Thursday, December 31, 2015

3ኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺዝም አብዮት! ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ)

ስትፈልጉ “From Fascism to Fascism (Aleme Eshete) ወይንም በኔው አገላለጽ The Recycling of the Ormo Fascism! The third cycle of the oromo Fascism” (Getachew Reda) ብላችሁ ርዕሱን መተርጎም፤ መረዳት ትችላላችሁ። ወደ ትንታኔዬ ከመግባቴ በፊት መጀመሪያ አርበኛው፤አገር ወዳዱ እውነተኛው የኦሮሞ ተወላጁ እጅግ የማከብረው ኢትዮጵያዊው ወዳጄ ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ የኢትዮጵያ መሬት በፋሺስቱ የወያኔ ቡድን ለሱዳኖች በገጸ በረከት በድብቅ ለመሸለም በምስጢር እየተሯሯጠ ባለበት ጊዜ እየተደረገ ያለ የአገር ክሕደት በተያያዘ ጉዳይ ሰሞኑን ተቃውሞውን በሰላ እውቀቱ በዝርዝር በማስረዳት፤ ለሕዝባችን ማስተማሩ እጅግ አክብሮቴን እየገለጽኩ፤ እንደ ደ/ር ፍቅሬና እዚህ አብሮን አካባቢያችን የሚኖሮው ወዳጄ ደ/ር ደምሴ ኦሉማ እና ስማቸው ለመጥራት እጅግ የበዙብኝ ሀቀኛ የኦሮሞ ነገዶች፤ ስለ ኢትዮጵያ አገራቸው ክብርና ሰላም በመቆማቸው፤ አንባቢዎቼ እንድያመሰግኗቸው ጥሬዬን አቀርባለሁ። በተለይ ሁለቱም ወዳጆቼ ከተገንጣይ ቡድኖች ጋር ከፍተኛ የሆነ አታካራ በመግጠም፤ በሕዝብ ፊት ሃቀኛ ኢትዮጲያዊነታቸውን በማመስከራቸው፤ በተገንጣዮቹ በመጥፎ ዓይን የሚታዩ ታጋዮቻችን ናቸው። ለዚህም ክብር ምስጋና ይገባቸዋል።

በዚህ ጽሑፌ ስለ ተመለከተው ርዕስ ስተነትን ፤ እነዚህና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞ ወታደሮች፤ ምሁራን፤ገበሬዎች፤አትሌቶች፤የኪነት ሰዎች፤ሐኪሞች፤ የሃይማኖት መሪዎችና ምዕመናኖች፤ በአንድነት ሃይሉ የተሰገሰጉ ሃቀኛ ኦሮሞ ኢትዮጵያወዊያን ታጋዮች፤ጋዜጠኞች፤ ሰራተኞች፤የዛሬና የድሮ የኦሮሞ አርበኞችን እና የመሳሰሉ በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑ የኦሮሞ የሕብረተሰባችን ክፍሎች ፍጹም አይመለከትም። ይህ ርዕስ እና ትንታኔ የሚያተኩረው በኢትዮጵያ ሕዝብ ላብና መስዋእትነት ነፃነታቸውና ዜግነታቸው ጠብቆ “ለከፍተኛ ትምህርት” አድርሶ አስተምሮ፤ ለማዕረግ ያበቃቸውን የኢትዮጵያን ሕዝብ ለማበጣበጥ በውጭ ጠላቶች እየታገዙ ኦሮሞን ከወገኖቹ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ነጥለው አገር ለመመስረት ለብዙ ዓመታት ሳያቆሙ እስከ ዛሬ ድረስ ብጥብጥ በመፍጠር ላይ የሚገኙ የኦሮሞ ተገንጣይ ምሁራንን ነው የሚመለከተው።

 በዚህ ሰሞን የተከሰተው የኦሮሞ ተማሪዎች በፋሺስቱ ወያኔ ላይ እያካሄዱት ያለውን የአንገዛም አምቢተኛነት በወያኔ ስርዓት ላይ ያነጣጠረ ይሁን እንጂ ከስሩ/ከንጣፉ በታች (ኣንደር ዘ ራግ) “የሚጨሰው/የሚቦነው የእምቢተኛነት አቧራ” ያነጣጠረው ‘ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች’ ኦሮሞ የሚባል ክልል የባለቤትነት መብት እንደሌላቸው” የተንጸባረቀበት እንቅስቃሴ ነው። መፈክሮቻቸው “ኦሮሚያ የግላችን የኦሮሞዎች ነው!” ይላል። ይህ መፈክር፤- “የግንጠላ ዜግነት” ፍለጋ ጎልቶ የወጣበት፤ ተገንጣይ ኦሮሞ መሪዎችና ድብቅ ኦሮሞ የግንጠላ አቀንቃኞች በየሚዲያው ወጥተው “የአንቀጽ 39 መብት” እና “የራስን በራስ ማስተዳዳር “የነገድ ክልል”/ *የግሩፕ* መብት” እንዲከበር የቀሰቀሱበት ትዕይንት ነው።

ይህ “ባንቱስታናዊ ክልል” ስንመለከት፤ “ወያኔም ሆነ ተቃዋሚዎቹ” “ተቀናቃኞች ሆነዋል”። ይህ ማለት ለፖለቲካ የበላይነት የሚያደርጉት ግብግብ ውጤት ነው። በዝግታ እየተራመደ ያለው የሁለቱም “ተቀናቃኝ” ክፍሎች ባሕሪ ፤ በነገድ ላይ ያነጣጠረ “አዛዡ እኔ ነኝ፤ የኔ ነው፤ የኔ ነው፤ የድምበር ባለቤትነት” ክርክር በመሆኑ፤ “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ በኦሮሞ ምድር የበባለቤትነት መብት የማያከብር - ፤ ዜጎችን ባይተዋር ያደረገ” ስለሆነ፤_ ሁለቱም ተቀናቃኞች “ፋሺስታዊ ባሕሪያቸው” (ተማሪዎቹ የባንቱስታኒክ ክልል አክባሪዎች ሲሆኑ፤ ወያኔ ደግሞ ፋሺስት ነው) ወደ “ፈጣን ፋሺስታዊ የመገዳደል እምርታ” እንዲሸጋገር ፍላጎት አላቸው። ተዋናዮቹ ደግሞ፤ በውጭና በውስጥ ሆነው የመገንጠልንና ለባንቱስታናዊ የክልል መብት የቆሙት ሃይሎች፤ የሁለቱም ፍጥጫ በሰውም ብንብርትም የፈለገው ጉዳት ይምጣ ኣንዲገፉበት ይፈልጋሉ።

በአዲስ አበባ ከተማ ኦሮሞ ወሰን አካባቢዎች ያሉት መሬቶች፤ በማስተር ፕላን ምከንያት በብዙ መቶ ኪሎሜትሮች ርቀው የሚገኙ “በብዙ የኦሮሞ ከተማዎችና ክልሎች” የሚገኝ ኦሮሞዎች ተቃውሞው ለሳምንታት ሲዘልቅ “ከነጸብራቁ ብልጭታ” የሚነግረን ስዕል “ባንቱስታናዊም ሆነ ከዚያ ቢያልፍም የግንጣላ ፖለቲካ እውን እንዲሆን” ለፖለቲካ ሱፕረማሲ የሚደርጉት ግብግብ ነው። ኢትዮጵያዊነት የለውም የምልበትም ምክንያት ይህ ነው። ምክንያቱም “የአንድ ኦሮሞ ድምበር” ሲነካ ‘መላው ኦሮሞ አንደተነካ’ ተቃውሞአቸው በስፋት አስተጋቡ እንጂ 24 አመት ሙሉ “የአንድ አማራ ድምበርና ህይወት በኦሮሞ ወረበሎች ሲደፈር፤ “መላው ኦሮሞ አንደተነካ አላሳዩንም”። ጥያቄአቸው፤ ባንቱስታናዊ እንጂ አገራዊ አይደለም የምልበትም ለዚህ ነው።  

ይህም ቢሆን። በረብሻው ውስጥ የተጎዱ፤ህይወታቸው ያጡ በርካታ ኦሮሞ ወጣቶች “ነብስ ይማር” እያልኩኝ “ነብሰ ገዳዮቹም” ለፍርድ ቀርበው (ፍትሕ የለም እንጂ) ቅጣታቸው እንዲያገኙ የሚገባ መሆኑን እያመንኩ፦ ባጠቃላይ ቢያንስ “ለአንድ አመት ሙሉ” (ከአምና ጀምሮ) የታየው አመፅና የተደመጡት መፈክሮች የሚያሳየው “የማስተር ፕላኑ” ጭቅጭቅ “ምክንያታዊ ደማሚት” ይሁን እንጂ “ሁለት ፋሺስታዊ ንቅናቄዎች” (ጊዜ ወስዳችሁ ተገንጠሉ የሚለው ብረት የታጠቀው ወያኔ እና በአንቀጽ 39 የግንጣላ ርዕዮት የታጠቀው ተገንጣይ የኦሮሞ ክፍል) አገርን በማፍረስ ላይ ያነጣጠረ “የግሩፕ ሱፕረማሲ ትግል” ስለሆነ፤በሁለቱ ክፍሎች እያየነው ያለው ግብግብ ለአገራችን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ “ፈንጆች” ስለሆኑ ሁለቱም ክፍሎች ፋሺስታዊ ርዕዮት የሚከተሉ ናቸውና ቅዋሜዬን አቀርባለሁ።

ተቃዋሚዎቹ፤የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች እንደመሆናቸው መጠን “ሁላችንም ከነዚህ ወጣቶች የምንጠብቀው” የባንቱስታን አከላለል ‘በደም፤በቋንቋ፤በአጥንት፤በነገድ” መተዳደር “ናዚያዊ” ዘረኛነትን መከተል ስለሆነ እንቃወመዋለን እንዲሉ ነበር እንጂ “ባንቱስታናዊ ክልል” ሕጋዊ አድርገው እንዲተገበር የሚጠይቁ ወጣቶች ይከሰታሉ የሚል አምነት አልነበረንም። ስለሆነም ነው አደጋነቱን እንድታዩት የምፈልገው፡ ሁለቱም ግብግብ የገጠሙ ክፍሎች ፋሺስት ርዕዮት ያነገቡ ናቸው ብያለሁ። ፋሺስም ምን እንደሆነ ወደ ታች እንመለከታለን። ወያኔ ፋሺስት መሆኑን ሁላችንም የምናወቀው ሃቅ ነው። ኦሮሞዎች፤ የወያኔ ፋሺዝም “የኦሮሞ መሬትና ተፈጥሮአዊ ሃብት፤ ለኦሮሞ ቋንቋ ተናጋሪ “ብቻ” እንዲሆን ፋሺስታዊ ሕገመንግሥቱን አጽድቀወ፤ፈርመው አመስግነው ተቀብለውታል። ይህ ፋሺስታዊ ሕገ መንግሥት የቀየሱትም “እነ ሌንጮ ለታ/ኦነጎች” እንደሆኑ ሰሞኑን በግልጽ ነግረውናል (ጥንት የምናውቀው ምስጢር ቢሆንም)።

 ተማሪዎቹም እንደ ወያኔ ጀሌዎች “የፋሺስቶች ርዕዮት ተከታዮች” ናቸው። ወያኔዎችና ኦሮሞ ሊሂቃን ሕዝቡ እራሱ ወዴት እየመሩት አንደሆነ በሚገባ በግልጽ ያውቃል የሚል እምነት አለኝ። እየተጓዙበት ያለው አቅጣቻ፤ አምኖውበት ለ24 አመት ተቀብለውት እየተጓዘበት ያለው “የጎሰኛነት” (ፋሺስታዊ) ርዕዮት ቆም ብሎ የማሰብ ሁኔታ እያየን አይደለም። ስለሆነም ታማሪዎቹ፤ “ባልታወጀ በኦሮሚያ የዜግንት ምኞት” ሰክረዋል። ሕዝቡም፤ ኦሮሚያ የሚል ባንዴራ ተቀብሏል፤ላቲን ፊደል የኔ ነው ብሎ ተቀብሏል፤ ኦሮሚያ የሚል ባንቱስታናዊ/የክልል ድምበር የኔ ነው ብሎ ተቀብሏል። ሰለሆነም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በቀር “ከፍተኛ” ብጥብጥ እፊቱ ላይ ተደቅኗል። 

እኔ እንደ ትግሬነቴ ፤ለብዙ አመታት የትግሬ ሊሂቃን እና ሕዝብ የወያኔን ፕሮፓጋንዳ ተቀብለው ‘ጸረ አማራ” ሕሊና የመሸከማቸው ጉዳይ ባደባባይ ስኰንን እንደነበር ታወቃላችሁ። ኦሮሞዎቹም ከትግሬ ወገኖቼ የምትለዩበት ነገር የለም። ምናልባትም በባሰ መልኩ ኦሮሞዎች አፍራሽ ሃይሎችን ከውስጥም በውጭም ያሉት ጸረ አንድነት የሆኑ የኦሮሞ ምሁራንና ካድሬዎች እንደ መሪዎቹ በመቀበል፤ ኦሮሞዎች እየተጓዛቸሁበት ያለው “አደገኛ ድልድይ” መፈተሽ ይኖርባችሗል የምለውም ለዚህ ነው።

 ምስኪኑ ኦሮሞ ገበሬ ወደ እማያውቀውና ወደ አልተረዳው ገደል እየተገፋ ነው። ይህ የተነጠፈላችሁ አደገኛ ድልድይ በቅጡ ካልፈተሻችሁት፤ ለናንተም ሆነ ለመላይቱ አገራችን ከፍተኛ አደጋ አለው። ይህ ደግሞ ሁላችንም እሳት ውስጥ የሚጠብስ አደጋ ነው። በገንጣይ ሃይላት ተገፋፍታችሁ ከመላ ሕዝብ ጋር ያስተሳሰራችሁን ክር ይልቅ “የባንቱስታናዊ የጎሳ ኑሮ” ይበልጠናል ብላችሁ ከበጠሳችሁት “እናንተንም ሆነ” “በኮሎኒያሊሰትነት የተፈረጅነው የተቀረነው ኢትዮጵያዊያን/ኢትዮጵያ” ክሩን መልሰን እንቀጥለው ቢባል ፍጹም የማይቻል ይሆናል። ወደ ሃዘን ጭለማ አብረን አንጓዛለን። አንዴ ወደ ጭለማ ከተገባ ገንጣዮቹ አብረዋችሁ አይገኙም። አፋቸው ከመለፍለፍና በንዚን ከማርከፍከፍ አልፈው በውጭ አገር የተደላደለ ኑሮአቸው ጥለው እናንተ ወደ “ወደቃችሁበት ጭለማ” መጥተው ይረዱናል ብላችሁ አታስቡ።

 ካሁኑ ሽሽት ይዘው እየኖሩበት ያለውን “የተንደላቀቀ” የውጭ አገር ህይወታቸው ማስተማሪያ እንዲሆናችሁ ልብ በሉ።እዚህ ያሉት ኦሮሞ ምሁራንና ወጣቶች እንኳ በምሳሌ ብትወስዱዋቸው “ከፓልቶክ ፉከራና ራዲዮን ከፍተው በንዚን ከማርከፍከፍ” አልፈው፤ እያርከፈከፉበት ወደ አለው እናንተ ወደ እምትኖሩበት ጫካና ኑሮ “መጥተው” ለመዋጋትና መስዋዕት ለመሆን ዝግጁነት እንደሌላቸው የምታወቁት እውነታ ነው። ኤርትራዊያን እንኳ፤ ነፃ ለመውጣት አመታት ተዋግተው፤ነፃ ከተባሉ በኋላ አዋጊዎቻቸው፤ ተዋጊዎቹና ምሁራኖቻቸው ‘ከኤርትራ እየሸሹ”፤ የተደላደለ የውጭ ኑሮ መርጠዋል። ከዚህ ትምህርት ውሰዱ። ሞኛችሁን ፈልጉ! በሏቸው እላለሁ። ይህ አጭር ምክር ላብቃ እና ወደ ጉዳያችን እንግባ።

ግንጣላን ለሚያቀነቅኑ መልስ እነሆ። እዚህ ላይ መዘንጋት የሌለው ጉዳይ፤ ታሪክ በምጠቅስበት ጊዜ፤ ታሪክ እንደታሪክነቱ መቅረብ ስላለበት፤ ቅር የሚላቸው ወገኖች ካሉ፤ እኔን ሳይሆን መቀየም ያለባቸው ለዚህ ትንታኔ እና ክርክር እንድንበቃ እየገፋፉን ላሉት የኦሮሞ ተግንጣዮችን እንደሆነ ለመግለጽ እፈልጋለሁ። እነሱ ሲያብዱ አንተስ ማበድ አለበህ ወይ? የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ፡ ነገር ግን መታወቅ ያለበት ቢያንስ ሌላውን ዘመን ትተን ፤ ለ24 አመት እንኳ የተዘረጋው ውሸትና በነዚህ መሰሪ “ፋሺስት ተገንጣይ ኦሮሞዎች” አበራታችነትና መሪነት፤ “አማራን ከኦሮሞ ለማበጣበጥ” የተገነቡ “የጥላቻ ሃውልቶችና በየሚዚየሙ የተሰበሰቡ “የውሸት ቅሬቶች” እንዲሁም “የክልል-ድምበሮች” በተመለከተ ያለ ብዙ ተቃውሞ “ነገሩን ለማረጋጋት” እየተባለ በብዙ ወገኖች በትዕግስት እንደታለፈ ታውቃላችሁ። ይህ ውሸት ተደጋግሞ ያለ ተቃውሞ በመለቀቁ፤ ዛሬ ወጣት ኦሮሞዎች ውሸቱን እውነት አድርገው በመውሰድ

(አስገራሚ ቢሆንም፤ ወያኔን እና ተገንጣይ ሀይላትን እንቃወማለን የሚሉ አክቲቪስቶች ነን የሚሉ አንዳንድ ወገኖችም ሳይቀሩ፤ይህ ውሸት እውነት ነው ብለው የተቀበሉና፤ ኤርትራ ሄዳችሁ ስለ አማራ ይቅርታ ጠይቁ አንደተባሉ አንዳንድ “ሕሊናቸው የተነጠቁ” ግለሰቦች ባላነሰ መልኩ በመካከለችን የሚገኙ ተቃዋሚዎችም፤ “አማራ” የተባለ ገዢ ሥርዓት “ኦሮሞውን” አንደበደለ በማስመሰል ነገር እያምታቱ በየአዳራሹ በተቃዋሚ ጎራ ሆነው የሚዘላብዱና የሚጽፉ ይቅርታ ጠያቂዎችም ጭምር እብዳሉም አንስትም። የኦሮሞ ነገድ የሆነው ባንዳው ንአመን ዘለቀ (የሻዕቢያ ቱልቱላ) “ተገንጣያቹ ወደ ማሃል እየመጡ ነው” እያለ ስለ አንድነት የቆሙትን ሀይሎችን “ባለጌዎች” በሚል ዘለፋ በመዝለፍ ፤ በቅርብ ቀናት ሰሞን ጀሌዎቻቸው በሚሰበሰቡበት “ኢካዴፍ” በተባለ “ፓልቶክ ክፍል” የሰነዘረውን የተግማማ ባንዳዊ ማጃጃያ ፕሮፓጋንዳውን ልብ በሉ። )

ውሸታቸውንም ለማጠናከር እንዲመቻቸው፤ አማራውን “በጡት ቆራጭነትና በገዢነት እየፈረጁ”፤ ኢትዮጵያ የምትባል አገር “የመቶ ምናምን ዕድሜ ያላት” ምኒሊክ የመሰረትዋት አገር እንደሆነችና “የኬኒያ፤ የሶማሊ፤የታንዛኒያ…ኦሮሞዎች “ጋላ” የሚል ስም የሰጧቸው ምኒሊክ እና ሃይለስላሴ እንደሆኑ እና አሁንም የኬኒያ ጋላ ነገዶች ያንን ተቀብለው በዛው እየተጠሩ እንዳሉ በመዋሸት “ኦሮሚያ” የሚባል አገር፤ መንግሥትና ሰንደቃላማ የነበረው እንደነበረና፤ በሗላ ግን “አማራዎች” መጥተው እንደገዙት፤ አሁን ግን ከትግሬ እና ከአማራ “ኮሎኒያሊስቶች/ከኢምፓየር አቢሲኒያ” ነፃ መውጣት እንዳለበት ሰብከዋል።

ያንን ውሸት መሰረት አድርገው፤“ወያኔና ኦነግ” በቅጥፈትና በውሸት፤ አገሪቷን ለመዝረፍ እንዲያመቻቻው፤ ተማክረው በከለሉት ኦሮሞ በሚባል “የባንቱስታኒክ ክልል” ያለ መላው ኢትዮጵያ ሕዝብና የታሪክ ግኝት፤ የቤተሰብ ትስስር፤ የሰብአዊ ነክ ፤የምጣኔ ዘርፍና የፀጥታ ጉዳይ አዋቂዎች እና ስለ አገሪቱ ጠቅላላ ህልውና ምክክርና ተሳትፎ ሳያደርጉ፤ “ብቻቸውን” በረሃ ላይ “ሴራውን” በመቀየስ “ኦሮሚያ” የተባለ “አዲስ የፈጠራ ክልል/አገር” መስርተው ከወያኔ ቁጥጥር “ነፃ” ለመውጣት የተቻላቸውን ያህል በማድረግ ላይ ናቸው። ወደ ግንጣላ የሚመራቸው የመጀመሪያው ጉዞ ጨርሰውታል። ይህም “ክልል” ይባላል። አሁን እየታየ ያለው “የቡራዩ ኬኛ፤ ሱሉልታ ኬኛ፤ ኦሮሚያ ኬኛ!” መፈክር ፤ ግንጠላውን ለማፋጠን የሚደረግ አዳጋቹ “ሁለተኛውና የመጨረሻው ጉዞ” ፤የመጀመሪያው እርከን፤ የፍትጊያው እንቅስቃሴ ሂደት ጀምረውታል”።

ከዚህ እንቅስቃሴ በፊት እዛው ክልል ውስጥ ለዘመናት የኖረ ማሕበረሰብም በታጠቁ የኦሮሞ የክልል ወታደሮችና በኦነግ ወታደሮች ጥይትና ሳንጃ፤ የግድያ፤የዘረፋና የመባረር ከፍተኛ ወንጀል እንደተፈጸመበትና፤ በቅርቡም “በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አመያ ወረዳ በተባለ ወረዳ” በጅምላ ከተቃጠ ሉት የዐማሮች መኖሪያ መንደሮች አንዱ ከዚህ በታች የተመለከተው የፎቶ ማስረጃ ይመለከቱ። ዘርዝር ዘገባው ለማወቅ “ሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት”ረቡዕ ታኅሣሥ ፲፫ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም. ያወጣውን አንድነት ከማን ጋር? ሚለውን ሃተታውን ይመልከቱ። (ምንጭ፦ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ቁጥር 22 ቅጽ 3 ታሕሣሥ 12 ቀን 2008 ዓ.ም.)  

ይህ የምታዩት የፈቶ ማስረጃ የተቃጠለ መንደር የአማራ ገበሬዎች መንደር ነው። በአመያ ወረዳ በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች፦ ማለትም «አብቤ መድኃኒዓለም»፣ «ኩኖ ቁሊት (ቀርሳ ቁሊት)» እና «መሪ መገሪ (ባሬዳ)» በተሰኙት ነዋሪ የነበሩ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ንብረት ውስጥ 1,000(አንድ ሺህ) ቤቶች ማጀት በጎረሰ፣ ደጃፍ በመለሰ ያለ የሌለ ንብረታቸው ከነቤቶቹ ተቃጥለው ወደ አመድነት ተቀይረዋል። በእያንዳንዱ የቀበሌዋ ነዋሪ ዐማራ ከ70,000 (ሰባ ሺ) እስከ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር የሚገመት በርበሬ ተቃጥሏል” (አባሪ ፎቶግራፍ ይመልከቱ)። ይህ አማራ እየተገፋ ባለበት ትኩስ የግፍ ዜና ፤ያውም “በባንቱስታኒክ ኦሮሞዎች” ሲፈጸም፤ የወያኔ ተቃዋሚ ሃይሎች ነን የሚሉ በሺዎቹ የሚቆጠሩ ውጭ አገርና ውስጥ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተቃዋሚ ሃይሎች፤ ቡራኬአቸውና ድጋፋቸው የለገሱት እንዲሁም ጮክ ብለው እየጮሁላቸው ያሉት ለቡራዩ ኬኛ! ፤ለሱሉለታ ኬኛ!፤ለኦሮሚያ ኬኛ! “ባንቱስታኒክ” ፈካሪዎች መሆኑን ልባችንን አድምቶታል። 

ይህ ሳንነጋገርበት ለ24 አመት በቸልተኝነት ዝም እየተባለ፤ ዛሬ “ወጣት ኦሮሞዎች” ከገንጣይና አስገንጣይ ክፍሎች የቀሰሙትን የ24 አመት ቅስቀሳ፤ ”ቡራየ፤ኬኛ፤ ሰበታ ኬኛ…….ኦሮሚያ ኬኛ….” ወደ እሚለው የግንጠላ መፈክር ደርሰዋል። አሁን ዝምታችን መስበር የግድ ነው!!! ይህ ደግሞ በወያኔ ዘመን የተወለደ “ወጣት ኦሮሞ” ይህን “የፈጠራ ታሪክና የኤትኒክ ፌደራሊዝም አደገኛ አወቃቀር” ከህጻንነቱ ጀምሮ እየተኮተኮተ “እውነትነት ያለውና ጤነኛ አስተዳዳር መስሎት” ያለ ምንም “ሕሊናዊ ምርመራ” አምኖ በመቀበሉ፤ በየታላላቅ የትምህርት ተቋማት ሳይቀር ፡ “ ኢሚፓየር ኢትዮጵያ” “ሳብጁጌሽን” የሚሉ ቃላቶችን በመጠቀም በግልጽ ሳይሸሽጉ፤ ሳያፍሩና ሳይሸማቀቁ “በዩቱብ አውድዮ እና ቲቪ ሚዲያዎች” የለጠፉት የተለያዩ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኦሮሞዎች ተቃውሞ ተመልከቱ። አምና በተለቀቀው አውዲዮ ላይ ወደ መጨረሻ ገደማ የሚያሰሙትን መፈክር አድምጡ፡- የተቀረጸውን ስታደምጡ፤ ወጣቱ እውነትም ነጋሪ በማጥት ሕብረተሰቡም ሆነ እራሱን ይዞ ገደል እየገባ መሆኑን ማየት ትችላላችሁ። እነኚህ አፍላ የኦሮሞ ወጣቶች ለብዙ ዘመናት “አፍሪካኖችና ጃማይካኖች” እንደ “ብሌን ዓይናቸው” የሚመለከትዋትን ሰንደቃላማችን “አያውቋትም”። 

“ኦነጎች የቀየሱላቸው “የዋርካ ዛፍ ምስል” ያለበት እና ሌላው ደግሞ “በእስለማዊ እና በዓረብ አገሮች፡የሚውለበለቡ ቀለማት ያሉበት ባንዴራ” ነው አሁን ወጣቶቹ የሚያውለበልቡት (አገርም ውስጥም/ ውጭም)። ችግሩ እርግጥ አገር ከመሰረቱ በሗላ ቀርቶ፤ ገና ኦሮሞዎቹ አገር ሳይመሰርቱ ዛሬ “እርስ በርስ” በመናከስ ኤርትራ እና እዚህ ሜኔሶታ/አሜሪካ ውስጥ ፍርድ ቤት ድረስ እየተካሰሱ “እኔ ነኝ ሕጋዊው ኦነግ”፤ “መሪያችን እገሌ እንጂ እገሌ አይደለም” “ስትፈልጉ እናንተ ስማችሁ ቀይሩ እንጂ ኦነግ እኛ ነን” ወዘተ…ወዘተ…በሚል አታካራ ገብተው “እየተራኮቱ” ናቸው። አገር ቢመሰርቱ ካሁን በፊት እንደገለጽኩት “ኦሮሞ እስላም/ከኦሮሞ አርቶዶክስ/ “አሮሞ ፕሮቶስታን/ ከኦሮሞ ኦርቶዶክስ” ኦሮሞ እስላም ከሁሉም እምነት፤ ሁሉም አምነቶች ከዋቆ፤ ዋቆ ከወዘተ…ካፒታሊዝም/ሊበራሊዝም/ገዳኢዝም/ሶሺያሊዝም/ካሊፋ- ኢዝም/ሸሪዓ-ኢዝም… ወዘተ.. ወዘተ…ወዘተ… እየተናከሱ “ምድሪቷ የአልሸባብ ሶማሌ ዓይነት ኦሮሚያ” እንደሚያደርጓት ሳይታለም የተፈታ ነው።

ስርዓቱም፤ ስፓኒሾች እንደሚሉት “ley de la calle” እንግሊዞቹ “mob rule” አማራዎቹ “ወሮ በላ ስርዓት” የሚሉት። በሳይንሳዊ የፖለቲካ ስሙ “ኮሎክቲቪዝም/ፋሺዝም/ማብ-ሩል/ማፍዮኢዝም/ኦሊጋርኪ” የሚባለው። በእነ ጃዋር “የትንቢተ ስርዓታቸው” ፖሊሲ “የሜንጫ ስርዓት” የሚሉት ማለት ነው። የኦሮሞ ፋሺዝም አዙሪት ምን ማለት ነው? ፋሺዝምስ ምን ማለት ነው? በውስጡ ባሉትና በዙርያው ባሉ ማሕበረሰብ ክፍሎች የራሱን ጎሳ የበላይነት (ኤትኒክ ሱፕረማሲ ‘ሴት/ንብረት/መሬት/ሥልጣን/ሃይማኖት…’) ለመንጠቅና ለማስፈን፤ ያንን የበላይነት እውን ለማድረግ ከመዋጋት አልፎ፤ ለማመን እና ለማየት እጅግ በሚዘገንን ጨካኝ ጭፍጨፋ’ዝርፊያና አመጽ” በሌሎቹና እሱን በሚቃወሙት የራሱ ጎሳዎች ሳይቀር “ሰይፍ በመምዘዝ” “ፀጥ” በማሰኘት ሕብረተሰቡን ሽብር ውስጥ አስገብቶ በፍርሃት የሚገዛ፤የሚያርበደብድ፤ሰላም የሚነሳ፤ ሁውከተኛ የብጥብጥ ስርዓት ነው።
የዘመኑ ፋሺዝም ብዙ ትንታኔዎችን ቢሩትም በቃላሉ “የሰው ልጅ ፤ከግለሰብ ነፃነት እየወጣ፤ በሕብረት መተዳዳር ከጀመረ ጀምሮ “ጀነሪክ ፋሺዝም” የሚሉት፤ አገርን በማውደምና መንደሮችን ማቃጠል፤ጭካኔን ምርኩዝ እያደረገ፤ እረፍት የሚነሳ፤ በደም ጥራት የሚጓዝና የሚያስተዳድር፤ ጥቂት ወረበሎች የሚፈጥሩትና የሚመሩት የሽብር ስርዓት ነው፤ ፋሺዝም ማለት!” ኦሮሞዎች እንዲህ ዓይነት ጭካኔና ስርዓት ፈጽመዋል? የሚል ጥያቄ ሊቀርብ ይችላል።

 መልሱ፦ “አዎን፤ በሚገባ!!”። የጥንት ኦሮሞዎች ድሮ “ጋላ ሲባሉ የነበሩ ነገዶች፤ መንደር፤ሕዝብ፤አገር አውድመዋል። ይህንን ሲፈጽሙ እጅግ ዘግናኝ እርምጃ እየወሰዱ ነበር የፈጸሙት። “ዲሞክራሲ” ነበር እያሉ በውሸት የዛሬ የተማሩ ኦሮሞዎች የሚያሞግሱት “የገዳ ስርዓት” እንኳ ሳይቀር ስትመለከቱ “እጅግ ማመን የሚያዳግት” ባሕሪዎች ታይተውበታል። ይህ ደግሞ በጽሁፍ መረጃ “ኦሮሞዎች ወደ መሃል አገር፤ወደ “ከፋ” (እርግጥ ከፋ ውስጥ ጥቂት ነገዶች ከጋላዎቹ ጭፍጨፋ ድነዋል፤ለዚህ ምክንያት “የደኑ ብዛት” የኦሮሞዎቹ ከብቶች ማስገባት ወደ ውስጥ ሰርስረው መዝለው ስላቃታቸው፤ ወደ ውስጥ ደን ገብተው ነዋሪውን መጨፍጨፍ አልቻሉምና ከመአቱ የዳኑ ጎሳዎች እንደነበሩ እንደዳኑ፤ታሪኩን ያጠኑ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ።) እንዲሁም “ጅማ”፤ ሸዋ፤ትግሬ፤ወሎ፤ጎጃም ጎንደር……ሲስፋፉ በወቅቱ የተፈጸመ ድርጊት፤ ፋሺስታዊ ዘግናኝ ጭፍጨፋና ዘረፋ ተካሂዷል። 

ይህ አሁን “ኦሮሚያ ኬኛ” እያሉ ወጣቶች የሚዘምሩት መፈክር፤ በዘረፋና ባሰቃቂ ጭፍጨፋ የድሮ ጋላዎች ከነባር ኗሪዎች የነጠቁት መሬት እንደነበር በግልጽ ማወቅ ይኖርባቸዋል። በወቅቱ እንዲህ ያለ ፈጣን እና ባጭር ወቅት ወደ ኢትዮጵያ የተስፋፉበት ምክንያት ፤በወቅቱ” ኢትዮጵያ “በግራኝ አህመድ” ጂሃዳዊ ወረራ ምክንያት ሃይሏ ተዳክሞ ሕዝቧ አልቆና በጦርነቱ ደክሞ፤ ታርዞና መዋጋት ሰልችቶት ስለነበር፤ ኦሮሞዎቹ ከታች ከኢትዮጵያ ድምብር ገሰግሰው በመምጣት አጋጣሚውን ተጠቅመው ሰፊውን መሬት ከኗሪው እየነጠቁ ዛሬ ለራሳቸው አድርገውታል። ሃቁ ይህ ነው።

ከወረራው በፊትና በወረራው ወቅት የነበሩ ግዛቶችና “የቦታ ስሞች” በውጭ አገር ጎብኚዎች በወቅቱ የተነሱ የካርታ ምስክሮች ዛሬም በሊቃውንት ቤቶችና መጽሐፍት ቤቶች ይገኛሉ። እነሱ ማን ምን ይባል እንደነበር ቁልጭ አድርገው ይነግሩናል። የተረሳው ፋሺስታዊ አዙሪት ነብስ ዘርቶ እንደገና ሌላ ዘላቂ ‘የሁውከት” አዙሪት ከመደገሙ “ግልፅ ግልፁን” በመነጋጋር እንዲህ ማዝገም ስለሌለበት ዝምታችን መስበር የግድ ነው!!! አማራው ሕዝብ “በባንቱስታኒክ ኦሮሞዎች” ቤቱና ህይወቱ እየወደመ “ወደ መሃል እየመጡ ነው” “ግንጠላን ትተዋል” የሚሉንን ደላሎችና ከጂዎችን ማመን አቁሙ! (በዚህ በሰሜን ክፍላችን ደግሞ የወልቃይት አማራ ወገኖቻችንን “በትግሬ ፋሺዝም ተስፋፊ አይዲኦሎጂ” ምክንያት እየደረሰባቸውና የገጠማቸው ፋሺስታዊ የዘር ማጥፋት በትልቁ ሳይረሳ ማለቴ ነው!!!!)

በ15ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የታየ አገርና መንደርን ማውደም፤ ዛሬ በቃ ማለት ጊዜው ነው! ጥንት በኦሮሞ ከብት አርቢ ወራሪዎች “በአማራ፤ በጉራጌ፤በሐረሬ፤በሲዳማ፤በጋሞ…በወላይታ…ወዘተ…ኗሪዎች ግፍ ፈጽመዋል። በወቅቱ የነበሩ ጅማ “ሙርጡላ ማርያም” (?ከተሳሳትኩ አርሙኝ) ገዳም ውስጥ የነበሩ ሊቃውንት (ለምሳሌ አባ ባሕርይ) የመሳሰሉ በዓይናቸው ያዩት “ፋሺስታዊ ዘግናኝ ድርጊት” በጽሑፍ መዝግበው ትተውልናል። በነገራችን ላይ መነኩሴው አባ ባሕርይ የኦሮሞን ባሕል፤ታሪክ፤ነገድ አመጣጥ/ትውለደ ሐረግ… ከማንኛውም ኦሮሞ ነኝ ባይ እንደሳቸው አውጣጥቶ በንፁር የዘገበ የለም። ለኦሮሞውና ለተቀረነው ትውልዶች መዝግብው የተውለትና ያስተማሩት ባለውለታ ናቸው። በኦሮሞዎቹ የታሪክ ምሁራን በእነ ዶ/ር መሐመድ አህመድ ፧ ሳይቀሩ የአባ ባሕሪ የኦሮሞዎች ትውልደ ሐረግ ዝርዝር/ጥናት አምነው በአክብሮት የተቀበሉት ሃቅ ዩሆነ ሰነድ ነው። 

ባለውለታ ናቸው የምልበትም ምክንያቱም “ጋላዎቹም” ሆኑ የዛሬዎቹ “ኦሮሞዎች” የንግግር እንጂ “የጽሑፍ ሥልጣኔ ቋንቋ” ስለሌላቸው ለመጀመሪያ ጊዜ በግዕዝ ጽሑፍ ጽፈው “የጋላ ትውለድና ክፍሎች፤ እና አስተዳዳር” በሚገርም አተናተን ዘርዝረው ስለተውላቸው ብዙ ኦሮሞዎችና የውጭ ምሁራን/ተመራማሪዎች ያንን የመጀመሪያና ብቸኛ ትምህርትና፤የዓይን ምስክርነት ሰነድ ምንጭ ሰለሆነ ኦሮሞዎች ዛሬ ሐረጋቸው እየቆጠሩ ያሉት እሳቸው ሰንደው በተውላቸው ሰነድ ነው።ሆኖም እሱም (ዶ/ር መሃመድ አሕመድ) ሆነ የመሳሰሉ ተገንጣኢ ኦሮሞ ምሁራን “ያቺን የሃይማኖት ችግራቸውና ተገንጣይነት” ሉጓም ሆና ስለምትይዛቸው፤ ሙሉ በሙሉ አባ ባሕሪን አያመሰግኗቸውም። ስለሆነም ተገንጣዮቹ የአባ ባሕርይ የዓይን ምስክርነት መፋቅ ስለማይቻላቸው ለግንጣላ ታሪክ አልመች ስለምትል የሳቸውን እና ሌሎችን “የሃገር ውስጥ ምንጮችን አይቀበሉም”።

ካለመቀበል አልፈውም “ያጥላላሉ”።የደብተራ ጥናትም ሲሉ ያጥላሉታል። ግብዝነት አደጋ ነው፤ ይባል የለ! ክቡር ፕሮፌሰር ጌታቸው ሃይሌ እንዲህ ይላሉ፤ “የሀገር ውስጥ ምንጮችን የሚያጥላሉ ዘመናዊ ታሪክ ጸሐፊዎች ካሉ ባይመዘገብ የሚወዱት ስለተመዘገበ ነው….።”(ጌታቸው ሃይሌ፤ ገጽ 31 የአባ ባሕርይ ድርሰቶች፤ ኦሮሞዎችን ከሚመለከቱ ሌሎች ሰነዶች ጋር)። እውነት ነው። ይህ ወርቃማ አገላለጽ፤ ከሺህ ገጽ መጽሐፍ በበለጠ ከፍተኛ ትርጉም እና ቀላል አገላልጽ የያዘች ዓረፍተነገር ስለሆነች፤ ምን ማለት እንደሆነ ሁላችሁም በትኩረት መገንዘብ አለባችሁ። ባይመዘገብ የሚወዱት ክፍሎች እነማን ናቸው? በውሸት የሚጓዙ የጋላ ታሪክ ባይመዘግብ የሚመርጡ እንደ እነ ኦነጎች የመሳሰሉ ፋሺስት ክፍሎች ናቸው። በወቅቱ “ጋላ” ተብለው ሲጠሩ የነበሩት “የኛ ዘሮች ናቸው” የሚሏቸው የዛሬዎቹ ኦሮሞ ምሁራን (ጋላዎቹ እርግጥ ከወረራ በሗላ ከተቀረነው ኢትዮጵያዊያን በደም በስጋ ስለተዋሃዱ፤ እነ አባ ባሕርይ በነበሩበት ጊዜ የነበሩ ንፁሕ “ጋሎች” አይደሉም የዛሬ ኦሮሞ ነን እያሉ እየነገሩን ያሉት “ኦሮሞዎች”።

ምክንያቱም አሁን ያሉት “ኦሮሞ ነን” የሚሉት “ከተቀረነው ጋር” ከተደበላለቁ በሗላ የመጣ ድብልቅ/ክልስ የጋላዎቹ ትውልደ ሐረግ መሆኑን አንባቢዎቼ ልብ አንድትሉ እፈልጋለሁ። ምናልባትም ብዙዎቹ ኦሮሚኛ ስለሚናገሩ ከዘመናት የመደባለቅ ሂደት በኋላ ኦሮምኛ ተናጋሪ ይሁኑ እንጂ “ኦሮሞዎች” ያልሆኑ በሚሊዮኖች እንደሚቆጠሩ እርግጠኛ ነኝ። ትግሬዎች በመባል እየተጠራን ያለን የዛሬዎቹ ትግሬዎች “የድሮ አክሱማዊያን” “ያልተደባለቀን ንጹሕ “አክሱማዊያን”/”አጋአዚያን”…ማለት የዛሬዎቹ ትግሬዎች ነን ብለን በልበ ሙሉነት መናገር አንደማንችል ሁሉ (የሚያገናኛቸው ነገርና ሐረግ ቢኖርም የዛሬ ትግሬዎች የድሮ አክሱሞች ነን ብለን 100/100 እርግጠኛ ልንሆን አንችልም) ፤ ኦሮሞም የድሮዎቹ ንፁሃን ጋላዎች፤ የዛሬዎቹ “ክልስ ኦሮሞዎች” “ንፁህ /ያልተደባለቅን ጋላዎች/ኦሮሞዎች፤ ነን” ቢሉም “ከስሜትና ከቅዠት” የተነሳ “ድንቁርና እና ፋሺስታዊ ስሜት ያሰከረው ንፁህ ደም” ፍለጋ ባሻገር ከመሆን ዘልሎ ሊሄድ አይችልም።

ታሪክ ነው እየተነጋገርን ያለነውና ታሪከ እንደ ታሪኩ እንድትረዱልኝ እፈልጋለሁ። ግልፅ ግልፁን! አለ ወዳጄ ጋዜጠኛው ድምጸ መረዋው “ኢሳያስ ልሳኑ”! የጀመርኩት ጭብጥ ከመቀጠሌ በፊት ግን ይህ “ጋላ” የሚባል ነገድ ዛሬ በኬኒያ በሶማሌ እና በመሳሰሉ እንዳሉ ይታወቃል። የኛዎቹ “ኦሮሚያ ነን” የሚሉ አስገራሚና አስቂኝ ኦሮሞ ተገንጣዮች “ጋላ” የሚለው ስያሜ “ስድብ” ነው ብሎ፡የነገራቸው ማን እንደሆነ እና ስድብ ነው የሚል የትኛው መጽሐፍ እንዳገኙት ባናወቅም፤ “ጋላ” የሚለው ትከክለኛ የተከበረ የድሮ የጋላ ነገድ ስም (የተከበሩ ክቡራን ወላጆቻቸው “የጋሊቷ ልጅ” እያሉ ወላጆቻቸው በቀና እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ሲፎክሩበት አንዳልነበረ ሁሉ) ነውር ነው/ደሮጋቶሪ ነው//አስጸያፊ ስም ነው” ፤ እያሉ ብዙ ኦሮሞዎች በፈጠራ ፕሮፓጋንዳ ተታልለው በብዛት ተቀብለውታል። የለወጡትም በደረግ ጊዜ ነው። 

ደርግ ሲመጣ፤ የደርግ ስርዓት የመሩት ኦሮሞዎች ስለነበሩ” ያንን ስም ወደ ሁለተኛው ስም በቀላሉ ወደ ሁለተኛ ስማቸው ወደ “ኦሮሞነት” እንዲለወጥ በማድረግ፤ “ጋላ የሚለው ሌላኛው “ከጥንት ጀምሮ እስከ ኬኒያ፤ ሶማሌ… ድረስ ሲጠራበት የነበረ ሕጋዊ የነገዱ አጠራር” “ስድብ” ነው፤ ብለው “ብረይን ኮንትሮል ፍሪኮቹ” አስቁመውታል። ይህ ሲሆን፤ በውሸት ወጣቱንና ሕዝቡን አሳመኑት። ይህንን በሚመለከት ከኢትዮጵያ ድምበር አልፈው ሌላ አገር ድረስ፤ ማለትም ኬኒያ ድረስ ተሻግረው ጋላ የሚለው ስያሜአቸው ወደ ኦሮሞ እንዲለዉጡ “ሌላ አገር” የሚኖረውን ሰላማዊው “የጋላ” ነገድ “ኦሮሞ ተብሎ አንዲጠራ ኢትዮጵያን አገራችንን “በጥብጠው”፤ በሰው አገር ድረስ ተሻግረው ለማበጣበጥና “ሕጋዊ የነገዳቸውን ስማቸውን” ለማስቀየር የጻፉትን ማመልከቻ ከዚህ በታች ያለውን ለማስረጃ ባጭሩ ተመልከቱልኝና ወደ እዛው እንቀጥላለን። ባጭሩ አንዲህ ይላል፦ 

FROM: OROMO REFUGEE TEACHERS, THE OROMO REFUGEE COMMUNITY LEADERS, KENYA. December 20, 2013

 TO: KENYAN EDUCATION MINISTRY NAIROBI, KENYA. P.O.BOX 30040-00100,

REQUEST TO REMOVE AND BAN THE USAGE OF TERM GALLA IN KENYA.

We, the Oromo teachers from Oromo refugee community in Kenya, are writing to you to bring into your attention the negative impact of the usage of a derogative and abusive word Galla to identify the Oromo in the text books of social studies used in primary and secondary education in Kenya. It is wrong terminology usage against Oromo identity which is unjustifiable historically to educate the nation. In fact the people identify themselves as Oromo and their language as Afan Oromo, which is the correct terminology usage. Although the Oromo nation is the second largest in Africa, it is forgotten by or still unknown to the majority of the world today, even the name Oromo. This is partly because of the colonial Ethiopian Emperors Menelik and Haile Sellesie and their successors which continued until today to treat Oromo with utmost cruelty due to their resistance to colony. The Oromo people endured a stagnant existence where ignorance and famine have been coupled with ruthless oppression, subjugation, and exploitation in all spheres of life and above all extermination. Everything possible was done to destroy Oromo identity, language, culture, custom, tradition, name and origin. In short, the colonizers maintained the general policy of genocide against the Oromo and use the term Galla to dehumanize and victimize Oromo and to destroy their identity and language. Such insulting name to the nation were abolished and eradicated by oppressed nation of 1974 revolution in Ethiopia and the usage of the term Galla is officially banned. And sadly, to deny the Oromo the right to identity and as if this is not enough and to add insults to injuries, the term Galla is in use interchangeably for Oromo in text books of social studies used for education system in Kenya. To cite few books; the Evolution World, a History and Government course Form 1, by Oxford new edition 2010, under the topic Cushitic…………………the Cushites group comprised of……….Galla(Oromo)………>> on page 78 and under the topic Borana…………..the Boran are branch the Oromo or Galla people……….they speak Cushitic language called Galligna……on page 81 and also in other course book-Milestone in History and Government Form 1 by Longhorn publishers…..reprinted in 2010 under the topic Eastern Cushitic comprise of the Elmolo, Gabra, Oromo(Galla)…..on page 40. And also in some many other course books published by Kenya Literature Bureau. Hence, as we clearly tried to indicate above, such wrong terminology usage for Oromo identity is illegal and it allows subjugation and victimization of Oromo children and people at large,infact it is clear violation of basic human Right Declaration of children’s basic right to good education and right to identify of Oromo nation.And this should not be allowed to continue by free and Democratic nation of Kenya and Africa. Therefore,kindly we the Oromo refugees in Kenya would like to request the honourable education office and concerned authorities of institutions to totally remove the use of the term Galla from educational books and further ban the usage of such abusive term against people in any written or oral form in Kenya. THANKS FOR YOUR UNDERSTANDING AND LEGAL ACTION! YOURS TRULY, THE OROMO REFUGEE TEACHERS THE OROMO REFUGEE COMMUNITY LEADERS KENYA

ክቡራን አንባቢዎቼ ሆይ! ይህ ጉደኛ ደብዳቤ ተጻፈው ከሁለት አመት በፊት ነው ወደ 2013 አካባቢ ‘በፈረንጅ’። አስገራሚ የሚያደርገው ደግሞ፤ “ጋላ” የሚለው ስያሜ የሰጡት አፄ ምኒሊክና አፄ ሃይለስላሴ በማስመሰል፤ ኬኒያ ፤ ሶማሊ፤ኢትዮጵያ፤ ሌሎች አገሮችም ካሉ፤ እራሳቸው ይዘርዝሩት፤…… ሁለቱ ንጉሦች ጋላ ብለው የሰየሙዋቸው ይመስል፤ በውሸት እየከሰሱ፤ ይህ ኦሮሞ የተባለ የነገድ ስም “ጋላ” እንደተባለ እና “ሰፊው” የኦሮሞ ሕዝብ (ሰፊ፤ትንሽ፤ ትልቅ፤ማይኖሪቲ/ማጆሪቴ የሚለው የትምክህት/ኢጎ/ ትንታኔ ምን ማለት እንደሆነ ባይገባኝም) “በዓለም ሕዝብ” እንደ “አገር” አንዳይታወቅ ያደረጉት እነኚህ ሁለት ንጉሦች መሆናቸውን ባስቂኝ ደብዳቤአቸው ገልጸዋል። እነኚህ ተገንጣያችና ፋሺስቶች እያመለከቱ ያሉት “ለኬኒያ” ነው። ኬኒያ ደግሞ ኢትዮጵያ አይደለም። ምኒሊክም ሆኑ ተፈሪ አልገዙትም፤ ስለሆነም ጋላ ብለው ነገዱን አልሰየሙትም። ጋላ ማለት ነውር ነው ብለው የነገድ ስም ለማስቀየርና ብጥብጥ ለማስነሳት እየጣሩ ያሉት፤ ባዕድ አገር ሆነው ነው። 

እየነሩት ያሉትም በጥገኛነት ነው። የኬኒያ መንግሥት እነዚህ ሰዎች አያውቃቸውም; ዜጎቹ ሳይሆኑ ስደተኞች ናቸው፤፡ እዛው ኬኒያ ያሉ የጋላ ነገዶችም እነኚህ ነገሥታት እንደገዟቸው አስመስለው ነው ስማቸው በዓለም እንዳይጠራ አድርገው እነዚህ ነገሥታትን እየከሰሱዋቸው ያሉት። ጋላ የሚለው ስም አማራዎች ሰጡን ሲሉን የነበረው፤ አሁን ደግሞ ኬኒያ ያሉት አውነተኛ ጋሎችን “አማራ” የሚባል ገዢ (ምናልባትም በፋሺስቶቹና ተገንጣዬቹ ውንጀላ ‘በምኒሊክ/በሃይለስላሴ’) እንደተሰጠ አስመስለው ነው “ስለ የኬኒያ ጋላ ነገዶች” ተቆርቁረው “ኦሮሞ እንዲባሉ” ነው ለኬኒያ የትምህርት ሚኒስትር ደብዳቤ የጻፉት።

ይህንን ዕብደት ስትመለከቱ በምን ቃላት ልትገልጹት ትችላላችሁ፤ “እናንተየ!!”? በስደት እየኖሩ በሰው ጋር ሄደው የሌላ አገርን ነገድ ስም ይቀየር ብለው ሲሟገቱና የዛው አካባቢ “ነገደ ጋላ” ባላሰበውና ባላስተነተነው ዓላማ “ለማቃዠትና ለማነሳሳት” ሞመከራቸው፡ እነኚህ ተገንጣዮች፤ ለመሆኑ ድምበር፤ ዜጋ፤መንግሥትና ስርዓት እንዲሁም “ስደተኛ” ማለት ምን ማለት አንደሆነ ያወቃሉ? ወይስ የኬኒያ ጋላዎችቹንም ኢትዮጵያዊያኑን ኦሮሞዎች እንዳሳሳትዋቸው ጭምር የኬኒያዎችንም እንዲሁ እያሳሳቱ “ከኬኒያ ገንጥለው” ኦሮሚያ ለምትባል አዲስ የቅዠትና የፋሺስቶች ቅርምት ሊጨምሯቸው ዕቅድ ስላላቸው? እነዚህ ክፍሎች “የዜጋነትና የድምበር ትርጉም ስለማይገባቸው” ድምበር እየተሻገሩ፤ አንዲህ ያለ ብጥብጥ እየፈጠሩ ስለታዘቡ መሰለኝ ባለፈው ወር፤ በኢትዮጵያና በኬኒያ የፀታ የጋራ ስምምነት ሲያደርጉ “ኦ ኤል ኤፍ” የተባለ “thug” “ወረበላ” ሲሉ የኬኒያ ጋዜጦች፤ቃል በቃሉ፤“thug” “ወረበላ” ሲሉ ጽፈውባቸዋል።

ኬኒያኖቹ እራሳቸው በደምብ አድርገው የዚህ ወረበላ /mob ምንነት ስለሚያውቁ፤ የኬኒያ ጋሎችን ሰብከው ኬኒያንም ለማበጣበጥ፤ እስከ ታንዛኒያ ድረስ እየሰበኩ እንደነበረ አንድ ሰነድ ሳነብ አጅግ ገርሞኛል። ይህ ዕብደት ከማለት አልፋችሁ ከዚህ የከፋ ሌላ ቃላት ካላችሁ እባካችሁ ፈልጋችሁ በክፍተቱ ሙሉት። እንግዲህ ይህን ላሳያችሁ የፈለግኩት ውሸታሞቹ ወደ ኬኒያ ድረስ ማመልክቻ እየጻፉ ኬኒያዎችንም “ጋላ” አይደላችሁም” ኦሮሞ ነው የምትባሉት እያሉ የስደተኛ ህይታቸው የኬኒያን ሕግና ስርዓተ ትምሕርት አክብረው ህይወታቸው እንዳይገፉ፤ አገራቸው ያልሆነውን ኬኒያን ሌላ ብጥብጥ ለመፍጠር የኬኒያ ዜጎች ምንም ሳይሰማቸው፤ ስለ እነሱ አፈቀላጤ ሆነው “ጋላ” የሚለው የጥንቱ እውነተኛ የነገድ ስም “ኦሮሞ” እንዲባል እዛም በስደት እየኖሩ በህፃናት ሕሊና ላይ ጥርጣሬ እንዲያድርባቸው “ሁውከትና የራስ የበታችነት ስሜት” ለመፍጠር፤ ድምበር ተሻግረው እንኳ ሳይቀር የሚሰሩት ባሕርይ ለመግለጽ ነው መረጃው የጠቀስኩት። የኬኒያ የጋላ ነገዶች ከተቀረው የኬኒያ ሕዝብ ጋር በስም ለውጥና አጠራር ሕዝብን ከሕዝብ የማጋጨት ባሕሪያቸው ድምበር ሸገርም አልተዋቸውም። 

እሺ ኢትዮጵያ ያሉትንስ “አማራዎች/ምኒሊክ/ሃይለስላሴ…..” ጋላ ብለው ስሙን ሰጡን ይበሉ፤ እሺ፤ ኬኒያና ሶማሌ ያሉትንስ ስማቸው ካልሆነ ጋላ ብሎ ማን ሰየማቸው? ምኒሊክ/ሃይለስላሴ/አማራ? በየት በየት ተሻግረው? አረ እባካችሁ እነኚህ ሀፍረተቢሶች በምን ቃላት አንደምገልጻቸው አሁንስ እየጨነቀኝ ነው!? እንግዲህ ጋላ የሚባል ስም ለምን እንዳስጠላቸው፤ እራሳቸው ከሚፈለስፉት ቅዠት በቀር ሌላ መረጃ የላቸውም። EEDN በኖርኩበት የውይይት መድረክ ውስጥ ይህንን ለብዙ አማታት እንዲያብራሩልኝ ፤ ምንጫቸውም እንዲያቀርቡ ጠይቄአቸው፤ ከመሪዎቹም ቢሆን አንድም መልስ ለመስጠት አልቻለም። ዛሬም “ድፈን፤ድፈን ነው መልሳቸው”። አሳዛኙ ግን፤ የዚህ ነገድ ክፍሎች በራሳቸው ላይ “የበታችነት ስሜት የሚፈጥሩ የአሮሞ ምሁራን ግን፤ ከዚህ ሊማሩ አልቻሉም። ኦሮሞ የሚለው አንዳንዱ “ሖሮሞ” “ዎሮሞ” “ሃራሙያ” እያለ ገበሬው ስለሚጠራው እሱንም አስጠልቶናል እና ‘ኦሮሞ’ የሚለው ትትን “ሌላ ስም ለውጠናል” ይሉን ይሆናል። ማን ያውቃል! ከጋሊቷ ልጅ ኢትዮጵያዊ ፉከራ ፤ ወደ ኦሮሚቷ ልጅ ከዚያ ደግሞ “ነገ ሌላ ስም ሊፈጥሩ ይሆናል (ልክ እንደ ተለያዩ ባንዳራዎቻቸው፤ መጠሪያቸውም እንደዚሁ)።ማን ያውቃል። 

ጠርጥር! ያለ ማን ነው፤አንድ ፀሐፊ አንቢቤአለሁ፤ ጥሩ አባባል; ጠርጥር! ወደ ርዕሳችን እንመለስ።ኢትዮጵያ ሳይሆን አቢሲኒያ ነው የሚሉን። እኛ ኦሮሞዎች በዲሞክራሲ እንተዳደር ነበር፤ ግን አቢሲኒያዎች/ምንሊክ “የቅኝ ተገዢአቸው አደረጉን” ገዙን ይሉናል። አንድ ባንድ እንመለከታለን።፡የጋላ ነገድ ዲሞክራሲ ነበር እያሉ ይዋሻሉ። ስሙም “የጋዳ ሥርዓት” ይባላል ይላሉ። እኔ ግን “ፕሪሚቲቭ/ፐሪማቱር ፋሺዝም” እለዋለሁ። በዝርዝር ባጭሩ እንመለከተዋለን። የዛሬዎቹ “የግንጠላ ጠበቃዎችና፤ የኦሮሞ ባንቱስታን የክልል አስተዳዳር አቀንቃኞች” የሆኑ የኦሮሞ ፋሺስቶች ባሕሪ መነሻ የሚያደርጉት፤ “ከዚያ ከፕሪማቱር የገዳ ፋሺዝም ዘመን የመነጨ” ባሕሪ ነው። ያንን ያከብሩታል።

 ለኦሮሞ ህልውናም ዛሬ እያሳዩን ያለውን “የቦታ ሄጂመኒ/ነጠቃ/ወረራ/” መሰረታዊ መመሪያቸው ሲሆን፤ ከዚያ ዘመን ጀምሮ ወደ ሰፊዋ ኢትዮጵያ፤ ከዚያም ኦሮሞዎች “ደርግ የሚል ወታደራዊ ስርዓት መስርተውና ተሰግስገው ኢትዮጵያን ሲያስተዳድሩ” ያሳዩት ፋሺስታዊ ስነምግባር እና ከዚያም ሲወድቁ፤ ያደራጁትን “ኦነግ” የተባለው ገንጣይና እጅግ “ፋሺስታዊ” የሆነ ወንጀለኛ ድርጅት ከወያኔ ጋር ሰምሮ፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አማራዎችና ኦሮሞ ወታደሮች በትኖ፤ ለልመና ዳርጎ፤ የቀሩትንም ጨፍጭፎ፤ከክልሉ አስወጥቶ የሰራውን ግፍ፤ ታሪክ ዘግቦታል። (ደርግ ኦሮሞዎች ነበሩ ያስተዳዳሩት ሲባል፤ ግራ የሚገባቸው ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ምስጢር በኋላ ነው የተገለጸልን። አስገራሚው ደግሞ “ደርግ” አማራ እያሉ ኦነጎች አውቀው ሲወነጅሉት፤ ደርግን የመሩ አማራዎች ሳይሆኑ አብዛኛዎቹ “እራሳቸው ኦሮሞዎች ነበሩ”።

ወንጀለኛው ኦነግም፤መኢሶንም የደርግ ዋና የቀይ ሽብርና የወንጀል ታካፋዮች ነበሩ።ከቁንጮው ከሊቀመንብር መንግሥቱ ጀምሮ፤ተካ ቱሉ፤ተስፋዬ ገብረኪዳን፤ ደበላ ዲንሳ፤ደምሴ ቡልቶ፤ መርዕድ ንጉሴ፤ ረጋሳ ጂማ፤ ወብሸት ደሴ… ስንቱን ኦሮሞ ባለስልጣኖችንና ወታደራዊ አዛዦችና ደብዳቢ ካድሬ ኦሮሞዎች የነበሩትን ስንት ብለን እንቁጠር….! የፖለቲካ ክፍሉን የመሩት እነ ነገደ ጎበዜና፤ሃይሉ ፊዳ የማሳሉትን የፖለቲካ ቀያሾቹ ስንት ብለን እንቁጠራቸው! አሁን፤ አሁን፤ ደርግን በአማራነት እየከሰሱ “አማራውን” ሲያብለጠልጡት መስማት አጅግ ይገርማል። አስገራሚው ደግሞ “ባለፉት ግፈኛ ስርዐቶች” ኦሮሞ ሕዘብ ተበድሏል ይላሉ፤! ደብዳቢው፤ ግፈኛውማ ገዢው፤ማን እንደነበር እየተዋወቅን! ) ‘ ውሸቱ እንደካሁን በፊቱ ውሸት እየተቀበልን በቸልተኛነት መቀጠል የለበንም፤! ግልፅ ግልፁን! እንነጋገር። ቀስ በቀስ በለመዱት ብልጣብልጥ ስልታቸው፤ ቀስ ብለው በወያኔ ትከሻ ተንጠልጥለው፤ የገቡት፤ ኦነግ ብቻ ሳይሆኑ፤ የኦሮሞ “አክራሪ” እስላማዊ ፋሺስታዊ ኦሮሞ ድርጅቶች” እንዲሁም፤ ለ24 አመት የቀጠለ “የቀኝ አክራሪ ፋሺስታዊ ኦሮሞ ምሁር” እና አሁን እንደ አዲስ የተፈጠረው “በወጣት ኦሮሞ ምሁራን” የቀጠለው አዲሱ “የሜንጫ ኦሮሚያ አብዮት” የሚባለው ምሁራን የሚመሩት ፋሺስታዊ ቅስቀሳውን ባጭሩ ዳስሰን እንሰናበት።

ባጭር አገላለጽ፤ አሁን ላለው “ኦሮሚያ ኬኛ” የተማሪዎች መፈክር ምንጩ የሚከተለው ይሆናል። 1) ጋላዎች ከቦታ ቦታ፤ ካገር አገር፤ከግጦሽ ወደ ግጦሽ፤ በመዘዋወር ጥንት ከብት በማርባት ሲኖሩበት ከነበሩበት “ገላን” ከተባለ ከታች የኢትዮጵያ ጠረፍ በመነሳት እነኚህ “ጋላ” በመባል የታወቁ የተለያዩ የጋላ ነገዶች ወደ መሃልና ወደ ከፍተኛው ቦታ፤ አንዲሁም ምስራቅና ምዕራብ፤ እንዲሁም ሰሜን ኢትዮጵያ ውስጥ በየማአዝናቱ ተከፋፍለው ንብረት/አገር/መሬት/ሴት/ከብት ለመዝረፍ የተከተሉት ፋሺስታዊ የወረራ ጭፍጨፋና ቤቶችን ገዳማትን በማቃጠል፤ የተፈጸመ ፋሺዝም እንመለከታለን፡ 2) በደርግ ወቅት የተካሄደው ኦሮሞዎች የመሩት ፋሺስታዊ ስርዓት 3) በወጣት ምሁራን ኦሮሞዎች የተካሄደው ኦነግ፤ እና “ኢስላማዊ ኦነግ” እንዲሁም “የሜኒጫ አብዮት” ተብሎ የሚታወቀው “የኦሮሞ ፋሺዝም” ያካሄደው በአማራ ነገድ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ።

 እነዚህ የኦሮሞ ፋሺስታዊ ስርዓቶች ማለትም “From Fascism to Fascism (Aleme Eshete) ወይንም በኔው አገላለጽ “The Recycling of the Ormo Fascism!” The third cycle of the oromo Fascism” (Getachew Reda) ወይንም “ሦስተኛው ዙር የኦሮሞዎች ፋሺስታዊ አብዮት” ምንነት በየተራ እንመለከታቸዋለን። የገዳ ሰርዓት የጀመረው እጅግ ኋላ ቀር የሆነ የጭካኔ አስተዳደሩን እንመለከታለን፤ ከዚያ ያነሳሁዋቸው በየደረጃቸው ያሳዩት ፋሺስታዊ ድርጊቶችን ባጭር ባጭሩ እንመለከታለን። ከዚያ ማን ነው የተበደለው? ማን ነበር ስርዓት ላይ የነበረ፤ አሁን ኦሮሞዎች “የኛ ነው” እያሉ ማንም ሰው መግባት ማረስ፤መውጣት፤ ማስተማር ፤ማስተዳዳር፤መኖር፤ ካለ ኦሮሞዎች በጎ ፈቃድነት “አይፈቀድለትም” በማለት የራሳቸው አጥር አጥረው ለግንጠላ እየተበረታቱ ያሉ ወጣቶችን “ራስ በራስ” ማስተዳዳር ማለት “ሞብ ሩል” የወረበሎች/ኦሊጋርኪ ስርዓት እንጂ “የግለሰብ ነፃነት” የሚባል ነገር “በነገድ ፌደራሊዝም ከቶ መጠበቅ ቅዠትና ስህተት መሆኑን እንመለከታለን። እነዚህ አሁን ሰፊ መሬት አለን፤ ሰፊ ነን፤የኛ ነው፤ ማጆሪቱ ሩል….ወያኔ ራሳችን አንድናስተዳዳድር “በነገድ ፌደራሊዘም ሕገመንግሥት ተፈቅዶልናል” ወዘተ እያሉ የሚፎክሩበት “ክልል” የማን መሬት ነው? የኢትዮጵያ ሕዝብ መሬት ነው! አይደለም እንዴ? ዜጎች አይደለንም የሚሉ ከሆነ ተማሪዎቹ በግልጽ ይንገሩን። ሆኖም እነሱ ወደ እሚሉንም ብንሄድም፤ ‘መብታችን በሕገመንግሥቱ መሰረት” ራስችን እንድናስተዳድር ይፈቀድልን፤ የሚለው ቅዠት፤ የክልል ፌደራሊዝም ስርዓት “ሞብ ሩል/የወረበሎች/ ያካባቢ የመሳፍንቶች ሰርዓት አስተዳደር ነው” ነው። ማንኛውንም ኗሪ ራሱን ሊያስተዳድር ኣይፈቅድለትም።

 ምክንያቱም “ፈቃጅ ካለ፤ በማንኛውም ጊዜ ፈቃጁ የሰጠህን ፈቃድ ሊነጥቅህ ይችላል”። ምክንያቱም ኤትኒክ ፌደራሊዝም “ሞብ ሩል” ስለሆነ” “ዐለም ዓቀፍ መስፈርት የተከተለ “ሰውን እንደ ሰውነቱ” በሕግ አያውቀውም። ፀባዩ አይፈቅድለትም። “ኮለክቲቭ ራይት” ብቻ ነው የሚያውቀው። ሁሌም የጅብ መንጋዎች ከታችም ከውጭም፤ከላይም ስለሚያፈራ “ኦሊጋሪኪ/ሩል” እንጂ ግለሰቦች ነፃነት የላቸውም። መሬት የመንግስት ነው፤ የክልል ነው። የግለሰብ አይደለም። ስለሆነም፤ ንብረት ስለሌለህ “ነጻ’ ልትሆን አትችልም፡ “የፌደራልና የክልሉ ዴፐንዳንት/ጥገኛ ነህ”። ልትሸጥ፤ልትለውጥ አትችልም። ተከራይ ጭሰኛ ነህ። ቴናንት ነህ። ዜጋ አይደለህም። የክልሉ ወይንም የማአከላዊ ፌደራል መንግሥቱ ጭሰኛ ነህ ከሆንክም፤ “ነፃ” ዜጋ አይደለህም። የክልሉ መንግሥት ጭሰኛና ተከራይ እስከሆንክ ድረስ ስለ የመሬትና ንብርት መከራከር መብት “የቅዠት መብት” ብቻ ነው ሊኖርህ የሚችለው። ክልል ፌደራሊዝም ያንተው የግለሰብ ሁለተኛው ላንድ ሎርድ/ጌታህ ሲሆን/ የእርሱም ዋናው ጌታ “ማዕከላዊ መንግስት/ፌደራል” የሚባል “በሞብ ሩል ሕግ” የሚመራ አካል አለ። በነዚህ ውስጥ “አንተ” የሁለቱም “ጭሰኛ ነህ”። አራት ነጥብ!!!!!!!! አሁን ኦሮሞዎች የያዙት መሬት እንዴትና ከማን ነጠቁት? ስለ ጋዳ ስርዓት ትንሽ ልበልና ልደምድም። እውነት ነው ጋላዎች የተለያዩ ጎሳዎች ነበሩ። በዘመኑ ወደ መሃል ኢትዮጵያ የተስፋፉ “ጋላዎች” አንድነት አልነበራቸውም።

 እርስ በርስ ሲጋደሉና ሲዘራረፉ አንደነበር ሊቁ ጌታቸው ሃይሌ ገልጸውልናል። ቀደም ብየ የገለጽኩት መጽሐፋቸውን (የአባ ባሕርይ ድርሰት ተመረኩዘው ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተረጎሙልንን ተመልከት)፤ ለዘመናት ጀምሮ የተረጋጋን የኢትዮጵያ መንግሥት “ጋላዎቹ” ከገቡ በኋላ፤ አገሪቷን ብትንትኗ እንዳወጧት አባ ባሕርይ ንብረታቸውና መጽሐፍታቸው እንዲሁም ገዳማቸው ጅማ ውስጥ ሲያቃጥሉላቸው ያዩትን ነግረውናል። ጋዳ ወይንም “ሉባ” (ኦሮሞዎች አስተዳደር ዲሞክራሲ ነው) ተብሏል። ምን ማለት ነው? እኔ “ፋሽሰታዊ የወንዶች ራስን በራስ የማስተዳዳር ስርዓት” እለዋለሁ።

 5ቱ ጋላ ነገዶች 8ት፤ 8ት አመት ይሾማሉ፤ የተሾመው መሪ “ሉባ” ይሉታል። ስርዓቱ ወንዶችን በየበላይነት ያስቀመጠ፤ ወንድም ቢሆን ለሥልጣን እርከን ለመድረስ ፤ግድያ፤ብልት ሰለባ ፤ጸጉር በቅማልና በቁጫጭ መበላትን፤ ልጆችን መጣልን ወዘተ…ወዘተ.. ያጠቃልላል። ዲሞክራሲ የሚሉት ይህንን ፋሺስታዊ ባሕሪ ያካተተ ነው ዲሞክራሲ ነው እያሉ ወጣቱን በዛሬው ባሕሪ እንዲጓዝ የሚመሩት። ይህ ሁሉ የዛሬዎች ኦሮሞ ምሁራን ውሸት ከጥንት ጀምሮ “ከጋላ” ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ሕዝባዊ ዲሚክራሲ ነበረን፤ አቢሲኒያዎች/አማራዎች/ምኒሊክ…ወዘተ.. ነጠቀን፤ የሚሉትን ቅዠታቸውን እስኪ ታሪኩን ባጭሩ እንመልከትና እንደምድም። የጋሎችን ታሪክ የተወሉንን የመጀመሪያው የዓይን ምስክርና የጋላ ታሪክ ዘጋቢ አባ ባሕሪይ የጻፉትን በሊቁ ጌታቸው ሃይሌ የተተረጎመ (የአባ ባሕሪይ ድረሰቶች በገጽ 152 የተዘገበውን እንመልከት። “…ከማህላቸው አባ ሙዳ የሚሉትን አንዱን ወንድ አይሁድ ሙሴን፤እስላሞች መሐመድን እንደሚተማመኑበት ይተማመኑበታል። 

ከሩቅ አገር ድረስ ወደእሱ እየሄዱ እጅ እየነሱ የማሸነፊያ ቡራኬና የመዝረፊያ ቡራኬ ይባረካሉ። ምራቁን በድኝ ላይ ይተፋላቸዋል፤ እነሱም ከሚወጉት ዘንድ ሁሉ የውጊያ ዕለት ተስፋ እንዲሆናቸው (ምራቁን) በድኝ ቋጥረው ይይዙታል። ደግሞ ጋሎች ሁሉ በየነገዳቸው ሁነው አምስት መደቦች ናቸው። (አምስቱ መደቦች) በየተራቸው በየስምንት ዓመት ይሾማሉ። የተሾሙት ባለተራዎች ሉባ ይባላሉ። ይኸ ሹመት ማለት ሉብነት እስኪደርሳቸው ድረስ እስኪታቸውን አይገዘሩም፤ወንድም ሆነ ሴት (ልጅ) ሲወልዱ (ልጆቹን) እደጅ ይጥሏቸዋል እንጂ እንደወላጆች ሥርዓት አያሳድጓቸውም። ደግሞ በሹመታቸው ዘመን ሰው ካልገደሉ የራሳቸው ጠጉር አይላጩም። የሞት ፍርድ እንደተፈረደበት ዘወትር እያለቀሱ በሐዘን ላይ ይኖራሉ እንጂ ሰው ለመግደላቸውም ምልክት (የሚሆነውን) ቁንጮ አያወጡም። … እነዚህን የጋላ ልምዶች ሁሉ ንጉሥ ሥልጣን ሰገድ አስተዋቸው። በአብ፡ በወልድ፡ በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቋቸው አዘዘ። ወረነሻዎች ሁሉም ተጠመቁ። የጌታችን የመድሃኒታችን የእየሱስ ክርስቶስን የሥጋውንና የደሙን ምስጢር ተቀበሉ። (ቆረቡ)። ከክርስትያኖቹ ሁሉ ጋራ ያንድ እረኛ አንድ መንጋ ሆኑ። ወረንሻዎች ከሰባቱ በረንቱማ ነገዶች አንዱ ነገድ ናቸው።” (ጌታቸው ሃይሌ - እንደላይኛው ገጽና ምንጭ)።

ክቡራን አንባቢዎቼ፤ ይህ እውነታ ነው የኦሮሞ ምሁራን “ዲሞክራሲ ነበረን” እያሉ ሳይሸማቀቁ በየጋዜጣ፤ መጽሐፍት ጭምር እየጻፉ አግላይና፤ በነገድ ሐረግ ብቻ የሚተዳደር ስርዓት፤ ወንድ የሚነግሥበት፤ ሴት የምትናቅበት፤ለዚህ ስርዓት መሪ ለመሆንም “ዘግናኝ የሆነ፤ ሰውን በመግደልና በመስለብ ጭካኔን እንደ አዋቂና አስተዳዳሪ ማሳያ ተደርጎ፤ የሚወሰድ “የጫካ ሕግ” ነው፤ ዲሞክራሲ ነበር እያሉ ማሕበረሰቡንና የዋህ ፈረንጆችን እየዋሹ የሚያሳስትዋቸው። ይህ ስርዓት ነው፤ራስን በራስ በዲሞክራሲ ስንተዳዳር የነበረውን ሥርዓታችን አቢሲኒያዎች አፍርሰው ኮሎኒ አደረጉን እያሉ የሚመጻደቁብንና ወጣት ኦሮሞውን የሚያጃጅሉት (ልክ አንደ ኤርትራ አሳፋሪ ውዥምብራም ፤ውሸታም ሊሂቃኖች)። እነኚህ ነገዶች “ሉባ” በሚባለው ዝርፍያውና ወረራው እንዲቀናቸው እየመረቀ ወደ ወረራ ሲያሰናብታቸው፤ አሁን ድረስ ተንሰራፍተውበት የሚታዩትን እስከ ትግሬ ድረስ መጥተው የሰፈሩበት ምክንያት በሰላም ሳይሆን “ወረራና የጭፍጨፋ” ድርጊት እየፈጸሙ ነበር የያዙት፦ ከላይ የጠቀስኩት ምንጭ እንዲህ ይላል፤- (መስከረም የ 1633 ዓ.ም መጀመሪያ፤ዕለት ቅዳሜ፤(ዘመኑ) ማቴዎስ፤ (ንጉሡ) ጎጃም ሄደ።

በዚህ ዓመት ስሙ ለበቻ፤ መጠኑ አርባ ሺሕ የሆነ ጋላ ወደ ትግሬ መጣ፤ ሰራዌንም አወደማት። ሲመለስ የፅራዕና የተምቤን ሹማምንት በምድረ አላ ላይ ከበው ምንም ሳያስተርፉ ፈጁት። ንጉሡ በዶቢት ተቀመጠ። የበኽር ልጁ አቤቶ ቄስጠንጢኖስ ሞተ።(ምንጭ የአባ ባሕሪይ ድርሰቶች፤ ደራሲ ጌታቸው ሃይሌ፤ ገጽ 136) እንግዲህ በአለም የተደነቀ ራስን በራስ የማስተዳዳር ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ኦሮሞች ነበራቸው፤እያሉ የሚዋሹንን የጋላዎች ዲሞክራሲ እስከ ትግሬ ድረስ በዝርፊያ፤በግድያና በወረራ የመስፋፋት ባሕሪይ በየክፍላተ ምድሩ “ጥንታዊ ፋሺዝም” ኦሮሞዎችም እንዴት ያራምዱት እንደነበረ ባጭሩ ለማየት በቅተናል። ይህ ሁሉ ርቀት ተጉዘው ባጭር ጊዜ የኢትዮጵያን ሰፊ መሬት ሊቆጣጠሩ የቻሉበት ምክንያት አስቀድሜ እንደገለጽኩት፤ የተመለከትናቸው የጋላ ከብት አርቢዎች፤ ያገሪቱ /ኢንዲጅነስ “ነባር ሕዝብ” እያባረሩ፤ ሰው የሌለበት ጭር ያለ “ቤት የሚጠብቅ” ጠባቂ “ከልብ” (ውሻ) ሳይቀር፤ በጦር እየወጉ፤ መሬቱ፤ሚስቱ፤ንብረቱ፤እርሻውና ቤቱ፤የተነጠቀበት ምክንያት “ግራኝ አህመድ” አገሪቷን አቃጥሎ ስላዳከማት፤ ክፍት ቦታ አግኝተው ፤ ሰተት ብለው መላውን ሰፊ ቦታ ተቆጣጥረው፤ ዛሬ “ኦረሚያ ኬኛ” (ኦረሚያ የኛ) ወደ ማለት የደረሱበት ዋና ምንጩ “አገር ያወደመ” የጋሎቹ ወረራ ውጤት ተጠቅመው ነው ዛሬ “በክልላችን ማንም ሰው ዝር እንዳይል” በማለት ክልል የተባለ ባንቱስታናዊ “ዘረኛ አስተዳዳርን” በአክብሮት ተቀብለው ወደ ግንጠላ ጉዞ እያዘነበሉ “አንቀጽ 39ኝን” ማስፈራሪያ ካርድ እያሳዩ ሊያስፈራሩን እየሞከሩ የሚገኙት።

ለማጠቃለል፤በ24 አመት ውስጥ ለእልፍ አእላፍ አማራ ሕብረተሰብና ገበሬ ከኦሮሞ አካባቢ አገርህ አይደለም “ውጣ” እየተባለ የተባረረ፤እርጉዞች ማህጸናቸውና ሆዳቸው በቢላዋ የተዘረገፉበት፤ህጻናት በፋሺስታዊ ቢላዋ “አንገታቸው የታረዱበት” ንግዳቸውና አንብረታቸው እየተዘረፉ፤በግፍ የተጨፈጨፉ አማራዎች “ዜግነታቸው” የተነጠቁበት ምክንያት “የኦሮሞ ባንቱሳናዊ “የክልል” አስተዳዳር ቀያሾችና ጀሌዎቻቸው ምክንያት የቀየሱት “ሦስተኛው ዙር *የኦሮሞዎች የፋሺዝም* አብዮት ውጤት መሆኑን ልነገራችሁ እፈልጋለሁ። “ሦስተኛው ዙር *የኦሮሞዎች የፋሺዝም* አብዮት ተጠያቂዎች እነማን ናቸው? ወያኔዎችና የወያኔ ጀሌ ኦሮሞዎች፤እንዲሁም፤ በዕድሜ የገፉ “የኦነግ መሪዎች”፤ እንዲሁም “የሜኒጫ አብዮት” ተብሎ በእስላም የኦሮሞ ምሁራን ወጣቶች ልብ ያደረው እነ “ጃራ” የመሰረቱት “እስልምናን ከፖለቲካ አቀናጅቶ፤ የኦሮሞ እስላም ማሕበረሰብ፤ ኦሮሚያን ነፃ አድርጎ፤ እስላማዊት ለማድረግ፤ የተመሰረተው “ኦሮሞአዊ ፖለቲካል ኢስላም” አራማጆችና ተከታዮቻቸው ናቸው። የኦሮሞ ፋሺዝም” ያካሄደው በአማራ ነገድ ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ አልፎ፤ ‘አሮሚያ” ነፃ ካወጡ ፤ ኦሮሞ ማሕበረስብ እንደሚቀዳጅ የተሰበከውን “ማርና ወተት፤ራስን በራስ ማስተዳዳር ዲሞክራሲ ያገኙ ይሆን? ወይስ ኢስላሚክ ኦሮሚያ፤ በሸሪዓ እንድትተዳዳር በሚሉ ክፍሎችና፤ “ሞብ ሩል” በሚከተሉ “ኦነጎችና መሰል ተመጻዳቂ ምሁራን ኦሮሞዎች” ፍጥጫና እንደ ሶመሌ “የዕርስ በርስ” ፍጅት ተከትሎ “የኦሮሞ ሜንጫ ካሊፋት አብየተኞች” የበላይነት ይዳኙ ይሆን? ይህ ከሆነ ወጣት ኦሮሞ ሴቶች ምን ይገጥማቸው ይሆን? “ማስተማሪያ አትንሳኝ” ይባላል እና ትምህርት ቢሆናቸው የአፍጋኒስታናዊያን ወጣት ሴት ልጃገረዶች የተናገሩትን ትምህርት “በጥቅስ የተናገሩትን” አንብቡና እንሰናበታለን።

 "Every girl," recalled Saira Noorani, a female surgeon, "could go to high school and university.We could go where we wanted and wear what we liked. We used to go to cafes and the cinema to see the latest Indian film on a Friday and listen to the latest music. It all started to go wrong when the mujaheddin started winning. They used to kill teachers and burn schools. We were terrified. It was funny and sad to think these were the people the West supported."

ኦሮሚያ ተመስርታ ያ ሁሉ ቀውስ ቢመጣ፤ ካፌና ሲነማ መሄድ የለም፤ እምየ ኢትዮጵያ ሞታለች፤ መሰደጃ፤መላወሻ መረማመጃ፤መሸሺያና መጠለያ መንገድ አይኖርም። ሁሉም እንዴት እዚህ አረንቋ ልንገባ ቻልን? የሚል ሶማሌዎች መልስ ያጡበት ጥያቄ “በየአጥሩ ታጥሮ” “እየተጫፋጨፈ” መልስ ሊያገኝ ቢለፋ፤ መልስ ሰጪ አይኖርምና ከዚያ ከመአቱ ይሰውረን! አመሰግናለሁ። 

ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ Ethiopian Semay) getachre@aol.com

Tuesday, December 29, 2015

አንድነት ከማን ጋር?

የተለያዩ ወገኖች የሚያቀርቧቸ የአንድነት ጥሪ ጥያቄዎች፣ የዐማራውን መቀበሪያ ጉድጓድ፣ ዐማራው ራሱ እንዲቆፍር የሚያዘጋጁ እንዳይሆኑ ጥንቃቄ ያሻል!  

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማን ለማሥፋፋት የወጣውን ማስተር ፕላን ተግባራዊነት በመቃወም ሕዝባዊ አመጽ መቀስቀሱ ይታወቃል። ይህንን ተከትሎ የትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝን የሚቃወሙ፣ የፖለቲካ፣ የሲቪክ እና የሙያ ማኅበራት ድርጅቶች የሚያሰሙት የአንድነት ጥያቄ ይበል የሚያሰኝ ነው። ጥያቄው ዕውነት እንደሚሉት ከሐቅ የቀረበ ከሆነ ደግሞ፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከልብ የሚቀበለው ጥያቄ ነው። ለጥሪው አዎንታዊ መልስ መስጠት ያለብንም፣ አንድነት መልካም ነገር ስለሆነ ነው። «አንድነት» ቃሉ ራሱ ለጆሮ የሚጥም፣ ለኅሊና የሚስማማ ነው። መልካምነቱም፥ አንድነት፣ ውበት፣ ኃይል፣ ጥንካሬ እና የማድረግ ብቃትን የሚያጎናጽፍ በመሆኑ ነው።
ለዚህ ዓይነቱ ጥሪ የትናንቶቹም ሆኑ የዛሬዎቹ የዐማራው ልጆች፣ ቀስቃሽ የሚያሻቸው አይደሉም። ምክንያቱም ዐማራው ሲፈጠር ጀምሮ አንድነት፣ ኅብረት፣ ኢትዮጵያዊነት የሚሉት ጽንሰ ኃሣቦች ለአስተሳሰቡ እና ለአመለካከቱ ምሕዋር በመሆናቸው ነው። እናም ዐማራው ስለአንድነት ጥሪ ተቀባይ ሳይሆን፣ ጠሪ ነው።  ይህም ባለፉት 25 ዓመታት ሁሉም ነገዶች የወያኔ እጄታ ሆነው በዐማራው ላይ የጥፋት እጃቸውን አንስተው ሲገድሉት፣ ሲያስሩት እና ሲያፈናቀሉት፣ ዐማራው በተቃራኒው «አንድነት ወይም ሞት!»፣ «ኢትዮጵያዊነት ወይም ሞት!» ብሎ የቆመ መሆኑ ይታወቃል። በዚህ አቋሙም በትግሬ-ወያኔ ዘረኛ አገዛዝ እንደ ዐማራው የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል የተፈጸመበት፣ በአውራ ጠላትነት ተፈርጆ በፕሮግራም ሠፍሮ በተግባር ከ5ሚሊዮን በላይ ሰው የጠፋበት ነገድ የለም። በወሊድ መቆጣጠሪያ እንክብል ስም የሚያመክን ክኒን የተሰጠው፣ ኤች.አይ.ቪ. ቫይረስ በመርፌ ሆን ተብሎ የተስፋፋበት ሌላ ነገድ የለም።
ዐማራውን ለዚህ ዓይነቶቹ የጥፋት ዘመቻዎች የዳረገውም «አንድነት»፣ «ኢትዮጵያዊነት» የሚሉት ጽንሰ ኃሣቦች አራማጅ በመሆኑ ነው። የትግሬ-ወያኔ ለተነሳበት ኢትዮጵያን በነገድ ከፋፍሎ ለማጥፋት ላነገበው ዓላማው፣ ዐማራው ተባባሪ እንደማይሆነው  አስቀድሞ ያውቃል። በመሆኑም የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን በነገድ ከፋፍሎ ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት በጠራው የሽግግር ጊዜው ምክር ቤት፣ ተወካይ ያልነበረው ዐማራው ብቻ እንደነበር ይታወሳል። በዚህ ምክር ቤት የተገኙ የነገድ ድርጅቶች ሁሉም በሚባልበት ደረጃ፣ የፀረ-ዐማራ ግለሰቦች እና ቡድኖች ስብስብ ነበር። ይህ ስብስብ ኢትዮጵያን አፍራሽ ለሆነው የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ መደላድል በመሆን፣ ዛሬ አገሪቱ ለምትገኝበት የውድቀት ደረጃ እንዳበቃት ማንም ይስተዋል አይባልም። የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያውያንን በቋንቋ ከፋፍሎ ዛሬ ለምናየው ሁለንተናዊ ጥፋት ዳርጎናል። ይህ ከታሪካችን አንዱ አሣፋሪ ምዕራፍ ነው። መነጣጠል ውድቀት መሆኑን መማር የነበረብን ከወደቅን በኋላ ሳይሆን፣ አስቀድሞ ነበር። ይህንንም ከቀደሙት አባቶቻችን መማር ነበረብን። የውድቀታችን መሠረቱ አባቶቻችን የሠሩትን እና የነገሩንን እንደተረት አይተን፣ ጥራዝ-ነጠቅ የፖለቲካ ድርጅቶቻችን የነገሩንን ፈጠራ እና ልብ ወለድ እንደ ደረቅ ሐቅ አምነን፣ የእነርሱ ተከታይ በመሆናችን ነው። የእኛም ትውልድ ካለፈው መራራ ጉዟችን እንደተረዳነው፣ ኢትዮጵያውያን ውሕድ አካሎች እንጂ፣ የተነጣጠልን አይደለንም። ስለዚህ በዚህ ወቅት የተናጠል ጉዟችን የትም እንደማያደርስ ተገንዝበን በአንድነት ለመሰባሰብ መፈለጋችን እሰየው የሚባል ነው። ዞሮ ዞሮ ፈጽሞ ሣያደርጉ ከመቅረት ዘይግቶም ቢሆን ወደ ትክክለኛው መንገድ መምጣት የተሻለ ነውና። ስለዚህ የአንድነት ጥሪው የዘገየ ቢሆንም፣ ለወቅቱ ችግር መፍቻ ተገቢው መልስ ነው።
የአንድነት ጥሪው ግን ከዕውነት፤ ከልብ የቀረበ መሆን ይገባዋል። ዐማራው ምንጊዜም ለአንድነት፣ ለኢትዮጵያዊነት የቆመ መሆኑ ባያጠራጥርም፣ በእርሱ ፈጽሞ ጥፋት እና በእርሱ መቃብር ላይ የሌሎች ማንነት እንዲለመልም የሚሻ አለመሆኑ ሊታወቅ ይገባል። ባለፉት 25 ዓመታት ዐማራው በዘረኛው የትግሬ-ወያኔ እና የእርሱ እጄታ በሆኑ ቡድኖች የደረሰበት ሁለንተናዊ ግፍ የሚዘነጋ አይደለም። ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ነገዶች እና ጎሣዎች ተወላጆች ሆን ተብለው ተነጥለው የመፈናቀል፣ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀሎች የተፈጸሙባቸው ዐማሮች፣ ባለፉ ጊዜያት የደረሱባቸውን በደሎቻቸውን ሁሉ ያለምንም የወደፊት የኅልውና ዋስትና ትተው ወደማያስፈልግ የይስሙላ እንድነት እንዲመጡ መጠበቅ የለበትም። ስለሆነም የሚቀርቡት የአንድነት ጥያቄዎች የዐማራ ነገድ አባሎችን እና በእነርሱ ስም የተደራጁ ድርጅቶችን መሠረታዊ ሥጋቶች የሚያለዝቡ ሊሆኑ ይገባል ብለን እናምናለን። በመሠረቱ ዐማራው ለዕኩልነት፣ ለአንድነት፣ ለኢትዮጵያዊነት፣ ለሰላም፣ ለመቻቻል፣ እንዲሁም አብሮ ለመኖር ባይተዋር አይደለም። በታሪክም እንደሚታወቀው ዐማራው ለእነዚህ ዕሴቶች ከፍተኛ ዋጋ የከፈለ እና ለመክፈልም የተዘጋጀ ነገድ ነው። ሆኖም ባለፉት 50 እና 60 ዓመታት በአገራችን የተካሄዱት የፖለቲካ ትግሎች ዐማራውን ያገለሉ እና በጠላትነት የፈረጁ መሆናቸውን ዐማራው ከደረሰበት እጅግ መራራ የሆነ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ዘመቻ ተምሯል። ይህ ክፉ እና ዘግናኝ ጥፋት ከዐማራው ትውልድ አዕምሮ ሳይጠፋ እና ያንን የሚያስረሳ ሁኔታ ሳይፈጠር፣ እኒህንም በደሎች ለመካስ ምን ምን ነገሮች መሠራት እንዳለባቸው በጋራ ሳንመክር፣ «የእንተባበር» ጥሪዎች ከዚህም ከዚያም ይነሣሉ። አሁን ባለንበት ወቅት እንኳን «የእንተባበር» ጥያቄው መነሻ በሆኑት ሕዝባዊ አመጾች መቀጣጠል የተነሳ ዐማራው በዘሩ ተለይቶ የጥፋቱ ሰለባ ሲሆን እያየን ነው። በተቃራኒው ግን፣ የአንድነት ጥሪ የሚያቀርቡ ወገኖች በዐማራው ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጥፋት ከማውገዝ እና የደረሰውን ችግር ሕዝብ እንዲያውቀው ጥረት ከማድረግ ይልቅ፣ ጥፋቱን ለመሸፋፈን ሲሞክሩ ይታያሉ። ስለሆነም ከተለያዩ ወገኖች የሚቀርበው የአንድነት ጥሪ ከልብ ሣይሆን አፋአዊ፣ ለሥልጣን ለተዘጋጁ ወገኖች መረማመጃነት ዐማራውን ለጥይት ማብረጃ ለማድረግ እንጂ፣ ከዕውነት ለሕዝቡ ነባር አንድነት ዳብሮ መቀጠል ከመነጨ ውስጣዊ ፍላጎት የመጣ አለመሆኑን እነዚህ ቡድኖች የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በተጨባጭ ይመሰክራሉ።
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ይህን ለማለት የተገደደው በሚከተሉት አብይ ምክንያቶች ነው።
አንደኛ፦ «የኦሮሞ ተወላጆች የአዲስ አበባ ከተማን ለማስፋፋት የተዘጋጀውን ማስተር ፕላን ተግባራዊነት በመቃወም አስነሱት» እየተባለ በስፋት የሚዘገቡት ዜናዎች እና ዘገባዎች፣ እንቅስቃሴው በኦሮሞ ተወላጆች ብቻ እንደተጀመረ፣ የእንቅስቃሴውም ብቸኛ ተዋንያን ኦሮሞች እንደሆኑ የሚሳይ ነው። አንድ እንቅስቃሴ የሚጀመረው ከአንድ ቦታ፣ በአንድ ሰው ወይም ቡድን መሆኑ ነባራዊ ዕውነታ ነው፤ ይህን መለወጥ አይቻልም። እንቅስቃሴው ሁሉን-አቀፍ እንዲሆን ግን ማሳወቅ እና ማስተባበር ከእንቅስቃሴው ጀማሪዎች ይጠበቃል። ለዚህም የሚረዳው የእንቅስቃሴውን ዓላማ አገር አቀፍ አድርጎ ማሳየት ነው። ሆኖም ይህ ሲደረግ አይደመጥም። የሚደመጠው ዜና የአንድ ነገድ እንቅስቃሴ፣ መስዋዕትነት የሚከፍሉትም የአንድ ነገድ አባሎች እንደሆኑ ነው። ይህን ለማረጋገጥ የአቶ በቀለ ገርባን መግለጫ ማዳመጥ ይበቃል። የአንድነት ጥሪ የሚያቀርቡ ቡድኖች እና ድርጅቶች ኃሣባቸውን፣ «የኦሮሞ ሕዝብ ትግል» ብለው ጀምረው፣ የሚጨርሱት «ድል ለኦሮሞ ሕዝብ» እያሉ ነው። የሚያቀርቡትም ጥሪ «የኦሮሞን ሕዝብ እንቅስቃሴ ተቀላቀሉ» የሚል ነው። ገና ከመነሻው ይህ አባባል አግላይነት አለው። አቅጣጫውም «ትግሉን የሚመራው የኦሮሞ ሕዝብ ነው፣ እናንተ ተከተሉን እንምራችሁ» የሚል እንደምታ አለው። ከልብ በአንድነት ለመታገል ከፈለጉ ግን መባል ያለበት ትግሉ የትም ይሁን የት፣ መሪው ማንም ይሁን ማን፣ ፀረ-ወያኔ መሆኑን ማሳየቱ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ያገባል።
ሁለተኛ፦ በእንቅስቃሴው በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ደረሰ ከሚባለው ጥፋት የበለጠ የተጎዱት የዐማራው ነገድ አባሎች ናቸው። ለአብነትም ያህል ይህን እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ በአገር ቤት የሚታተመው «የቀለም ቀንድ» የሚባለው ጋዜጣ በቁጥር 22 ቅጽ 3 በታሕሣሥ 12 ቀን 2008 ዓ.ም. ባወጣው ዕትሙ፥ በአመያ ወረዳ በሚገኙ ሦስት ቀበሌዎች፦ ማለትም «አብቤ መድኃኒዓለም»፣ «ኩኖ ቁሊት (ቀርሳ ቁሊት)» እና «መሪ መገሪ (ባሬዳ)» በተሰኙት ነዋሪ የነበሩ የዐማራ ነገድ ተወላጆች ንብረት ውስጥ 1,000(አንድ ሺህ) ቤቶች ማጀት በጎረሰ፣ ደጃፍ በመለሰ ያለ የሌለ ንብረታቸው ከነቤቶቹ ተቃጥለው ወደ አመድነት ተቀይረዋል። በእያንዳንዱ የቀበሌዋ ነዋሪ ዐማራ ከ70,000 (ሰባ ሺ) እስከ 1,000,000 (አንድ ሚሊዮን) ብር የሚገመት በርበሬ ተቃጥሏል (አባሪ ፎቶግራፍ ይመልከቱ)። የሦስቱ ቀበሌ ነዋሪዎች ለዘመናት ከኖሩበት አካባቢ ተሰድደው ለርሃብ እና ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠዋል። ከቤቶቹ መቃጠል ሌላ የአምስት ዐማሮች ሕይዎት አልፏል። በጋዜጣው ዘገባ መሠረት፣ የዐማሮቹን ቤቶች እየነጠሉ ያቃጠሉት ሰዎች የኦሕዴድ እና የኦነግ አባሎች መሆናቸው፣ ለዚህም በፖሊስ ምርመራ ወቅት መታወቂያቸው መያዙን ጋዜጣው ይፋ አድርጓል። «የዐማሮቹ ቤቶች ተነጥለው እንዲቃጠሉ የተደረገበት ምክንያት ምንድን ነው? ዐማራዎቹ ምን ወንጀል ሠርተዋል?» የሚሉትን ጥያቄዎች ቤቶቻቸው ለተቃጠሉባቸው ሰዎች ጋዜጠኛው ላቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት መልስ አንድና አጭር ነው። መልሳቸው «ወንጀላችን ዐማራ መሆናችን ብቻ ነው» የሚል እንደሆነ ጋዜጣው ዘግቧል። አዎ! ዐማራው አገር የሌለው፣ ያገኘ የሚያርደው የፋሲካ በግ ከሆነ ዓመታት ተቆጠሩ። ይህ ግፍ እና በደል በዜና ዘጋቢዎች እና በፖለቲከኞች ንግግሮች ትኩረት አልተሰጠውም። በተጨማሪም በንቅናቄው ዐማራው ሆን ተብሎ የጥቃቱ  ሰለባ መሆኑ አይዘገብም። ስለሆነም የሚቀርበው የ«እንተባበር» ጥሪ «እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳበላ ግፋው» ዓይነት ነው።
በደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ አመያ ወረዳ በጅምላ ከተቃጠሉት የዐማሮች መኖሪያ መንደሮች አንዱ (ምንጭ፦ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ)
ሦስተኛ፦ የትግሬ-ወያኔ ሰሜን ጎንደርን ወደ ትግራይ ለማጠቃለል ባለው ዕቅድ መሠረት፣ ለዕቅዱ ማስፈጸሚያ ኮትኩቶ ያሳደጋቸው ጥቂት የቅማንት ተወላጆች፣ ጎንደር ተወልደው ካደጉ ትግሬዎች ጋር አቀናጅቶ ባዘጋጀው የመነጣጠል ሤራ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ዐማራ በጭልጋ፣ በደንቢያ፣ በመተማ፣ በቋራ እና በጎንደር ከተማ በግፍ ተገድሏል። ከሁሉም በላይ ከ80,000(ሰማንያ ሺህ) ስኩዬር ኪሎሜትር በላይ ስፋት ያለው የምዕራብ ኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን ገጸበረከትነት ቀርቦ እያየን እና እየሰማን የምንጮኸው ድምፅ ጎልቶ አይሰማም። ስለዚህ ዝምታው «በዚህ አካባቢ ተጎጂውም ዐማራ፣ መሬቱም የጎንደር ነው» የሚል እንደምታ ያለው አስመስሎታል። አንድ የሚያደርገን ከዚህስ የከበደ ምን ብሔራዊ አጀንዳ ይኖራል? የብሔራዊ አንድነት መገለጫ ከሆኑት አንዱ ዳር ድንበር መሆኑ ግልጽ ነው። ስለሆነም የሰሞኑ የ«አንድ እንሁን» ጥያቄ ይህን አጀንዳ የኔ ብሎ መያዝ ይገባዋል ብለን በጽኑ እናምናለን።
ከሁሉም በላይ የአንድነት ጥሪው ተገቢውን መልስ እንዲያገኝ፣ ካለፉት የእርስ በእርስ መጠላላፎች ተምረን ወደፊት በአዲስ መንፈስ እና ወኔ ለመጓዝ እንድንችል፣ ሁሉንም የትግሬ-ወያኔ ተቃዋሚ ኃይሎች ሊያሰባስብ የሚችል የግንኙነት እና የአሠራር ሥልት ሊነደፍ ይገባል። ለዚህም ጊዜ ሳይወስድ የሚመለከታቸው አካሎች ተገናኝተው በአንድነት ሊሠለፉ የሚያስችሏቸውን ጉዳዮች ነቅሰው ከማውጣት ጀምሮ፣ ከትግሬ-ወያኔ በኋላ ስለምትኖረው ኢትዮጵያ አመላካች የሆነ ንድፈ-ኃሣባዊ ቀመር ሊያወጡ ይገባል። ከዚህ ስምምነት ላይ እንዲደረስ «በኢትዮጵያ ጉዳይ ያገባናል» የሚሉ ኃይሎችን እና ቡድኖችን አሰባስቦ ወደ ተፈለገው ግብ ሊያመሩ እንዲችሉ የሚገናኙበትን እና የሚወያዩበትን መድረክ የሚያመቻች አንድ ወገን ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል። ይህን ኃላፊነት አባቶቻችን እንደሚሉት «ሊታረቅ የፈለገን ንጉሥ፣ እረኛ ሽማግሌው ይሆናል» ነውና፣ ዕውነት አንድነቱን፣ መስማማቱን እና አብሮ መሥራቱን ከልብ ከፈለግነው፣ የ«አንድ እንሁን»ን ጥሪ ከተቀበልነው፣ አስማሚ እና መድረክ አዘጋጁ ማንም ሊሆን ይችላል። ይህ ግን ቀና ከመሆን የሚመነጭ ሊሆን ይገባል። ስለሆነም ይህን መድረክ የማመቻቸቱ እና የማገናኘቱን ኃላፊነት፣ (1) ከሕጋዊው እና የስደተኛው ሲኖዶስ አባቶች፣ (2) ከእስልምና እምነት መሪዎች (3) ከፕሮቴስታንት እና ከካቶሊክ እምነቶች አባቶች የተውጣጣ ኮሚቴ ኃላፊነቱን ቢወስድ ሁሉንም የሚያስማማ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። የመወያያ አጀንዳዎችን ለመቅረፅ፣ «ያገባኛል» የሚሉ ወገኖች የየራሳቸውን ኃሣቦች አዘጋጅተው ለዚህ ኮሚቴ ቢሰጡ ሂደቱን ለማፋጠን ይጠቅማል። ኮሚቴውም ከሁሉም ወገኖች በተወከሉ ሙያተኞች እየታገዘ ሥራውን በአስቸኳይ ቢጀምር ለሚፈለገው የአንድነት ጥሪ ተገቢ መልስ ለመስጠት ከማስቻሉም በላይ፣ የትግሬ-ወያኔን አገዛዝ ግብዓተ-መሬት ያፋጥናል። ዐማራው ከአንድነት የበለጠ እና የከበደ አጀንዳ የለውም። አባቶቻችን «የሞትንም እኛ የነገሥንም እኛ» እንደሚሉት፣ ያለፈውን ጥፋት ለፍትሕ ጉዳይ ትተን፣ ወደፊት የሁላችንም መኖሪያ ለምትሆነው አገራችን አንድነት እና ሰላም መቆም እንችላለን። ስለዚህ ከየአቅጣጫው የሚቀርበውን የአንድነት ጥሪ የምንቀበለው፣ በአንድነቱ ዐማራው ባያተርፍም ተጎጂ እንደማይሆን ስለምናምን ነው።
የኢትዮጵያ አንድነት በቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ተጠብቆ ይኖራል!

Tuesday, December 22, 2015

የአገር ፍቅር ፋና፤

እኔ የዘጠና ሁለት ዓመት አዛዉንት ነኝ፤ ከሃገሬ ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ደህንነትና እድገት፤ ሰላምና ነጻነት፤ ድሮም ዛሬም
የመፈልገው ነገር የሌም። ህይዎቴን በሙሉ ያሳለፍኩት እክሌ ከእከሌ ሳልለይ አገሬን ህዝቤን በማገልገል ነው። ከልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ጎሳዎች የተዋለድኩ የተዛመድኩ ”ተዋህዶ ክርስትያን አማራ” ኢትዮጵያዊ ነኝ።

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ አማራዉን ለማጥፋት፤ ከኢትዮጵያ ለማቃቃርና ለመለያየት የተጀመረው ዘመቻ አሁንም እየቀጠለ
ነው፤ አገር ዉስጥ ቦታ የላችሁም ተከለሉ እንባላለን፤ ሴቶቻችን ኢየተፈነገሉ በችጋር ግፊት ለባርነትና ለዝሙት ለአረብ አገር እየተሸጡ ነው፤ ወንዱም ሴቱም ኢየተባረረ ስደትኛ ወይም የርካሽ ጉልበት ምንጭ ሆኗል፤ ያልተከሰስነው
ያልተወንጄልነው ሃጥያት የለም፤ ጡት ቆራጭ ሰላቢ ተብለናል፤ በሽታ የሚከላከልክትባት ኢየተባለ በአማራው አገር ላሉ
ኢህቶቻችን የምያመክን መድሃኒት ክትባት እየተሰጠ የአማራው ህዝብ ቁጥር በሚልዮን እንዲቀነስ ተደርጓል፤ በየአይነቱ

 ግፍ ሲደርግብን በጊዜ ያልፋል ብለን ታግሰን ነበር፤ አሁን ግን በቃ ብለናል።

በምንም መንገድ ስልጣን የሚፈልጉ ፖሊካኞች አብረን ዎያኔን እንዉጋ ይሉናል፤ ነገር ግን እኛ የምናውቀው አንድነት በሃቅና በእኩልነት ሲመሰረት ነው፤ ኢኛ የምንመኛት የምንሞትላት ኢትዮጵያ ሁሉም ዜጋ በነጻንት መብቱ በህግ
ተጠብቆ፤ በኢትዮጵያ ጠረፍ ዉስጥ የትም ሂዶ፣ የትም ዉሎ፤ የትም ሰርቶ፤ የትም አፍርቶ፤ የሚኖርባት አገር ስትሆን
ንው። ብርሃብ በበሽታ በችጋር በደሀየ በተራበ ህዝብ ላይ የፖሊቲካ ገበያተኞችና የውጭ ግርፍ ወረበሎች የሚሻሻጡባት የገበያ ሸቀጥ ስትሆን አይደለም። ሲለዚህ እኝ አማሮች ለሃገራችን ያለንን ግዴታ ለመፈጸም ከሁሉ አስቀድሞ ራሳችንን
በህብረት በማደራጀትና በማጠናቀር፤ ብርቱ ሃይል ምቋቋም አለብን፤ በደካማነት እኳን አገርን ራሳችንንም ከጥፋት

ለማዳን እንደማንችል ግልጽ ነው።

እንዲሁ የተከበራችሁ እናቶች እህቶች ሴት ውጣቶች ኢትዮጵያ እኮ አንቺ የምትባለው በናንተ ጾታ ነው፤ ምጣችሁ
ተሰቃይተችሁ ወልዳችሁ፤ ቤተሰቡን አቅፋችሁ ጠብቃችሁ የምታኖሩ እናንተ ናችሁ፤ በኢትዮጵያ ታሪክ ያላችሁ ከፍተኛ ሚናና ትግባር የነጻነትዋ መሰረት ነው፤ በታሪክ እንደሚባለው “ ርሳ አሊ ለአማቻቸው ለተዎድሮስ ለፋሲካ አንድ ወርች ልከውላቸው ተቀይመዉ ለሚስታቸው ለምንትዋብ ‘አይሽ አባትሽ የሚያደርጉኝን’ ብለው በቢስጭት ቢነግሯቸው
ምንትዋብ ‘ታድያ ተነሳ ምን ተጠብቃለህ ‘ ቢሏቸው ነው የሸፈቱት ተበሎ ይነገራል። የኢትዮጵያን ሴቶች ጉብዝናና ብልትሙና መዘረዘር አያሻም የታወቀ ነው፡ በዛሬ ወቅት ደግሞ በብዙ ዓይነት ገጽ የተማሩ የላቁ የተሰማሩ ባለሞያዎች ናቸው፤ የአገር አናቶች ናችሁ ተንሱ አስነሱ እያልኩ እማለዳለሁ።

ኢድል በማጣት እንጂ ሰው ደሃ ሁኖ አይፈጠርም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ መንፈሳዊና ባህላዊ ኢሰቶች ከማንም ብሔረሰብ
አያንሱም፤ ህዝባችን ብሩህ ተታሪ ትጉ ባለሞያ ነው፤ የሁለት ታላላቅ ሃይማኖቶች ባለአደራ ሁኖ በማንም ሳይገዛ ብዙ ሺ ዘመናት ነጻነቱን ጠብቆ ኖርዋል፤ ለዚህ ራዥም የነጻነት ትግል ብዙ ምስዋእት አድርጓል፤ አጉል እድል እየደረሰበት
እድገቱንም አዘግይቷል፡ አሁን ደግም በከተምንበት በኖርንበት አገር የፈረንጅ ግርፊት ወሮበሎች ተነስተው ባእድ ናችሁ
ቦታም የላችሁ ይሉናል፡ ዛሬ ደሞ ዙረው ኢንደምያርዱን እያወቅን አብረን ኢንዝመት ይሉናል።

 ዝምታችን ትግስታችን ሞኝነት መስሏቸዋል።

አዎን ለሕዝባችንና ለሃገራችን ነጻነትና ህልዉና እንታገላለን እንሞታለን፤ እርስ በራሳችን ሊለያዩንና ሊያቃቃሩን
የሚፈልጉትን መንጋዎች አንቃወማለን፤ በምሳሌ የአማአራና የኦሮሞ ጎሳዎች ከአምስት መቶ ዓመት (፭መቶ) ይበልጥ
አብረው ኖረዋል ተጋብተዋል ተዛምደዋል፤ ኢንዲሁም ከሌሎቹ የኢትዮጵያ ጎሳዎች ተዛምደዉና ተባብረው አገራⶨዉን ኢትዮጵያን በነጻነት አስከብረው ቆይተዋል፤ ይሄም ታሪክ የሚመሰክረው ሃቅ ነው፤ እንደዚሁ የትግራይ ሕዝብ ስጋችን ወንድማችን ነው፤ የወያኔን ወመኔዎች የምናቃወመው ስልጣን የዘው ሃገራⶭንንና አንድነታችንን በማፍረስ፤ ሃብትዋን
በመዝረፍና በማራከስ፤ ሰፊዉን ህብረሰቡ በማቆርቆዝና በሃይል መጨኮንና በግፍ ህገ ቢስ በሙስና የተለወሰ አስተዳድር
በማድረጋቸው፤ ለዉጭ ሃይሎችና ነጋዴውች አግሪትዋን በመሸጥቸው ነው። አሁን ይህ የግፍና የዉንብድና አገዛዝ በቃው ብለናል። የዎሬ ዘመን አልፏል ይትግባር ጊዜ ነው።

አማራ ተነስ መብትህን ጠብቅ፤ የአትዮጵያ ሕዝብ ተነስ አለኝታህንና ነጻነትህን አስከብር ኢላለሁ።
እ፤ዘ፤ ትሕሳስ ፪ሺ፰
///////////// ************ //////////// ************ ////////////

Tuesday, December 15, 2015

«ቅማንት ዐማራ፣ ዐማራም ቅማንት ነው»

ማክሰኞ ታኅሣሥ ፭ ቀን ፪ሺህ፰ ዓ.ም.                                    ቅፅ ፬ ፣ ቁጥር 


ቅማንት እና ዐማራ የተባሉት ነገዶች ለዘመናት አብረው ኖረዋል። አብረው በመኖራቸው ብዛትም በረጅሙ የአገራችን የመዋሐድ እና የመቀላቀል ሂደት አንድ ሆነዋል። ስለዚህ እኒህ ሁለት ነገዶች በጊዜ ሂደት የጋራ ኃይማኖቶች ተከታዮች፤ አንድ መግባቢያ የአማርኛ ቋንቋ፣ አንድ የጋራ አገር እና መልከዐምድራዊ መለያ፣ ከዚህም በላይ አንድ የነፃነት ታሪክ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል። በመሆኑም የወል የሆነ ማኅበራዊ ሥነልቦና መስርተዋል። በዛሬው ዘመን የነገዶቹን ተወላጆች ሁለንተናዊ ማንነትን መነሻ አድርጎ ለመለያየት መሞከር፣ ውኃ እና ወተት ከቀላቀሉ በኋላ እንደገና ለመለየት እንደመሞከር ይቆጠራል፥ ውሕድ አካል ሆነዋልና።

ሆኖም የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ዐማራን ለማጥፋት ላለው ረጅም ዕቅድ ብቸኛ ማሳኪያ መንገድ አድርጎ የወሰደው የ«ከፋፍለህ ግዛው» ሥልትን ነው። የዚህ ሥልት ማስፈጸሚያ በሕገ-አራዊቱ ያሠፈረው አንቀፅ ፴፱ መሆኑ ይታወቃል። በተግባርም እንደሚታየው የትግሬ-ወያኔ ነገድን ከነገድ፣ ጎሣን ከጎሣ፣ ኃይማኖትን ከኃይማኖት ማለያየት እና ኢትዮጵያውያን አብረው ስለጋራ አገራቸው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮቻቸው እንዳይመክሩ እና በአንድ እንዳይቆሙ አድርጓቸዋል። ለዚህም የዐማራውን ነገድ፣ ጨቋኝ፣ አፋኝ እና ገዥ፣ በተቃራኒው ደግሞ ሌሎችን ኢትዮጵያዊ ነገዶች ተጨቋኝ፣ ታፋኝ እና ተገዥ በማስመሰል በመካከላቸው መተባበር፣ መተማመን፣ መከባበር፣ መቻቻል እና በአንድ ማሰብ እንዳይችሉ ማድረግ የዘወትር ተግባሩ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን እኩይ ዓላማውን ለማሣካት በየነገዱ እና በየጎሣው ስም ድርጅቶችን ሲቀፈቅፍ፣ ለይስሙላ ያህል የእነዚያ ነገዶች ወይም ጎሣዎች ተወላጆች «የድርጅት መሪዎች» ቢባሉም፣ በተጨባጭ ግን እኒህ ድርጅቶች የሚመሩት በትግሬ-ወያኔዎች መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው። ሰሞኑንም ቅማንትን ከዐማራ ለማፋጀት ተብሎ የሚዶለተው ሤራ የዚህ ሥልት አካል ነው።

የትግሬ-ወያኔ ቅማንትን ከዐማራ ለመለየት የሚፍጨረጨረው የራሱን የረዥም ጊዜ ግብ ለማሣካት እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል። በመሠረቱ ቅማንትን በፀረ-ዐማራነት አደራጅቶ፣ አሰልጥኖ እና መርቶ ከጎንደር ዐማራ ጋር እንዳይኖር እና የራሱን ክልል እንዲመሠርት የተፈለገው ለቅማንት ነገድ በመቆርቆር አይደለም። የመጨረሻው ግብ አዲስ የሚመሠረተውን የቅማት ክልል፣ የትግሬ-ወያኔ በኃይል «የትግራይ አካል ናችሁ» ካላቸው የወልቃይት እና የጠገዴ ወረዳዎች ጋር በማገናኘት ሰሜን ጎንደርን በትግራይ ክልል ውስጥ ለማጠቃለል መሆኑ ግልፅ ነው። ይህንን ሤራ እንዲያስፈጽሙ ከቅማንት ነገድ ተወላጆች መካከል ጥቂት የፋሽስት ጣሊያን ባንዳ ልጆች ተመልምለዋል፤ በቀዳሚነት የሚታወቀውም የባንዳው ልጅ እና የዘመናችን ባንዳ ነጋ ጌጤ ነው። ከታሪክ እንደሚታወቀው በፋሽስት ጣሊያን ጊዜ «ደጃዝማች ጣሹ» የተባሉትን የቅማንት አባት እና ጀግና መሪ፣ በፀረ-ዐማራነት ሕዝቡን እንዲያደራጁ እና የራሳቸውን አስተዳደር እንዲመሠርቱ፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጀው እንዲያጠፉት ላቀረበላቸው የመነጣጠል ጥያቄ፣ «አሻፈረኝ!  ቅማንት ዐማራ ነው፣ ዐማራም ቅማንት ነው!» ብለው ለአንድነት በመቆም የፋሽስት ጣሊያንን ሤራ ማክሸፋቸው ይታወቃል። በተቃራኒው ግን «ጌጤ» የተባለው የነጋ አባት ለጣሊያን ፍርፋሪ በመገዛት ቅማንቱን እና ዐማራውን ለመለያየት መሣሪያ እንደነበር ታሪካችን ያስታውሰናል። በተመሣሣይ ሁኔታ የትግሬ-ወያኔ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ፣ የቅማንትን ነገድ አደራጅቶ የራሱን ክልል እንዲመሠርት፣ ዐማራውን በጠላትነት ፈርጆ እንዲያጠፋው፣ የቅማንትን ነገድ በነቂስ በዚህ ዓላማ ዙሪያ እንዲያደራጅ ኃላፊነት የሰጠው ለባንዳው ልጅ ነጋ ጌጤ እንደነበር ይታወሳል። የታላቁ ባንዳ የጌጤ ልጅ፣ የትግሬ-ወያኔ ምልምል የሆነው ባንዳው ነጋ ጌጤ፣ ይህን ኃላፊነት ከጌቶቹ ተቀብሎ ቅማንትን ከዐማራ ለመለያየት ያልማሰው ጉድጓድ፣ ያልቧጠጠው ገደል የለም። ነጋ ጌጤ እንደአበደ ውሻ ሕዝብን ከሕዝብ ለማናከስ የሚያደርገውን መክለፍለፍ እንዲያቆም፣ የጎንደር ጌጦች እና ኃውልቶች የሆኑት ዕውነተኛዎቹ የቅማንት አባቶች እና እናቶች፦ እማሆይ አበቅየለሽ ይመር፣ ግራዝማች ካሰኝ ዓለማየሁ እና የመሳሰሉት፣ በወቅቱ መክረው እና ገስጸው ከትግሬ-ወያኔ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዳይወጣ ማድረጋቸውን የጎንደር ሕዝብ ቅማንቱ እና ዐማራው በነቂስ የሚያውቀው ጉዳይ ነው።

ስለሆነም በነጋ ጌጤ አማካይነት ዐማራውን እና ቅማንቱን የመነጣጠሉ እና ለታላቋ ትግራይ መሥፋፋት የሚሆነው ሠፊ መሬት ማግኛ መንገድ በሕዝቡ እንቢተኝነት ሳይሳካ በመቅረቱ፣ ለትግሬ-ወያኔ የእግር እሳት ሆኖበት ቆይቶ ነበር። በዚህም ምክንያት የትግሬ-ወያኔ ዓላማውን ሳያሳካ ከደደቢት በረሃ የነደፈው «የታላቋ ትግራይ» ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል በማመን ሌላ ሥልት ነደፈ። ይኸውም «ቅማንት ተደራጅቶ የራሱን ክልል ካልመሠረተ ነገድ አይደለም፣ ዐማራ ሆኗል» በማለት፣ ምንጊዜም የኢትዮጵያ ነገዶች አንድ ተብለው ሲቆጠሩ፣ ከቁጥር ጎድሎ የማያውቀውን የቅማንትን ነገድ በ1999 ዓ.ም. ባካሄደው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ አስቀድሞ በተጠነሰሰ ሤራ እንዲሰረዝ አደረገው። ይህ በታሪካችን ሆኖ የማያውቅ ድርጊት መፈጸሙን ያዩ የነገዱ አባሎች፣ የትግሬ-ወያኔን ነጣጥሎ የማጥፋት ሤራ ሳይረዱ፣ ላቀደው ዕቅድ መሣካት መሣሪያ ሆነው ቀረቡ። እነዚህ ወገኖች በቅማንቱም ሆነ በዐማራው ዘንድ እጅግ የተከበሩ ሰዎች ነበሩ። አገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው የተማሩ እና ያወቁ ከሚባሉት የሚመደቡት እነ አምባሣደር ዘመነኝ ካሰኝ እና ዶክተር ማለደ ማሩ ለትግሬ-ወያኔ የተንኮል ወጥመድ ሰተት ብለው በመግባት፣ የቅማንቱ እና የዐማራው መጠፋፊያ እጄታ ሆነው ቀረቡ። በዚህም ምክንያት እነ ግራዝማች ካሰኝ ዓለማየሁ፤ እማሆይ አበቅየለሽ ይመር እና ሌሎችም ያከሸፉት ቅማንትን እና ዐማራን የመነጣጠል ዓላማ እንደገና ሕይዎት ዘርቶ እንዲያንሰራራ አደረጉት።

ስለሆነም በነጋ ጌጤ አማካይነት ዐማራውን እና ቅማንቱን የመነጣጠሉ እና ለታላቋ ትግራይ መሥፋፋት የሚሆነው ሠፊ መሬት ማግኛ መንገድ በሕዝቡ እንቢተኝነት ሳይሳካ በመቅረቱ፣ ለትግሬ-ወያኔ የእግር እሳት ሆኖበት ቆይቶ ነበር። በዚህም ምክንያት የትግሬ-ወያኔ ዓላማውን ሳያሳካ ከደደቢት በረሃ የነደፈው «የታላቋ ትግራይ» ግንባታ ተፈጻሚ ሊሆን እንደማይችል በማመን ሌላ ሥልት ነደፈ። ይኸውም «ቅማንት ተደራጅቶ የራሱን ክልል ካልመሠረተ ነገድ አይደለም፣ ዐማራ ሆኗል» በማለት፣ ምንጊዜም የኢትዮጵያ ነገዶች አንድ ተብለው ሲቆጠሩ፣ ከቁጥር ጎድሎ የማያውቀውን የቅማንትን ነገድ በ1999 ዓ.ም. ባካሄደው የሕዝብ እና ቤቶች ቆጠራ አስቀድሞ በተጠነሰሰ ሤራ እንዲሰረዝ አደረገው። ይህ በታሪካችን ሆኖ የማያውቅ ድርጊት መፈጸሙን ያዩ የነገዱ አባሎች፣ የትግሬ-ወያኔን ነጣጥሎ የማጥፋት ሤራ ሳይረዱ፣ ላቀደው ዕቅድ መሣካት መሣሪያ ሆነው ቀረቡ። እነዚህ ወገኖች በቅማንቱም ሆነ በዐማራው ዘንድ እጅግ የተከበሩ ሰዎች ነበሩ። አገሪቱ አሉኝ ከምትላቸው የተማሩ እና ያወቁ ከሚባሉት የሚመደቡት እነ አምባሣደር ዘመነኝ ካሰኝ እና ዶክተር ማለደ ማሩ ለትግሬ-ወያኔ የተንኮል ወጥመድ ሰተት ብለው በመግባት፣ የቅማንቱ እና የዐማራው መጠፋፊያ እጄታ ሆነው ቀረቡ። በዚህም ምክንያት እነ ግራዝማች ካሰኝ ዓለማየሁ፤ እማሆይ አበቅየለሽ ይመር እና ሌሎችም ያከሸፉት ቅማንትን እና ዐማራን የመነጣጠል ዓላማ እንደገና ሕይዎት ዘርቶ እንዲያንሰራራ አደረጉት።

የሁለቱን ነገዶች ተወላጆች አብሮ የመኖር ጤናማ ግንኙነት፦ ከሰላም ወደ ብጥብጥ፣ ከፍቅር ወደ ጠብ፣ ከመከባበር ወደ መናናቅ፣ ከመቻቻል ወደ ሆደባሻነት፣ ከአንድነት ወደ መነጣጠል ያሸጋገረውን የነባር አንድነትን የማጥፋት ድርጊት በዚህ ወቅት እንዲፈጸም የተፈለገበት ዋናው ምክንያት ግልጽ ነው። የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን ለመናድ የትጥቅ ትግል በሚያካሂድበት ዘመን የሱዳን መንግሥት ለዋለለት ውለታ፣ ከምዕራብ ኢትዮጵያ ከሰሜን ወደ ደቡብ 1,600(አንድ ሺ ስድስት መቶ) ኪሎሜትር ርዝመት፣ ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ ደግሞ ከ50 እስከ 60 ኪሎሜትር ወርድ ያለው ለም እና ድንግል መሬት ለመሥጠት ስምምነት ማድረጉ ይታወቃል። ይህን ስምምነት ተፈጻሚ ለማድረግ የወሰን መካለያ መሥመር(ችካል) ለመቸከል በሱዳን መንግሥት እና በወያኔ በኩል ዝግጅት እየተደረገ ነው። ይህን ሠፊ የሆነውን የኢትዮጵያ ታሪካዊ መሬት ለማስከበር፣ ዐፄ ዮሐንስ 4ኛ አንገታቸውን ለደርቡሽ የሰጡበት፣ ዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ከቱርክ ጋር የጦርነት ገና የተጫዎቱበት እና ተደጋጋሚ ድል የተጎናጸፉበት፣ በደማችን የቀላ መሬት ነው። የሁለቱ ነገዶች፣ ማለትም፥ የቅማንት እና የዐማራ ነገዶች ተዋጊዎች፣ ለአገራቸው ነፃነት ቀናዒ፣ ለሠፊ መሬታቸው ብቻ ሳይሆን፣ ለጭብጥ አፈሯ ጉጉ የሆኑት ካልተለያዩ እና እርስ በራሳቸው መናቆር ካልጀመሩ፣ ወደ ራሳቸው የውስጥ ጉዳይ ካላዩ፣ የድንበር ማካለሉን ተግባር በቀላሉ ማከናወን እንደማይችል ግልጽ ነው። ለዚህም እንዲረዳው የትግሬ-ወያኔ ለቅማንቱ በዚህ ጊዜ መሬት አካልሎ መስጠቱ በሁለት መንገዶች ጥቅም ያስገኝለታል። አንደኛው ከሱዳን መንግሥት ጋር የሚያደርገው የድንበር መካለል ያለብዙ ችግር ይከናወናል ብሎ ያስባል። ሁለተኛው ደግሞ ሁለቱ ነባር እና ውሕድ ነገዶች በመሬቱ መካለል ሳቢያ በመካከላቸው የነበረው አንድነት ላልቶ እና ጠፍቶ ወደ ጦርነት ይገባሉ። ይህ ጦርነት በቅማንቶቹ ላይ በሚፈጥረው ጫና ምክንያት «ቅማንቶቹ ለሰላማቸው ሲሉ ወደ ትግራይ እንጠቃለል ብለው ጥያቄ አቀረቡ» በሚል ስበብ ሰሜን ጎንደርን ወደ ትግራይ የማጠቃለሉ ዓላማቸው የሰመረ እንዲሆን ያስችለናል ብለው ያስባሉ። ለዚህም መደላድል ይሆናቸው ዘንድ በሰሜን ጎንደር አካባቢ፣ በስሜን አውራጃ፣ በበየዳ ወረዳ የሚገኘውን ታላቁን የአገሪቱን ተራራ ራስ ዳሼንን፣ በስድስተኛ ክፍል የትግራይ ትምህርት ቤቶች የማስተማሪያ መጽሐፍ «በኢትዮጵያ ትልቁ ተራራ ራስ ዳሼን የሚገኘው በትግራይ ክልል ነው» ሲሉ ጽፈው ትውልዱ ከወዲሁ ሰሜን ጎንደር ወደ ትግራይ መጠቃለሉ የማይቀር እንደሆነ እንዲያውቅ አድርገዋል።

ይህ የትግሬ-ወያኔ እቅድ «አልሠራም» የሚባል አይደለም። በአሁኑ ሰዓት የቅማንት እና የዐማራ ነገድ ተወላጅ ባንዳዎች፣ ለትግሬ-ወያኔ አሽከር በመሆን ሕዝብን ከሕዝብ የማነጣጠል ሥራ በመሥራት፣ በሁለቱ ነገዶች ተወላጆች መካከል ደም የማቃባት ድርጊት እየተፈጸመ ነው። በጭልጋ፣ በአርማጭሆ፣ በመተማ፣ በቋራ፣ ወዘተርፈ በሕዝቡ መካከል ጠቡ እየሠፋና እየከረረ በመምጣቱ በየጊዜው የሚታየው የሕዝብ መፈናቀል እና ሞት በግልጽ ያሳያል። ይህን ድርጊት የጎንደር ሕዝብ እና በተለይም የሁለቱ ነገድ ተወላጆች በዝምታ ወይም በችልታ ሊመለከቱት አይገባም። ጉዳዩ እጅግ ተባብሶ በርካታ ሰው ከመፈናቀሉ፣ ከመሞቱ እና ከመሰደዱ በፊት የሁለቱ ነገዶች የአገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች መጠፋፋቱ ሥር ሳይሰድ እና መመለሻው ሳያጥር የወያኔን የመከፋፈል ዓላማ ሊያመክኑ ይገባል። በተለይም የወያኔ እጄታ ሆነው የተሰለፉትን ግለሰቦች እና ቡድኖች በመለየት ከማኅበረሰቡ የማግለል ሥራ ማከናወን ወቅቱ የሚጠይቀው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።
የትግሬ-ወያኔ የሚያካሂደውን ሕዝብን ከሕዝብ የማፋጀት እና የትግራይን ግዛት የማሥፋፋት ተግባር እንዲሠምርለት ተግተው በባንዳነት ከሚያገለግሉት የቅማንት ተወላጆች መካከል ዋነኞቹ የሚከተሉት ናቸው፦
አቶ ካሤ መንግሥቴ፦ ይህ ሰው ቀደም ሲል መምህር የነበረ እና በአሁኑ ጊዜ በጡረታ የተገለለ ነው። መኖሪያ ሠፈሩም ጎንደር ከተማ፣ ልዩ ስሙ ቸቸላ አካባቢ እንደሆነ ታውቋል። ቅማንትን እና ዐማራን ለማለያየት ለሚሠራው የማፋጀት ሥራ የትግሬ-ወያኔ በየወሩ 2,500 (ሁለት ሺ አምስት መቶ) ብር እንደሚከፍለው ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት አረጋግጧል።
(2)     አቶ ተስፋሁን ሙላት፦ በቀድሞው መንግሥት ወታደር የነበረ እና ቦርድ የወጣ፣ በአሁኑ ሰዓት ማራኪ ዩኒቨርሲቲ የሚሠራ የወያኔ ካድሬ እንደሆነ ተረጋግጧል።
(3)     ዶክተር ይግዛው ከበደ፦ የማራኪ ዩኒቨርሲቲ ሐኪም ሲሆን፣ ሁለቱ ነገዶች በነባር አንድነታቸው እንዳይቀጥሉ ከልቡ ሌት ተቀን የሚሠራ ፀረ-ዐማራ እና ፀረ-ኢትዮጵያ ግለሰብ እንደሆነ የደረሱን መረጃዎች ያረጋግጣሉ።
(4)     አቶ ዐባይነህ ዘውዱ፦ ይህ ሰው በትግሬ-ወያኔ የአገዛዝ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ጋይንት አውራጃ ውስጥ ተመድቦ ይሠራ ነበር። በዚያን ወቅት ጋይንት አውራጃ ውስጥ በትግሬ-ወያኔ ለተገደሉት 3 ሰዎች ሕይዎት ተጠያቂ ነው። በዚህ ተግባሩም ከትግሬ-ወያኔ ባገኘው ታማኝነት ዳኛ እንዲሆን አድርገውት አያሌ ሰዎችን በፍርደ-ገምድልነት ወኅኒ የከተተ እና የአያሌዎች ቤት እንዲፈታ ያደረገ ወንጀለኛ ግለሰብ ነው። የትግሬ-ወያኔ መጥጦ መጣል መለያ ባሕሪው ነውና፣ በአሁኑ ሰዓት ይህ ግለሰብ ከዳኛነቱ ተባርሮ በጥብቅና ሥራ እንደሚተዳደር ታውቋል። ሆኖም ለቅማንት እና ለዐማራ መለያየት ተግተው ከሚሠሩት መካከል አንዱ ነው።
(5)     አቶ ከፍያለ ማሞ፦ ይህ ሰው ጭልጋ ውስጥ የሚኖር፣ የከፋፋዩ ቡድን አስኳል ከሆኑት አንዱ ነው። 
(6)     አቶ መልኬ ዓለም፦ ጎንደር ከተማ የአቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ውስጥ የሚሠራ፣ ቅማንትን ከዐማራው ከሚለያዩት ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነ።
(7)     አቶ ብርሃኑ አቃናው፦ በትምህርት መገናኛ መሥሪያ ቤት የሚሠራ እና የከፋፋዩ ቡድን አባል። 
እኒህ ከላይ የተጠቀሱት ግለሰቦች በከብቶች በረት ውስጥ እንደሚያውክ ኮርማ ይመሰላሉ። በአንድ በረት ውስጥ ተዋጊ እና ነሻሪ ኮርማ ካለ የበረቱ ከብት በሙሉ ሰላም እንደማያገኝ ይታወቃል። የበረቱ ሰላም መሆን የሚረጋገጠው ተዋጊው ኮርማ ከበረቱ ሲነጠል ብቻ ነው። የቅማንት እና የዐማራ ነገዶችም ሰላማቸው የተረጋገጠ የሚሆነው በመካከላቸው ያሉ የትግሬ-ወያኔን የጥፋት ዓላማ አራማጆች «አውቀንባችኋል» በማለት ከውስጣቸው ማግለል ሲችሉ ብቻ ነው። እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ግለሰቦች እና በውስጣቸው ያደራጇቸውን አገር እና ትውልድ አጥፊ ግብረ-አበሮቻቸውን፣ የጎንደር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ «ጥቁር ውሻ ውለዱ» ብሎ ከማውገዝ አልፎ፣ ከማንኛውም ማኅበራዊ ግንኙነት ሊያገልላቸው ይገባል። በመሆኑም የቅማንቱን እና የዐማራውን ነባር አንድነት በዳበረ መልኩ እንዲቀጥል ማድረግ ለነገ የሚባል ተግባር አይደለም። ስለዚህ ማኅበረሰቡ በግልፅ ከማውገዝ አልፎ፣ ከመጥፎ ከፋፋይ ተግባራቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀው ግዴታ ነው። ይህ ካልሆነ ግን ግለሰቦቹ መበጥበጣቸውን፣ የሰላማዊ ዜጎችን ሕይዎት እና ንብረት ከማጥፋት አይቆጠቡም። ለዚህም ሰላምን እና አንድነትን ፈላጊው የጎንደር ሕዝብ እነዚህን እና መሰሎቻቸውን ነቅቶ በመጠበቅ፣ በተለመደው ጀግንነቱ አገራዊ ዳርድንበሩን ከቆረሳ እንዲከላከል ጥሪያችን በታላቅ አክብሮት እናቀርባለን።
ዐማራን ከፈፅሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃልኪዳን ነው!
ኢትዮጵያ በታማኝ እና ቆራጥ ልጆቿ መስዋዕትነት ለዘለዓለም ፀንታ ትኖራለች!


Monday, December 7, 2015

የሸዋ ኦሮሞ አማሮችን እየጨፈጨፈና እየመነጠረ ነው(ኢሰመጉ)

የሸዋ ኦሮሞ አማሮችን እየጨፈጨፈና እየመነጠረ ነው(ኢሰመጉ)
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ከዘመነ ሚኒሊክ እስከ ደርግ ከየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት ተወላጆች በበለጠ በሃገሪቱ ላይ የስልጣንና የፈላጭ ቆራጭነት ሚና ባለቤት የነበረው የሸዋ ኦሮሞ ጨቋኝና ወራሪ በሚል አማራን እየጨፈጨፈ ነው። ይህ የኢሰመጉ ሪፖርት በሸዋ የሚኖሩ አማሮችን አሳዛኝ የመከራ ህይወት ፍንትው አድርጎ ያጋለጠ ነው።

“ብልታችንና የሴቶቻችን ጡት በፒንሳ እየተጠመዘዘ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ከተሰቃየን በኋላ ተባረናል” ከምዕራብ ሸዋ የመጡ የአማራ ተወላጆች
December 3, 2015
ሰሚ ያጣው የሰመጉ ጩኸት
( በሙሉቀን ተስፋው )



ሰብአዊ መብት ጉባኤ ጽሕፈት ቤት ስደርስ ቤቱ በጋዜጠኞችና በውጭ ዲፕሎማቲክ ቡድን ተወካዮች ተሞልቶ ነበር። ሰመጉ “ብሔር ተኮር ማፈናቀልና እንግልት እንዲሁም በልማት ስም በዜጎች ላይ የሚፈጸም የማፈናቀልና የንብረት ማውደም በአስቸኳይ ይቁም!” በሚል ያዘጋጀውን መግለጫ ለመስማት ነበር። ከአፋር ክልል መንግሥት የቴምር ዛፍ የወደመባቸውንና በምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ሀብት ንብረታቸው ተቃጥሎ የተባረሩ አማራ አርሶ አደር ተወካዮችን ጭምር በማስመጣት ምስክርነት እንዲሰጡ ፊት አካባቢ ተቀምጠዋል። የተለያዩ የሰመጉ የሥራ ኃላፊዎች መግለጫውን ካነበቡ በኋላ ከሁለቱም ቦታ የመጡ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የነበረውን ሁኔታ ሲናገሩ የሚያሳዝንም ተስፋ የሚያስቆርጥም ነበር።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ በእርሻ ሥራ የሚተዳደሩ የአማራ ተወላጆች የተለያየ ዓይነት ሰብሎችን በመዝራት ራሳቸውን፣ ቤተሰባቸውንና ክልሉን በአጠቃላይ ለአገሪቱ ገበያ የሚቀርብ ምርት በማምረት የሚታወቁ ውጤታማ አርሶ አደሮች ነበሩ። ይሁንና በአካባቢው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የጸጥታ ኃፊዎች እነዚህን አርሶ አደሮች “እናንተ የዚህ አካባቢ ተወላጅ ሳትሆኑ ሀበት እያፈራችሁ የአካባቢው ተወላጅ ግን ከእናንተ ያነሰ ገቢ ያላቸው ናቸው፤ ይህን ገቢ ያገኛችሁት በእኛ መሬት ላይ ነው፤ ስለዚህ የክልሉ ተወላጆች ባለመሆናችሁ ክልሉን ለቃችሁ ውጡ” በማለት ንብረታቸውን በተለያየ ጊዜ በመንጠቅ እነዚህን አርሶ አደሮች በተለያየ ጊዜ ለእስራት ዳገዋቸዋል። የአካባቢውን ሕዝብም “በእናንተ መሬት ነው ሀብት ያፈሩት” እያሉ ጥላቻና ግጭትን ሲሰብኩ እንደቆዩ በሰመጉ በ136ኛ መግለጫና ምስክርነታቸውን በሰጡ አርሶ አደሮች ተነግሯል።


ምስክርነታቸውን ከሰጡት መካከል በአካባቢው ተወልዶ ያደገው አቶ አለሙ አስፋው “በ1996 ዓ.ም. በዞኑ መዳሉ ወረዳ 52 እንዲሁም በ2002 ዓ.ም. ደግሞ በዳኖ ወረዳ 152 የአማራ ቤትና ንብረት ሲቃጠል ምንም የተወሰደ እርምጃ የለም” ሲል ከዚህ በፊትም ስለነበረው ብሔር ተኮር ጥፋት ይናገራል። የሰመጉ መግለጫና ገበሬዎቹ እንደሚያረጋግጡት መጋቢት 27 ቀን 2007 ዓ.ም. አቶ ዘውዱ እንዳለ የተባለ የኦሮሞ ተወላጅ ተገድሎ ይገኛል። ተገድሎ የተገኘውን ገዳይ ሁሉም ኀብረተሰብ ወንጀለኛውን ለማገኘት እየተረባረበ ባለበት ሰዓት “ይህ ግድያ የተፈጸመው በአማራ ብሔር ተወላጆች ነው” በማለት የኖኖ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ኃይሉ ድሪባ፣ የኖኖ አሎ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ ጎሳየ ገችና መቶ አለቃ ገነነ በየነ የተባሉ የፖሊስ አባላት የቀበሌና የፖሊስ አባላትም በማስተባበር የአካባቢው ሕዝብ በአካባቢው በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ እንዲነሳሳ በማድረግ ሚያዚያ 9 ቀን 2007 ዓ.ም. 85 አርሶ አደር አባውራዎችን ለእስራት ከዳረጓቸው በኋላ ቅዳሜ ማለትም ሚዚያ 10 ቀን 2007 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡00 ሰዓት አካባቢ ዘር በመምረጥ የአማራ መኖሪያ ቤትና ንብረት ነው ያሉትን እየመረጡ በእሳት እንዲቃጠል አድርገዋል።

የታሰሩትን ወንዶችና ሴቶችም ብልታቸውንና ጡታቸውን በፒንሳ እየጠመዘዙ ቤቱን ለሚቃጠልበት የሚውል ለነዳጅ በማለት ከእያንዳንዳቸው 300 ብር ተቀብለዋቸዋል። ከ27 ገበሬዎች ብቻ 8100 ሰብስበዋል። ገበሬዎቹ ሲወጡ ሀብት ንብረታቸውም ሆነ የነበራቸው ነገር ሁሉ ወድሞ ነው ያገኙት። በንግድ ሥራ የምትተዳደር ወ/ሮ ጽጌ የተባለች የአካባቢው ነዋሪ የነበረውን ሁኔታ ስትገልጽ “ቤታቸው ሲቃጠል ልብሳቸውን ሁሉ አጥተው ራቁታቸውን ደብቂን እያሉ ወደኔ በርካታ ልጆች መጡ። ማጀት አስገብቼ ወደ ፖሊስ አዛዡ ቢሮ በመሄድ ‹ኧረ ተው በሰው ስቃይ እንዲህ አትደሰት?› ስለው ገና አንቺም ትቃጠያለሽ አለኝ” በማለት የነበረውን ሁኔታ ትናገራለች።


አቶ ዓለሙ አስፋው በበኩላቸው “የሚሊሻ ኮማንደር ነኝ። በጊዜው ሰላሳ ጎራሽ ክላሽ ይዤ ነበር። የፖሊስ አዛዡ አቶ ደመና ግዘውን ሲገድላቸው ቆሜ እየተመለከትኩ ‹እንዴ ተው ሕግ ባለበት አገር› ስለው ‹አማራ እኮ ነው አይመለከትህም› አለኝ፤ በያዝኩት ጠመንጃ አይደለም እርሱን 30 ሰውም መግደል እችል ነበር፤ ግን ያን ባደርግ የሁሉም ችግር መንስኤው እርሱ ነው ስለምባል እያነባሁ ዝም አልኩ፤ እኔ ሰላም ለማስከበር ላይቤሪያ ድረስ ሄጃለሁ፤ ሆኖም በአገሬ ሰላም የለም። የሰው አገር ሰላም ሳስከብር በአገሬ ላይ ግን ስለሰላም መናገር እንኳን አልቻልኩም” ሲል በምሬት ገልጿል።


አቶ ደመና በሚያዚያ 12 ቀን 2007 ዓ.ም. ልጃቸውን ሊድሩ ዘመድ አዝማድ ሁሉ ተጠርቶ ዝግጅቱ ሁሉ አልቆ ነበር። ሆኖም የልጃቸውን ደስታም ሳይመለከቱ ሰርጉ አንድ ቀን ሲቀረው በመንግሥት የፖሊስ አዛዥ ተቀጥቅጠው ሞተዋል። የሟች ወንድም “ወሊሶ ሆስፒታል ሳይደርስ ነው የሞተው፤ የግፋቸው ግፍ ራሳቸው የገደሉትን አስከሬን ለምርመራ አዲስ አበባ መላክ አለብን ብለው 6000 (ስድስት ሽህ ብር) አምጣ አሉኝ። የለኝም ስላቸው አስከሬኑን አውላላ ሜዳ ላይ አስቀምጠው መውሰድ እንደማልችል ተነገረኝ። አስከሬኑ ሜዳ ላይ ፈራርሶ ከሚቀር በማለት ተበዳድሬ ሰጠው። የራሴን እንኳ እንዳልሰጥ ያለኝን በሙሉ አቃጥለውታል። የግፍ ግፍ ነው የተሰራብን” በማለት በእንባ ነው የተናገሩት።

ሰመጉ በ136ኛ መግለጫው የአንድ ሰው ማለፉን፣ 10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን፣ 99 የእሳር ክዳን ቤቶች በእሳት መቃጠላቸውንና 25 የቆርቆሮ ክዳን የመኖሪያ ቤቶች በእሳት መውደማቸውን ገልጿል። የአርሶ አደሮቹን መኖሪያ ቤትና ንብረት ቃጠሎ ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች፣ ሕጻናትና አቅመ ደካሞች የሚገኙባቸው ተፈናቃዮች በአካባቢው በመሰደድ ወደ ደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሸጌ ወረዳ ድንኳን ውስጥ ተጠልለው ሲረዱ መቆየታቸውንም አስታውሷል። ሰመጉ በጋዜጣዊ መግለጫው ጥፋት የፈጸሙት የመንግሥት አካላት ምንም አይነት ሕጋዊ እርምጃ እስካሁን እንዳልተወሰደባቸውና የተፈናቀሉ ገበሬዎችም ተመልሰው በሰላም መኖር ለመቻላቸውን ጠቅሷል። ይባስ ብሎም ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሮንድ እንዲጠብቅ የተመደበውን አቶ አቢ ተክለማርያም በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል። ገበሬዎቹ እንደሚናገሩት ከሚለብሱት ልብስ ጀምሮ በጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ ያስጠጓቸው የአካባቢው ሰዎች እንደሰጧቸውና ተመልሰው ግን ለመኖር እስካሁን አዳጋች እንደሆነባቸው ነው ለዝግጅት ክፍላችን የገለጹት።


በአዲሱ ዓመት ዋዜማ በጥይት ተደብድቦ የተገደለውን አቶ አቢን ተክለማርያምን አገዳደል በተመለከተ ሲናገሩ “የሌሊት ጥበቃ ሮንድ ከአራት ኦሮሞዎች ጋር ተመደበ። ሆኖ ተብሎ እንደዚህ እንደተመደበ የሚያውቀው ነገር አልነበረም። ነገር ግን በጥይት ተደብድቦ ተገደለ” በማለት የተሰራውን ሴራ ይገልጻሉ። እንደአርሶ አደሮች ገለጻ ከሆነ ይህን በዋናነት ሲያስተባብሩ የነበሩ የኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ባለሥልጣናት ምንም ዓይነት ሕጋዊ እርምጃ አልተወሰደባቸውም። አርሶ አደሮቹም የወደመባቸው ንብረት ሊሰጣቸው ቀርቶ ተመልሰው እንኳን ሕጋዊ መሬታቸውን ለማልማት እንዳልቻሉ ነው የሚገልጹት። በተያያዘም በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ ዋሙሌ ቀበሌ በስኳር ኮርፖሬሽን ለሸንኮራ አገዳ ልማት በሚል የቴምር ዛፍ የወደመባቸው ከፊል አርብቶ አደሮችን ሕይወት አመሰቃቅሏል። የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት የነዋሪዎቹን ፈቃደኛነት ሳይጠይቅ ካሳም ሳይፈጽም ከ8300 በላይ የቴምር ዛፎች እንደተመጠሩና ነዋዎቹም ችግር ላይ መሆናቸውን ሰመጉ በ138 ልዩ መግለጫው ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ቢሆንም እስካሁን ድረስ ችገሩ አለመቆሙን ነው በጋዜጣዊ መግለጫው ይፋ የተደረገው። ከአፋር ክልል የመጡት ነዋሪዎች እንደሚሉት “አካባቢውን ለቀን ወደ ጅቡቲና ሶማሊላንድ እንድንሰደድ ይፈለጋል። እኛ ግን የምንሄድበት የለንም። የምንመገበው ቴምር ነው፤ ለቤት መሥሪያና ለመኝታም የምንጠቀመው የቴምር ዛፍን ነው፤ ሆኖም አሁን ሁሉም እንዳልነበር ሆኗል” ሲሉ ገልጸዋል። ሰመጉ በ138 ልዩ መግለጫ የአፋር ባህልን መሠረት በማድረግ አንድ የቴምር ዛፍ ሲቆረጥ ካሳ የሚሰጠው ሰባት የቁም ከብት እንደሆነ ጠቅሷል። ሆኖም ነዋሪዎቹ እስካሁንም ምንም ዓይነት ክፍያ ካለማግኘታውም ባሻገር አቤቱታቸውንም የሚሰማቸው አካል ማጣታቸውን ጭምር በምሬት ገልጸዋል።


(ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው ሰመጉ ሕዳር 16 ቀን 2008 ዓ.ም የሰጠውን ጋዜጣዊ መግለጫ እንዲሁም 136ኛና 138 ልዩ መግለጫዎቹን መሠረት በማድረግ ነው)



Wednesday, December 2, 2015

አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም?

ጌታቸው ኃይሌ

መግቢያ፤


መጀመሪያ ለመግቢያ ያህል፥ “ዘመድ” የሚለውን ቃል እንዴትና ለምን እንደተጠቀምኩበት ላስረዳ። “ዘመድ” ማለት “ወገን” ማለት ነው። በእንግሊዝኛ “kin, family, tribe” ማለት ነው። በየሊቃቸው የሚመሩ የተለያዩ የመላእክት ሠራዊት “ዘመድ” ወይም “ነገድ” ነው የሚባሉት”--ዘመደ መላእክት፣ ነገደ መላእክት። ሌሎች ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው መጠሪያዎች “ቤት” (ቤተ አምሐራ)፣ “ጎሳ” (የጉጂ ጎሳ)፣ “ዘር” ናቸው። ዛሬ ደግሞ “ብሔረ ሰብ” የሚለው መጠሪያ ነግሧል። ከነዚህ ስሞች ውስጥ አንዳንዶቹን የሚጠሏቸው ሰዎች አሉ። “ዘመድ” የሚለውን መጠሪያ የመረጥሁት ዝምድና ስለሚያስተሳስብና አምላክ የሰውን ልጅ ከመላእክት ደረጃ መመደቡን ለማስታወስ ነው። ቅዱስ ዳዊትም ጌታን “የሰውን ልጅ ከመላኮችህ ብዙ አላሳነስከውም” ይለዋል። ሰው እንደ መላእክት ክቡር ነው። መላእክት የተፈጠሩት እግዚአብሔርንና ሰውን ለማገልገል ነው። ዓለም ራሷና በውስጧ ያሉት ሁሉ የተፈጠሩት የአዳምን ልጆች ለማገልገል ነው። ክርስትና እንደሚያስተምረን አምላክ ሰው ሁኖ ለስቅላት የደረሰው የሰውን ልጅ ከጥፋት ለማዳን ነው። የመላእክት ሠራዊት የተለያዩ ቢሆኑም፥ ፍጥረታቸውና ደረጃቸው እኩል ነው። የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠራዊት ከሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሠራዊት አይበልጡም አያንሱም። ዘመደ መላእክት ይተባበራሉ እንጂ አይጣሉም። አንዱ ሊቅ ልብለጣችሁ ቢል ከነሠራዊቱ ተሽቆልቁሎ እንጦርጦስ ወርዷል። ዘመደ ኢትዮጵያውያንም አይበላለጡም አይተናነሱም። የሚያበላልጠን ካለ የኛም የእግዚአብሔርም ጠላት፥ የሳጥናኤል ወዳጅ ነው። የሰውን ልጅ በሚነካ ጉዳይ ላይ በዋልን ቍጥር፥ በተለየ ልግዛ የሚሉ ባለጡንቾች፣ ማንን እንደሚነኩ ያስተውሉ። የሰው ልጅ የሚያንከባክቡት እንጂ የሚደፍሩት አይደለም።

የሞኞች ወይስ የአላዋቂዎች ጥያቄ፤

“አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም?” የሚለው ጥያቄ የሞኞች ነው። ሞኝ የሚባለው ዓይን እያለው፥ ሰው ሁሉ የሚያየውን ግዙፍ ነገር የማያይ፥ ሰው ሁሉ የሚያውቀው የወልና የጋራ ዕውቀት እንግዳ የሚሆንበት ነው። ሞኝ ዛሬ የተወለደ ይመስል የሚያጋጥመውን ነገር ሁሉ ሰው ሳይጠይቅ በራሱ አይደርስበትም። እውነት እንዲህ ያለ ሰው አለ? “አማራ የሚባል ዘመድ አለ ወይስ የለም?” ብሎ የሚጠይቅ ሰው ካለ እሱ አንዱ ነው።

ቃል ያንድ ነገር መጠሪያ ነው። ለምሳሌ፥ “ዛፍ”፣ “ድመት”፣ “ቤት” የምንለው በነዚህ ቃላት የሚጠሩ ነገሮች ቢኖሩ ነው። ባይኖሩ ኖሮ ቃላቱም አይኖሩም ነበር። አንዳንድ ቋንቋዎች ውስጥ ያሉ ቃላት እሌላው ቋንቋ ውስጥ የማይኖሩት በእነዚያ ቃላት የሚጠሩት ነገሮች የዚያ ቋንቋ ተናጋሪዎች ዘንድ ስለሌሉ ነው። ለምሳሌ bird በአማርኛ “ወፍ” ነው። ወፍ የተባለችው ፍጥረት ኢትዮጵያ ስላለች “ወፍ” የሚለው መጠሪያ ወጣላት። ለ kangaroo ግን አማርኛ የለንም። የሌለን kangaroo የሚባል ፍጥረት በሀገራችን ስለሌለ ነው። በአንጻሩ፥ መዝገበ ቃላት ውስጥ ያሉ ቃላት በሞላ ላለ እና ለታወቀ ነገር መጠሪያ የተፈጠሩ ናቸው። በመፈጠር የቅደም ተከተል ሂደት፥ የሚጠራው ነገር ይቀድማል፤ መጠሪያው ይከተላል። ውይይቱን ሰፋ ለማድረግ፥ መጽሐፋችን እንደሚለው፥ አባታችን አዳም ፍጡራኑን በዕብራይስጥ ላም፣ በሬ፣ ርግብ፣ ዋኖስ፣ ዝሆን፣ አንበሳ፣ ነምር፣ በሬ፣ ግስላ፤ ንስር፣ ወፍ ብሎ የጠራቸው ተፈጥረው ስላገኛቸው ነው።
የሌለ ነገር ስም ስለማይወጣለት መጠሪያ ስም ከሚጠራው ነገር ቀድሞ ተፈጥሮ አያውቅም። “ምናልባት አንዳንድ ነገሮች የተፈጠሩ ወይም ድንገት የተገኙ እንደሆን መጥሪያ ይሆናሉ” ተብለው የተከተቱ ቃላት ወይም ስሞች የሉም።

2
እርግጥ አንዳንድ ሰዎች “ወንድ ልጅ የወለድኩ እንደሆነ እገሌ (አሰፋ)፣ ሴት ልጅ የመለድኩ እንደሆነ እገሊት (አልማዝ) እላታለሁ” ይሉ ይሆናል። እነዚህም ስሞች ቢሆኑ፥ ለታሰቡት ልጆች በመጠሪያነት የሚያገለግሉት መጀመሪያ ልጆቹ ከተወለዱ በኋላ ነው። ልጆቹ ካልተወለዱ ላልተወለዱት ልጆች ስሞች አይሆኑም። በአጭሩ በአንድ ቋንቋ ውስጥ ያሉ ቃላት ሁሉ ላሉ ነገሮች መጠሪያ ናቸው፤ ቃል ካለ ነገር አለ።
አማራ አለ፤
እንዲህ ከሆነና “አማራ” የሚል መጠሪያ ቃል ካለ ተጠሪ አለ ማለት ነው። ተጠሪው ዘመደ አማራ ነው። “አማራ የሚባል ዘመድ የለም” ከተባለ ስሙ የተፈጠረው ማን እንዲጠራበት ነው? አማራ የሚባል ዘመድ ለመኖሩ ዋናው ማስረጃ መጠሪያ ስሙ መኖሩ ነው። አማሮች እንደ አግዓዝያን፣ እንደ ሐርላ ስማቸውን ትተውልን ሊጠፉ ይችላሉ፤ አሁን ግን አሉ።
ለአማሮች መኖር ሁለተኛው ማስረጃ፥ አማራ ነን የሚሉ ሰዎች መኖራቸው ነው። ቍጥራቸውም ቀላል አይደለም። አማራውን “አማራ ነኝ ካልክ የለህም (You do not exist)” አይሉትም። ቢሉትም ይኖራል።
ለአማሮች መኖር ሦስተኛው ማስረጃ አማራው የገዢ ዘመድ ነው እየተባለ ከመንግሥቱ ኃይለ ማርያም እስከ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ባለው የጨለማ ዘመንና የጨለማ ግዛት መጠቃቱ ነው። ይህን ጽፉፍ በማረቅበት በአሁኑ ሰዓት ሳይቀር በኢትዮጵያ መንግሥት አበረታችነት አማራው ተለይቶ እየተመታ ነው--ያለውን እንዳይኖር ለማድረግ፤ የሚያስፋፋውን ኢትዮጵያዊነት ለማቆም።
እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የብዙ አዝማድ አባል ነው--የጾታ፣ የቋንቋ፣ የትውልድ። አባልነቱ በራሱ ምርጫ የመጣ ስላይደለ ሊክደውም ሊያፍርበትም አይገባም። ለምሳሌ፣ ሴት ወይም ወንድ መሆን ሊካድ አይቻልም፤ ሊታፈርበትም የማይገባው እግዚአብሔር የመረጠው ጾታ ስለሆነ ነው። ዘመድም እንደዚያ ነው። የጾታ ባሕርይ አለው፤ አማራነት፣ ጉራጌነት፣ ዶርዜነት የማይደበቅ፥ የማይካድና የማይታፈርበት ነው።

ግን ጾታና ዘመድ ትልቅ የሚለያዩበትም ባሕርይ አላቸው። ጾታ ለብዙ ከፍተኛ ጉዳይ መመዝገብ ሲኖርበት ዘመድን በተለይ በመንግሥት ደረጃ መመዝገብ ለተንኮል ነው። ጾታን ለይቶ ማሳወቅ ለጥቅም ነው፤ ለሐኪም ቤት፥ ለመጸዳጃ ቤት፣ ለጋብቻ፥ ለልብስ ሰፊ፥ ወዘተ. በመታወቂያ ወረቀት ላይ ሳይቀር በወል ሊታወቅ ያስፈልጋል። ልብስ ለመግዛት ወደልብስ ተራ ስንሄድ “የወንዶች”፣ “የሴቶች”፣“የሕፃናት” ክፍል እናገኛለን። ዘመድና ሃይማኖት ግን የግል ናቸው። በልብስ ሱቅ ውስጥ “የአማራ”፣ “የቱለማ” ፣ “የጉራጌ” . . . ክፍል አናይበትም። አንድ ኢትዮጵያዊ የየትኛው ዘመድ እንደሆነ እንኳን በመታወቂያ ወረቀት ላይ መስፈር ቀርቶ በተራ ውይይትም ቢሆን ለባህል ካልሆነ በቀር ሌላ ጥቅም የለውም። በባህል ረገድም ቢሆን፣ የአማራን ዘፈን ትግሬው ይዘፍነዋል፤ የከረዩንና የጉራጌውን ጭፈራ መንዜው ያሳምረዋል። ግን ሴት ያለ ተፈጥሮዋ ወንድ መሆን፣ አትችልም ወንዱም ሴት መሆን አይችልም።

የኢትዮጵያዊ መታወቂያ(ዎች)፤
“አማራ አለ ወይስ የለም?” ስለሚለው ጥያቄ አንድ ነገር ማወቅ ይኖርብናል። ዕውቀቱ ምናልባት ሞኙን ጠያቂ ከሞኝነት ያድነው ይሆናል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሁለት የባህል መታወቂያ (identity) ሲኖረው አማራው በተለየ መታወቂያው አንድ ብቻ ነው። ባለሁለት መታወቂያዎች አንዱ መታወቂያቸው የጎሳቸው ባህል ሲሆን ሁለተኛው መታወቂያቸው የመንግሥቱ ባህል ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በተስፋፋበት ጊዜ፥ ባህሉ (ሥርዓቱና አስተዳደሩ) በታሪክ አጋጣሚ በአስፋፊዎቹ ቋንቋ (በአማርኛ) ተገልጿል። የመንግሥቱና የተከታዮቹ መታወቂያ አማርኛ
3
ሆኗል። የአንድ መንግሥት ባህል በአንድ ቋንቋ መገለጽ በየትኛውም ታሪካዊ ሀገር የተፈጸመ ነው። በኢትዮጵያና በሌሎችም ሀገሮች እንዴት እንዲህ እንደሆነ ታሪኩን እናውቀዋለን፤ እዚህ እንዳንተቸው ንባብ ሰልቺ ያበዛል።
የጎሳ ወይም የዘመድ ባህል ከቤተ ሰብ ይወረሳል፤ የመንግሥት ባህል ከቤተ መንግሥት ይወጣል። ሁለቱንም የሚጐናጸፉ ኢትዮጵያውያን ባለሁለት መታወቂያዎች ናቸው። የመንግሥቱ ባህል መገለጫ ወይም መታወቂያ አማርኛ ነው ብያለሁ። የጎሳን (የዘመድን) ቋንቋና የመንግሥቱን ቋንቋ (አማርኛን) የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን/ት ባለሁለት መታወቂያዎች ናቸው (ጉራግኛ-አማርኛ፤ ትግርኛ-አማርኛ፤ ሱማልኛ-አማርኛ፤ ወዘተ.)። የመንግሥቱን ባህል ብቻ ይዘው የሚጓዙ መታወቂያቸው አንድ ብቻ ሆኗል (አማርኛ ተናጋሪዎች)። የታሪካችንን ሂደት ለተመለከተው አማርኛ ተናገሪዎች ሁለት ዓይነት ናቸው፤ (ሀ) “xxx-አማርኛ”፤ (ለ) “አማርኛ-አማርኛ” ልንላቸው እንችላለን። (ሀ) “xx-አማርኛ” የምላቸው አማራነታቸው “ከጉራግኛ-አማርኛ”፣ ወይም “ከትግርኛ-አማርኛ”፣ ወይም “ከወላይታኛ-አማርኛ” ወዘተ. የሆኑትን ነው። ጥንቱ ግንዳቸው ጉራግኛ፥ ትግርኛ፥ ወላይትኛ፥ ወዘተ. ነበር፤ አሁን ግን አማሮች ሆነዋል ለማለት ነው። (ለ) “አማርኛ-አማርኛ” የምላቸው ጥንቱን በግንዳቸው አማሮች የነበሩትንና መንግሥቱን ለመከተል አዲስ ቋንቋ ማወቅ ያላስፈለጋቸውን ነው። ዛሬ እነዚህ ሁሉም (ሀ እና ለ) እኩል አማሮች ይባላሉ፤ (ሀ) የቤተ ሰብ ቋንቋ ያልወረሱ አማሮችና (ለ) የወረሱ አማሮች ።

በይበልጥ ለማብራራት፥ ዛሬ አማርኛ ብቻ የሚናገሩ ባለአንድ መታወቂያዎች ናቸው። ከእነሱ ውስጥ ብዙዎቹ እንደ ሌሎቹ ሁሉ ባለሁለት መታወቂያዎች ነበሩ (ሀ)። በታሪክ ሂደትና በዘመን ብዛት የጎሳቸውን መታወቂያ እየተዉ የመንግሥቱን መታወቂያ ብቻ ይዘው ቀሩ፤ ከባለአንድ መታወቂያዎች ጋር አንድ ሆኑ። መንግሥት አማርኛን መታወቂያው ከማድረጉ በፊት የጎሳ መታወቂያቸው አማርኛ የነበረ ኢትዮጵያውያን ነበሩ (ለ)። እነዚህ ኢትዮጵያውያን አማርኛ የመንግሥቱ መታወቂያ ስለሆነ በጎሳ መታወቂያቸው ላይ የመንግሥት መያወቂያ ባህል አልተጨመረባቸውም። ቍጥራቸውም ቀላል አልነበረም። መጀመሪያውኑ ባህላቸውን የመንግሥቱ ባህል ያደረገው የቍጥራቸው ትልቅነት ነው። ባለሁለት መታወቂያዎች የነበሩም የጎሳ መታወቂያቸውን እየተዉ የመንግሥቱን ባህል መታወቂያቸው ያደረጉም (ሀ) ጥቂቶች አይደሉም። እነዚህ በታሪክ ሂደት የመንግሥቱን ባህል መታወቂያቸው ያደረጉ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው ባለሁለት መታወቂያ የነበረ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

እነዚህን የጎሳ መታወቂያቸውን ትተው የመንግሥቱን ባህል ብቻ መታወቂያቸው ያደረጉትን ኢትዮጵያውያን በዘመድ፣ በቤት፣ በብሔር ረገድ ማን እንበላቸው? ከጥንት ተነሥተን አማሮች እንዳንላቸው ጥንታቸው አማራ አይደለም። “አማራ የለም” የሚሉ ሰዎች ዋናው ምክንያታቸው ይህ ነው። የአማርኛ መስፋፋትና የመንግሥቱ ጥንካሬ አማራ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው። መንግሥቱን በማቀፍ አማራ ያልነበረው ሕዝብ አማራ ሆነ። ዛሬ በትውልድ ከአማራው ቤተሰብ በመጡ አማሮችና ከሌላ ቤተሰብ በመጡ አማሮች መካክል ምንም ልዩነት የለም። ማን ከየትኛው ጥንት (origin) እንደመጣ እንኳን አይታወቅም። ሁሉም ከየመጡበት መጥተው የመንግሥቱን መታወቂያ እኩል መታወቂያቸው አድርገዋል።
ዘመድ መለወጥ ወደ አማራነት መዛወር ብቻ አይደለም፤ ከረዩ ያልነበሩ ብዙ ኢቱዎች ከረዩ ሆነዋል። አግዓዝያንና ሐርላዎች ጠፍተዋል፤ ጠፉ የምንለው ስለጠፉ ሳይሆን አጠገባቸው ወዳለው ጎሳ ስለተዛወሩ ነው። ግን በሁለቱ የለውጥ ዓይነቶች መካከል ያለው ልዩነት ትልቅ ነው። አንዱ ለውጥ የኢትዮጵያ መንግሥት (የአገር-አቀፍ) አባል ለመሆን ሲሆን፥ ሁለተኛው ለውጥ የጎሳ (የአካባቢ-አቀፍ) አባል ለመሆን ነው። የመንግሥቱ መታወቂያ አማርኛ የሆነው የአፄ ይኩኖ አምላክ ቤተ ሰብ የመንግሥቱን ሥልጣን በትልቁ ሕዝብ (ቋንቋው አማርኛ በሆነው) ላይ ስለመሠረተ ነው።
4
የወያኔ መንግሥት የመንግሥቱ ቋንቋ እንዳይስፋፋ ብዙ ጥረት ሲያደርግ ይታያል። የቋንቋ አገልግሎት መግባቢያ ከሆነና አማርኛ ያንን አገልግሎት ለአፍሪቃ ቀንድ ሲሰጥ ዘመናት ከአለፉ በኋላ ዛሬ አገልግሎቱን መግታት ምን ጥቅም ለማግኘት ነው? በአማሮቹ ቀንተው እንደሆነ፥ የቋንቋ ባለቤት ተናጋሪው ግለሰብ ነው፤ ባለቤቱ ጎሳው መሆኑ ከቀረ ዘመናት አልፈዋል። ማለት፥ የአማርኛ ባለቤት የጥንቶቹ አማሮች ብቻ ከሆኑ ታሪክ ሆኖ ከቀረ ዘመናት አልፈዋል። አማሮች አሉ፤ ግን አማራ የሚባል የአማርኛ ባለቤት ከግንዱ ወጥቶ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ጥንታዊ ጎሳ ግን የለም። ያለው የመንግሥትን ባህል (ኢትዮጵያዊነትን) ብቻ ባህሉ ያደረገ 

“አማራ” የተባለ ዘመድ ነው።
ባይታሰብበትና ክፋት ስለሌለበት ነው እንጂ የዛሬዎቹ አማሮች “አማራ” መባልም አልነበረባቸውም። ባይገርመን ጎጃም፥ ጎንደር፥ ሸዋ፥ ወሎ በከፊል በመሠረቱ አማራ አይባሉም ነበር። “አማራ” (አምሐራ) እንደ ጎጃም፥ እንደ ጎንደር፥ እንደ ሼዋ የክፍለ ሀገር ስም ነበር። የነዚህ ክፍለ ሀገር ነዋሪዎች ሁሉ እንዴት አማራ እንደተባሉ የሚገመት እንጂ በማስረጃ የተደገፈ ዕውቀት የለንም።
ዛሬ ሁሉም ማኵረፊያ (ሌላ መታወቂያ) ሲኖራቸው፥ አማሮች ሁሉን ትተው ከተከተሉት ከመንግሥቱ (ከኢትዮጵያዊነት) በቀር ሌላ መታወቂያ የላቸውም። ወያኔዎች አንድ ቦታ ከለሏቸው እንጂ የነሱ ክልል የኢትዮጵያ መንግሥት የተዘረጋበት ነው። ኢትዮጵያ እንዳትበታተን የሚፈልጉት ክልላቸውና መታወቂያቸው ስለሆነች፥ ራሳቸውንና አባቶቻቸው የመሠረቷትን ኢትዮጵያ ከመጥፋት ለማዳን ነው። መታወቂያቸው መላዋ ኢትዮጵያ ብቻ ስለሆነች፥ በክልል መወሰንን ባለሁለት መታወቂያ ኢትዮጵያውያን ሲቀበሉት አማሮች አይቀበሉትም። የወያኔ መንግሥት የዛሬዎቹን አማሮች የሚያጠቃው ኢትዮጵያን በጎሳ ለመበታተን የሚያደርገውን ጥረት አንቀበልም በማለት እንቅፋት ስለሆኑበት ነው። የአማራው ቍጥር እንዲቀነስ፥ የተረፈው ለሀገር አንድነት ድርና ማግ መሆኑ እንዲያቆም ከየቦታው እያሶጡ አንድ ቦታ እንዲታጎር፥ ሙሉ ዘመቻ ዘምተውበታል።

የወያኔ የሐሰት ክስ፤

ወያኔዎች አማሮችን፥ “ኢትዮጵያዊነት ኢትዮጵያዊነት የምትሉት የመንግሥቱ ባህል የናንተን ባህል ስለያዘ ነው” ይሏቸዋል። የዚህ ወቀሳ ምንጩ ታሪክ ከአለማወቅ የመጣ ወይም አንገት ለማስደፋት የታቀደ ተንኮል ነው። የሆነው ግን ወያኔዎቹ እንደሚሉት ብቻ ሳይሆን፣የተገላቢጦሽ ሂደትም አለበት። አማሮች (ሀ) ናቸው የመንግሥቱን ባህል ወስደው አማራ የሆኑ እንጂ የጥንቱ መንግሥት ባህል የአማሮች ባህል አልነበረም። መንግሥቱ ሲቋቋም የራሱ ባህል ነበረው፤ ቋንቋውም ግዕዝ ሳይሆን አይቀርም። ከላይ እንደገለጥኩት መንግሥት አማርኛን ቋንቋው ያደረገው የአማርኛ ተናጋሪው ቍጥር ትልቅ ስለነበረ ነው። እርግጥ መንግሥቱ አማርኛን ቋንቋው ማድረጉ ለአማርኛ መስፋፋት ረድቷል፤ ግን አማርኛ የተስፋፋው የመንግሥት ቋንቋ በመሆኑ ብቻ አይደለም። የመንግሥቱ እጅ እማይደርስበት ቦታ ሁሉ አማርኛ ይነገርበት ነበር። ደግሞስ መንግሥት ያቋቋሙት አማሮች ከሆኑ ያስከብራቸዋል እንጂ አያስወቅሳቸውም። እማን ላይ ቆመው በአማራው ያማርራሉ!

ወያኔዎችና አማሮች አይግባቡም፤

ወያኔዎችና አማሮች ከማይግባቡባቸው ጉዳዮች ዋናው፥ ወያኔዎች “በጎሳ ተከፋፈሉ” (አገሪቷ ትበታተን) ሲል አማሮች “አሻፈረን” ማለታቸው ነው። ከጎሳዎች ውስጥ አንዳንዶች መከፋፈሉን ይደግፋሉ። አማሮች የኢትዮጵያን በጎሳ መከፋፈል የሚቃወሙት የጎሳዎች መብት መከበርን ለመቃወም ይመስላቸዋል። ግን ሁለቱ ግንኙነት የላቸውም። እርግጥ የጎሳ ቋንቋዎች መጻፊያ እንዳይሆኑ መንግሥት የከለከለበት ጊዜ ነበረ። አንደኛ፥ ለዚያ ተጠያቂው አማሮች አይደሉም፤ ሁለተኛ፥ የጎሳዎች መብት ባይከበር አማሮች ምንም የሚያገኙት ጥቅም የለም። ጥቅም ካላገኙበት ለምን ይቃወማሉ? ሦስተኛ፥ አሁን ያ ከአለፉት ጋር አብሮ አልፏል፤ አራተኛ፥ አማርኛ
5
ተናጋሪዎች “ባህል ይጨቆን” አይሉም፤ “የሚሉት ባህልን ማስከበር የሚቻለው ሰላምንና የሀገርን ጥንካሬ በሚያመጣ ስልት እንጂ የግድ መለያየትን፣ መበታተንን፥ በሚያስከትል መንገድ መሆን የለበትም” ነው።
አራተኛውን ነጥብ ለማብራራት፥ የጎሳውን ቋንቋና የአካባቢውን ታሪክ ከኢትዮጵያ ታሪክና ከብሔራዊ ቋንቋ ጋር ጎን ለጎን ማስተማር አማራጭ ሊኖረው የማይገባ ዘዴ ነው። መንግሥት የሚቋቋመው የሀገር ዳር ድምበር ለማስከበር፥ የሕዝብን ሰላም ለመጠበቅ፣ ሕዝቡ ኢኮኖሚውን እንዲያዳብር መንገዱን ለመጥረግ፣ ክፍትና ሰላማዊ ለማድረግ ነው። ወያኔዎች የመጡት ግን ይህን ሁሉ ለመቃረን ስለሆነ ይኸን አማራጭ ዞር ብለው እንደማያዩት በሥራ አሳይተውናል። አንድነትን ጠብቀን በምርጫ ጊዜ ለኢኮኖሚው እድገት የጎሳየ ሰው ይጠቅመኛል የሚል እሱን መምረጥ ይችላል።

የሀገርን ኢኮኖሚ ከማዳበር የተለየ የፖለቲካ ዓላማ ያለው ዜጋ ካለ ሌላው ሞኝ ነው። ደንቆሮም ክፉም ልንለው እንችላለን። የሀገር ኢኮኖሚ ሊዳብር የሚችለው ሕዝብ የሚቆጣጠረው መንግሥት ሲኖር ብቻ ነው። በተገላቢጦሽ እንደወያኔ የሕዝብን ሕይወት የሚቆጣጠርና ዳር ድምበር የማያስከብር መንግሥት ለኢኮኖሚው መዳበርና ለሀገሪቱ ጥቅም ማሰብ አይችልም፤ ዘበት ነው። ይህ ነቀፌታ ከብዙዎች የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሊቃውንት በተነሣ ቍጥር የወያኔዎችና የደጋፊዎቻቸው መልስ፥ “በሀገራችን የምንገነባውን አታዩም ወይ? ኢትዮጵያን ለውጠናታል” የሚል ነው። ኢኮኖሚስቶች እንደሚነግሩን መጀመሪያ መገንቢያው ገንዘብ አገር በቀል አይደለም፤ ከውጪ የመጣ ነው። እርግጥ ከውጪ ገንዘብ ማምጣት መንግሥታት ሁሉ የሚመኙት ነው። ግን ገለልተኛ ተቆጣጣሪ ከሌለ ገንዘቡ ለታሰበው ሥራ መዋሉ በምን ይታወቃል? ፎቅ ቤቶች የሚያሳዩን ከውጪ የመጣውን ገንዘብ ሁሉንም አልጠጣንበትም፥ ሁሉንም የግል ግምብ ቤት አልሠራንበትም፥ ሁሉንም የግል ንግድ አላቋቋምንበትም፥ ሁሉንም እውጭ አገር ባንክ 
በየስማችን አልሸሸግነውም ለማለት አይደለም?

ወያኔዎችና አማሮች ከማይግባቡባቸው ሌላው ዋና ጉዳይ የዲሞክራሲና የነፃነት ነገር ነው። ወያኔዎች ለዲሞክራሲ ዋጋ እንደማይሰጡት አስመስክረዋል። በዚህም ትልቋን ኢትዮጵያ አዋርደዋታል። ውርደቱን አለመቀበላችንን በቃል ሳይሆን በሥራ ማሳየት ይኖርብናል። የአንድ ሀገር ዜጋ ለዲሞክራሲ አስተዳደር ቅድሚያ ካልሰጠ ኋላ ቀር ደንቆሮ ነው። ለዲሞክራሲ አስተዳደር በመታገል ፈንታ መገዛትን ከተቀበለ፥ ደረጃውና ክፍሉ ከመላእክት ደረጃ ወርዶ ከእንስሳት ጋር ይሆናል፤ ይነዳል፤ እንደ አጋሰስ ጭነት ያጓጕዛል። በዚያው አንጻር የሕዝብን የዲሞክራሲ ጥያቄ የሚጨቁን ገዢ የዲያብሎስ መልክተኛ ነው።

መደምደሚያ፤
ድርሰቴን በተነሣሁበት ለማጠቃለል፥ በዘር ሲታይ የአማራ ጎሳ የለም። በመንግሥት ባህል ሲታይ አለ። ወያኔዎች ስለኢትዮጵያ አንድነት የሚቆረቆረውን ሁሉ ሲያጠፉ አማራውን ለምን ተቀዳሚ ዓላማቸው እንዳደረጉት ሊገባንና በግላጭ ልንቋቋመው ይገባናል። ዓላማቸው “የኢትዮጵያ አንድነት የለም” ለማለት ነው። በሥራ “እምቢ አሻፈረኝ” እንበል። የሚገርመው አማራው የሚመታው የኢትዮጵያን አንድነት ያነገበና የአንድነት ባንዲራ የሚያውለበልብ መሆኑ እየታወቀ፥ “ኢትዮጵያ አንድ ናት” ከሚለው ወገን ውስጥ የደረሰለት ቍጥሩ ኢምንት ነው። ይኸ ብቻ አይደለም፤ አማራው ራሱ “ለአማራው ብቆረቆር ጎሰኛ እሆናለሁ/እባላለሁ፤ ለአማራው እየተቆረቆርኩ ለጎሳው የሚቆረቆረውን እንዴት እነቅፋለሁ?” በማለት ጭጭ ብሎ ራሱን ደፍቶ መርዶውን ያዳምጣል። በሞኝነት ከወያኔ ወጥመድ ገብቷል። “ኢትዮጵያ አንድ ነች፤ አትከፋፈልም” በማለቱ ለሚያጠቁት የአንድነት ወገን መድረስ ኢትዮጵያዊነት እንጂ ጎሰኝነት አይደለም። ወያኔዎች አማራውን የሚመቱት የአንድነት ኃይልን ለማዛል መሆኑ የገባቸው በቍጥር ናቸው። ግን የአማራውን ሕዝብ መሠረት ያላደረገ የአንድነትና የነፃነት ትግል አለት ድንጋይ
6
እያለለት ቤቱን አሸዋ ላይ እንደመሠረተ ሞኝ ሰው፥ ወይም መድፉን ከካዝና ቈልፎበት በሽጉጥ እንደዘመተ ሠራዊት ይቈጠራል ነው።