ከእለኔ አለሙ
የዛሬ ዓመት የእሳት ራዲዮ ና ቴሌቪጅን የተመሰረተበት አምስተኛ ዓመት የሚከበርበት ና በሜሪላንድ ግዛት 31 ኛውን
የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ፣ የሙዛቃና የባህል ፌስቲባል በሚካሄድበት ዋዜማ ግንቦት ሰባት አርበኞች ግንባር በጉጉት
ይጠበቅ የነበረው የግንቦት ሰባት ንቅናቂ መች ኃይል የመጀመሪያውን ታሪካዊ የማጥቃት ጦርነት በህዋት ወያኔ
ጦር በወልቃይት ጠገዴ ላይ አድርጎ ሃምሳ ወታደር ገድሎ ሰልሳ አቁስሎ ብዛት ያላቸው ወታደሮችን ከባድና ቀላል
መሳሪያዎችን ማረከ የሚል በእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን በሰበር ዜና ንፋ እምቢልታ ጎስም ነጋሪት ቃና ባለው ሙዚቃ ተጅቦ
ተነግሮናል። የግንባሩ ቃለ አቀባይ ዘመነ ካሴ ጦርነቱ ተካሄዶል የተባለውም ውጤት ተገኝቷል አሁን ፊሽካው ተነፍቶአል ከዚህ
በኃላ ወደ ፊት እንጂ ወደ ኃላ አይታሰብም ብሎ ሲረጋግጥ በተከታዩ ሁለተኛ ቀን የግንቦት ሰባት ሠራዊት ከኤርትራ አምስት
መቶ ኪሎ ሚትር በመጓዝ በደቡብ ጎንደር በደብረታቦር አውራጃ መሽጎ በነበረው የኢህአዴግ ጦር ላይ ድንገተኛ የማጥቃት
እርምጃ ወስዶ በብዙ መቶ የሚቈጠር ጦር ደምስሰውና አቁስለው ቁጥሩ ከፍተኛ የሆነ ኃይል መማረካቸው በእሳት ራዲዮና
ቴሌብጅን በሰበር ዜና ተበሰረልን። በሦስተኛው ቀን ወደ ጎንደር ከተማ ዙርያ በመገስገስ ከአዘዞ ከተማ በአምስት ኪሎ ሚትር
ርቀት ላይ የነበረውን አለ የሚባለውን የወታደር መሣሪያ ዴፖ በማጋየት በወያኔ መንግሥት ላይ ትልቅ ኪሳራ ማድረሱ
ተገለፀልን። እንደ ዜናዉና እንደ ሠራዊቱ የፍጥነት እንቅስቃሴ በትንሽ ቀናት ዋናውን መናገሻ ከተማን አዲስ አበባን
ይቆጣጠራል የሚሰኝ ነበር።
የሠራዊቱ እንቅስቃሴና የዜናዉ ፍጥነት በ1983 ዓ/ ም ሻቢያ አስመራን ለመቆጣጠር ወያኔ
ኢህአዴግ አዲስ አበባን ለመቆጣጠር ካደረጉት የጦርነት እርመጃና ፍጥነት የግንቦት ሰባቱ ሠራዊት እንቅስቃሴ በአስር
እጥፍ ይፈጥን ነበር። ያ ህዘብ በተለይም በውጭ ሀገር የሚገኘውን ኢትዮጵያዊ ያማለለው የግንቦት ሰባት ድርጅትና የእሳት
ራዲዮ የተናገሩት ዜና ቱሪናፋና የተጭበረበረ ደረጃውን ያልጠበቀ ውሸትና የሐሰት ፕሮፖጋዳ እንደነበር አይረሳም።
ግንቦት
ሰባት ድርጅትና የሻቢያ መንግሥት የወልቃይት፣የጠገዴን ና የጠለምት ህዝብ ያነሳውን የማንነትና የመብት ጥያቄ
በመጥለፍ የእነርሱ የፕሮፕጋንዳ ፍጆታ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከር ትክክል አለመሆኑና የወለቃይት ህዝብ መብቱን
ለማስከበር ከህገ መንግሥታዊ አካሄድ ጀምሮ እስከ የነፃነት የትግል ፊልማው በራሱ በህዝቡ ጊዜ የሚወሰን መሆኑና ከዚህ
አይነት አሳፋሪ ፕርፖጋንዳ እንዲታቀቡ የወልቃይት ንቅናቂ ለእሳትና ለግንቦት ሰባት ድርጅት ማስጠንቀቂያ ሰጠዋል።
በተለይም አንዳንድ የአካባቢው ተወላጆች ለዚህ ፕርፖጋንዳ ተባባሪ በመሆናቸው ቅሬታቸውን ገልፀዋል በመጨረሻ እኛ
የወልቃይት ህዝብ ከወያኔ ነፃነታችንና መብታችን ለማስከበር የግንቦት ሰባትን ወይም የሻቢያን ሞግዚትነት አያስፈልገንም
በሌላ በኩል ሀገራችን ኢትዮጵያ ነፃ ለማውጣት በጋራ ልንሰራና ልንታገል እንችላለን ሆኖም ይህ በወልቃይት ምድር
ያላደረጋችሁት ጦርነት አደረግን ያልዋላችሁበትን የጦር ሜዳ ገድል ገደልነን ማረክን ፍሽካ ነፋን ማለት በእኛ ህዝብ ላይ
ያላችሁ ንቀት ሲሳይ በተጨማሪ ውጭ ሀገር ያለው ወገናችን ለትክክለኛ ትግል እንዳይረዳ ሕዝቡን በእኛ ስም እያታለላችሁ
ገንዘቡን እየዘረፋችሁ ስለሆነ ከዚህ ድርጊት እንዲታቀቡ በማለት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል ።
ከዚያም በሆላ በጎንደር ክፍለ ሀገር
ወያኔ በፈጠረዉ የቅማንትና የአማራ ማህረተሰብ ግጭት የፓለቲካና የፕሮፕጋንዳ ፍጆታ ለማግኘት ግንቦት ሰባትና አሳት
ራዲዮ አንዲ የቅማንት ህብረሰብ ተቋርቋሪ በመምሰል የማንነት ጥያቄ አንስተው ከስርአቱ ጋር የሚፋለሙና እየተዋጉ ያሉ
ጀግናው የቅማንት ህዝብ ሲሉ፣ በሌላ ጊዜ ወያኔ ጠፍጥፎ የፈጠራቸው ሲላቸው በዚህ ግርግር በመተማ የተፈጠረውን ግጭት
ስበብ በማድረግ የግንቦት ሰባት አርበኞች መተማ ላይ የማጥቃት እርምጃ ወሰደን ብለው ያስተላለፉት ዜና እሳት ራዲዮ ና
ግንቦት ሰባት በጎንደር ሕዝብ ሙሉ በሙሉ እንዲናቅ አድርጎታል ። ከዚህ በኃላ በሃገራችን ትልቁ ንቅናቂ የተደረገው
በኦሮምያ ክልል ወያኔ ኢህአዴግ በልማት ስም ሊካሄድ የነበረው የመሬት ነጠቃና በዚህም ስበብ በተማሪዎች የተጀመረው
አመጽ አድጎ መላውን የኦሮሞ ህዝብ ያነሳሳው ከስድስት ወር በላይ የቆየውን ተቃውሞ ለብዙ ወጣቶች ሞት በሺ
የሚቆጠሩትን ለእስርና ለግዞት የዳረገውን የወያኔን ስርአት ያናወጠውን ህዝባዊ አመፅ የኛዎቹ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበርና
የእሳት ራዲዮ በመግለጫቸው በኦሮሞይ ክልል የሚደረገው ህዝባዊ አመፅና ትግል ከጀርባው የአርበኞች ግንቦት ሰባት
ድርጅት አለበት። አመፁ ከአሮሞይ ክልል ወጦ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአመፁ እንዲቀላቀል ድርጅታችን ጠነክሮ እየሰራ ነው
ነበር ያለው ።
ቢያንስ እንኳ ለዚህ አመፅ መነቃቃትንና ስራ ሰርተዋል በሚል የኦሮሞ አክትቪስቶችን በሀገር ቤት ያሉ የኦሮሞ
የፖለቲካ ድርጅቶችን እንኳን የተወሰነ ድርሻ አልሰጣቸውም ። የኦሮሞይን አመፅ ከኋላ ሁኘ የምመራውና የማስተባብረው
እኔ ነኝ አለ ብርሀኑ ነጋ። ብርሀኑ ማለት ለእኔ ድፍረቱና የብልግናው መጠን ስለካው ከአንድ አባ ወራ ቤት ገብቶ ዘሎ
ከአባወራው መኝታ ቤት ገብቶ አባወራውን እስቲ የእግር ውሃ አሙቅልኝ ይህችን ካልሴም እጠብልኝ ብሎ ሴትዮቱን ጎትቶ
ወደ መኝታ ቤቱ የሚስገባ ባለጌ አድርጌ ነው የማየው የሚሰራቸው ስራዎች የሚሰጡኝ ትርጎሜ ይህው ነው። ከኋላ ሁኘ
አመጽን የምንመራው እኛ ነን ብሎ የግንቦት ሰባት ሊቀመንበርና ኮማንደር በሰጠው መግለጫ የኦሮሞ አክቲቪስቶች ና
ፓለቲከኞች እንዴት እንዳላገጡበትና እንዳሾፍበት ለተከታተለ በጣም የሚሳፍር ነው። ናዳ ። የግንቦት ሰባት መሪዎች
አያፍሩም እኛ ግን ስለ እነርሱ በማፈር ሰውነታችን አነሰ ።
ስለሆነም ግንቦት ሰባት ድርጅት ባለፈው ዓመት ፈፀምኩት ያለው
የጦርነት ገድል ከወልቃይት እስከ ኦሮማይ ምድር ምንም የሌለበት አንድም ጥይት አልተኰሰም የወደቀበትም የገደለውም የለ
አራት ነጥብ። በዚህ ፕርፖጋንዳ በመጠቀም የዋሁን ህዝብ እንዴት ከየትና መቼ ብሎ የማይጠይቀውን
ገንዘቡን መትልፈዋል። እነሆ የዚህን የዋህ ህዝብ የማስታወስ ችሎታው በጣም አጭር መሆኑን በመረዳት በዓመቱ የእሳት
ሬዲዮና ቴሌብጅን የተመሰረተበትን ስድስተኛ ዓመት በአሜሪካና በአውሮፓ እየተከበረ የገንዘብ እርዳታ በሚጠየቅበት
የሰሜን አሜሪካ 32 ዓመት በካናዳ በሚከበርበት ዋዜማ ላይ የግንቦት ሰባት የአርበኞች ሠራዊት 1800 ኪሎ ሜትር በመጓዝ
በአርባንጭ ከተማ ጥቃት ሰንዝሬ ሀያ ወታደሮችን ደምስሸ ስልሳ ወታደሮችን ማረኩ ሲል በሰበር ዜና በእሳት ተነግሮናል ።
አስቂኙ ድራማ የህዋት ወያኔ የመረጃና ደህንነት በአርባ ምንጭ ከኤርትራ የመጡ " ሽብር" ፈጣሪዎችን ከነ ሙሉ
ትጥቃቸውና ዝግጅታቸው ከመነሻቸዉ ስከታተል ቆይቸ ብዙዎችን በቁጥጥር ስር ካዋልኩ በኃላ ትንሾቹ ለማምለጥ ሲሉ
እርምጃ ወስደን ደመሰስናቸው የሚል ሰበር ዜና በኢትዮጵያ ቴሌቪጅን በተነገረን በአምስተኛው ቀን ነው ግንቦት ሰባት
ኃላፊነቱ የኔ ነው ያለው ። ሌላው አስቂኙ ድራማ የግንቦት ሰባት ሠራዊት በዚህ ጦርነትና ግዳጅ እያለ የሠራዊቱ ጠቅላይ
አዛዥ ኮማንደር ብርሀኑ ነጋ አውሮፓ ነበሩ። ይህ ሰውዬ መመላለስ አበዛ ላልመባል በአርባ ምንጭ ዜና አምታተው መግለጫ
ሰጠው ።
አቅጣጫ አስቀይረው ተቀላቀሉ ። ኮማንደር ብርሃኑ ነጋ ስለ አርባምንጩ ወታደራዊ ኦፕሪሽን መግለጫ
ከመስጠታቸው በፊት እንዴትና ምን ማለት እንዳለባቸው ከሻቢያ ወታደራዊና የመረጃ ክፍል የሚነገራቸውና የእሳት ራዲዮ
ምን መጠየቅ እንዳለባቸው ትዕዛዝ እንደሚሰጣቸው አያጠያይቅም ። የወያኔ ባለ ሥልጣኖች መግለጫ ሲሰጡ በወያኔ ፀጥታና
ደህንነት ኮች( ስልጠና ) እንደሚሰጣቸው ሁሉ ማለት ነው። አሰቂኙ ድራማ የእሳት ጋዜጠኛ መሳይ ሲጠይቅ ፕሮፌሰር
ብርሀኑ ይህ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ኃይል ከኤርትራ ተነስቶ አርባ ምንጭ በእግሩ ተጉዞ ጥቃት ሰነዘር ለማለት ለማመን
ይከብዳል ለመሆኑ ሠራዊቱ አርባ ምንጭ እንዴት ነው የደረሰ የሚል ነው። ኮማንደሩ ሲመልሱ ልክ ነህ መሳይ ከኤርትራ
አርባ መንጭ በጣም ሩቅ ነው ። ከዚህ ቀደም እንዳልነው ሠራዊታችን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል ይንቀሳቀሳል ።
አሁን
በተባለው ቦታ ከወያኔ ሰራዊት ጋር የተፈጠረው ግጭት ከአንዲት አንስተኛ ቡድን ጋር የተፈጠረ ነው ቡድኖም በተገቢ መንገድ
ግዳጆን ተወጣለች የተወሰኑ ጓዶች ተሰውተውብናል የሚል ነው። ዶክተር ብርሀኑ ስለዚህ የወታደር ቡድን
የሚውቀው አንድም ነገር የለም ይህን ቡድን የሚውቀው የሻቢያ መንግስትና የወያኔ ኢህአዴግ የመረጃና የፀጥታ ክፍል ብቻ
ነው የሚውቁት ። ቡድኑ የተላከው በእርግጥም በሻቢያ የደህንነትና የፀጥታ ክፍል ለተወሰነ ግዳጅ የተላከ ነው።
እንደሚታወቀው ሻቢያና ወያኔ አነዳቸው በአንዳቸው ላይ የስለላ ተግባር ይፈጽማሉ ።
በተለይ የወያኔ ፀጥታና መረጃ ትልቅ
ድርሻ አለው ።በዚህ መሠረት በእርግጥም የወያኔ የመረጃና የፀጥታ ክፍል ይህን የታጠቀ ኃይል ክትትል አድርጎበት የማጥቃት
እርምጃ ወስዷል ። የታጠቀው ቡድን በአብዛኛውን ሲያዝ ከፊሎቹ ተደምስሰዋል። ይህን በወያኔ ታጣቂ የደረሰበትን ሽንፈት
ሻቢያ ኃላፊነት መውሰድ አልፈለገም ። በብዙ መለኩ በፓለቲካም በዲፕሎማሲ መልኩ ኪሳራ የሚደርስበት ከመሆኑ በላይ
በሽብርተኝትት የሚስጠይቀው ሰለሆነ ኃላፊነቱን ብርሃኑ ይውሰድ ለእነርሱ ለፖለቲካ ፕሮፖጋዳ ይጠቅማቸዋል ገንዘብም
ያሰባስቡበታል ተብሎ ከሻቢያ ደህንነትና ፀጥታ ክፍል በተሰጠው ትዕዛዝ ነበር ኃላፊነቱ የእኛ ነው በሚል ኃላፊነት የጎደለው
መግለጫ የሰጠው ። ለመሆኑ እንደ ኮማንደር ብርሀኑ ነጋ ገለፃ ህዝባዊ እምቢተኝነትና የአመፅ ንቅናቄ ያለባቸውን ቦታዎች
እያሉ ለምን በአርባምንጭ ፀ በሣር ፓርክ ጦራቸው መገኘቱ ለምን አስፈለገ ቢባሉ ምን ሊሉ ይችላሉ ። በመጨረሻ ሀተተየን
በሁለት መሰረታዊ ጉዳዮች በማንሳት ፅሁፌን እቆጫለሁ ።
1ኛ/ ወያኔ ኢህአዴግ ና ግንቦት ሰባት የሚፈላለጉ ፣ ተናበውና ተስማምተው የሚሰሩ ድርጅቶች መሆናቸውና በተለይም
ህዋት ወያኔ በኢህአዴግ ስም ከፈጠራቸው ድርጅቶች በላይ ለግንቦት ሰባት ትልቅ ክብር እንዳለውና የዚህን ድርጅት መዳከም
በፍፁም እንደማይፈልግ ለማስረዳት ልሞክር
ህዋት ወያኔ የሚከሰስበት የኢትዮጵያን ህዝብ በዘር በጎሳ በመለያየት በክልል መንግሥት ሕዝብና ሀገር በመከፋፈል በፈላጭ
ቆራጭነት የሚገዛ አምባገነን ና የአነድ ዘር የበላይነት ያለው መንግስትና ሀገሪቱ ልትበተን የምትችልበትን የህግ ድንጋጌ አነቀፅ39
የሚራመድ መንግሥት ነው ተብሎ ይከሰሳል። ለዚህ የግንቦት ሰባት ድርጅት የኢትዮጵያዊነት ካባ በመልበስ ነፃነታችን አሁኑኑ
የሚሉና እኛ ከወያኔ ህዋት ጋር ያለን ልዬነት የምንፈልገው በአርቲክል 39 ከአብስኔዬ ኢትዮጲያ ጋር መኖር ሳይሆን መገንጠል
ነው ከሚሉ የኦሮሞ ነፃ አውጭ ድርጅት፣ከኦጋዴን ነፃ አወጭ፣ከሲዳሞ ነፃ አውጭ ድርጅት ከመሳሰሉት ከዘጠኝ ነፃ አወጭ ጋር
በሻቢያ የበላይ አስተዳደር እየተመራ የሚሰራ ድርጅት በመሆኑ ህዋት ወያኔ የኢትዬጱያ ህዝብ ከሻቢያ ከግንቦት ሰባትና
ከዘጠኙ ነፆ አውጪ ድርጅቶች አማራጭ አሁኑኑ ነፃነት በሚል ሀገሪቱን በአስቸኳይ ለማፍረስ ከተዘጋጅ አጥፊዎች ይልቅ እኔ
እሻሀለሁ የሚለውን አማራጭ የፈጠረለት አንድ ግንቦት ሰባት በመሆኑ ህዋት ወያኔ ይህን ድርጅት ባለውለታው
ያደርገዋል ይጠብቀዋል ይንከባከበዋል።
2/ኛ ህዋት ወያኔና የግንቦት ሰባት ድርጅት እየተነበቡ እየተቀናጅ የሚሰሩ ድርጅቶች ናቸው እንዴት ? በምን መልኩ? የህዋት
ወያኔ የ ደህንነትና፣የፀጥታና የስለላ ዘርፍ የግንቦት ሰባትን ድርጅት ማወቅ ብቻ ሳይሆን አብሮ በጋራ እንዲውም ብዙሀን
በመሆነ የሚሰራ ተቋም ነው። ለዚህ ማስረጃው ለውስጥ የደህንነቱ ስራ አደገኛ ነው ተብሎ የተጠረጠረውን የግንቦት ሰባት ዋና
ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌን በግንቦት ሰባት ውስጥ ያለው የወያኔ ደህንነት አንዳርጋቸው ከእንግሊዝ ወደ አስመራ
ሲጓዝ የጉዞውን ዶክመንት ከሀ እስከ ፐ በመላክ የመን ላይ የሚኖረውን ቆይታ በማሳወቅ የወያኔ የፀጥታ ቡድን ሄልኮብተርና
የፀጥታ ወታደሮችን በመያዝ በተባለው ቀንና ሰዓት ከየመን ሴኩሪት ጋር ይዘውት የሄዱት ከውስጥና በቅርቡ ከግንቦት ሰባት
አመራር ጋር ቀረቤታ ያለው የደህንነት ክፍል ሥራ ነው።ግንቦት ሰባት የድርጅቱ ዋና ፀሀፊ ጨምሮ በውሰጥ የህዋት የሰለላ
ኃይል እየተጠቃ ቢሆንም ይህን ለመፈተሽና ድርጅቱን ለመገምገምና ለማጥራት አቅም የለውም። ምክንያቱም ይህ የደህንነት
ኃይል በየ ቦታው ያለው ቁልፍ ቦታ መያዝ ብቻ ሳይሆን ለድርጅቱ ማጠናከሪያና ለእሳት ራዲዮና ቴሌብጅን መጠናከር
የማይታመን ገንዘብ ስለሚሰጡና ለግንቦት ሰባት ተቆርቆሪና ግንባር ቀደም ታጋይ ስለሚመስሉ ድርጅቱ የውስጥ ፍተሻና
ግምገማ በማለት የውስጥ ትግል ቢደርግ አንደኛ አቅም የለውም ሁለተኛ ድርጅቱ ይናዳል የገነዘብ ምንጭ ይቆማል። ሰለዚህ
የድርጅቱ ሰዎችም ሆነ ለውጥና ነፃነት ፈላጊው የእውነት ታጋዮ ጨምሮ ሳይነጋገሩ ተግባብተው ዝምታን መርጠዋል። ለዚህ
ነው አንዳርጋቸው ፅጌ እንዴትና በምን በወያኔ ደህንነት እጅ ወደቀ የሚለውን መልስ መስጠት የማይችሉት። ከዚህ ይልቅ ስለ
አንዳርጋቸው ፅጌ በህዋት ወያኔ እጅ አወዳደቅ በፈጠሩትና በፈለሰፍት ፕሮፖጋዳ አባሎቻቸው፣ ሕዝብን እራሳቸውን
አሳምነው እየተጓዙ ነው። ግንቦት ሰባት ድርጅት ራሱን ከጠላት የሚጠብቅበት ምንም ሜካኒዝም የለውም። የወያኔ ደህንነት
የግንቦት ሰባትን ድርጅት የሚየው የቤቷን በር ከፍታ አረቅቄና አረንቻታ የምትሸጥ ገንዘብና መተዳዳሪያ ብቻ የምትፈልግ
የሴት አዳሪ ቤት አድርጎ ነው የሚየው።
ስለዚህ ህዋት ወያኔ ባሳለፋቸው ተሞክሮዎች አስቸጋሪና አደገኛ በተባሉ ቦታዎች ሁሉ የስለላና የመረጃ ክፍሉ በውጤት ያለፈ በመሆኑ እንደ ግንቦት ሰባት ድርጅት አይነት ጥባ ጥቢ ለማጫወት በጣም ቀላል ነው። ከዚህ በላይ ያቀረብኩት አንስተኛ ማስረጃ የህዋት ወያኔ መረጃና የስለላ ተቋም በግንቦት ሰባት ድርጅት ውስጥ ወሳኙን ሚና መጫወት ላይ እንዳለ በማስረዳት ይህ ቡድን ግንቦት ሰባት ድርጅትን ማጥፋት ሳይሆን በመንከባከብ ማዳከም ለምን እንደ መረጠ ለማስረዳት ነው የተፈለገው ቀደም ሲል በተራ ቁጥር 1 እንደተገለጠው ግንቦት ሰባት ድርጅት ኢትዮጵያን ከሚበተን የነፃ አውጭ ድርጅቶች ጋር ስለሚሰራ ህዋት ወያኔ የተሻለ ድርጅትና የተሻለ ለሀገር አንድነት እኔው እበልጣለሁ የሚለውን የፓለቲካ ፍጆታና ትርፍ ስለሚገኝበት ነው ። ሌላውስ ምንድን ነው የወያኔ መረጃና ደህንንት ከግንቦት ሰባት የሚጠቀመው ።
2ኛ/ ለህዋት ወያኔ የግዛት ዘመን አደጋ በሃገር ቤት ያሉ በሰላማዊ መንገድ በህጋዊ መድረክ የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ድርጅቶች፣የሲቢክ አክትቪስቶች ፣ጋዜጠኞችና ብሎግይስቶች መሆናቸውን ህዋት ወያኔ ያምናል። እነዚህ ኃይሎች የሥርዓቱን ገመና በማጋለጥ ህዝቡን በማንቃትና በማደራጀት የሥርዓቱን ኢ ዲምክራሳዊነትና ዘረኝነት ለዓለም ህብረተሰብ በማጋለጥ ትልቅ ሚና የተጫወቱና የህዋት ወያኔን ሥርዓትን ፈተና ላይ የጣሉ ናቸው። ምርጫ 97 ና ከዚያም በፊት የታዮ ንቅናቄዎች የነዚህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎች ውጤት ናቸው። ስለዚህ ህዋት ወያኔ እነዚህን ተቋማት እንዲጠፍ ይፈልጋል። በዚህ ተግባር ላይ ከህዋት ወያኔ መረጃ በበላይ ትልቁን ሰራ እየሰራ ያለው የግንቦት ሰባት ድርጅት ነው።
ስለዚህ ህዋት ወያኔ ባሳለፋቸው ተሞክሮዎች አስቸጋሪና አደገኛ በተባሉ ቦታዎች ሁሉ የስለላና የመረጃ ክፍሉ በውጤት ያለፈ በመሆኑ እንደ ግንቦት ሰባት ድርጅት አይነት ጥባ ጥቢ ለማጫወት በጣም ቀላል ነው። ከዚህ በላይ ያቀረብኩት አንስተኛ ማስረጃ የህዋት ወያኔ መረጃና የስለላ ተቋም በግንቦት ሰባት ድርጅት ውስጥ ወሳኙን ሚና መጫወት ላይ እንዳለ በማስረዳት ይህ ቡድን ግንቦት ሰባት ድርጅትን ማጥፋት ሳይሆን በመንከባከብ ማዳከም ለምን እንደ መረጠ ለማስረዳት ነው የተፈለገው ቀደም ሲል በተራ ቁጥር 1 እንደተገለጠው ግንቦት ሰባት ድርጅት ኢትዮጵያን ከሚበተን የነፃ አውጭ ድርጅቶች ጋር ስለሚሰራ ህዋት ወያኔ የተሻለ ድርጅትና የተሻለ ለሀገር አንድነት እኔው እበልጣለሁ የሚለውን የፓለቲካ ፍጆታና ትርፍ ስለሚገኝበት ነው ። ሌላውስ ምንድን ነው የወያኔ መረጃና ደህንንት ከግንቦት ሰባት የሚጠቀመው ።
2ኛ/ ለህዋት ወያኔ የግዛት ዘመን አደጋ በሃገር ቤት ያሉ በሰላማዊ መንገድ በህጋዊ መድረክ የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ድርጅቶች፣የሲቢክ አክትቪስቶች ፣ጋዜጠኞችና ብሎግይስቶች መሆናቸውን ህዋት ወያኔ ያምናል። እነዚህ ኃይሎች የሥርዓቱን ገመና በማጋለጥ ህዝቡን በማንቃትና በማደራጀት የሥርዓቱን ኢ ዲምክራሳዊነትና ዘረኝነት ለዓለም ህብረተሰብ በማጋለጥ ትልቅ ሚና የተጫወቱና የህዋት ወያኔን ሥርዓትን ፈተና ላይ የጣሉ ናቸው። ምርጫ 97 ና ከዚያም በፊት የታዮ ንቅናቄዎች የነዚህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ኃይሎች ውጤት ናቸው። ስለዚህ ህዋት ወያኔ እነዚህን ተቋማት እንዲጠፍ ይፈልጋል። በዚህ ተግባር ላይ ከህዋት ወያኔ መረጃ በበላይ ትልቁን ሰራ እየሰራ ያለው የግንቦት ሰባት ድርጅት ነው።
የግንቦት ሰባት ድርጁት በሃገር ቤት ያሉ የፓለቲካ ድርጅቶች እንደ መኢአድና አንድነት ያሉ
አንጋፋ ድርጀቶች የፋይናንስ ምንጫቸው በውጭ ሀገር የሚኖረው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ መሆኑን ስለሚውቁ
በየሰቲቱ የነበሩትን የመኢአድ፣ የአድነትና የመድረክ የድጋፍ ኮምቴዎችንና ስብስቦችን ማዳከምና መበተን ጀመሩ።
ግንቦት ሰባት በግልፅና በስውር ሰላማዊ ትግሉ ያለቀለት እንደ ሆነ በሰላማዊ ትግሉ አዎንታዊ ተፅእኖ የሚደርጉ
የድርጅቱን መሪዎች ስም በማጥፋት በማብጠልጠልና በማሸማቀቅ የድጋፍ ኮምቴዎችን በማፍረስ የግንቦት ሰባት ጋሻ
ጃግሬ አደረጋጎቸው ። በሗላም እንደ ሰማያዊ ፖርቲ አይነት በወጣት ሙሁራን የተገነባ ድርጅት በሀገር
ቤት በተለይም በውጭ ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ተሰሚነትና አድማጭ እንዳይኖረው ትልን ስራ የሠሩት የግንቦት
ሰባት ድርጅትና እሳት ራዲዮ ቴሌቪጅን ናቸው።
በሰላማዊ ትግል የተሰማሩ ድርጅቶችን ከህዋት ወያኔ በበላይ ጥቃት
የደረሰባቸው በተቃዋሚ ድርጅት ስም ቆምኩ በሚለው በግንቦት ሰባት ድርጅት በእሳት ራዲዬና ቴሌብጅን ነው።
እነዚህ ድርጅቶች በግንቦት ሰባትና በወያኔ ደህንነት በሚደርስባቸው ወከባ ከነበራቸው ጥንካሬ ይልቅ እየጫጩና
እየተዳከሙ መጡ። በግንቦት ሰባት ድርጅት ውስጥ ያለው የወያኔ የመረጃና የስለላ ቡድን በተጨማሪ በሀገር ቤት
ያሉ አብሪ ኮከብና በተለይም በወጣቱ ተሰሚነት ያላቸውን የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችን ጋዜጠኞችንና
ብሎገርስቲቶችን ከግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር ቀጥተኛና ስውር ግንኙነት እንዳላቸው በማስመሰል በኢሜላቸውና
በአድራሻቸው በመላክ ይህንም በደህንነቱ ና በፀጥታ ክፍሉ በማሳወቅ በሽብርተኝነትና በሀገር ማፍረስ ወንጀል
እንዲከሰሱና ማስረጃዎች እንዲቀርብባቸው እየተደረገ ነው። ዛሪ አነ አንዶለም አንዳርጌ እነ እስክድር ነጋ እነ
ውብሸት እና በሺ የሚቆጠሩ በየክፍለሃገሩ አውራጃና ወረዳ የነበሩ ይህን የወያኔ ሥርዓት መፈናፈኛ አሳጣው የነበሩ
ዛሪ በህዋት ወያኔ አሰቃቂ እስር የሚገኙት ወጣት ሙሁራን ሰለባ የሆኑት በግንቦት ሰባት ድርጅትና በዚሁ በህዋት
ወያኔ መረጃ የተቀናጀ ስራ ነው።
አስገራሚው ነገር ከህዋት ወያኔ አምልጠው ነብሳቸውን ለማዳን ወደ ጎረቤት ሀገር
ወይም ወደገጠር ሲሸሹ በፀጥታው ኃይል የወደቁትን ወገኖች አገር ቤት ያለው ደህንነት በግንቦት ሰባት ሰም
በሽብርተኝነት መክሰስ ከፈለገ በግንቦት ሰባት ባለው ድብቅ ደህንነት አማካኝነት በእሳት ራዲዮና ቴሌቪጅን እነ
እገሌና እገሌ የሚባሉ አርበኞች ግንቦት ሰባትን ሊቀላቀሉ ሲል በወያኔ የፀጥታ ኃይል ተያዙ በማለት ለክስ ማስረጃ
ዜናና መግለጫ ይሰጣሉ ህዋት ወያኔ ለስርአቴ አደገኛ ናቸው የሚላቸውን ከግንቦት ሰባት ጋር በመሆን የፓለቲካ
ድርጅቶችን ካዳከመ መሪዎችን ሰለባ ከአደረገ በኃላ በተለይም በአድነት ፓርቲ በመኢአድና በሰማያዊ ፓርቲ የሱን
ደህንነቶች አስርጎ በማስገባት ከምክር ቤት እስከ ሥራ አመራር ያለውን ወሳኝ ቦታዎችን ከመያዝ የየፓርቲዎችን
አብዛኛውን ወንበር በመያዝ በሰጣቸው የጊዜ ገደብ ፓርቲዎችን እንዲፈረካከሱ አድርጎል ይህን ትልቅ ስራ ለህዋት
ወያኔ የሰራለት ብአዲን አይደለም ኦብዲኦ አይደለም ግንቦት ሰባት ነው።
ህዋት ወያኔ ግንቦት ሰባትን በመጠቀም
ይህን ያህል ካተረፈ ግንቦት ሰባትስ ከህዋት ወያኔ ጋር እየተናበበ በመስራቱ ምን ያተርፋል ? የሚለው መመልከት
ተገቢ ነው ህዋት ወያኔ ግንቦት ሰባት ወርውሮ አንድ መለኪያ እንደ ማይጥል ያውቀዋል ነገርግን የግንቦት ሰባትን
ስም በማግዘፍ የሀገርና የፀጥታ ስጋት ሽብርተኛ ድርጅት መሆኑን በሕግ በማውጣት ለሥርዓቱ አደገኛ የሆኑትን
የተቃዋሚ የድርጅት መሪዎችን ጋዜጠኞችንና አክቲብስቶችን ከዚህ ድርጅት ጋር በማያያዝ አጠቃበታለሁ በሚል
የግንቦት ሰባትን ድርጅት ከነ አልካይዳ፣ ኦነግና ሻቢያ ጋር ደምሮታል። ህዋት የግንቦት ሰባት መሪዎች ጀብደኞች
እንደሆኑ ያውቃሉ ስለዚህ ወያኔ በሰጣቸው ልኬታ ተመፃድቀው እየተኳፈሱ ይህው የህዋት ወያኔ መንግሥት
የሚፈራው እኔ ነው። ሽብርተኛ የሚለው ትልቁ ኒሻን የተሰጠኝ ለግንቦት ሰባት ድርጅት ነው ሰለዚህ ወያኔ
ኢህአዴግ የሚፈራው እኔ ነው የሚታሰሩት ወደ ግንቦት ሰባት አርበኞች ሊወጡ ሲሉ የተያዙት የእኔ አባላት ናቸው
። በእስር ያሉት የፓለቲካ ድርጅት መሪዎች ጋዜጠኞች ሲቢልና የወታደር አዛዦች ከእኛ ጋር ናቸው። ስለዚህ
የኢትዮጵያን ህዝብ ነፃ ማወጣውና ከነፃ አውጭው ድርጅት ጋር አዲሲቷን ሀገር መገንባት የምችለው ብቸኛው
ኢትዮጱያዊ ድርጅት እኔው ነኝ የሚል ዲስኩር እንደሚነፋ ወያኔ ያውቃል።
የወያኔ ደህንነትና ስለላ ድርጅት አሁን
ባለው የድርጅቱ አካሄድና አሰላለፍ ግንቦት ሰባትን ለመበተንና ብርሀኑ ነጋን እንደ ኮረኔል ጎሹ ወልዴ አድራሻውን
አጥፍቶ በገጠሪቱ አሜሪካ መንኖ ለማኖር ከፈለገ በአንድ የጉባኤ ስብሰባ ለይ የማድረግ አቅሙን በራሱ በግንቦት
ድርጅት ውስጥ ገንብቷል ። ነገር ግን አሁንም ወያኔ አሁንም ግንቦት ሰባት እንዲሰራላቸውቸው የሚፈልጉት ስራ
ስላለ አይጠናወቱትም። ከላይ ያብራራሁት የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት ግንቦት ሰባትን ለምን ይፈልገዋል ምንድነው
የሚጠቀምበት የሚለውን ለማብራራት ሞክሪለሁ ይህውም ግንቦት ሰባት ከአብስኒያ ኢትዮጵያ አሁኑኑ ነፃነት ከሚሉ
ድርጅቶች ጋር መጋባቱና መስራቱ ወያኔን ኢህአዴግን መልካም መልክ ቅርፅና ወርድ ስለሚሰጠው ሀገሪን ከሚፈርሱ
ስብስቦች ይልቅ ይህ አምባገነን መንግሥት ይሻለኛል የሚል አቋም የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲኖረው የሚዳርግ ስራ
በግንቦት ሰባት በመሰራቱ።
ሁለተኛ ለወያኔ ኢህአዴግ ሥርዓት አስጊ አደገኛ ናቸው የተባሉ ፓለቲከኛ ና
አክትቪስቶችን በግንቦት ሰባት ስም እንደሚታስርና ድርጅቱም የግንቦት ሰባት አባል ስለመሆናቸው ማስረጃና
አሜኔታ ስለሚሰጥ የወያኔ ኢህአዴግ የመረጃና የስለላ ቡድን ግንቦት ሰባትን እንደ አጋር ድርጅት ያየዋል ።
3ኛ/ የወያኔ ደህንነትና የስለላ ክፍል ግንቦት ሰባትን እንደ አጋር ድርጅት የሚያይበት ሌላውና ዋነኛው መንገድ አገራዊ ራእይ
ያላቸው የኢትዮጵያን መኖርና እንደ ሀገር መቀጠል የሚፈልጉ ለዚህም የሚጥሩና የሚታገሉ ድርጅቶችንና ሙሁራንን
ማዳከምና ከፖለቲካው መድረክ መግፋት ሲሆን ይህን ለመስራት ግንቦት ሰባት ያለመታከት ሲሰራ በስሩ በግልፅና በስውር
የኦነግ ተከታዩችን የሻቢያ ካድሪዎችን የህዋት ወያኔ ደህንነቶችን አሰልፎ ነው። ዛሪ ወያኔ ኢህአዴግ ያስተማራቸውና
ያሰለጠናቸው ደህንነቶችና ካድሬዎች ውጭ ሀገር ሲመጡ እንዲሆኑ የሚፈቀድላቸው የግንቦት ሰባት ድርጅት አባል ወይም
ደጋፊ እንዲሆኑ ነው የሚፈለገው። ግንቦት ሰባት ድርጅት ስሙ ነው እንጂ የወያኔ ደህንነትና የስለላ መማሪያ ማሰልጠኛ ተቋም
ነው ማለት ይቻላል።
ሻቢያ የወያኔን ሞትና ይህች ለኤርትራ አገራዊ ልዑላዊነት አደጋ የሆነች ሀገር በዘጠኝ ቦታ መበተን ብሎ ወስኖ
አለብኝ ብል ጠንክሮ እየሰራ ነው። ለዚህም የአንድነት ኃይሉ መመታት አለበት ብሎ ስለሚምን የግንቦት ሰባት ካባ ለብሶ አብሮ
አየሰራ ነው ።
ኦነግ ዛሬ ከሕዝባዊ ወያኔ ከአብስኔያ ቅኝ ተገዥነት ነፃ ብወጣም ነገ ይህ የአንድነት ኃይል ችግር የሚመጣብኝ
ስለሆነ አሁንም አብሪ ጭንቅላት ጭንቅላቱን መምታት አለብኝ ብሎ ስለአመነ እርሱም አንደ ሻቢያ፣ ወያኔ መረጃና
ደህንነት የግንቦት ሰባትን ዱሪቶ ካባ ለብሶ በአንድነት ኃይሉና ኢትዮጵያዊነትን በሚስቀድሙ የፓለቲካል አክትቢስቶች ና
ሙሁራን ላይ የተባበረ የማጥቃት እርምጃ በመውሰድ በማሸማቀቅና አንገት በማስደፋት የእነርሱን የብተና ፖለቲካ
የሚራምድት ለዚህ ነው። ለዚህ ነው ብሽን ኦፍ ሆርን ኦፍ አፍሪካና ብሽን ኦፍ ኢትዮጵያ ብለው በግንቦት ሰባትና በእሳት ራዲዮ
አጋፋሪነት በሻቢያ የፋይናንስ እገዛ በተደረገው ስብሰባ ላይ በድምሩ ኢትዮጵያን ካሻን እናፈርሳታለን ከፈለግን እንደ አዲስ
እንፈጥራታለን የሚሉ የጎሰኞቸና የጠባቦች ሊህልቃን የተፈላሰፍብን።
ዋ! ኢትዮጵያ ሀገራችን የነበረች፣ያለችና ዘላለም
የምትኖር ነች ። ወደ ተነሣሁበት ነጥብ ልነሳና የህዋት ወያኔ ፀጥታና መረጃ ከግንቦት ሰባት ድርጅት ጋር በመሆን ከአስር ዓመት
በፊት ጠንክሮ ና ተደራጅቶ በፀረ ወያኔ አቋም ይንቀሳቀስ የነበረውን ትግል ከወለል በታች አድርገው አዳክመውታል ሳይሆን
ገለውታል። ግንቦት ሰባት ጠንካራ ዲስፕሊን ያለው ለሀገሩ ራዕይ ያለው አባላትን ሳይሆን አንቀራቸው ያልተገረዘ ተናዳፊና
ተናካሽ ካድሪዎችን በማሰማራት አንቱ በሚባሉና ለሀገራቸው አስተዋጽኦ የሚደርጉትን ሙሁራንን ከወያኔ ኢህአዴግ ጋር
አሳደደ በተቃዋሚው ጎራ ተስፋ እንዲቆርጡ አደረገ ። ስለ ኢትዪጵያ አንድነት የሚሰብኩ ዌብ ሳይቶችን
አንበርክከው የእነርሱ የሀሰት የፕሮፖጋንዳ መጠቀሚያ አድርጓቸው ። ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚል በዚህ
የፀና ፖለቲከኛ ፈልጎ ማይገኝበት በሚስቸግር ምድር ላይ አስቀመጡን።
የግንቦት ሰባትና የእሳት ሬዲዬ የበሬ ወለደ
ቀዳዳን አዎ እውነት ነው የሚሉ ደናቁርቶችን ፈለፈሉብን ለእኔ ግንቦት ሰባትና ወያኔ አንድም ሁለትም ናቸው።
ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር።
ትግላችን ከወያኔ ደህንነትና
ከግንቦት ሰባት ደናቁርት እናድን ።