Wednesday, October 28, 2015

የዐማራውን ማንነትና ታሪክ በማንቋሸሽንና በመካድ ከኢሣት ራዲዮና ቴሌቪዥን ጋር ላደረጉት ቃለ-ምልልስ

ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ ድሌቦ፦

 የተሰጠ የአጸፋ መልስ ፤
1 መንደርደሪያ፦ ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌ ድሌቦ ማናቸው?

  •  ላጲሶ በነገድ የሐዲያ ነገድ  አባል ናቸው።
  • በሃይማኖት የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ናቸው። 
  • ያጠኑት የሙያ መስክ ታሪክ ነው። ዶክትሬታቸውን የሠሩት በ1960ቹ አሜሪካ በሚገኘው ሐዋርድ የጥቁሮች ዩኒቨርስቲ ነው።
  • የፖለቲካ አቋም፦ ላጲሶ እንደ ስልሳዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ትውልድ ይኸነው የሚባል ሚናቸው ጎልቶ የሚነገር የለም። በአንዳንድ እርሳቸውን በሚገባ የሚያውቁ ሰዎች አዕምሮ ቀድሞ የሚመጣው፣ በአብዮቱ ዋዜማ ላይ « የምኒልክ ሀውልት አዲስ አበባ ላይ ምን ይሠራይ ፤ ይፍረስ» ብለው ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ከሚያሰሙት ውስጥ አንዱ የነበሩ መሆናቸውን ነው። በሌላ በኩል የፀና ፖለቲካዊም ሆነ ማኅበራዊ ሥብዕና የሌላቸው፣ ገዥዎች በተፈራረቁ ቁጥር የነርሱን ፍላጎት ተከትለው `` አለኝ የሚሉትን የታሪክ ዕውቀት`` እንደ መሣሪያ በማድረግ የገዥዎች አፍ ሆነው የሚቆሙ መሆናቸው በሚያውቋቸው ሰዎች ተደጋግሞ የሚነገር ነው። ይህ ደግሞ ለመኖርና ለሥልጣን ሲሉ የሚያደርጉትና ለዚህም የዳረጋቸው ከአናሳ ነገድ መውጣታቸው  እንደሆነ የሚጠቅሱ አልታጡም። ለነዚህ አባባሎች እንደ ማሳያ ሆነው የሚቀርቡት ማስረጃዎች የሚከተሉት ናቸው።

አንደኛ፦ ቅድመ 66 የምኒልክ ሐውልት ይፍረስ ይሉ የነበሩ፣ በአብዮቱ ይህን አቋማቸውን ለውጠው የብሔረሰቦች ኢንስቲትዩት የታሪክ ኤክስፐርት ተብለው፣ የደርግን ዓላማና ፕሮግራም በግንባር ቀደምትነት ሲያስፈጽሙ ከነበሩት ውስጥ አንዱ የነበሩ መሆናቸው፤ ኢትዮጵያ አሀዳዊ መንግሥት ሆና ለብዙ ዘመናት የኖረችና በዚሁ ሪጂናል ኦቶኖሚን የአስተዳደሩ አካል በማድረግ በአሐዳዊነት መቀጠል አለባት ብለው ጥናቱንና ሕገመንግሥቱን ካረቀቁት ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው።

ሁለተኛ ፦ በዘመነ ወያኔ ደግሞ፣ ተገልብጠው፣ «ዛሬ ገና አብዮት ተካሄድ» በማለት ለኢትዮጵያ የሚበጃት መከፋፈል ነው፣ በነገድ(ቋንቋ) ላይ የተመሠረተው ፌደራላዊ አስተዳደርና ነገዶች ባሻቸው ጊዜ የመገንጠል መብታቸው መረጋገጡ ተገቢ ነው» እያሉ የሚሰብኩና ከበሮ በተደለቀበት ቦታ ሁሉ በመገኘት እኔ ልደልቀው የሚሉት ናቸው።

  ስለ ዶ/ር ላጲሶ ይህን ያህል ካልኩ፣ ከኢሣቱ ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ስለተናገሯቸው ከሐቅ የራቁ ብቻ ሳይሆኑ ሆን ተብሎ የዐማራውን ነገድ አንገት ለማስደፋት ከጌቶቻቸው የተጋቱትን መልሰው ለባለቤቱ ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለዐማራው ነገድ የነገሩትን ቅጥፈት አንድ ባንድ ተገቢ የሆነውን አጸፋ ራሳቸውን ነቃሽ በማድረግ እንደሚከተለው አቀርባለሁ።

   1 «ካሁን በፊት የነበረውን የዐማራ ተረት ተረት ታሪክ ውድቅ አድርገን አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ እየሠራን ነው።»
ይህ የዶ/ር ላጲሶ አባባል በሚከተሉት ምክንያቶች ራሳቸውን ከከፍተኛ ግምት ውስጥ ከመክተት በስተቀር፣ በሕዝብ ኅሊና ውስጥ ተቋጥሮ የሚቆይ ፍሬ ነገር አለው ወይም የሚጻፈው ታሪክ የዐማራውንና የኢትዮጵያን ታሪክ ውድቅ ያደርገዋል አይባልም። እንዳውም በተቃራኒው ሰዎች በልዕልህ ተነሳስተው የተደበቁ ታሪኮች እንዲወጡ ያደርጋል እንጂ፣ የነበረ ታሪኩ ይፋቃል፣ አይኖርም ወደሚል መደምደሚያ አያሸጋግርም። ለዚህ ማሳመኛው አንዱ ራሳቸው « ኢትዮጵያ--የታሪክ መነሻ» በሚል ርዕስ በ1983 በዝንግሊዝኛ ያዘጋጁትና በተርፋሳ ድጋ ወደ አማርኛ የተተረጎመው መጽሐፍ በትውልድ እጅ የገባ ከመሆኑ በላይ፣ እርሳቸው እንደሚሉት የታሪክ ተመራማሪ ሳይሆኑ፣ የቅስቀሳ ሰው መሆናቸውን የሚያጋልጣቸው ሰነድ አለ። በዚህ መጽሐፍ ስለኢትዮጵያ ታሪክ እንዲህ ይሉናል፤

«-- በታሪክ ሠሪነቱና በባህል አመንጭነቱ ፣ደግሞ ከአለት ደንጋይ ተፈልፍለው በአስደናቂ ጥበብ የተተከሉ ሾጣጣ የደንጋይ ሀውልቶችና የቋጥኝ አብያተክርስቲያናትና መስጊዶች አንጿል። ፊደልና ሥነ-ጽሑፍ አዳብሯል። መንፈሣዊ ዜማና ሽብሻቦው የክርስትናና እስልምና ሃይማኖቶች ግንባር ቀደም አስተናጋጅና ባለቤትነቱ ምስክሮች ናቸው። የተለያዩ ባህላዊ ጨዋታዎቹና የቆየ የነፃነት ፍቅሩና ኩራቱ የረጅም ታሪክና ቅኝ ተገዥ ሆኖ ላለማወቁ ጉልህ ማስረጃዎች ናቸው።» ይህ በራሳቸው በላጶሶ የተጻፈ ዕውነተኛው ታሪክ ነው። ይህ ለሁሉም አባባላቸው ከበቂ በላይ ማስረጃ ነው። ሆኖም ግን እያንዳንዱን ነቅሶ በማውጣት የዘሩትን ሀሰት ሰብስቦ ለማቃጠል ስለሚረዳ ከላይ ራሳቸው ያሏቸው ጥቅል ዕውነታዎች ምን ማለታቸውና የማን ታሪኮች እንደሆኑ ላብራራ።

          i. ማንም የኢትዮጵያን ታሪክና የማኅበረሰቡን ሃይማኖቶች መገለጫ የሚገነዘብ ሰው ሊረዳው እንደሚችለው፣ ክርስትናና ዐማራ የሚሉት ቃሎች ወይም ጽንሰ ሀሳቦች ተለዋዋጮች ናቸው። በቀድሞው ጊዜ አንድ ሰው ተጠምቆ ክርስቲያን ሲሆን፤ ዐማራ ሆነ ነበር የሚባለው። ዐማራ ማለት ክርስቲያን፣ ክርስቲያን ማለት ዐማራ ማለት ነበሩ። ለዐማራው ነገድም እንስከቅርብ ጊዜ ድረስ ክርስትና ማተቡ፣ መለያ መታወቂያው ነበር።  በደረቱ፣ በግንባሩና በእጁ ላይ የሚነቀሳቸው መስቀሎች የክርስቲያንነቱ ምልክቶች ናቸው። በመሆኑም ከክርስትና ጋር ተያይዘው የሚነገሩ፣ የተሠሩ፣ ነገሮች በሙሉ ሲጠቡ፣ የዐማራው፣ የትግሬውና የአገው ታሪኮች ናቸው። ሲሠፉ ደግሞ የኢትዮጵያውያን ታሪኮች ናቸው።

                      ii.        ውቅር አብያተ ክርስቲያኖች በላጲሶ አባባል የታሪክ ማሳያ አሻራዎች ከሆኑ፣ በዕውነትም ናቸው፣ እነዚህ ቤተክርስቲያኖች በብዛት የሚገኙት፣ በኤርትራ፣ በትግሬ፣ በወሎ፣ በሸዋ፣ በጎንደርና በጎጃም ነው። እነዚህ ደግሞ የዐማራው፣ የትግሬውና የአገው መፍለቂ ቦታዎች ናቸው። ስለሆነም ታሪኩ የነዚህም ነገዶች ብቻ ነው ማለት ተገቢና አግላይነት ያለው ቢሆንም፣ ነገሩን ቀረብ ብለን ካየነው ያለጥርጥር አመዛኙ የነርሱ ነው። ይህን እንዴት መካድ ይቻላል?

                iii.        ፊደል የሥልጣኔ መገለጫ፣ የታሪክ መመዝገቢያ፣ የታሪካ ማሸጋገሪያ መሣሪያ መሆኑ ዕውነት ነው። ይህም በመሆኑ የባለታሪክነት መገለጫ ነው። በዚህ ላይ ላጲሶ ልዩነት የለም ። በዚህ ከተማመንን፣ ከአማርኛ ፊደል በፊት የነበረውን የግዕዝ ፊደል፣ ቀጥሎም የአማርኛውን ፊደሎች ማን ቀረጻቸው? ማንስ ፈጠራቸው? ማንስ ሥርዓት አስይዞ ለጽሑፍ አገልግሎት አዋላቸው? የሚሉትን ጥያቄዎች አንስተን ብንወያይ የምንደርስበት መደምደሚያ ዐማራው፣ ትግሬውና ከዚያ በፊት የነበሩ ነገዶች የሚል እንደሚሆን በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። ሰው ሳይኖር ቋንቋ አይኖርም። ቋንቋ ሳይኖር ደግሞ ፊደል አይኖርም። ስለዚህ ለዐማርኛ ቋንቋ መኖር የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ ማኅበረሰብ መኖር ቅድመ ግዴታ ነው። ቋንቋው ካለ ደግሞ ፊደሉ ይከተላል። ይህም ደግሞ ማንም ሳይሆን የሚያዘጋጀው የቋንቋው ባለቤት ኅብረተሰብ ነው። ይህም የዐማራው ታሪክ የዚህን ያህል ያማረ፣ የጠለቀ፣ የሠፋና በከፍተኛ ገድል የታጀበ ነው። ይህን መካድ ይቻላል። ማጥፋት ግን በፍጹም አይቻልም። ነባራዊ ነውና!

      iv.     መንፈሣዊ ዜማና ድርሰቶች የተባሉት ደግሞ፣ድጓ፣ ፆመ-ድጓ፣ ዝማሬ ፣ዝማሬ መዋሴት፣ቅኔ፤የመጽሐፍትና የመጽሐፍት ትርጓሜ የመሳሰሉት ናቸው። የእነዚህ መገኛና ማስመስከሪያ ጥንታዊ ተቋሞቹ የሚገኙት በጎንደር፣ በጎጃምና በወሎ ነው። የድጓና ፆመ ድጓው ማስመስከሪያው ቤተልሄም ጋይንት አውራጃ ጎንደር ክፍለሀገር የሚገኝ ነው። የዝማሬ መዋሴት ዙርአምባ ማርያም የሚገኘው ጋይንት አውራጃ ነው። የቅኔው ዋሸራ ጎጃም ብቸና ነው። እነዚህ ደግሞ የዐማራው ዕምብርት ቦታዎች ናቸው።

ዶ/ር ላጲሶ ከላይ በመጠኑም ቢሆን በዝርዝር ለማየት የሞከሯቸውን ጉዳዮች የታሪክ ፋይዳ ያላቸው  ናቸው። እነዚህ ደግሞ የሚመሰከሩት የዐማራውን ማንነትና ታሪክ ነው። የአማርኛ ፊደል በሥራ ላይ መዋል የጀመረው በ320 ዓም በአባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ዘመን ነው። ከዚህ ዓመት በፊት የፊደሉ አቀማመጥ ቅደም ተከተል አ  በ  ገ  ደ-- ነበር። በዚህ በ320 ላይ ይህን የፊደሉን ቅደም ተከተል አቀማመጥ ወደ  ሀ  ለ  ሐ   መ --- ተለወጠ። ይህም ከፍ ሲል ለመጥቀስ እንደተሞከረው፣ ሕዝብ ሳይኖር ቋንቋና ፊደል ሊኖሩ ስለማይችሉ ቋንቋውም ሆነ ፊደሉ የዐማራው ነገድ ሀብቶች መሆናቸውን መካድ ራስን መካድ ነው።

ስለሆነም በላጲሶ «የዐማራው ታሪክ ተረት ተረት ነው» የሚሉት የአፍ ወለምታ ወይም ሆን ተብሎ በወያኔ የተሰጣቸውን የዐማራን ማንነት የማቋሸሽና የማጉደፍ ተልዕኮ ለማስፈጸም ካልሆነ ታሪኩ፣ ገዝፈው በሚታዩ ሀውልቶች፣ በውቅር ቤተክርስቲያኖች፣ በጥንታዊ ሃይማኖታዊ ሥነጽሑፎች ፣ዝማሬዎችና የነገሥታት ዜና መዋዕል በአካል የሚታዩ፣ በእጅ የሚዳሰሱ፣ የሚነበቡ ወዘተ  በመሆናቸው ጥፉ ቢሏቸው የሚጠፉ አይሆኑም።

ዶ/ር ላጲሶ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፋቸው የጥንቱ ግብፃውያን ጽሑፍ ሃይሮግላፊክስ በተባለው ከ5ኛው እስከ 8ኛው ሥርዎ መንግሥት የነበሩት የግብፅ ፈርዖናውያን ታሪክ ጠቅሰው፣« ሀበሻ»  እየተባለ ይጠራ ከነበረው የዘመኑ የኢትዮጵያ ነገሥታት ጋር በንግድና በመጻጸፍ ግንኙነት ያደርጉ እንደነበር ገልጠዋል። በዚህም መሠረት ከ2743 እስከ 2731 ዓመታ ዓለም ከኖሩት  ቡሃሬን እና ሃትቬፕሱት ጋር ከፑንታዊያን ጋር መጻጻፋቸውን ገልጸዋል። ይህ የአገሪቱን ጥንታዊነት ከማስረዳቱም በላይ ከውጭ አገሮችም ጋር መሥርታው የነበረውን ግንኙነት የሚያስረዳ ነው።

2 « የአክሱም ግዛት ከዛሬው ትግሬና ኤርትራ ክልል አያልፍም።» ስላሉት፥ የላጲሶ ታላቅ ውሸትና ክህደት የሚታየው ደግሞ እዚህ ላይ ነው። ላጲሶ፣ ላጲስ ካልሆኑ በቀር ይህን ራሳቸውን 360 ዲግሪ በዞረ መልኩ ትናት ያሉትን ብቻ ሳይሆን በጽሑፍ ያሠፈሩትን የካዱበት ሆኖ አገኝቸዋለሁ። ዕውነታው እንዲህ ነው። የመረጃው ምንጭ የራሳቸው ሥራ ነው። ያራሳቸውን መረጃ ለማቅረብ የፈለኩት እርሳቸውን ዐዋቂ ብቸኛ የታሪክ ተመራማሪ አድርጌ ቆጥሬ ሳይሆን፣ ለሁለት ምክንያቶች ነው። አንደኛው «ቀጣፊን ሲረቱ በወንድሙ በእህቱ» ስለሆነ ተረቱ ፣ ባራሳቸው ሥራ ራሳቸውን ለመሞገትና መነሻቸው ምን ሆኖ መውደቂያቸው ምን እንደሆነ ለማሳየት ነው። ሁለተኛው በዚህ መጽሐፋቸው ያሠፈሩዋቸው ነገሮች በአመዛኙ ከኢትዮጵያ ዕውነተኛ ታሪኮች ተብለው በዓለም የታሪክ ተመራማሪዎች ተቀባይነት ያላቸው በመሆናቸው ነው።

                               i.        ኢትዮጵያ የታሪክ መነሻ በተሰኘው ሥራቸው «የአክሱማውያን ግዛት ግብፅና መርዌን ያጠቃለለ እንደነበር ጽፈዋል። አስተምረዋል።(ገጽ 9)
                              ii.        አክሱማዊው ንጉሥ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ባካሄደው ዘመቻ፣ ለኡኮመ ፣ ኬናይዳኮልፕቴና እና ኦራቢቴ ተብለው ይጠሩ የነበሩ 3 የዐረቢያ አካባቢዎችን በቁጥጥሩ ሥር አውሎ ያስተዳድር እንደነበር አረጋግጠው ጽፈዋል።
                             iii.        በ4ኛው ምዕተ ዓመት ዐፄ ኢዛና ዘመነ መንግሥት የአክሱማውያን የዐፄ መንግሥታት ግዛት የሕማርያ፣ የካሱ፣ የሣባ፣ የሐበሻ፣ የረዳይን፣ የሣህሌን፣ የጽሞ፣ የቤጃ፣ ወዘተ አገሮችና ሕዝቦችን ዝርዝር በግዕዝና በግሪክ ቋንቋዎች ተመዝግቦ መገኘቱንና በዐፄዎቹ ግዛት ሥር ይገዙ እንደነበር አረጋግጠዋል። ሕማርያ እና ሣባ የሚባሉት ዛሬ በዐረቢያ ውስጥ የሚገኙ አገሮች ናቸው። ሣህሌን የሣባውያን ከተማ የነበረ ነው። ካሱ የመርዌ ሌላው መጠሪያ ነው። ይህም በአሁኑ ሱዳን ውስጥ የሚገኝ አገር ነው።

                             iv.        ላጲሶ የአክሱማውያንን የግዛት ስፋት የነገሥታቱን ዜና መዋዕል ዋቢ አድርገው እንዲህ ሲሉ ገልጸውታል።« ከ4ኛው  እስከ 6ኛው ምዕተ ዓመት ባለው ጊዜ በሰሜን ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘው ሠፊ አካባቢ ማለትም በቀይ ባሕርና በኤደን ባሕር ሰላጤ መካከል፣ በምሥራቅና በደቡብ ምሥራቅ ታችኛውን የአዋሽ ሸለቆ በደቡብ ምዕራብ የዐባይን ወንዝ መፋሰሻ ይዞ የነበረው ሠፊ አካባቢ የአክሱማውያን ግዛት እንደነበር ተረጋግጧል» በማለት በ1983 የጻፉትን ፣ዛሬ በምን ተአምር ሊክዱት እንደፈለጉ ምክንያቱን የሚያውቁት ራሳቸው ላጲሶ ብቻ ናቸው።

ማንም እንደሚያውቀው አንድ ሐገር ትናንትም ሆነ ዛሬ ለኃያልነቱ መረጋገጫ ከሆኑት ጉዳዮች አንዱ የግዛት ቆዳ ስፋት ነው። በተለይ በዚያን ጊዜ ይህ ወሣኝ ጉዳይ ነበር። አክሱማውያን በ2ኛውና በ3ኛው መቶ ክፍለዘመን በዓለም ላይ ከነበሩት ኃያላን መንግሥታት አንዷ እንደነበረች ማኒ የተባለው ፖርቹጋላዊ የታሪክ ተመራማሪ አስፍሮታል። ላጲሶ እንዳሉት የአክሱማውያን የግዛት ክልል በኤርትራና በትግሬ ብቻ ቢወሰን ኖሮ፣ ኃያል ለመሆን ቀርቶ አክሱማውያንን ስማቸውንም የሚያውቅ ሊኖር ይችላል ለማመን ያስቸራል።

« የነገሥታት ዜና መዋዕል ተረት ተረት ነው» ስላሉት፤

 ዶ/ር ላጲሶ «የአክሱማውያን መንግሥተ ዘመንና ክርስትና ከ100---1100 ዓም» በሚል ርዕስ  ባቀረቡት ጥናት፣ ለጥናታቸው ትክክለኛነትና ታማኒነት በማስረጃነት ካቀረቡዋቸው ዋቢዎች አንዱ የነገሥታት መዋዕለ ዜና ነው። እንዲህ ይሉታል፤ « --በ4ኛው ምዕተ-ዓመት በግዕዝና በግሪክ ቋንቋዎች የተጻፉ የዐፄ ኢዛና መዋዕሎችና፣ በ6ኛው ምዕተ-ዓመት የተጻፈው የዐፄ ካሌብ ዜና መዋዕል ዋነኞቹ የታሪክ ማስረጃዎች ናቸው። »   ይህ እንግዲህ « የዐማራ ታሪክ ተረት ተረት ነው፤ የነገሥታት መዋዕለ ዜናዎች ታሪክ አይደሉም» ላሉት ከበቂ  በላይ መሳያ ነው። ይህ አባባላቸው የሚሠሩትን የማያውቁ፣ ትናንት ያመኑበትን ዛሬ የሚሽሩ፣ በቃላቸውና ባሉት የማይረጉ በራሳቸው ሥራ  ራሳቸውን የሚቃረኑ የሕይዎት ወይም ለመኖር ሲሉ የአቋም እና የአመለካከት አመንዝራነት የተጠናዎታቸው ሰው መሆናቸውን ያሳያል ብየ አምናለሁ።

4 «አማራዎች የአማራን ታሪክ ብቻ ለመጻፍ ሲጥሩ ሁሉም ጠፋ።» ላሉት፣
በየትኛውም ዘመን እኔ ወይም እኛ አማረነን ብሎ በአማራ ስም ሥልጣን የያዘ ሰው ወይም ቡድን የለም። አማራነትንም ማዕከልና ቋሚ አድርጎ የተጻፈ ታሪክ እስከ ዘመነ ወያኔ ድረስ የለም። የተጻፈው ነገሥታቱን ማዕከል ያደረጉና በነገሥታቱ ዜና መዋልዕ ዙሪያ የሚሽከረከሩ በየዘመኑ ባሉ የታሪክ ጸሐፊዎች መጽፉ ዕውነት ነው። የዘመኑ ሁኔታ የሚፈቅደው ያንን ነው። ከነባራዊ ሁኔታ ውጭ መውጣት እንኳን በዚያን ጊዜ ዛሬም የሚቻል አይሆንም እንኳ ባይባል እጅግ አስቸጋሪ ነው። የአገሪቱን መሪዎች ወይም ነገሥታት መዋዕለ ዜና የጻፉት ደግሞ በዘመኑ የመጽፍ ዕውቀቱና ችሎታው የነበራቸው የየጊዜው ሊቃውንት «ደብተራ» የሚባሉት ናቸው። እነዚህ ሊቃውንት ደግሞ የየትኛው ነገድ አባሎች እንደሆኑ በግልጽ የሚታወቅ መረጃ የለም። ለምሳሌ የጎጃምን ሕዝብ ታሪክ የጻፉት አባ ተክለየሱስ በትውልድ ኦሮሞ ናቸው። አማራ አይደሉም። በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎቹ የመጻፍ ችሎታ የነበራቸው ትግሬ፣ አገው፣ ኦሮሞ፣ ወዘተ ሊሆኑ ይችላሉ። «ዜና ዘ ጋላሁ» ወይም የጋላ ታሪክን የጻፉት የጋሞ ተወላጅ ናቸው የሚሉ አሉ። እርግጠኛውን ፈላልጎ ማወቁ የታሪክ ተመራማሮዎች ሥራ ነው።

በሌላ በኩል ነገሥታቱ ሁሉም  አማራዎች አይደሉም። ከዐፄ ኢዮአስ ጀምሮ እስከ ዘመነ መሳፍንት ፍጻሜ ድረስ አገሪቱን የመሩት ኦሮሞዎች ናቸው። ዐፄ ሱሲኒዮስ በጉዲፍቻ ያደጉ የኦሮሞን ባህልና ማንነት የተላበሰ በባህል፣ በሥነ ልቦናና በአመለካከት የያዙ  ኦሮሞ ናቸው። ለውድቀታቸው ምክንያት የሆነውም ይህ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ውጭ ሆኖ ማደጋቸው ያሳደረባቸው የሃይማኖት መላላት ያስከለው የሃይማኖት ለውጥ የቀሰቀሰባቸው ሕዝባዊ አመጽ መሆኑ ይታወቃል።

በ14ኛው መቶ ክፍለ-ዘመን የይፋት እና የደዋሮ ሡልጣኖች ከክርስቲያኖች ጋር ያደረጉት ተከታታይ ጦርነት አስወግዶ ሰላምና አንድነትን ለማምጣት ሲሉ ዐፄ አምደጽዮን ከሡልጣኖቹ ጋር የጋብቻ ዝምድና መመሥረታቸውና አንፃራዊ ሰላም መፍጠራቸው ይታወቃል። በዚህም መሠረት ራሳቸው ዐምደጽዮን የደዋሮውን ሡልጣን ገራልድን ልጅ ጽዮን ሞገሣን አግብተው ወራሲ መንግሥቱን በዕደማርያምን መውለዳቸው ይታወቃል።
ዐፄ በዕደማርያምም በበኩላቸው የእናታቸው ዘር የሆኑትን እቴጌ ዕሌኒንና እቴጌ ሮማነ-ወትቅን አግብተው እቴጌ ዕሌሊ እስከ ልብነድንግል ባሉት ዘመናት የነገሥታቱ ዋና አማካሪና ፖሊሲ ቀያሽ እንደነበሩ ይታወቃል። ዐፄ ናዖድ በበኩላቸው የነዚሁ የደዋሮው ሡልጣኖች ተወላጅ ከመሆናቸውም በላይ እቴጌ ናዖድ ሞገሣን የደዋሮውን ባላባት ልጅ አግብተው ልብነ-ድንግልን የወለዱ መሆናቸው ግልጽ ነው። 

ወደ ኋላም  ስንመለስ የዘርዓ ያዕቆብ እናት ትግሬ ናቸው። የገላውዲዎስና የሚናስ እናት የሐማሴን ተወላጅ ትግሬ ናቸው። ወደ ቅርቡ ስንመጣም የምኒልክ እናት ጉራጌ ናቸው። ከጉራጌም ዝቅተኛ ቤተሰቡ የተወለዱ። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ባባታቸው በራስ ተፈሪ መኮንን በኩል የዶባው ባላባት የወልደሚካኤል ጉዲሣ ልጅ ናቸው። በእናታቸው በወ/ሮ የሽመቤት ዓሊ በኩል በእናታቸው በወ/ሮ ወለተጊዮርጊስ በኩል ጉራጌ ናቸው። ባባታቸው በዓሊ በኩል የወረይመኑ ኦሮሞ ናቸው። ኮ/ሌ መንግሥቱ ኃይለማርያም ኦሮሞና አማራ ናቸው። እንደዚህ እያልን ሁሉንም ብንዘረዝር ከቅድመ ወያኔ በፊት የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ኢትዮጵያውያን እንጂ፣ የአንድ ነገድ አባል በትውልድም፣ በሀሳብም ፤በተግባርም አልነበሩም።

 አማራው ላጲሶና መሰሎቹ በፀረ-ኢትዮጵያዊነት ተኮትኩተው ያደጉ ቡድኖች ኢትዮጵያን ለመበታተን አማራን አጥፉ በሚለው መመሪያ መሠረት የሚንቀሳቀሱ ሁሉ አማራውን የሚከሱት በሌለበት በዚህ መልክ ነው። እናም አማራው በብቸኝነት ኢትዮጵያን ገዝቶ አያውቅም፣ የራሱንም ታሪክ አልጻፈም። የተጻፈው የኢትዮጵያ ታሪክ ነው። ጸሐፊዎቹም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ይህም በመሆኑ ለዐማራ ተብሎ የተጻፈ ታሪክ የለም። ባለመኖሩም ቅድመ ወያኔ የተጻፉ ታሪኮች በሙሉ የኢትዮጵያውያን ናቸው። ያልተጻፈ ይኖራል። ያን ፈልጎ መጽፉ ደግሞ የሙያተኞች ነው።

ዛሬ ላጲሶ እጽፈዋለሁ የሚሉት ታሪክ እንደሚሉት ከጻፉት፣ መነሻና ግብ የሚያደርገው ዘርን ስለሚሆን ታሪኩ በአማራ ጭፍን ጥላቻ እና ባለፉት 40 ዓመታት ከበሮ በተደለቀባቸው አጥፊ መንገዶችን የሚከተል ስለሚሆን ውጤቱ አጥፊ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ከላጲሶ ንግግር መረዳት እንደሚቻለው የሚጽፉት « በዐማራ ጥላቻ ላይ የተመሠረት» ታሪክ፣ ታሪክ ከሆነ፣ የአማራውን ነገድ አንገት የሚያስደፋ ይሆናል ብለው ባሰቡት መንገድ እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተዋል። ይህ ደግሞ ይደክማሉ እንጂ፣ የዐማራው ታሪክ በሁለት ምክንያቶች የሚሞትም፣ ትውልዱም አንገቱን የሚደፋ አይሆንም።

አንደኛ፤ እስከ ዛሬ በችላታ፣ እስቲ እንያቸው የሚለውን የዐማራ ምሑር የሚቀሰቅስ ይሆናል። ይህም የነበረ ታሪኩን ቁልጭና ቅልብጭ አድርጎ እንዲጽፍ ማቀጣጠያ ነዳጅ ይሆናል።

ሁለተኛ፣ የዐማራው ታሪክ ፍፁም ጠበቃ አያሻውም። ራሱን ችሎ የትም ቦታ ይናገራል።  የዘንተራን፣ የእንትጮን፣ የሽምብራ ኮሬ፣ የመቅደላ፣ የሣር ውኃ፣ የጉራ፣ የጉንደት፣ የድሆኖ፣ የመተማ፣ የዶጋሊ፣ የዐድዋ፣ የአምባላጌ፣ የመቀሌ፣ የማይጨው ጦርነቶችና ድሎችና ሽንፈቶች የዐማራው ናቸው ብለን ከደመደምን፣ እነዚህ ታሪኮች የሚያወሱት ዐማራውን ነውና ማንም ሊያጠፋቸውና ሊያደበዝዛቸ አይችልም።

ታሪኮቹ የዓለም ታሪክ ተመራማሪዎች ሀብት ሆነዋልና የየትኛውም አገር ዜጋ አሳምሮ የሚጽፋቸው ናቸው። ለዚህም ጥሩው ምሳሌፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንክረስት፣ ጆን ስፔንሰር፣« የኢትዮጵያ ታሪክ» የጻፉት ፖላንዳዊዎቹ አንድርዜን ባርቲኒስኪ እና ዮዓን ማንቴል-ኒየችኮ  ወዘተ የመሳሰሉ ጸሐፊዎች ይወለዳሉ። ይህም የኢትዮጵያ ታሪክ በብዛት የተጻፈው በዐማራዎችም በኢትዮጵያኖችም ሳይሆን በውጭ ሰዎች  መሆኑን ልብ ማለት ያሻል። አፍ እንዳመጣ መናገር የአዋቂነትም የብልኅነትም መለኪያ አይደለም። «ከመጠምጠም መማር ይቅደም » የሚሉት አባቶች ከዚህ ዓይነቱ ስሕተት ላለመውደቅ ነው።

5 «የዐማራው ታሪክ ተረት ተረት ነው።» ላሉት፦
 ከዚህ በላይ በተሰጡት መልሶች የዐማራው በብቸኝነት ዐማራ ነኝ ብሎ አገር የመራበት ወቅት ባለመኖሩ የብቻው ታሪክ እንደሌለው፣ ያለው የአገሪቱ  ታሪክ ፣ እንደ ተሳትፎአቸው፣ እንደ ብዛታቸው  ወዘተ መጠን የሁሉም  ታሪክ ነው። የለም ታሪኩ ሁሉ የዐማራው  ነው ብለው ላጲሶ ለዐማራው ከሰጡት ደግሞ፣ የተሠራው ሥራ ተረት ሳይሆን ዕውነት፣ በጀግኖች ሕይዎት፣ ደም፣ አጥንታና ላብ የተገነባ ሕያው ታሪክ ነው። ይህን ላጲሶ ተረት ተረት ነው ካሉትም፣ ዐማራውን የሚያስከፋው አይሆንም። ምክንያቱም ተረት ተረት የሚመሠረተው ከዕውቀት፣ ከነባራዊ ዓለም፣ ከሰዎች ግንኙነትና አስተሳሰብ የሚመነጭ በመሆኑ፣ ዐማራው ባለው ሠፊ ዕውቀቱና የማድረግ ጥረቱ የተረት ባለሀብት መሆኑ ዕውነት ነው። ተረት ተርት እኮ ዕውቀት በተለያዩ መንገዶች ከትውል ወደ ትውልድ የሚተላለፍበት ነው። ላጲሶ የዐማራውን ታሪክ ተረት ተረት ነው ሲሉ የኦሮሞውን ምን ሊሉት እንደሚችሉ የሚያውቁት እራሳቸው ብቻ ናቸው። የዐማራውን ታሪክ ተረት ተረት ነው ሲሉ ሁለት ነገሮችን የሳቱ ወይም የካዱ መሆናቸው ይስተዋላል።

አንደኛው ለታሪክ ምንጭነት ከሚያገለግሉት ጉዳዮች አንዱ « ተረት ተረት» በንግግር ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሸጋገሩ ትውፊት የሚባለው ነው። ይህ በተባበሩት መንግሥታት ሳይቀር ተቀባይነት ያለው የማስረጃ ዘዴ ነው። ሁለተኛው ራሳቸው የኦሮሞን ወረራ፣እርሳቸው «ፍለሳ» በማለት  የወርቅ ቅብ ይቀቡታል፣ ከፍተኛ ምንጭ አድርገው የተጠቀሙት «የኦሮሞ አባቶች ከትውልድ በቃል ተላለፈልን» ያሉትን ትውፊት ወይም ተረት ተረት ነው። እነዚህን እንዴት ሳቱ? እርግጠኛ ነኝ ስተው ሳይሆን፣ ክደውና ወያኔ የጫናቸውን እርሳቸውም በምድጃ ዙሪያ ከወላጆቻቸው ተኮትኩተውበት ያደጉት ፀረ-ዐማራ አቋማቸው ወጥሮ የያዛቸው ሆኖ እንደሆነ መጠራጠር አይቻልም። ዐላማቸው ወይም የአባባላቸው መሠረቱ የዐማራውን ማንነት በማንቋሸሽ፣ ትውልዱን አንገት ያስደፋል ከሚል ወያኔአዊ አመለካከት የተቀዳ ለመሆኑ መጠራጠር አይቻልም።

ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው ተረት ተረት ወይም ትውፊት የታሪክ ምንጮች ከሆኑት አንዱ ነው። ይህ በብዛት የሚገኘው ደግሞ የዳበረ ቋንቋ፣ ባህል፣ ሥነጽሁፍ፣ ማኅበራዊ መስተጋብር ያለው፣ ነገሮችን ከተለያዩ አቅጣጫዎች የመመልከትና የመመዘን ባህልና አመለካከት ያዳበረ፣ ክስተቶችን ከተለያዩ አቅጣጫና ማዕዘን የማየት፣ የአመላካከት ምጥቀትና ስፋት ያለው ማኅበረሰብ ይጠይቃል። በዚህ ረገድ፣ ዐማራው  አንፃራዊ በሆነ መልኩ፣ ቋንቋው የዳበረውና ባህሉ የደረጀ መሆኑ ፣ በአካባቢውና በዓለም ዙሪያ ለሚከሰቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ባህላዊና ሃይማኖታዊ ጉዳዮች በርካታ ጥልቅ ሚስጢር ያላቸው፣ ቀልዶች፣ ተረቶች፣ አባባሎችና ምሳሌዎች የዐማራው ነገድ ማዳበሩ ዕውነት ነው። ይህ ደግሞ የዕድገት መገለጫ፣ በተለያዩ መንገዶች ሀሳብን ማሰራጫ ዘዴ እንጂ፣ ዋጋ-ቢስ ክስተት ወይም ሁነት አይደለም። እናም  ተረት ተረት ትውልድን አንገት የሚያስደፋም፣ የሚያሸማቅቅም አይደለም። ያኮራል እንጂ! ስለሆነም ዐማራው በታሪኩ፣ በባህሉ በቋንቋው የሚኮራውን ያህል በተረት ተረቶቹም ይኮራይ፤ ይመካልም።

ምክንያቱም ተረት ተረት ነገሮችን በቀላሉ ለሕፃናት እያዝናኑ ማስተማሪያ ናቸው። ነገሮችን በምሳሌ ማሳያ፣ ረጅሙን ባጭሩ፣ ረቂቁን በገሐዱ፣ ውስብስቡን በቀላሉ ማሳወቂያ ዘዴ ነው። ወይም ሀሳብን በረቀቀና በተመሰጠረ ቅኔና ወርቃወርቅኔ፣ ሰም-ለበስ በሆነ መንገድ ሰዎች ሀሳባቸውን የሚገልጹበት፣ የሚያሞካሹበት፣ ብሶትና ቸግራቸውን የሚገልጹበት ነው። ይህ በተጨባጭ ነገሮች ላይ የሚመሠረት እንጂ በምናብ አይደለም። ላጲሶ ተረት ተረት ሲሉ ውሸት ማለታቸው መሆኑ ግልጽ ነው። ይህን አባባል የኩሩው፣ የጀግናው፣ የሆደ-ሠፊውንና ለአንድነት ቀናዒ የሆነው የዐማራውን ነገድ አባል ቀርቶ፣ የእርሳቸው ነገድ አባሎች ፣የሚያፍሩበት እንጂ፣የሚመኩበትና የሚኮሩበት ይሆናል ተብሎ አይታሰብም።

ዶ/ር ላጲሶና መሰሎቻቸው ይኸን ዓይነቱን ነገሮች ደጋግመው የሚሉት፣ የዐማራው ልጆች ስለአባቶቹ የሚባሉት ነገሮች ትውልዱን ያዋርዳሉ፣ አንገቱን ያስደፋሉ መስሏቸው ይሆናል።  ነገሩ የተገላቢጦሽ ነው። በዐማራው ጠላቶች የሚባሉት ሁሉ ዐማራው የሚኮራባቸው እንጂ ፣የሚያፍርባቸው አይደሉም።
ነፍጠኛ ሲሉ ነፍጠኝነት የሚያሳፍር ወይም የሚያዋርድ መስሏቸው ነው። አዎ! ዐማራው ነፍጠኛ ነው። ነፍጠኝነቱን ጠቅለው ለዐማራው ከሰጡት ያኮራዋል ፣ይመካበታል እንጂ፣ አያፍርበትም። ምክንያቱም የነርሱ አባቶች የከብት ጭራ ተከትለው፣ትኩስ ወተት ከዕርጎ ጋር እያፈራረቁ እየጠጡ ተኝተው ሲያድሩ፣ የእኛ አባቶች የሌሊቱን ቁር፣ የቀኑን ሐሩር፣ ተቋቁመው፣ እግራቸውን ለጠጠር ፣ ደረታቸውን ለጦር ሰጥተው፣ የአገርን ዳር ድንበር ከወራሪ፣ የሕዝብን ሐብት ከነጣቂ ይጠብቁ ነበርና! የእኛ አባቶች ለራሳቸው ሳይሆን ለገርና ለወገን ሕይዎታቸውን ቤዛ ያደረጉ ነበሩና! ተረት ተረት ይሉናል።

አዎ ተረት እናውቃለን። እነርሱ ተረቱን ለመሥራት አንድ ነገር መሥራት ይኖርባቸዋል። ያን ካልሠሩ ተረቱ መነሻ አይኖረውም። መነሻ ከሌለው ደግሞ መቋጫ አይኖረውም። ስለዚህ ተረት ለመናገር መነሻው የላቸውም። ላጲሶ ይህን ሲሉ  ዐማራው እንዲህ እንደሚያስብ ስላልገባቸው የሰደቡና ያዋረዱ መስሏቸው አመስግነውናል፣ ታሪካችን ነውና ይገባናል! በፀጋ ተቀብለነዋል!

6  « የዐማራ ገዥዎች ታሪኩን አጨማለቁት» ላሉት፦
 ተደጋግሞ ለማለት እንደተሞከረው፣ የራሱን ታሪክ የጻፈ ገዥ የለም። ዐማራው ብቻውን አገር ገዝቶ አያውቅም። ለብቻውም ታሪክ አልጻፈም። የተጻፉት ታሪኮች በየጊዜው በነበሩ የጽሑፍ ሙያተኞች ነው። የሚጻፈው ታሪክ ደግሞ ታሪክ የሠሩትን ነው። ታሪክ ሣይሠራ ታሪክ አይጻፍም። ስለሆነም እኔ ዐማራ ነኝ ብሎ ራሱን ገልጾ፣ የጻፈ ሰው ስለሌለ የተጻፈው ዐማራ ጻፈ ብሎ መናገር ተገቢ ካለመሆኑም በላይ ወንጀልም ነው።  ከሁሉም በላይ የቃሉ አጠቃቀም የመደዴ ሰው ነው። ኢትዮጵያም ሆነ ዐማራው የሚያኮራ እንጂ፣ የተጨማለቀ ታሪክ የላቸውም። ከላይ የተጠቀሱት የጦርነት አውድማዎች፣ የነዐድዋ፣ የነማይጨው፣ የነመቅደላ፣ የነዘንተራ፣ የነሽብራኮሬ ወዘተ የሚያኮሩ እንጂ የሚያሳፍሩ አይደሉም። ይህ የሚያሳፍራቸው ለጣሊያን ያደሩ የባንዳ ልጆችና በአምስት አመቱ የአርበኝነት ትግል ወቅት ከሱዳን ጋር ተቀላቅለው እንግሊዝ እንዲገዛቸው ደብዳቤ ያስገቡት የባንዳ ልጆች ብቻ ናቸው። እናም ዐማራው የኢትዮጵያ ፈርጥና ድንቅ ታሪክ ሠሪ እንጂ አጨማላቂ አይደለም። የተጨማለቀ ታሪክ ካለ ማን እንዳጨማለቀው የሚያውቅ ያውቀዋል። ማን ነበር የአምስት አመቱ አርበኛ? ደቡብ ወይስ ሰሜን? ለዚህ መልስ ላጲሶ የፕሮፌሰር ባሕሩ ዘውዴን የኢትዮጵያ ታሪክ መጽሐፍ በማገላበጥ እንደሚያገኙት ልጠቁማቸው እወዳለሁ።

7 « ከኦሮሞው መሬት ላይ ዐማራው ሠፈረ፤ አዲስ አበባ የኦሮሞ ናት፤» ስላሉት፦
ይህ ታላቅ ክህደት ነው። ሸፍጥ ነው። ሲበዛም በኦሮሞ ላይ ምፀት ነው። ዶ/ር ላጲሶ « ታላቁ የማኅበረሰቦች ፍለሳ፣ ከ1520 እስከ 1660 ዓም» በሚል ርዕስ ባዘጋጁት ጥናት እንዲ ብለዋል።
« የኢትዮጵያ ጥንታዊ የባሌ፣ የደዋሮ፣ የአዳል፣ የሸርካ፣ የፈጠጋር፣ የማያ፣ የዳሞት፣ የጋፋት፣ የቦሻ፣ የእናርያ፣የጎንጋ እና የቢዛሞን ነባር ማኅበረሰቦች ከእያካባቢያቸው አንድም ጠፍተዋል፣ወይም በኦሮሞ ፣በሶማሌና ባፋር ተውጠዋል።» ይላሉ። አይይዘውም፣ የግራኝ አሕመድ ጦርነት እና የታላቁ ማኅበረሰቦች ፍለሳ፣-- ሦስቱ የሶማሌ፣ የአፋርና የኦሮሞ ማኅበረሰቦች በሌሎች ላይ ሠፊ መስፋፋት አድርገዋል። ከሦስቱ ማኅበረሰቦች በተለየ ሁኔታ ኦሮሞው እጅግ ሠፊ አካባቢን መያዙን አስረድተዋል።»

የኦሮሞ ማኅበረሰብ ምንጩ ከየት እንደነበርና ከየት ተነስቶ የት እንደደረስ እንዲህ ይላሉ። የኦሮሞ ሕዝብ በአፍሪካ ቀንድ ለመጀመሪያ ጊዜ በታሪክ ሰነድ ``ጋላ`` በሚል ስም ተጽፎ የተገኘው በ16ኛው ምዕተ ዓመት መሆኑን ገልጸው፣ ይህም በዘመኑ በሬቱማና ቦረና በተባሉ ሁለት ጎሳዎች የተከፈለ ማኅበረሰብ እንደነበር አስረድተዋል። ላጲሶ አያይዘው እንዳስረዱት፣ እስከ ዛሬ ድረስ የተገኙት የሰነድ ፣የሊንጉዊስትክ እና የትውፊት ማስረጃዎች በአንድነት እንደሚያመለክቱት ማኅበረሰቡ (ጋላ) በመጀመሪያ በፍለሳ ስምሪት የተንቀሳቀሰው በደቡብ ምሥራቅ በዓባያ ሐይቅና በገናሌ ወንዝ መካከል በዛሬው የሲዳሞ ቦረና አካባቢ እንደሆነ ያረጋግጣሉ። ይህን «የኢትዮጵያ ታሪክ በ16ኛው ክፍለ ዘመን» በሚል ርዕስ የጻፉት አቶ ይልማ ዴሬሣ እና የዘመኑን ታሪክ ያጠኑ የታሪክ ጸሐፊዎች ይስማሙበታል።

ይህ ዘመን እኤአ ከ1520 እስከ 1620  ባለው ጊዜ ውስጥ ኦሮሞዎቹ  በዚያን ጊዜው ስማቸው ጋሎቹ  ከአፍሪካ ቀንዱ ጫፍ ተነስተው ኤርትራ ድረስ በወረራ መድረሳቸውን ላጲሶ እያመኑ፣ አዲስ አበባ የኦሮሞዎቹ ብቸኛ  አገር እንዴት ልትሆን  እንደምትችል ማስረጃ የላቸውም። ከወረራው በፊት በአዲስ አበባ  ወይም ፊንፊኔ ወይም ሸገር የትኞቹ ነገዶች ይኖሩ እንደነበር በግልጽ ይታወቃል። የዐማራዎቹ፣ የሜያዎቹ፣ የአርጎባዎቹ፣ ወዘተ ነበረች፣
ከዚህ ላይ ላጲሶ የኦሮሞ ፍለሳ እያሉ ደጋግመው ሲናገሩና ሲጽፉ ይደመጣሉ፣ ይታያሉ።  ጋሎቹ (ኦሮሞዎቹ ) ወረሩ እንጂ፤ አልፈለሱም። ከዚህ ላይ የሁለቱ ቃሎች ማለትም ወረራ እና ፍልሰት(ፍለሳ) የሚሉት ተገቢ ትርጉም የሚያሻቸው ናቸው። ወረራ ስንል አንድ ቡድን፣ ማኅበረሰብ አስቀድሞ አስቦና ተዘጋጅቶ አንድን አካባቢ፣ የራሱ ያልሆነን በኃይል አስገድዶ፣ አስሮና ገድሎ የራሱ የሚያደርግበት ዘዴ ነው። ቅሚያ፣ ዝርፊያ፣ንጥቂያ ነው። ፍልሰት ሲባል ደግሞ አንድ ማኅበረሰብ በሰው ሠራሽ ወይም በተፈጥሮ ችግር ሳቢያ ባካባቢው መኖር ሲያቅተው በቡድን ወይም በተናጠል ወደ አንድ የራሱ ወዳልሆነ አካባቢ ሂዶ ከነባሩ ሕዝብ ጋር ተስማምቶ ለመኖር የሚችልበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው። ከዚህ የጽንሰ ሀሳብ ግንዛቤ ስንነሳ ፣ ጋሎቹ ከጥንት ከአፍሪካ ቀንድ ጫፍ ተነስተው ወደ ወላቡ እና ኦዳ ነቤ የመጡት በሁለት ምክንያቶች ነው። አንዱ ኑሮአቸው በከብት ርቢ ላይ የተመሠረተ ዘላኖች ስለነበሩ፣ ለከብቶቻቸው መኖና ውኃ  ባካባቢያቸው በቂ ሆኖ ስላላገኙት፣ በቂ ውኃና መኖ ወዳለበት በፍለሳ መልክ የመጡ ናቸው። ሁለተኛው ምክንያት የጥንት ጎረቤቶቻቸው ሱማሌዎቹና ባንቱዎቹ በተመሳሳይ በዘላንነት የሚኖሩ በመሆናቸው፣ በግጦሽ መሬትና በውኃ ተደጋጋሚ ግጭት ያደርጉ ስለነበር ያን መቋቋም ሲሳናቸው አካባቢያቸውን ለመልቀቅ መገደዳቸው ናቸው። በሁለቱም በኩል ያደረጉት አካባቢን መልቀቅ በአመዛኙ ፍለሳ ነው።

በሌላ በኩል ከወላቡ እና ከኦዳ ነቤ ወደ ፈጠጋር፣ ደዋሮ፣ እና ኤርትራ ድረስ ያደረጉት ጎዞ በፍልሰት ሳይሆን በወረራ ነው። ወላቡ ከገቡ ጀምሮ ባካበቱት የከብት ሀብትና ባገኙት  ሰላም የተነሳ የሕዝባቸው ቁጥር በመበራከቱ ጥንት ከነበሩበት ቦታ ሲንቀሳቀሱ ያልነበራቸውን አዲስ «ገዳ» የተሰኘ የአስተዳደር፣ የወታራዊና የፍርድ ሥርዓት የሚያከናውን መዋቅር መሠረቱ። የገዳው ዋና ተግባር ወንዶችን በዕድሜ ክልል አደራጅቶ ሠፊ መሬት በወረራ መያዝ የሚለው ነበር። ለዚህም እያንዳንዱ በገዳው ሥርዓት ውስጥ የገባው ወንድ ልጅ በፈረስ ጉግስና ግልቢያ፣ ጠላትን በማጥቃትና በመከላከል፣ በጦር ውርወራን ምከታ ይሰለጥናል።

የእያንዳንዱ ገዳ ጀግንነት መመዘኛውም ወሮ የያዘው መሬት ስፋት ስለሆነ ሁሉም የማኅበረሰቡን ሞገስ  ለማግኘት ራሱን ያዘጋጃል። በሌላ በኩል በኦሮሞ ባህል ትልቅ አውሬ ያልገደለ ወይም ከነገዱ ውጭ ያለ ሰው ካልሰለበ ሚስት አያገባም። ፀጉሩን አይላጭም። ይህ ደግሞ በማኅበረሱ ዘንድ የበታችነት  መገለጫ በመሆኑ ሁሉም አውሬ ለመግደል ወይም ለመስለብ የተጋ ይሆናል።

በዚህም መሠረት ከ1515 እስከ 1535 ባለው የግራኝ ወረራ የተዳከመውን ሕዝብ የግራኝን እግር በመከተል የወረራ ሥራ በማካሄድ እስከ ፈጠጋርና ደዋሮ ድረስ ደረሱ። ከዚህ በተጨማሪ የገዳው ሥርዓት ከጎሣው ውጭ የሆነውን ነገድ ወሮ ከያዘ በኋላ «ሞገሣ» በሚሉት ሥርዓታቸው ጋላ (ኦሮሞ) ያደርጉታል። ከዚህ በተጨማሪ «ጉዲፉቻ» በሚለው ዘዴ የሌሎች ሰዎችን ልጆች በማሳደግ ኦሮሞ ያደርጋሉ። በአጠቃላይ ኦሮሞቹ ከወላቡ ወደ መላው አገሪቱ የተስፋፉት በወረራ፣ በኃይል ነው። ቁጥራቸው የበዛው  ደግሞ አንደኛ ወረው የያዙትን ኅብረተሰብ በመስለባቸው ፣ ሁለተኛ በወረራው ወቅት በመግደላቸው፤ ሦስተኛ በሞጋሣና በጉዲፍቻ ኦሮሞ በማድረጋቸው፣ አራተኛ አንድ ሰው ብዙ ስለሚገባ በከፍተኛ መጠን መዋለዳቸው ወዘተ ናቸው።

የኦሮሞዎቹ አመጣጥና ስርጭት ወረራ መሆኑን አቶ ተክለጻዲቅ መኩሪያ፣ አቶ ይልማ ዴሬሣ፣ ዶ/ር ተወልደ ትኩዕ እና መሰሎቹ ይስማማሉ። ከዚህ የሚለዩት የኢትዮጵያን ነባር ታሪክ ጥዬ አዲስ ታሪክ እጽፋለሁ የሚሉት ላጲሶ ብቻ ናቸው።
8  « ክብረ-ነገሥትና ፍትሓ ነገሥት ተረት ተረት ነው፤» ስለማለታቸው፣
የነዚህን መጽሐፎች ትርጉምና ዓላማ አንብቦ ለሚረዳ ሰው፣ የዚያን ዘመኖቹን አባቶች ጥልቅ  የአስተዳደር፣ የፍርድ አሰጣጥ፣ የሃይማኖታዊ ሥርዓት፣ የባህልና የማኅበራዊ ግንኙነት ስለነበራቸው ችሎታና ዕውቀት የቱን ያህል  ምጡቅ እንደነበር ይረዳል።  እነዚህም መጽሐፍት ተረት ተረት ወይም ዉሸት ናቸው ለማለት በቅድሚያ የሚሉትንና የያዙትን መሠረታዊ ዓላማ ከዚያን ጊዜው ነባራዊ ሁኔታ ጋር አገናዝቦ መረዳት ያሻል።  ሲነበቡ ደግሞ ጸሐፊዎቹን በዐማራነት ፈርጆ ሳይሆን፣ ምን ነገር በውስጣቸው እንደያዙ፣ ለምን ዓላማ እንደተዘጋጁ፣ እንዴት እንደተዘጋጁ፣ አበጥሮ ለማወቅ ከልብ በመነጨ ፍላጎት መሆን አለበት። እንደ ላጲሶ አስቀድሞ አቋም ወስዶ ማንበቡ ከተፈላጊው ዕውነት ላይ አያደርስም። አስቀድሞ ፍርድ ሰጥቷልና። መጽሐፎቹ በራሳቸው ፣በዕውኑ ዓለም ያሉ ስለሆነ እያንዳንዱ ተመራማሪ እነርሱን በማገላበጥ ሐቁን ሊረዳ ይችላል።  መጽሐፎቹ በደንብ ቢፈተሹ ኢትዮጵያውያን ልንከተለው ስለሚገባን የአስተዳደር፣ የፍትሕ አሰጣጥና የማኅበራዊ አኗኗር ዘዴ ሁነኛ መሠረት ሊያስጨብጡ እንደሚችሉ ዕውነት ነው። የተጻፉት ከዚያን ጊዜው የሕዝቡ አኗኗር፣ ባህል፣ እምነትና አስተዳደር ጋር ተገናዝበው ስለሆነ፣ በሁለንተናዊ መልኩ የተቋረጠ እንኳን ቢሆን፣ ክሩ ውሉ ሳይጠፋ ቢፈተሹ ለገጠሙን የመበታተን አደጋ መፍትሔ ይገኛቸዋል ብየ አስባለሁ።

ከዚህ በተረፈ ዶ/ር ላጲሶ መጽሐፎቹን ተረት ተረት ናቸው ያሉበት ምክንያት ይገባናል። ምክንያቱ ግልጽና አንድ ነው። እነዚህ መጽሐፍት የተመሠረቱበትን ሕዝብና አገር ለማፍረስ መሆኑ ማንም ይስተዋል አይባልም።  ላጲሶ ከወያኔ የተሰጣቸውን የቤት ሥራ ለመወጣት ነው። መለስ የኢትዮጵያ ታሪክ መቶ ዓመት አይሞላውም ላለው፣ እነዚህ መጽሐፍቶች የዚህ አስተሳሰብ ማፍረሻ ቋሚ ሰነዶች በመሆናቸው፣ እነርሱን ዋጋ ለማሳጣት የተሰነዘረ የጥፋት መልዕክት ነው።

9 « ዐማራው የውጭ አስተማሪ ቀጥሮ ተረት ተረት ፈጠረ» ስላሉት፥
በዕውነቱ ይህ አባባል በጣም የሚያስገርም፣ የሚያሳዝንም ነው። በላጲሶ አባባል፣ እርሳቸውን ያጠመቃቸውን ፓስተር ቀጥሮ ያመጣቸው ዐማራ ነው፤ በአክራሪነት ከኢትዮጵያ የመገንጠልን ሀሳብ የሚያቀነቅኑትን ኦሮሞዎች ለያዙት አቋም ኮትኩቶ ያሳደጋቸውንና « ኦሮሞ ብሉ ኦሮሚያ» የሚል አገር እንዲፈጥሩ ያስተማረና ንድፈሀሳባዊ ቀመር ቀምሮ ዛሬ ለደረሱበት ደረጃ ያበቃቸውን ጀርመናዊ ዮሓን ክራፍን ቀጥሮ ያመጣው ዐማራው ነው፤እንደማለት ነው። ይህ ሲበዛ ዐማራውን መናቅ ነው። በሌላ በኩል « ሴት የላከው ጅብ አይፈራም » ዓይነት ነው።  ይህ የላጲሶ አባባል ከራሳቸው ጋር ይጋጫል። ባንድ በኩል የተጻፈው ታሪክ በዐማሮች ነው፣ የጻፉትም የራሳቸውን ነው፣ እርሱም ተረት ተረት ነው አሉ። ከዚህ ላይ ደግሞ የውጭ ሰዎች ቀጥሮ ተረት ተረት ፈጠረ አሉ። እንደውነቱ ከሆነ ዐማራው የራሱን ታሪክ ለመጻፍ የውጭ ሰዎች መቅጠር አያሻውም። አልቀጠረምም። የትኛው መጽሐፍ በምን ቅጥረኝነት እንደተጻፈ ሊያስረዱን ይገባል። « ይቺ ወፍ አዙራ ነፋች ይላል ያገሬ ሰው፣ የነገር ተገላቢጦሽ ሲሰማ» ይህ ዳርዳርታ እርሳቸው በወያኔ ተቀጥረው( ተገዝተው) ያለፈውን ታሪክ ጥለው የወያኔን ታሪክ እየጻፉ መሆኑን እየነገሩን መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። 

10 « የምኒልክ ታሪክ የኢትዮጵያi ሳይሆን፣ የዐማራ የበላይነት ነው» ስላሉት፦
ይህ አባባል ራስን ከኢትዮጵያዊነት የመነጠልና ወያኔዎቹ የሚያራምዱት የፀረ-ዐማራ ዘመቻ አካል ነው። የምኒልክን ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን፣ አስደናቂ ሰውነትን፣ ማንቋሸሽ ነው። ላጲሶ «የውጪ ኃይሎች ግፊትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ አንድነት ትግል ከ1855 እስከ 1900 ዓም» በሚል ርዕስ ባሳተሙት ጥናት ውስጥ ስለምኒልክ እንዲህ ብለዋል።

   « እስከ 1889 ዓም እኤአ ባሉት ዓመታት ከሆለታ፣ ከእንጦጦና ከአዲስ አበባ ማዕከሎች በተንቀሳቀሱ ዘመቻዎች አማካኝነት የመጫ፣ የጉድሩ፣ የሊሙ፣ የእናርያ፣ የጎማ፣ የጌራ፣ የጅማ፣ የሌቃ፣፤ በስተምዕራብ ደግሞ ፣የቱለማን፣ የሰዶን፣ የማርቆን፣ የጉራጌን፣ ፤በስተደቡብ፤ የቀበናን፤ በደቡብ ምሥራቅ፣ የአርሲና የሐረርን አካባቢዎች በግዛታቸው አጠቃለሉ።» ካሉ በኋላ ምኒልክ የጣሊያንን ቅኝ ገዥ በ1896 ዐድዋ ላይ ከ120 000 እስከ 145,000 የሚገመት ሠራዊት አንቀሳቅሰው ድል ማድረጋቸውን አብስረዋል።
ይህ ድል ደግሞ የዐማራው ብቻ አይደለም። ሲጠብ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፤ሲሠፋ የአፍሪካና የጥቁር ሕዝቦች እንደሆነ መስክርነት ሰጥተዋል። ዕውነታውም ይኸ ነው። ዓለም የሚያውቀው ዕውነተኛ ታሪክ ይህ ሆኖ እያለ ፣ በምን ታምር ነው የምኒልክ ታሪክ የዐማራ የበላይነት ታሪክ የሚሆነው? ዶ/ር ላጲሶ ምኒልክን የገባር ሥርዓትን በመትከል ይከሳሉ።  የሰው ልጅ ጠባይ ሆኖ ወይም የከሐዲዎች መለያ የቱ እንደሆነ በቅጡ ባላውቀውም ብዙውን ጊዜ ሰዎች የተሠሩ መልካም ነገሮችን ትተው ወይም ረስተው ወይም ዋጋ ባለመስጠት ብዙ ጊዜ የሚያነሱት ከመልካሞቹ ጋር ሲነፃጸር ሚዛን የማይደፋውን ተበደልን ፣ክፉ ነገር ተሠራብን የሚለውን ነው። አዎ! ምኒልክ የገባር ሥርዓትን መሥርተዋል። በዚያን ጊዜ መንግሥታዊ ተግባሮቻቸውን ለመወጣት ከዚህ የተሻለ አማራጭ አልነበራቸውም ወይም አያውቁም። የገባር ሥርዓት ጣሉብን እያሉ የሚከሷቸው ወገኖች ግን የማያነሱት ምኒልክ ከሠሩላቸው መልካም ነገሮች መካከል አንዱ የየጎሣቸው ባላባቶችና ገዥዎች እንደፍየልና በግ እያራቡ ቋንጃቸውን እየቆረጡ ለባርነት ይሸጧቸው የነበሩትን «ሁሉም የሰው ልጅ የአምላክ ፍጡር ነው። ሁሉም የአምላካ ባርያ እንጂ፣ ሰው የሰው ባርያ የለውም» ብለው ከባርነት ነፃ ያወጡዋቸው ምኒልክ ናቸው። በዚህ ረገድ የጎሣቸውን አባሎች በባርነት ይሸጡ የነበሩት የሚከተሉት ዋነኞቹ ነበሩ፦
1)     የጉራጌው ኢሚር አማር ባቅሳና ከርሱ በፊት የነበሩት ኢሚሮች፣
2)    የሓዲያው ኢማም ሐሰን ኤጃሞና ከእርሱ በፊት የነበሩት ኢማሞች፣
3)   የከምባታው ወማዕ ድልበዩ ደጎዬና እና ከርሱ በፊት የነበሩ ወማዕዎች፣
4)   የወላይታው ካዎ ጦና ጋጋ እና ከእርሱ በፊት የነበሩ ካዎዎች፣
5)   የከፋው ታቶ ጋኪ ሼሮቾ፣ እና ከእርሱ በፊት የነበሩ ታቶዎች
6)   የጅማው ሱልጣን አባጅፋር እና ከእርሱ በፊት የነበሩት ሡልጣኖች፤
7)   የለቀምቱ  ደጃዝማች ሞሮዳ ባካሬ ፣
8)   የሐረሩ ኢሚር አብዱላሂ እና ከርሱ በፊት የነበሩት ኢሚሮች፤
9)   የቄለሙ  ደጃዝማች ጆቴ ቱሉ ነበሩ።

ምኒልክ እነዚህን የአካባቢ ገዥዎች እሽ ብለው የገበሩላቸውን ግዛታቸውን እየፈቀዱ፣ አሻፈረኝ ያሉትን በኃይል በማስገደድ በፍላጎታቸው ሥር በማዋል የኢትዮጵያን አንድነት ትንሣዔ ዕውን ከማድረጋቸው በተጨማሪ ባርነትን በጽኑ በመኮንን አስቀርተዋል።  በዚያን ዘመን የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ይህን ታላቅ ሥራ የሠሩትን ንጉሥ መልካም ዝናና ታሪካቸውን ማጉደፍ ራስን አለማወቅ ነው። ለዚህም ነው ታዋቂው የታሪክ ምሑር ዶ/ር ኃይሌ ላሬቦ « ምኒልክን ብትወቅሱ ማንነታችሁን ትረሱ» በሚል ርዕስ ለምኒልክ ከሳሾችና ወቃሾች ዕውነታውን ለማሳወቅ የጣሩት።

በሌላም በኩል የጋሞው ተወላጅ አቶ አሰፋ ጫቦ ደጋግመው በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች እንዳስረዱት ምኒልክን ተከትሎ ወደ ደቡብ፣ ምዕራብና ምሥራቅ የተጓዘው ነፍጠኛ አብዛኛው ኦሮሞ መሆኑን ስም በመጥቀስ ነግረውናል። ምኒልክ እነዚህን አካባቢዎች ወደ ነባር አንድነታቸው በቀላቀሉበት ዘመቻ ዓመቶች (1857—1879) የሸዋ ንጉሥ እንጂ፣ የኢትዮጵያ ንጉሠ-ነገሥት አለመሆናቸው ይታወቃል። በነዚህ ዓመታት በርካታ የዐማራ ሕዝብ ያለባቸውን ጎጃምን። ጎንደርንና ወሎን አይገዙም። ጎጃም የንጉሥ ተክለሃይማኖት ግዛት ነው። ወሎ የራስ አርኣያ ዮሐንስ ቀጥሎም የራስ ሚካኤል ዓሊ ግዛት ነው። ጎንደር የንጉሠ-ነገሥቱ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ እልፍኝ ነው። በዚህም ምክንያት ከነዚህ አካባቢዎች ምኒልክን ተከትሎ የዘመተ ነፍጠኛ የለም። የዐማራው ነፍጠኛ ከመንዝና አካባቢው ነዋሪ ከሆነው ሕዝብ ነው። ይህ ደግሞ ለዘመቻው በቂ የሆነ የሰው ኃይል ምንጭ 
አይደለም።

አብዛኛው በማስገበሩ ሥራ ላይ የዘመተው ኦሮሞው ነው። ይህም ያለምክንያት አይደለም። የዘመቻው መሪዎች ራስ ጎበና ዳጬ፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዲ፣ ፊታውራሪ ገበየሁ ተክሌ፣ ደጃዝማች ባልቻ ሣፎ ሥር የተሰለፈው የኦሮሞና የጉራጌ ነፍጠኛ ነው።  የአካባቢው ገዥዎች በሰላም ለምኒልክ የገቡት የነበራቸውን ሥልጣን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ሲደረግ፣ አሻፈረኝ ያሉት ደግሞ በኃይል ተንበርክከው በላያቸው ላይ የምኒልክ ታማኞች ሲሾሙ፣ ሌላው አገር ጠባቂው ሠራዊት በነፍጠኝነት በየአካባቢው መመደቡ ዕውነት ነው። ይህ ነፍጠኛ ግን በዘር ዐማራ አልነበረም። ሁሉም ክርስትናን የተቀበሉ በመሆናቸው እነርሱ ራሳቸውን እንደአማራነት ሲቆጥሩ፣ በሃይማኖቱ ምክንያት፣ በነፍጠኝነት የተሠሩበትም አካባቢ ዐማራ አላቸው እንጂ፣ በዘር ዐማራ በደቡብና በደቡ ምዕራብ አልተመደበም። ይህ ደግሞ የዐማራውን የበላይነት የሚያመለክት አይደለም። በየትኛውም ጊዜ ዐማራው ካንድ አካባቢ ሀብት አፍርቶ ወደ ራሱ ክልል ሀብት ያሸሸበትና አካባቢውን ያለማበት ሁኔታ የለም። ይህ በሌለበት ሁኔታ የዐማራ የበላይነት አሰፈኑ ማለት የሕዝብን የማወቅ አቅም ዝቅ አድርጎ መመልከት ነው። ዐማራው ንብ አይደለም። ንቦቹ ዛሬ ተፈጥረዋል። ከሩቅ አገር ሂደው ሀብት ዘርፈው ወደ በቀሉበት የሚያሸሹ። ይህን ላጲሶ ያስተዋሉት አይመስልም። ምኒልክም በዚህ አይታሙም።

11 « ለኦሮሞ ታሪክ ቅድሚ እሰጣለሁ» ስላሉት፤

ይህ የርሳቸው የምርጫ ጉዳይ ነው። ኦሮሞ ግን የኢትዮጵያን ነገዶች ወሮም፣ ሰልቦም፣ በሞጋሣና በጉዲፍቻ ፣ በውድም በግድም በነገዶች መካከል መዋሐድና መቀላቀል እንዲፈጠር አድርጓል። ይህ ዕውነት ነው። ይህ ግን የአገሪቱ የታሪክ መሠረት ነው አያሰኘውም። የአገሪቱ ታሪክ አንዱ አካል እንጂ! የኢትዮጵያ ታሪክ ሙሉ የሚሆነው ከጥንታዊ ነዋሪዎች ጀምሮ በሂደት እየተቀላቀሉ የመጡ ነገዶችና ጎሳዎችን አካቶ ሲይዝ ነው። ያንድ ነገድ ታሪክ የዚያ ነገድ ታሪክ እንጂ፣ የአገሪቱ ታሪክ አካል ከመሆን ውጪ፣ የአገሪቱ አጠቃላይ ታሪክ ሊሆን ከቶ አይችልም። ኢትዮጵያ የብዙ ነገዶች እናት አገር ናትና!

12  « ከአይሁድ ጋር ያለሴም፣ ኩሺ የሚባለው ነገር ከሃይማኖት ጋር ያለ ተረት ነው/» ስላሉት፦

በመጀመሪያ ዶ/ር ላጲሶ በተረትና በሃይማኖት መካከል ያለውን ልዩነት ያጤኑት አይመስልም። ሃይማኖት የደግና የክፉን፣ የጽድቅና የኩነኔን፣ የሰው ልጅ እንደ ሰውነቱ ማድረግ ያለበትንና የሌለበትን የሚያስተምር ፣የሚያሳውቅ፤ የሰው ልጅን እንስሳዊ ባሕሪ በመግራት ሰዋዊ እንዲሆን የሚመክር ነው። በመሆኑም በዕምነት የሚከተለው ሥርዓት ነው።ይህም በመሆኑ ተረት አይደለም። አማኙ በዕለታዊ ተግባሩ የሚያከናውነው ሥርኦት በመሆኑ ተረት ተረት ሊሆን አይችልም። ላጲሶ የእርሳቸው ጌቶች ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ፣ቀድመው መጥፋት ያለባቸው ተቋሞች ዘውዳዊ ሥርዓት፣ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትና የዐማራው ነገድ በየተራ ተነጣጥለው እንዲመቱ በዘረጉት የረጅም ጊዜ ዕቅድ ውስጥ የተካተተ በመሆኑ፣ ይህን ሃይማኖት በዚህ ስበብ ለማጥፋት ዘመቻውን በታሪክ ተመራማሪነት ስም እየገፉበት እንደሆነ የሚያመላክት ነው።
የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች በኢትዮጵያ ውስጥ ነበሩ። ዛሬም አሉ። የአማኞቹና የሃይማኖቱ ሕልው ሆኖ መኖር በምን ተዓምር ተረት ተረት ይሆናል? በ1983 ከኢትዮጵያ ነቅለው የወጡት በሺዎች የሚቆጠሩት ቤተእስራኤሎች የአይሁድ ሃይማኖት ተከታዮች መሆናቸው ግልጽ ነው። ይህ እንዴት ብሎ ተረት ይሆናል?
የሴማዊ ቋንቋ በኢትዮጵያ ስለመኖሩ ከማንም በላይ የሰበኩና ያስተማሩ ራሳቸው ናቸው። በይሁዲ፣ ሴምና ኩሽ መካከል ስላለው ግንኙነት አውቃለሁ ካሉ፣ ግንኙነቱ መኖር አለመኖሩን በመረጃ ማቅረብና ለሕዝብ ፍርድ መስጠት የራሳቸውና የመሰሎቻቸው ኃላፊነት ነው። በጭፍን ላይ በተመሠረት የዐማራ ጥላቻ ተነስተን ግንኙነቱ ተረት ተረት ነው ብንል የነበረውን ታሪካዊ ሁኔታ የሚለውጥ አይሆንም።

የንግሥት ሣባ እንደ ሰው በምድር ላይ መኖርና ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝ በመጽሐፍ ቅዱስ እና በየመን ታሪክ የተመዘገበ ነው።ግራሃም ኮክ በ1980ዎቹ መጨረሻ በጻፈው «ጽዮንን ፍለጋ» በተሰኘው መጽሐፉ ይህኑ አረጋግጧል።  ላጲሶ ይህን ዕውነታ መሻር የሚያስችል መረጃ ካላቸው ኳሱ በእሳቸው እግር ነው።

13 « የገዳ ሥርዓት ኢትዮጵያን ከገዙ የዐማራ ነገሥታት በላይ ኢትዮጵያን ያጠናከረ ሥርዓት ነው፤» ስላሉት፥
የገዳ ሥራዓት መሠረታዊ ዓላማ ቁጥሩ እየበዛ ለሄደው ጋላ(ኦሮሞ) ነገድ የሚኖርበት ሠፊ ግዛት ወሮ መያዝ እንጂ፣ መንግስታዊ ሥርዓት መሥርቶ የአገሪቱን አንድነት የማጠናከር ግብ ይዞ አለመነሳቱ ይታወቃል። ሆኖም በወረራ ወሮ የያዛቸውን ነገዶች፣ በመጀመሪያ በመስለብ የትውልዱን ተከታታይነት እንዲቀንስ አደረጉ። ከዚህ በማያያዝ ወረው የያዟቸውን ነገዶች «ሞጋሳ» በሚለው አሠራራቸው አስገድደው ጋላ(ኦሮሞ) በማድረግ ማንነታቸውን  አስለወጡ። «ጉዲፍቻ» ብለው በሚጠሩት ደንባቸው መሠረት ደግሞ ወላጆቻቸውን የገደሉባቸውን ሕፃናት የኛ ልጅ በማለት አሳድገው ኦሮሞ ያደርጓቸዋል።  ይህም  ቁጥራራቸውን  በማሳደግ ሠፊ ግዛት  እንዲይዙ ማድረጉ  ዕውነት ነው። የያዙት መሬት ግን የነርሱ የነበረ አይደለም። ነባር ነዋሪዎችን አጥፍተውና ማንነታቸውን አስክደው ነው። ምኒልክ የገባርን ሥርዓት ሲተክሉ፣ ባርነትን አስወግደው ነው። ኦሮሞዎቹ መሬት ሲነጥቁና ማንነት ሲያስለውጡ ለነባር ነዋሪው የሰጡት ነገር የለም።

ገዳ ማለት ሰዎችን፣ ከሰዎችም ወንዶችን ነጥሎ በ5 የዕድሜ ክልሎች የሚያደራጅ ነው። የመደራጀቱ ዓላማም ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን ለነገዱ ከማስገኘት አኳያ የተቃኘ የወረራና የዘረፋ ድርጅት ነው። ጋላዎቹ (ኦሮሞዎቹ) መላዋን ኢትዮጵያ በወረሩበት ዘመን ዋናው የማኅበረሰቡ ኢኮኖሚ ከብት ርቢ ነበር። ይህ ደግሞ ሠፊ መሬት፣ በቂ ውኃ ማግኘትን ይጠይቃል። ይህ በበኩሉ ሠፊ ግዛት ይሻል። የገዳ ሥርዓት የተባለው ዋና ተግባሩ ሠፊ መሬት በወረራ መያዝ ነው። ለዚህም ዓላማው ግብ መጨበጥ ደግሞ ሁሉም የኦሮሞ ወንድ የሆነ ሁሉ ከ8 እስከ 48 ዓመት ዕድሜ ያለው በአምስት የዕድሜ ክልል ተደራጅቶ ወረራን ማካሄድ የዕለት ተዕለት ተግባሩ አደረገ።
በየስምንት ዓመቱ የሚቀያየረው የገዳው ጀግንነትና ለነገዱ ያስገኘው ጥቅም የሚለካው ወሮ በያዘው የመሬት ሥፋት መጠን በመሆኑ፣ ሁሉም ትውልዶች ይህን ግብ ለመጨበጥ በርቶ መዋጋትን ሥራዬ ብሎ ያዘው። ሁሉም ፈረሰኛ፣ ሁሉም ጦር ወርዋሪ፣ ዋናተኛ፣ ቀስተኛ ሆነ። ይህን በተመለከተ አባ ባሕሪይ እንዲህ ይላሉ።« ጋላ ግን እነዚህ ያነሳናቸው ዘጠኝ ወገኖች የሉበትም። ሁሉም ከደቂቅ እስከ ሊቅ ለውጊያ የሰለጠኑ ናቸው። ስለዚህ ያጠፉናል።»

በዚህ መሠረት አገሪቱን ወረው፣ የወረሩትን አካባቢ ነገዶች አጥፍተውና አሸሽተው ቦታውን እነሱ ሠፈሩበት። በኦሮሞ ወረራ ከጠፉና ወደሌላ ከሸሹ ነገዶች ውስጥ ለምሳሌ ዐማራ፣ ሜያ፣ እናርያ፣ ዳሞት፣ ሻካ፣ ወዘተ የሚጠቀሱ ናቸው። ማንም የኢትዮጵያን ሕዝብ የአንድነት አመሠራረት የመረመረ ሊረዳው እንደሚችል፣ ፍልሰትና ጦርነት ሕዝቡ አንድነቱን ከመሠረተባቸው ምክንያቶች ዋነኞቹ መሆናቸውን ይረዳል። በዚህ ረገድ ሁለቱም በተለይም ጦርነት ያደረሰውን መጠነ ሠፊ ጥፋት ከአስገኘው አንድነት ጋር አመዛዝነን በጎ ጎኑን በማጉላት፣ ያለፈና የጠፋ አይመለስምና ወደፊት መጭውን ብሩኅ ለማድረግ፣ አዎ የኦሮሞው ወረራ ለአንድነቱ መሠረት ጥሏል እንላለን። ይህ ግን ቅንነትና ለኢትዮጵያ አንድነት ተጠብቆ መዝለቅ ከሚሹ ወገኖች የሚመነጭ አባባል ነው። በተመሳሳይ ሁኔታ ምኒልክ ያደረጉትን የአገር ግንባታ በዚህ መልክ ሳይመለከቱ ፣የኦሮሞውን ቅዱስ አድርጎ  ፤ የሚኒልክን ሰይጣን ማድረግ  ከማስተዛዘብ አልፎ ያስንቃል። አስተሳሰቡ ሚዛን የጎደለው ብቻ ሳይሆን ፣የሌለው በመሆኑ።

በግልጽ እንደሚታወቀው ዐማራው በአብዛኛው  የክርስቲያን  ሃይማኖት ተከታይ ነው። ይህ ሃይማኖት ደግሞ መሠረታዊ ሕጉ አትግደል ነው። በዚህም የተነሣ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ካልገጠሙት በቀር ለግድያ ራሱን አያዘጋጅም። ፍላጎቱን ለማሳካት ያስተምራል፤ በምሳሌ ያሳያል እንጂ፣ ትውልዱን ለነገዱ ጥቅም ሲል ወታደር አያደርግም። ምኒልክም ሥልጣናቸውንና የበላይነታቸውን በደቡብ፣ በምዕራብና በምሥራቅ የአገሪቱ ክፍሎች ሲያረጋግጡ« እንደአብትህ እደር» አሉ እንጂ፣ ኦሮሞዎቹ እንዳሉት እንደ እኔ እደር አላሉም።

ዶ/ር ላጲሶ እንደሚሉት የገዳ ሥርዓት የተዋጣለት ጥሩ ነው የሚባልለትና የሚዘመርለት አይደለም። ሥርዓቱ በፆታዎች ዕኩልነት አያምንም። ሴቶችን ያገላል። አንድ ወንድ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት ይፈቅዳል። ያበረታታል። ለአቅመ አዳም የደረሰ የኦሮሞ ሰው፣ትልቅ አውሬ ካልገደለ ወይም ከነገዱ ውጪ የሆነ ሰው ካልሰለበ ሚስት አያገባም። ፀጉሩንም አይላጭም። ይህ የዝቅተኝነት መግለጫ በመሆኑ ሁሉም ሰው ለመግደልና ለመስለብ እንዲሰለፍ የሚያደርግ ነው።  የሌሎችን ማንነት አይቀበልም። ስለዚህ ይህ ከምኒልክ አስተዳደር የተሻለ ነበር የሚሉ ምኒልክን የሚጠሉና በሰዎች ዕኩልንት የማያምኑ  ብቻ ናቸው።


Sunday, October 25, 2015

የኢሕአፓ ዘረኝነትና ዛቸው!

ጌታቸው ረዳ

ነብሱ ይማረው በገጣሚ ሃይሉ ገ/ዮሐንስ (ገሞራው) ግጥም ጽሑፌን ልጀምር።
 በመንቃት ላይ ባሉ ፍጡራን መካከል 
ህይወት የምንለው እንደ ጥሬ እህል
 በኑሮ ምጣድ ላይ ቢቆላ ቢማሰል
 የበሰለው ያራል ጥሬው እስኪበስል!! 
(ገጣሚው ገሞራው) 
አሁን ትልቅ አገራዊ ርዕስ በመጻፍ ላይ ስለሆንኩኝ፤ ጊዜ ላለመሻማት ስል ሌላ ቀን በሰፊው እስክመለስበት ጊዜ፤ ሰሞኑ ኢሕአፓዎች በድረገጻቸው በአሲምባ ላይ ስለ እኔ የለጠፉትን ‘ዘረኛና አግላይ ካርቱን” አማራና ኦሮሞን በማናከስ ዘርን ከዘር ለማጨራረስ በወንጀል የሚከሰሰው ኤርትራዊው ተስፋዬ ገበረአብ ጋር እኔን በማነጻጸር “እኝህ ሰው ምን ነካቸው ከአማራ በላይ አማራ! የከለላ ታሪክ ፤ጋጋታ ምን የሚሉት?” በማለት፤ “ትግሬው ለትግሬ” እንጂ ስለ አማራው አያገባውም፤ ሌላው ስለ አማራ የመጨነቅ፤ የመቆም መብት የለውም!’ ከማለታቸው ሌላ፤ እጅግ አስገራሚ ካርቱናቸው ደግሞ “የከለላ ታሪክ” በማለት እኔን ለአማራው ሕብረተስብ እንደ ባዕድ ወገን አድርገው በመሳል፤ ለሰሚው እጅግ አሳፋሪና ዝቃጭ የሆነ የመንደር ብስለታቸውን ለማንጸባረቅ ሞክረዋል።

በፓልቶክ ስሙ “ፋኖ” በመባል ወይንም “አደባባይ” በመባል የሚታወቀው እዚህ ሳንሆዜ ከኔ ጋር የሚኖር ምስኪን የኢሕአፓ ካልትም ሳይቀር፤ “አማራ፤ አማራ ፤የሚሉ ፡ስለ አማራ፤ ስለ ሞረሽ የወገኑ ሰዎች” አማራዎች ሳይሆኑ ከሌላ ጎሳ የተወለዱ የወታደር ልጆች ናቸው” ሲል ከኤርትራዊያን በባሰ መልኩ የዘቀጠ “ዘረኛነቱን” ሲያነበንብ የተደመጠውን በአውድዮ ቀድተው ወዳጆቼ የኢሕአፓ ‘ጉድ አደምጥ” ብለው የላኩልኝም አደምጬ ሰዎቹ ጭልጥ ብለው ወደ ዘር ቆጠራ መግበታቸው አጅግ አዘንኩላቸው።

ኢሕአፓዎች ስለ አርበኛቸው ስለ ማርክሲስቱ ዋለልኝ መኮንን እና ስለ ድርጅታቸው የተቸሁትን ተገቢውን መልስ ጽፈው መከራከር ሲገባቸው፡ የነቁ፤የበሰሉ መስለውኝ የነበሩት ሰዎች ወደ ዘረኛነትና ወደ አሉባልታ ሲገቡ ማየቴ በፕሮፓጋንዳው ዘርፍ እጅግ የወረዱ፤ ቢቆሉ፤ቢቆሉ የማይበስሉ መሆናቸውን ነው የታዘብኩት።

ስለ ኢሕአፓ በሰፊው ለወደፊቱ የምንነጋገርበት ሲሆን፤ ለአሁኑ ግን ለዚህ ዘረኛ እና ዝቃጭ ብስለታቸው አሁንም በድጋሚ ያስታወሰኝ ነገር ቢኖር “ገዴዎን ለቪን” የተባለው እስራላዊው የሰው ልጆች ተሟጋች እና ጋዜጠኛ “ሰለ ፍልስጢኤማዊያን ሰብአዊ መብት በመቆም እስራላዊያንን በመቃወሙ ምክንያት” ከእስራላዊያኑ የተሰጠው ስምና የካርቱን ጥላሸት “ከፍልስጥኤማዊያን በላይ ፍልስጢኤማዊ” ሲሉ ካርቱን ለጥፈውበት የነበረውን አስታውሰውኛል። ይህ በኢሕአፓዎች አልተጀመረም፤ ወያኔዎች ብለውኛል፤ ኦነጎች ብለውኛል፤ ዛሬ የአሲምባ ድረገጽና መሰል የኢሕአፓ ካልቶች የሚለፋደዱት ያንኑ ከአቻዎቸው የቀዱትን ዘረኛና ያልበሰለ ጥሬ መልሳቸው፤ በማስረጃ ለጻፍኩት መልስ፤ በመረጃ አስደግፈው መልስ መስጠት ሲያቅታቸው፤ መልስ ይሆናል ብለው ከወንጀለኛውና “አገሬ ኤርትራ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለም” ብሎ ኢትየጵያን ከከዳ ‘ከተስፋዬ ገብረአብ” ጋር ያነጻጸሩኝን ካርቱናቸውን ለማዬት ትዝብታችሁን ለማኖር ክቡራን አንባቢዎቼ ድረገጻቸውን እንድትመለከቱ እጋብዛለሁ።  

ከላይ የጠቀስኩት ፓልቶክ ውስጥ ሆኖ የጀገነ የኢሕአፓ ካልት ደግሞ “ድርጅቱ ድሮ ሲያደርገው እንደነበረው የግድያ ሱሱን በኔ ላይ ለመጀመር የቃጣው ይመስላል”፤ ወጣቱን በማደራጀት “የድሮ ዶሚናንስ ባሕሪያችን መመለስ አለብን” ይላል። በማርክሳዊያን ዓለም፤ ለዶሚናንት ባሕሪ መጓዝና መመኘት ምን እንደሚያስከትል እና ምን እንዳስከተለ፤ አሁንም ምን እያስከተለ እንዳለ የምናውቀው ይመስለኛል። የዚህ ጉረኛ ሰው የተለፋደደበትን ስድብና የማስጠንቀቂያው ዛቻ ወዳጆቼ እንዳደምጠው ቀድተው በአውድዬ ልከውልኝ፤አድምጬው፤ የካልት ድፍረት ምን ያህል ርቆ አንደሚሄድ አስገርሞኛል። ይህ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ነው።

ኢሕአፓዎች ለማስፈራራት የተነሱበትን ሰው ማንነት አለማወቃቸው ይገርመኛል። ወያኔ ዝቶ፤ዝቶ፤ዝቶ፤ ስሜን አጥፍቶ፤ጎሳየን ሰርዞ፤ ያልሆነለት፤ አሁን ምስኪኑ የኢሕአፓ ካልት “ኢሰፓ” ብሎ ሲወነጅለኝ፤ እንኳን ኢሰፓ ልሆን ፤ ኢሰፓ ሲመሰረት አገሪቱ ባልነበርኩበት እና ትርጉሙ ምን ማለት እንደሆነ እንኳን የማላውቀውን ሰውዬ፤ እኔን “ይሻለዋል” ብሎ ሲያስጠነቅቀኝ፤ ‘ተደራጁ እያለ የሚወተውታቸውን ወጣቶቹን “አስልኮ” ነጭ ሽብር ሊያራምድብኝ ካልሆነ በቀር ምን ሊያመጣ አንደሚችል ገርሞኛል። 

እነኚህ አርበኞች ናቸው፤ ተውአቸው እያልኩ ስከላከልላቸው ከስንት ወዳጆቼ እየተቀያየምኩ፤ ስከላከልላቸው የነበርኩኝ ሰውዬ፤ ዛሬ ‘ቢቆሉ፤ ቢቆሉ፤ የማይበስሉ ሆኖው ሳገኛቸው፤ እውነትም ከዛው ከ70ዎቹ ምድጃቸው አሁንም እዛው አመዱ ላይ ተዘፍቀው መውጣት እንዳቃታቸው ለማየት ችያለሁ።አይጥ ለሞቷ የድመት አፍንጫ ታሸታለች” ብሎናል ወዳጄ ገብረመድህን አርአያ ‘ እውነትም እኔን ለመጎነታተል አምሮአቸዋልና እሰየው! ምርጫቸው ነውና፤ አከብርላቸዋለሁ፤ ለሁሉም ኳሱም ሜዳውም እንሆ! እንፈታተሽ።ጥርሱ ያለቀበት ውሻ መጮህ እንጂ መናከስ አያውቅም፤ ኢሕአፓ በዘረኛነት ቢጮህም “የእኔ ከአማራው ሕብረተሰብ መቆም” ሊያስቆሙኝ ከቶውኑ አይችሉም! “እንደ እናታቸው ጡት ያጡት እንደሆን እንጂ ፤ “እኔ አማራም፤ ትግሬም አገውም፤ኦሮሞም፤ወላይታም፤ ሐረሪም ሶማሌም…..ወዘተ ወዘተ…. ነኝ” ኢሕአፓ “ባዕድ ነህ” ቢለኝም፤ ስለ አማራ የመቆም መብቴ ከተውኑ መንጠቅ አይቻለውም። እንዴት ደፋር ነው ይህ ኢሕአፓ እባካችሁ? ድፍረቱ ሌላ ሰው ጋር ቢያደርገው እንዴት ባማረበት ነበር። ወይ አለማወቅ! 

ኢሕአፓ ‘የዜጎችን ህይወት ሲያደርገው እንደነበረው” መሪና ተመሪ ሳይታወቅ ወደ አናርኪ ተለውጦ ህይወት በጥይት ሲቀስፍ እንደነበረው ሊቀስፍ ይችላል። ተጠያቂነትም አልነበረውም፤ እስካሁን ድረስ ተጠያቂነቱን አልወሰደም፤ “ገደሉኝ እንጂ ገደልኩ አይልም፡ አጥፍቻለሁ ተጠያቂ ነኝ አላለም። ይህ ደግሞ የተጠቂዎች ዝምታ ወደ ስንፍና ተተርጉሟል። እንግዲህ ማሾፍ ከቀጠሉ፤ አንድ የተቀናጀ ጥናት መደረግ አለበት እላለሁ።” የሰው ልጆች ህይወት በማርክሳዊ፤አናረኮዊና ፋሺስታዊ እርምጃው ሰውን የመቅሰፍ መብት በገዛ እጁ ሊኖረው ይችላል። የኔን እና የዜጎችን ጎሳነትና የማንነት መብት’ የመንጠቅ ወይንም የመስጠት” መብት አልተሰጠውም። ሊኖሮውም አይችልም። 

ቢፈልግ ፓልቶክ ላይ እንደ እኩያዎቹ ዘረኛ ምላሱን ሊዘረጋ ሊሰበስብ ይችላል። ያንን ዘረኛ መብቱን አከብርለታለሁ፤ ስለ አማራ ማሕበረሰብ መብት መከራከር መብቴን ግን ሊነጥቀኝ አይቻለውም። ወያኔም፤ኦነግም፤ሻዕቢያም ሞክረውታል፤ ኢሕአፓም፤ ሊላላጥ ካልሆነ በቀር ከቶ አይቻለውም!

አላርፍ ካላሉ፤ “ኢሕአፓ በታጋዮቹ አንደበት” በሚል የማወጣው ሰነድ ይኖራል።ተከታተሉ፡ ይቀጥላል። ጌታቸው ረዳ (ኢትዮጵያን ሰማይ ብሎግ አዘጋጅ) (Editor Ethiopian Semay) getachre@aol.com  

በአማራ ህዝብ ስቃይ፣ ስደት፣ መፈናቀልና ሞት እየጨፈረ ያለው ብአዴን

ነፃነት ለሃበሻ ፣ ቅዳሜ ጥቅምት ፲፫ ቀን ፪ሺህ፰ ዓም (October 24, 2015) ምንጭ፦ (https://freedom4ethiopian.wordpress.com/2015/10/24/%E1%88%B3wq/) 

ብአዴን የአማራን ህዝብ ማንነት፣ ባህል፣ እምነት፣ ቦታና ታሪክ ለማጥፋት በህወኃት የተፈበረከ የአማራ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው። ራያ፣ ቆቦ፣ ሁመራን ለትግራይ ያስረከበው ይህ የወያኔ ገረድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የጎንደርን ለም መሬቶች ለሱዳን በማስረከብ በህዝባችን ላይ የፈፀመው ግፍ ትውልድ ይቅር የማይለው ነው። የአማራ ህዝብ በዚህ ተላላኪ ድርጅት አማካኝነት በአደባባይ ተሰድቧል፣ ተዋርዷል፣ ተፈናቅሏል፣ ተሰዷል፣ ተገድሏል አሁንም በመፈናቀልና በመገደል ላይ ይገኛል።

 ወያኔ /ህወኃት የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ከተነሳበት ከ1967 ዓ• ም ጀምሮ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ለአገራቸውና ለህዝባቸው የሚቆረቆሩ ወገኖችነ እየታደኑ ተገድለዋል፣ በመገደልም ላይ ይገኛሉ። ይህ ሁሉ ግፍ አልበቃ ብሎ ወያኔ በሎሌው ብአዴን አማካኝነት የአማራን ህዝብ ማሰር፣ ማፈናቀልና መግደል አጠናክሮ ቀጥሎበታል። በአሁኑ ሰዓት በወልቃይት ፀገዴ የአማራ ህዝብ ተወላጆች ላይ እየደረሰ ያለው አሰቃቂ ስቃይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል ነው።

 በአማራ ህዝብ ስቃይ፣ ስደት፣ መከራ፣ መፈናቀልና ሞት ምክንያት የሆነውን ህዳር 11 ቀን የወያኔን የድል በዓል ለማክበር ከበሮ እየደለቀ ያለውን ብአዴንን በቃ ብሎ ህዝባችን ለነፃነቱ መነሳት አለበት። ስለዚህ በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የምትኖሩ የአማራ ተወላጆች በአስቸኳይ በመሰባሰብ ለዚህ አረመኔያዊ ግፍ የሚመጥን ቁመና በመፍጠር ህዝባችንን ከመፈናቀል፣ ከስደትና ከሞት ለመታደግ በእውነት የአማራን ህዝብ የሚወክል ድርጅት መመስረት ይጠበቅብናል። ይህን ግፍ እያየን እንዳላዬን፣ እየሰማን እንዳልሰማን ዝም ብንል መዳን ለአማራ ህዝብ ከሌላ ስፍራ ይመጣለታል። እኛ ግን በታሪክ መታሰቢያ አይኖረንም። በመሆኑም መላው የአማራ ተወላጅ ገበሬው፣ ተማሪው፣ ነጋዴው፣ ምሁሩና ወታደሩ በአስቸኳይ በያለበት በመደራጀት የትውልድ አድን ንቅናቄ እንዲጀምር እናሳስባለን። 

እኔ እንደ አማራ ተወላጅነቴና እንደ ኢተረዮጵያዊነቴ በዚህ ችግር ዙሪያ ከተለያዩ የአማራ ምሁራን ጋር ውይይት በማድረግ ላይ እገኛለሁ። በቅርብ ቀን ይህን የህዝብ ስቃይና ሞት የሚመክት እውነተኛ የአማራ ንቅናቄም እንፈጥራለን። እስከዚያው ግን ህዝባችን የብአዴንንና የወያኔን እኩይ ተግባር በያለበት በመመከት በቅርብ ለሚመሰረተው ንቅናቄ ግብአት የሚሆን አቅም እንዲፈጥር በአክብሮት እንጠይቃለን። ሁለንተናዊ ነፃነትና ክብር ለአማራ ህዝብ!! ነፃነት ለሃበሻ 


አሰግድ ታመነ