Wednesday, April 13, 2016

ያልተሳካው የኦክላንድ ስብሰባ

በወልቃይት ጠገዴ እና የጠለምት ተወላጆች ላይ በደረሰው የማንነት ጥያቄ ከጎናቸው ለመቆም 10 /4/2016 በኒውዚላንድ ሐገር በኦክላንድ ከተማ የተጠራው ስብሰባ አርበኞች ግንቦት 7  እና የኢሳት አስተባባሪዎች ድብቅ አላማ ምክንያት በዕለቱ የታሰበው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ሳይሳካ ቀርቷል። ከተሰብሳቢዎቹም መሀል ወልቃይት ጠገዴ ወገናችን፡ ነው ነገር ግን በአስተባባሪዎቹ ላይ እምነት ስለሌን፡ ሌሎች አማራጮችን ማየት ግድ ይላል፡ ሕዝብ የመረጠው ኮሚቴ ይቋቋም የሚሉ ሐሳቦች ተሰንዝረዋል። አስተባባሪዎቹም ተሰብሳቢውን በአሽሙር ሲሳደቡና ስብሰባውን ለመምራት ብቃት የሌላቸው መሆኑ ተስተውለዋል:: በአጠቃላይ ስብሰባው መልክ የሌለው እና ቅዠት የተሞላበት ሙሆኑን ተሳታፊዎቹ ስናገሩ ተደምጠዋል ወደፊት በዚህ አይነት ስብሰባዎች ላይ እንደማይገኙ የጠቆሙምም አሉ። ለዛሬ ይህችን ካልኩኝ ዝርዝሩን ወደፊት እመጣበታለው።