን ገለጻቸው በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስለሚኖራቸው ድርሻ ነበር። በኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለሚኖራቸው ሼር፤ ካምፓኒዎቻቸው በኢትዮጵያ ስለሚሰሩት መንገድ አይነት ነበር። የዚህ ሁሉ ምክንያት እኛ የተሻልን፤ የስለጠንን ነን የሚለው ሰወጡ የነበረው አስተሳሰብ ሲመለሱ የምንመራው እኛ ወደሚለው ማደጉ ያመጣው ጣጣ ነበር። እነዚህ የዋሆች ኢትዮጵያውያን በጊዜ ሂደት ሊያድጉ ሊለወጡ ይችላሉ የሚል እይታ ኖሮአቸው አያቅም። ለነሱ ኢትዮጵያ የብሄሮች ድምር ስለሆነች ፈራሽ ነች። የማፍረሱ ስራ ኮንትራቱን የወስዱት እነሱ ሲሆኑ የሁሉም ብሄር ነጻ አውጪ ነን ባይ ድርጅቶችም በአስመራ ጽፈት ቤቶቻቸውን ከፍተውን ባንዲራዎቻቸውን ሰቅለው ይኖራሉ ከዚያ እየተንቀሳቀሱም ኢትዮጵያን ይወጋሉ። ሻቢያዎቹ ኢትዮጵያ በትናንሽ መንግስት ተከፋፍላ እንሱ የአካባቢው ዋነኛ ህይል ለመሆን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በጣም የሚያመው የደብረ ቢዘን ልጆች ሶማሌ ድረስ ተጉዘው የአልሸባብ ጀሃዲስቶች ኢትዮጵያን እንዲያደሙ መርዳታቸው ነው። ይህም ጂሃዲስቱን አልሻባብን የረዱበት ዋነኛ ምክንያትም ይኸው እስከዛሬ የሚደክሙበት ያለው የኢትዮጵያ መበታተን ህልም ነው። የሻቢያዎቹን አካሄድ አይቶ አይቶ አንቅሮ የተፋቸው ኤልያስ ክፍሌ ያለው እዚህ ላይ ሊጠቀስ ይገባዋል። 

“From what I have observed personally over the past “From what I have observed personally over the pastfew years, few years, few years, and as many knowledgeable people have informed me for a long for a long Time, Shabia considers Eritrea not free until Ethio , Shabia considers Eritrea not free until Ethiopia is divided into is divided into is divided into Multiple mini ultiple mini-states. http//mereja.com/for states. http//mereja.com/for states. http//mereja.com/forum/viewtopic.php?t=1001 um/viewtopic.php?t=100199 um/viewtopic.php?t=100199

አንዳንድ የዋህን ኢትዮጵያውያን የድህረ ነጻነት ኤርትራና ኢትዮጵያ ፍጥጫ የሁለቱ አስመራና አዲስ አበባን በትጥቅ ትግል የተቆጣጠሩ ሃይሎች የመጠፋፋት ጉዳይ አድርገው ይመለከቱታል። ይህ ግን ቁንጽልና ጉዳዩን በጥልቀት ካለመመልከት የመጣ ነው። የኢትዮጵያን የኤርትራ ጉዳይ ከአሜሪካ-ራሻ ይመሳሰላል። በሶቭዬት ህብረትና በአሜሪካ የነበረው ቀዝቃዛው ጦርነት ዛሬም መልኩን ቀይሮ ሌላ ዙር ቀዝቃዛ ጦርነት ውስጥ እየገቡ ይገኛሉ። በኮሚዩኒዝም ጊዜ ተቃርነዋል ዛሬ ኮሚዩኒዝም በሌለበት ሁናቴ ወደ አደገኛ ቅራኔ እየገቡ ነው። ለአሜሪካኖች ዋነኛው ነገር ሩሲያ የነሱን ልእለ ሃያልነት እምትወዳደር መሆን አለመሆንዋ እንጂ የፖለቲካ ሲስተምዋ አይደለም። በተመሳሳይ መንገድ ለሻቢያ መሪዎች ኢትዮጵያ ማን ይምራት ማን ዋናው ጉዳይ የነሱ እንዳስትሪ ጥሬ እቃ አቅራቢ ትሆናለች አትሆንም ነው፤ ኤርትራዊ ማንነት በኢትዮጵያዊነት ላይ ብልጫው ጎልቶ መታየቱ ነው። ይህ እንዴት ይሆናል? መልሱ ሙዝ የመላጥ ያህል ቀላል ነው፤ ኢትዮጵያ በትናንሽ መንግስታት መከፋፈል አለባት። ሻቢያዎች በረሃ ሲወጡ ይዘዉት የወጡት የተሻልን ነን የሚል ስሜት፤ በአፍሪካ ትልቁ ጦር የደመሰስን ነን የሚል ጉራ ተደምሮ የፈጠረባቸው ስካር ገና አልበረደም። ራሳቸውን የእስራኤል ተምሳሌት አድርገው የቀረጹ ሰዎች አሁን የጅቡቲ እኩያ ምድባቸውን አእምሮአቸው ሊቀበለው አይችልም። የሚፈልጉት እነሱ እስራኤል እኛ አረቦች እንድንሆንላቸው ነው። ትልቁ አደጋ ሻቢያዎች ኤርትራዊ ማንነት በኢትዮጵያዊ ማንነት ላይ ብልጫ አለው ብለው እሚያምኑ ግብዞች መሆናቸው ነው። ይህንን በቀላል ምሳሌ ማሳዬት ይቻላል። ፕሮፌሰር ጌድዎን አባይ በሙያው የሂሳብ ፕሮፌሰር ሲሆን ሲናገር አፍ እሚያስከፍት የዘመኑ የሻቢያ ሰባኪ ነው። ፕሮፌሰር ጌድዎን ስለ ኤርትራ ማንነት ሲናገር ጀርመናዊው የሂትለር የፕሮፓጋንዳ ሃላፊ ፕሮፌሰር ጆሴፍ ጎብልስን ያስንቃል።

 እዚህ ቪዲዮ ውስጥhttps://www.youtube.com/watch?v=HML4dOqXorc ጌድዎን ዋሽንግቶን ውስጥ ለሻቢያ እምነት ተከታዮች(ልብ በሉ ወጣቶች በቦታው የሉም) ኤርትራዊ ማንነት ከሌሎች ማንነቶች ሲወዳደር ያለውን ብልጫ ጣራ በሚነካ ጩከትና ትእቢት ሲለቀው ይታያል። ስሙን ሳይጠራ ከኤርትራዊነት ጋራ እየተነፃፀረ እሚጎሸመው ያለው ያው የፈረደበት የኛው ኢትዮጵያዊነት መሆኑ የኤርትራውያን ሚዲያ ለሚከታተል ግልጽ ነው። ጌድዎን በዚህ የቪድዮ ሰባካው ክ40ኛው ደቂቃ ጀምሮ ከሚለው በጥቂቱ እንመልከት፤ 
  • ኤርትራዊ ማንነት ዛሬ አንድ ነገር ነገ ሌላ ነገር አይልም ።እንደ እሥሥት አይቀያየርም 
  • ኤርትራዊ ማንነት በሌሎች ሳንባ    አይተነፍስም። በራሱ እንጂ በድጋፍ አይቆምም 
  • ኤርትራዊ ማንነት እንደወርቅ በሳት የተፈተነ ነው 
  • ኤርትራዊ ማንነት በተረት የተመሰረተ አይደለም። ምኞት የወለደውም አይደለም። 
  • ከአማራና ከትግሬ ጋራ አምልኮ መፈፀም ኤርትራውነትን ያደበዝዛል  
ምንም እንኳን ጌድዎን ይህን ይበል እንጂ መሬት ላይ ያለው ሃቅ እሚያሳዬው ሌላ መሆኑ እሱም ልቡ አይስተውም። በደርግ ጊዜ በኢትዮጵያ ጠላትነት ላይ የቆመው ብሄረተኝነት ከናጽነት በኋላ የተሰጠው ተስፋ ሁሉ ውሃ ስለበላው ኤርትራዊነት በአዲስ ራእይ ማቆም አልተቻለም።ሻቢያዎቹ ኤርትራዊነትን ለማቆም ብቸኛ አማራጫቸው አሁንም በኢትዮጵያ ጠላትነት ዙርያ ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ካሳለፉት መከራ ብዙ የተማሩ በመሆናቸው ሻቢያ በስልጣን እንዲቆይ የሚረዳውን ያደርጋሉ ተብሎ አይጠበቅም። ኢትዮ ወኤርትራ ግንኙነት አንድ ቀን እርቅና ሰላም መውረዱ አይቀሬ ነው። ነገር ግን ይህ የሚሆነው ሻቢያ ያመጣው ያልተገራ ብሄረተኝነት(Wild Nationalism)ሲሰክን ብቻ ነው። ሻቢያ ፕላኑን 180 ዲግሪ ማዞር ይኖርበታል። ይህም በትናንሽ መንግስታት ከተከፋፈለች ኢትዮጵያ ሊያገኘው ያቀደውን ሰርዞ አንድነትዋ ከተጠበቀ፤ ሰፊ እምቅ ሃብት ካላት አገር በመከባበር እንዴት መጠቀም እንደሚችል ማዬት መቻል አለበት። ሻቢያዎች ከተሰቀሉበት ማማ ወርደው ከህዝብ ብዛታቸውና ከኢኮኖሚ አቅማቸው ተመጣጣኝ የሆነ በአካባቢው የሚኖራቸውን ስፍራ እየመረራቸም ቢሆን መቀበል አለባቸው። ኢትዮጵያን የማተራመስ አጀንዳም ግብጽ በረጅም እጅዋ ያልቻለችው እነሱ በውክልና ሊያስፈጽሙት እንደማይችሉ ሊረዱት ይገባል። ይህ ሲሆን ነው ለኢትዮጵያውያን እርቅና ሰላሙ ትርጉም ሊሰጥ የሚችለው። 

ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ ወይ ጣፍጠው ወይ መረው ታገኟቸዋላችሁ

ጌታቸው ኃይሌ
ከአንድ ዛፍ ፍሬ ለመልቀም የሚፈልግ ከመልቀሙ በፊት መጀመሪያ ፍሬውን መቅመስ ይኖርበታል። አንዳንድ ዛፍ ዠርገግ ብሎ ሲያዩት ልብ ይማርካል። አበባው በጭለማ ሳይቀር ይታያል፤ ያስደስታል። ለሕይወት የሚሆን ፍሬ ግን ላይኖረው ይችላል። እንደዚያ አምሮ ገምሮ ሳለ የሚጠቀሙበት ትሎች ብቻ ሊሆኑ ይችላሉ።

አንድ ሰው ስሙን ከአካዴሚክ ማዕረጉ (Ph.D) ጋር እየጻፈ ደብዳቤ ይልክልኝ ነበረ። ለማዕረግ ያበቃውን ድርሰት (dissertation) የጻፈው ስለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ነው። የኋላ ኋላ እንደተረዳሁት፣ አድራሻየን ፈልጎ የጻፈልኝ በችሎታው የሚያገለግልበትን ሥራ በማፈላለግ እንድረዳው ኖሯል። ዛፉ ዲፕሎማው ነው፤ ፍሬው ድርሰቱ ነው። የድርሰቱን ቅጂ በፈቃዱ ላከልኝ። ሳነበው አዘንኩ። እንዴት አንድ ዩኒቨርስቲ ይኸንን ድርሰት ለማዕርግ በቂ አድርዶ ይቀበለዋል? እኔ ብሆን ለPh.D ቀርቶ ለBAም እንኳን አልቀበለውም። እንዴት አንድ መርጦ በያዘው መስኩ የሚመራመር ሰው የአርዮስን ክሕደት ለንስጥሮስ ወይም የንስጥሮስን ክሕደት ለአርዮስ ይሰጣል? መምህሩስ (ምንም ሙስሊም ቢሆን) ይኸንን ስሕተት እንዴት ያሳልፈዋል? የአርዮስንና የንስጥሮስ ዳሕጽ ማማታቱን ለምሳሌ ያህል አነሣሁት እንጂ፥ ድርሰቱስ ስሕተት አልባ ገጾቹ በቍጥር ናቸው።

ይኸን ታሪክ ለምሳሌ እንዳነሣ ያሳሰበኝ አቶ ተክሌ የሻው ዶክተር ላጵሶ ዴሌቦ በኢሳት(ESAT) አማካይነት በሰጠው የኢትዮጵያ ታሪክ ትምህርት ላይ ስሕተት ስለታየው ያንን ለማረም በ10/30/ 2015 በቀረበ ጊዜ በሱና በጋዜጠኛው መካከል በተደረገው ውይይት ላይ የታዘብኩት ትዝብት ነው። ለዶክተር ላጵሶ አክብሮት አለኝ። መጻሕፍቱን ያነበብኩት እሱ ቸሮኝ ነው። የኢሳት ጋዜጠኞችና አቶ ተክሌ ወዳጆቼ ናቸው። ውገናየ ከታሪካችን ጋር ነው።

የጋዜጠኛውና የአቶ ተክሌ የሻው ውይይት አጀማመሩ ግራ የሚያገባ ነበር። ጋዜጠኛው፥ “ስሕተቱ ምንድነው፤ እስቲ ንገረን?” ብሎ በማስጀመር ፈንታ፥ የታሪክ ትምህርት ዲፕሎማ ሳይኖርህ፥ የታሪክ ባለሙያ (ባለ Ph.D) ለመሞገት ምን ችሎታ አለህ? የሚል መንፈስ ያዘሉ ጥያቄዎች አከታተለበት። እርግጥ ማንም ተነሥቶ ማንንም ቢተች አያምርበትም። አንድ ሰው እኩያው ያልሆነን ሰው ልተች ሲል መድረኩን መንሣት ይቻላል፤ የተለመደም ነው። መድረኩን ከሰጡ በኋላ ግን ሲያስፈልግ እንደጋዜጠኛ እየጠየቁ መልሱን በጥሞና ማዳመጥ እንጂ በፖሊስ ምርመራ ዓይነት በተሞጋቹ ስም መከራከር በጋዜጠኝነት ሙያ የተለመደ አይደለም። አዳማጮች የአቶ ተክሌን በመልሱ (በፍሬው) እንጂ በዛፉ (በዲፕሎማው) እንዳልፈረዱት እገምታለሁ። ደሞም እኮ መጽሐፉን ላነበበ አቶ ተክሌ ማንም አይደለም።

እርግጥ አንድ ሰው በአንድ ሞያ ላይ ለመዋል፥ ሞያውን ማስመስከር ይጠበቅበታል። Ph.D ሁሉ ተጠርጣሪ ነው አይባልም፤ እኔም አልልም። የፈለግሁት በሙያ ረገድ Ph.Dን ብቸኛ መተማመኛ ማድረግ ስሕተት ነው ለማለት ነው። ለምሳሌ የጋዜጠኝነት ዲግሪ የሌላቸው ታላላቅ ጋዜጠኞች እናውቃለን። ኢሳት ውስጥ አገራቸውን የሚያገለግሉ ሁሉ የጋዜጠኝነት ዲግሪ ያላቸው አይመስለኝም፤ ካላቸው አስተያየቴን በደስታ እለውጣለሁ።

የታሪክ ዕውቀት የሚገኘው የታሪክ ምንጮችን በማንበብ ነው። አቶ ተክሌ አንቱ የሚያስብል የታሪክ መጽሐፍ ደርሷ። በዚያ መጽሐፍ ውስጥ ዶክተር ላጵሶ ያለፋቸው ብዙ ቁም ነገሮችን አስተምሮናል። እኔም ብሆን ማንም የታሪክ አስተማሪ አላስተማረኝም። ታዲያ ከልጅነት ጀምሮ ውሎየ የኢትዮጵያን የታሪክ ሰነዶች ማንበብና መመራመር፣ ማመሳከርም ሆኖ ሳለ፥ ታሪክ አልተማርክምና ስለኢትዮጵያ ታሪክ ለመናገር ብቃት የለህም ብባል ማን እሺ ይላል?
ዶክተር ላጵሶ የመረመረው አቶ ተክሌ ያልመረመረው በሁለቱ ተራኪዎች ማህል ልዩነት የፈጠረው የታሪክ ምንጭ የትኛው ነው? እንዲያውም፥ ፕሮፌሰር ላጵሶ፥ “ዶክተር ስናይደር ነግሮኛል” ሲል ሰምቸዋለሁ። የታሪክ መምህራችን ዶክተር ላጵሶ ዶክተር ስናይደር ያነበበውን ደብተራዎች የጻፉትን አላየውም ማለት ነው። ትምህርት አስኪጨርሱ፥ ከመምህር በታች መሆን
ሥርዓት ነው። መምህር ከሆኑ በኋላ ግን፣ ሲሆን መብለጥ አለዚያም እኩል ሆኖ መገኘት ያባት ነው። ለመስማት የፈለግሁት
“ይኸንን ለዶክተር ስናይደር አስረድቸዋለሁ” ሲል ነበር።

በውይይቱ ላይ ለአቶ ተክሌ የቀረበለት ሌላው ጥያቄ፥ “ታሪክን መጻፍ የሚችል ማነው?” የሚል ነበር። ጥያቄው ያዘለው ምሥጢር ባይኖረው፥ መልሱ ቀላል ነበር፤ “ታሪክን መጻፍ የሚችል ታሪክ ዐዋቂ” ነው። ታሪክ ዐዋቂ የምለው፥ እንደ ዶክተር ላጵሶ ታሪክ የተማረውን፥ እንደ አቶ ተክሌ የታሪክ ምንጭ የመረመረውን፥ እንደ ፕሮፌሰር ታደሰ ታምራት ገድላቱንና ታምራቱን የታሪክ ምንጭነታቸውን ያሳየውን፥ እንደ ደብተራዎቹ ድርጊቱ ሲፈጸም በጊዜው የነበረውን (ማን ይናገር? የነበረ፤ ማን ያርዳ? የቀበረ) ነው። ግን ጥያቄው ንጽሕና የጐደለውና ምሥጢር ያዘለ ለመሆኑ፥ በየቀኑ የምንሰማው ትችት ይመሰክራል። “የኢትዮጵያን ታሪክ የጻፉ ደብተራዎች ናቸው፤ አማሮች ናቸው” የሚለውን ዋጋ ቢስ ትችት ያቀፈ ነው። ትችቱ በውይይቱ ላይም በግላጭ ተነሥቷል። ኢትዮጵያ ታሪካዊ አገር መሆኗን የነገሩንና ዓለምንም ያስረዱልን፣እኛንም ባባቶቻችን ታሪክ እንድንኮራ ያደረጉን “ደብተራዎችና አማሮች” ናቸው፤ ክብርና ምስጋና ይድረሳቸው።


ግን ታሪክ ጸሐፊነታቸው የተነቀፈው፥ደብተራዎችና አማሮች ስለሆኑ ነው ወይስ እንደሚታሙት “ተረት ተረት” ስለጻፉልን ነው? ታሪካችንን ማን እንዲጽፈው ነው የተፈለገው? ማንስ እንዳይጽፍ ማን ከለከለው? ምዕራባውያን ዘንድ ሄደን በታሪክ ዕውቀት የምንመረቀው ደብተራዎቹና አማሮቹ የጻፉትን ምዕራባውያን በየቋንቋቸው የተረጎሙትን አጥንተን አይደለም እንዴ? አውሮፓውያንና ኢትዮጵያውያን (አማሮችና ደብተራዎች) በጻፉት የኢትዮጵያ ታሪክ መካከል ያለው ልዩነት የት ላይ ነው? ምንም ልዩነት ሳይኖርባቸው አንዱ ዶክትሬት ያሰጣል፥ ሌላው ይነቀፋል። ስለ ግራኝ ዐመፅ ዐረብ ፋቂህ በዐረቢኛ የጻፈውንና ደብተራዎቹ የጻፉትን አስተያይታችሁታል? ከዝርዝሩና ከጸሐፊዎቹ የግል አስተያየት (ያላዩትን ከመጻፍ) በቀር እውነቱ ላይ በምንም አይለያይም። አንዱ “እገሌ ሞቶ ነፍሱ ገነት ገባች” ሲል፥ ሌላው ያቺኑ ነፍስ “ገሃነመ እሳት ገባች” ይላል።
አዲስ ማስረጃ ሲገኝ የተሳሳተ ታሪክ ማረም የተለመደ ነው። አሁን ዛሬ የትኛው አዲስ ሰነድ ተገኝቶ የትኛውን ተረት ሊያርም እንደቻለ ማስረጃ ይሰጠን። አብረን እንመረምረዋለን። ደብተራዎቹና አማሮቹ በዘመኑ ተገኝተው በዓይናቸው ያዩትንና በጆሯቸው የሰሙትን ጽፈዋል። ያላየና አዲስ ማስረጃ የሌለው ሰው የነሱን ድርሰት የመንቀፍ መብት እንዴት ይኖረዋል? ማስረጃ ተፈጥሮ እንደሆነ፥ ፍጡር ማስረጃ አንቀበልም።

ለአቶ ተክሌ የቀረበለት አስገራሚ ጥያቄ “አማራ ማነው?” የሚል ነበረ። ነገሩን የቆሰቆሰው ዶክተር ላጵሶ፥ ተጠያቂው አቶ ተክሌ! ሞረሽ ወገኔን ለምን መራህ ለማለት ይሆን? አለቦታው! ሌላው የሚናፈሰው ነቀፋ “የኢትዮጵያ ታሪክ የሚባለው የነገሥታት ታሪክ እንጂ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ አይደለም” የሚል ነው። ይህ መሠረት የሌለው ነቀፋ በውይይቱ ላይ ሰፊ ቦታ ተሰጥቶታል። የዚህ ነቀፋ ምንጭ ሊቃውንቱ በግዕዝ ያቆዩልንን ታሪክ ምዕራባውያን ሲያሳትሙት “Royal Chronicles” የሚል ስም ስለሰጡት ይመስለኛል። ነቀፋውን አንድ ሰው ጫረው፤ ሆድ የባሰው ሁሉ እየተቀባበለ አለኳኰሰው። እኔ እንዳነበብኩት ከሆነ፥ የተነቀፈው ታሪክ የኢትዮጵያ መንግሥት ታሪክ ነው። መንግሥት ደግሞ ንጉሥና ሕዝብ ነው። የሌላው ሁሉ አገር ታሪክም ቢሆን፥ እንደኛው የመንግሥቱ ታሪክ ነው፤ ከዚህ የተለየ የሕዝብ ታሪክ የሚባል ብሔራዊ ታሪክ የትም የለም። ምናልባት “እገሌ እገሊትን አግብቶ እነ እገሌን ወለደ። በዘመነ ሕይወቱ ይህን ይህን ሠርቶ ከዚህ ዓለም በሞት ወይም በምንኵስና ተለየ” የሚል የቤተ ሰብ ታሪክና የጻድቃኑ ገድላትና ተአምራት ቢጠራቀሙ የሕዝብ ታሪክ የሚባል ነገር ይወጣቸው ይሆናል። ዶክተር ላጵሶ ከእነዚህ ገድላትና ተአምራት ውስጥ ብዙዎቹን እንዳላነበባቸው የመጽሐፉ ይዞትና የዘረዘራቸው ዋቢ መጻሕፍት ይመሰክራሉ። ማስረጃዎችን ፈልጎ ያላጣ አላገኘሁም ብሎ አያጕረመርምም።

ለምሳሌ፥ ታሪክ ጸሐፊዎች ኦሮሞዎች ዳዩ ዳባ የሚባል ንጉሥ እንደነበራቸው ያውቃሉ? ደብተራዎቹ የጻፉትን ተአምረ ማርያም ካላነበቡ ከየት አምጥተው ያውቁታል? ተአምሩ እንዲህ ይላል፤

አረሚዎች (= ኦሮሞዎች) የክርስቲያኑን ሀገር (ዋካትን፣ ጠጠራን፣ ምድረ በረሐን፣ መቅደላን) ሊያወድሙ ተመካክረው ከብዙ ቦታ ዋጃ ላይ ከተቱ። ምክንያቱም፣ አረሚዎች፣ (አዲስ ንጉሥ) ሲያንግሡ የነገሠው አገር የማውደም ልምድ አላቸው። በዚያን ጊዜም ዳዩ ዳባ የሚሉት ነግሦ ነበረ። አገር የሚያወድሙበትና ጦር የሚያውጁት በኅዳር ወር በሊቀ መላእክት የቅዱስ ሚካኤል በዐል ዕለት ነበር። . . . እመቤታችን ማርያም አረመኔዎቹ አገሯን ለማጥፋት ጨክነው እንደተነሡ ስታይ፥ሳያስቡት፣ ወደምድረ አዳል መርታ ጠላቶቻቸው (ሙስሊሞቹ) እጅ ላይ ጣለቻቸው። ከ12 ነገሥታት (= የጎሳ መሪዎች) አንድ ንጉሥ ብቻ ተረፈ፤ ከሠራዊቱም አንዳንድ ለወሬ ነጋሪ ተርፎ ይሆናል።

ይህን እዚህ የጠቀስኩት “የአባ ባሕርይ ርድሰቶች” እሚባለው መጽሐፌ ውስጥ ስላልገባ ነው። ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ምዕራባውያን፥ ደብተራዎቹና አማሮቹ የጻፉትን መሠረት ሳያደርግ ተአማኝነት ያለውን የኢትዮጵያን ታሪክ መጻፍ አይችልም። እነሱን (በእነሱነታቸው) የጠላ በምዕራባውያን እጅ አዙር ይጠቅሳቸዋል።

(አባ ባሕርይና አለቃ ታየ ስለ ኦሮሞዎች የጻፉትን የሚተቸውን “የአባ ባሕርይ ርድሰቶች” ለማንበብ የፈለገ ከኢንተርነት ስላለ (The Works of Abba Bahriy – by Dr. Getatchew Haile) በነፃ ቀድቶ ማንበብ ይችላል።)

ግልጽ ደብዳቤ

ግልጽ ደብዳቤ 
ጥቅምት 17, 2008 / November 28, 2015

 የገላጋይ ቤተሰብ ዴንበር፡
ኮሎራዶ ሳን ሆዜ፡ ካሊፎርኒያ

ለአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪዎች 
ለኢሳት ተሌቪዥን አዘጋጅዎች
 ግልባጭ: ለተለያዩ የሚድያ ሴነተሮች

 ጉዳዩ። የተወገዘ ወንጀለኛ፡ የነጻነት አርበኛ አይሆንም ሰሞኑን በአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪዎችና የኢሳት ተሌቪዢን አዘጋጆች በኩል አምሳሉ ተሾመ የተባለ የተወገዘ ወንጀለኛ ግለሰብ በተመለከተ የተሳሳተ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲሰራጭ ሰንብቶአል። ይህ ዜና ከአርበኞች ግንቦት ሰባት እና ከኢሳት አልፎ በማህበራዊ ድረ-ገጾችም ላይ በስፋት ሲሰራች ሰንብቷል። ማን ያውራ የነበረ፡ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ፡ ይህን ወንጀል አደግ ግለሰብ በቀጥታ የምናወቀው ውድ ሀገራችን ለማየት ከአሜሪካ በሄድንበት ወቅት መንገድ ጠብቆ፡ ተወዳጅ አባታችንን በግፍ የተገደለብን፡ በአፈሙዝ በሰደፍ የተደበድብን የተዘርፍን፡ እንዲሁን 10 አመት ህጻን እያስለቀሱ ከአያቷ አስከሬን አጠገብ የዘረፈ ስለሆነ፡ ይህን ወንጀለኛ ስለዚህ ገልሰብ የምናውቀውን እውነት ለወገኖቻችን ማካፈል እንፈልጋለን። 

በፈርንጆች አቆጣጠር በ1995 አ/ም አራት ሆነን ቤተሰብ ለመጠይቅ ወደ ኢትዮጳያ ጉዞ ጀመርን። እስከ ባህር ዳር በአይሮፕላን ሄደን ወደ ጎንደር ደግሞ ሀገር ማየት እንድንችል፡ በመኪና ለመሄድ ታቀደ። አባታችን ልጆቻቸውንና 10 አመት የልጅ ልጃቸውን ለመቀበል መኪና ተከራይተው ባህር ዳር ጠበቁን። ከኛ ቤተሰብ ተጨማሪ ሌሎች ሰዎች ስለነበሩ የተከራዩልን መኪና ሰፋ ያለ ነበርና ሰባት ራሳችን ተሳፍረን ወደ ጎንደር ማምራት ጀመርን። አባታችን ከፊት ለፊት የልጅ ልጃቸውን አቅፈው የቦታዎን ስም እየነገሩን እኛም የሀገራችንን ውበት በጉጉት እያየን በጎዞ ላይ እንዳለን፡ ጨለማን ተገን አድርገው፡ ሳይታሰብ በኢራቅና ሶሪያ እንደምናያቸው አሸባሪዎች ፊታቸው የተሸፈኑ አራት የታጠቁ ወታደሮች እጅግ በሚያስፈራ ድምጽ መኪናው እንዲቆመ አዘዙ። መኪናው ድንገት ቆመ። ድንገት ያላሰብነው ስለነበር ሁላችንም ተደናገጥን። አባታችንም ወደ እኛ ዞር ብለው አይዟችሁ አሉንና ወደ ሽፍቶቹ ወጣ ብለው ምነው ደግሞ አገራችን ላይ ልትዘርፉን ነው እንዴ? እኔ ደማሴ ገላጋይ ነኛ። እነዚህም የኔ ልጆች ናቸው በማለት ለወታደሮቹ ከተናገሩ በኋ ወደኛ ዘውር ብለው እግራቸውን ይዛ የምታለቅሰውን የልጅ ልጃቸውን አይዦሽ እያሉ ለመከላከል ወጣ ብለው መነጋገር ሲጀምሩ በጭካኔ ከፊታቸን በጥይት ገደሏቸው። ሁላችንም በያለንበት በደንጋጤ ወድቀን፡ ተራችንን ስንጠብቅ እንደ አበደ ውሻ እየተራወጡ በአሙዝና በሰደፍ እያጋጩ የያዝነውን ንብረት ሁሉ ከተለበሰ ጫማ እስከ ህጻን ዳይፐር ለቃቅመው ዘርፈው ወሰዱ። ከነዚህ ሰዎች አንዱ የሰሞኑ “አርበኛ” ነበር። ታዲያ የጻነት አርበኛ እንደዚህ ነው እንዴ? 

በቤተሰባችን ላይ በደረሰው አደጋ በጥልቅ ያዘውነው የጎንደር ህዝብ ዳር እስከዳር ተንቀሳቅሶ ወንጀለኞችን መከታተል ጀመረ። እነዚህ ወንጀለኞች ከኛ የዘረፉትን ሀብት እየተከፋፈሉ፡ በውስኪ እየተሳከሩ አንታወቅም ብለው ሲንቀሳቀሱ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ ሴራው ተጋለጠና የአባትችን አስክሬን አፈር ሳይለብስ ወንጀለኞች አምበል የነበረው መሀል ጎንደር ከተማ ላይ ተገደለ። የሰሞኑ “አርበኛ” ደግሞ ለማምለጥ ሲሞክር ወጣትና ሴቶች ነብሰ ገዳይ ነብሰ ገዳይ እያሉ እያራወጡ ይዘው ከወንጀል ግብረ አበሩ ጋር ለፍርድ ቀርበው ወንጀላቸውን አምነው ተፈርዶባቸው ነበር። እንደነዚህ አይነት የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች አማካኝነት በጎንደር ከተማና በምዕራብ ጎንደር ገጠሮች ከፍተኛ የወንጀል መስፋፋት በርክቶአል። ባለንብረቶችን በሌሊት መዝረፍ፡ ሴተኛ አዳሪዎችን ማስገደድ፡ በተንቀሳቃሽ መኪናዎች ላይ አደጋ መጣል፡ ህጻናትን ጠልፎ ገንዘብ መጠየቅ። የሚያሳዝነው ግን ይህ ወንጀለኛ ለፈጸመው ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት ሳይገኝ፡ እንደገና መሳሪያ ታጥቆ ወንጀል በሰራበት፡ ደም ባፈሰሰበት፡ ንብረት በዘረፍት፡ ቤተሰብ ባስለቀሰበት ከተማ ታጥቆ ሌላ ሽብር፡ ሌላ ነብስ ግዲያ ለመፈጽም እድል ማግኘቱ ነው።

በተለይም ደግሞ፡ አርበኞች ግንቦት ሰባትና የኢሳት አዘጋጅዎች እንደነዚህ አይነት በወገን ላይ ኢሰባዊ ወንጀል የፈጽሙ ግለሰቦችና የተወገዙ ወንጀለኞችን “አርበኞች” የሚል ስያሜ ለጥፎ የሚያስራጩት ፕሮፖጋንዳ ለህብረተሰባችን አደገኛ ነው እንላለን። ለጊዝያዊ ለፖለቲካ ፍጆታ ሲባል ወንጀለኞችን ማሞገስ፡ ለነጻነት የሚካሄደውን ትግልም ሆነ ነጻ ሚዲያ ለመገባት ለሚካሂደው ጥረት አይበጀም። ስለዚህ፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪዎችና የኢሳት ቴሌቪዢን አዘጋጅዎች፡ ማሳሰቢያችንን ተገቢ ትኩረት ሰጥተው ግምገማና ማስተካከያ እንዲያደርጉ እናሳስባለን።

 የገላጋይ ቤተሰብ ዴንበር፡
 ኮሎራዶ ሳን ሆዜ፡ ካሊፎርኒያ